በኃያል ዓለማየሁ በኢትዮጵያ ከተመሠረተ 50 ዓመታት ገደማ ያስቆጠረውን ሬስ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከወራት ድርድር በኋላ ሙሉ በሙሉ እንደገዛውና ከዚህ ወር ጀምሮም እንደተረከበው ታወቀ፡፡

በአስራት ሥዩም ባለፈው ሐምሌ ወር በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፉ ማኅበራት ምክር ቤትና በቀድሞው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መካከል ስምምነት የተደረሰበት የጋራ የምክክር መድረክ የፊታችን ማክሰኞ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊካሄድ ነው፡፡

– ስለ አደጋው መንስዔ አይናገርም በቃለየሱስ በቀለ በቤይሩት አቅራቢያ ባለፈው ዓመት ጥር 17 ቀን 2002 ዓ.ም. ድንገተኛ አደጋ የደረሰበት የኢትዮጰያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን የአደጋ መንስዔ ለማወቅ የሚደረገው የአደጋ ምርመራ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ባለፈው ቅዳሜ በሊባኖስ ትራንስፖርትና ሥራ ሚኒስቴር …

የቤይሩት አውሮፕላን አደጋ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ ሆነ Read more »

“የቀጣና ስምሪትና የመለዋወጫ ዋጋ መናር ለኪሳራ ይደርገናል”   የሚኒ ባስ ባለንብረቶች“ኀብረተሰቡ ትክክለኛ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት አለበት”   የትራንስፖርት ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት በታደሰ ገብረ ማርያም

‹‹የተለየ እጥረት የተከሰተው በሰው ሠራሽ ችግር ምክንያት ነው›› የሐረሪ ክልል ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት‹‹የክልሉ የውኃ ችግር ከመጋቢት ወር ጀምሮ ሊፈታ ይችላል›› የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በታምሩ ጽጌ

በታምሩ ፅጌ ግንባታውን ጨርሶ በቅርቡ ማምረት እንደሚጀምር እየተገለጸ ያለው በአል-ሀበሻ ስኳር ፋብሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በሚስተር ሞሲን ሙጂድ አብዲል መጂድ ሞት በተጠረጠሩ ግለሰብ ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ ክስ መሠረተ፡፡

በዘካሪያስ ስንታየሁ | ሪፖርተር በሸራተን አዲስ ሆቴል የተፈጠረው ውዝግብ ባለፈው ረቡዕ እልባት ያገኛል ተብሎ ቢጠበቅም፣ እስካሁን መፍትሔ ማግኘት አልቻለም፡፡ ሆኖም ችግሩን ለመፍታት በሆቴሉ ማኔጅመንትና በሠራተኛ ማኅበሩ መካከል የተጀመረው ድርድር መቀጠሉን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የሆቴሉ ማኔጅመንት ባለፈው ማክሰኞ የሆቴሉን ሠራተኞች በሙሉ …

የሸራተን አዲስ ውዝግብ ቀጥሏል Read more »

– ‹‹ዶክተር›› ተብለው እንዲጠሩም ታዘዘ በታምሩ ጽጌ ሥልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም በሕዝብና በመንግሥት ሀብት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ከ1.5 እስከ 1.6 ቢሊዮን ብር የሚደርስ ጉዳት አድርሰዋል በሚል የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ክስ መስርቶባቸው የነበሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና …

የቀድው የቴሌ ሥራ አስፈጻሚ ተፈረደባቸው Read more »

ደቡብ ሱዳን በሕዝበ ውሳኔ ከሰሜኑ ክፍል መገንጠሉ እውን እንደሆነ በሚገለጽበትና የሱዳን የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም በሚባልበት በዚህ ወቅት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩና ከገጠራማ ቦታዎች የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሱዳን ኤምባሲ ሳር ቤት ከሚገኘው የሱዳን ክለብ ቪዛ ለማግኘት ሌሊቱን መንገድ ዳር እያደሩ፣ ቀኑን ተሰልፈው …

ጉዞ ወደ ሱዳን Read more »

– የአቅርቦት እጥረት ተፈጥሯል– በቢራ ፋብሪካዎች ላይ ትኩረት አድርጓል በውድነህ ዘነበ በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ተመን ከወጣ በኋላ በተፈጠረው የአቅርቦት ዕጥረት ምክንያት፣ ንግድ ሚኒስቴር የዋጋ ማስተካከያ በድጋሚ ሊያደርግ ነው፡፡

በውድነህ ዘነበ ከፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጎማ የማያገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞቹ የደመወዝ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከመጠባበቂያ በጀት ወጪ ተደርጎ እንዲሸፈን አዘዘ፡፡

– በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች አልተመደቡም በታምሩ ፅጌ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን፣ ኢትዮ ቴሌኮም በሚል ስያሜ እንደ አዲስ ከተዋቀረ በኋላ፣ በአዲሱ አወቃቀር ያልተመደቡ ሠራተኞችን ዛሬ በአምባሳደር ሲኒማ ሰብስቦ ያነጋግራል፡፡

‹‹ችግሩ ከእኛ ሳይሆን ከበላይ አካል ነው›› የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በብርቱካን ፈንታ በቅርቡ የተደረገው የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርን በመዝለሉ ሠራተኞቹ ቅሬታቸውን እየገለጹ ናቸው፡፡ አስተዳደሩ በበኩሉ ችግሩ የበላይ አካል መሆኑን እየገለፀ ነው፡፡

በታምሩ ጽጌ | ሪፖርተር በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የጋምቤላ ከተማ አስተዳደርና በቀበሌ 04 እና 05 ቤት የፈረሰባቸው ነዋሪዎች በከተማው ማስተር ፕላን ምክንያት እየተወዛገቡ ነው፡፡ በአስተዳደሩና በሁለቱ ቀበሌዎች መካከል ውዝግቡ የተፈጠረው፤ የከተማው አስተዳደር በቀበሌ 04 እና 05 ውስጥ ነዋሪዎቹ የሠሩዋቸው ቤቶች …

የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ቤታቸው አላግባብ እየፈረሰባቸው መሆኑን አስታወቁ Read more »

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት 480 ሚሊዮን ብር በጀት አፀደቀ በውድነህ ዘነበ ላለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ ግብረሰናይ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት መሥራች ካርል ሄንዝ በም በጤና መታወክ ምክንያት አስተዋጽኦቸው እየቀነሰ በመምጣቱ፣ ኢትዮጵያዊቷ ባለቤታቸው ወይዘሮ አልማዝ በም ሙሉ በሙሉ ሊተኳቸው ነው፡፡

በብርሃኑ ፈቃደ | ሪፖርተር በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ በመዠንገር ዞን የጐማሬ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር አመራሮች፣ ነዋሪዎችና የአካባቢ ተወላጅ ምሁራን በቀበሌያቸው ለዘመናት ሲጠበቅ የቆየ ደን ላልተገባ ኢንቨስትመንት መዋሉን ‹‹ሕገወጥ ነው›› በሚል ደጋግመው ለፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፣ የግብርና ሚኒስቴርን ጨምሮ ለተለያዩ አካላት …

የወያኔ የግብርና ሚኒስቴር የጋምቤላ ነዋሪዎችን ጥያቄ ውድቅ አደረገ Read more »

በዘካሪያስ ስንታየሁ | ሪፖርተር ሸራተን አዲስ ሆቴል ከአሥር ቀናት በኋላ እንደሚዘጋ የሆቴሉ ማኔጅመንት ለክፍል ኃላፊዎች ጥር 26 ቀን 2003 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡ የሆቴሉ ሥራ አስኪያጅ ዦን ፒር ማኒጐፍ ከሰው ኃይል አስተዳዳሪው አቶ ዳንኤል መዝገቡ ጋር የክፍል ኃላፊዎችን ሰብስበው የሠራተኛ ማኅበሩ ከማኔጅመንቱ …

የአላሙዲ ሸራተን ሆቴል ከ10 ቀናት በኋላ እንደሚዘጋ የሆቴሉ ማኔጅመንት አስታወቀ Read more »

– የኤርትራ ወታደሮች በዛላንበሳና አካባቢዋ የፀጥታ ችግር መፍጠራቸው ተጠቆመ በኃይሌ ሙሉና በየማነ ናግሽ በኤርትራ መንግሥት ሥልጠና በተሰጣቸውና በሻዕቢያ ኮማንዶዎች ታጅበው ድንበር በማቋረጥ ለሽብር ሰርገው የገቡ ሰዎች ከበርካታ ከባድ ፈንጂዎች ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታወቀ፡፡

• የምርት አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት ተሰግቷል በውድነህ ዘነበ በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ተመን መቀመጡን ተከትሎ የውጭ ምንዛሪ ጥያቄ እየተቀዛቀዘ መምጣቱን የንግድ ባንኮች አስታወቁ፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር ላለፉት 62 ዓመታት በመንግሥት ሥራ ላይ የቆዩትና ግብፅን ለ30 ዓመታት ያስተዳደሩት ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ተቃዋሚዎቻቸው ከሥልጣን ይውረዱ ቢሏቸውም እስካሁን ንቅንቅ አላሉም፡፡

– በቀን 1000 ቶን ስኳር ለማምረት አቅዷል በኃያል ዓለማየሁ በ90 ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች የተቋቋመው አምቦ ነመር አግሮ ኢንተግሬትድ ኤንድ ኢንዱስትሪስ አክሲዮን ማኅበር በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ 128,000 ሔክታር መሬት በማግኘት ቀዳሚ ኩባንያ ሆነ፡፡

በታምሩ ጽጌ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኝነታቸው በሰነድና በሰው ምስክሮች ተረጋግጦባቸው በዓመታት እሥራትና በከፍተኛ ገንዘብ የተቀጡ እስረኞች የእስር ጊዜያቸውን ቢጨርሱም፣ ገንዘቡን መክፈል ባለመቻላቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ ጠበቆቻቸው አስታወቁ፡፡

– ምርጫ ቦርድና የክልሉ ሕዝብ ድርጊቱን ለማስቆም እንዲተባበሩ ጠይቋል በየማነ ናግሽ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አባሉ በሆነው ዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዴሞክራሲ ላይ በሕገወጥ መንገድ ተወሰደ ያለውን ዕርምጃ አወገዘ፡፡

በዳዊት ታዬ የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት በአዳማ ከተማ የሚገኙ የቢራና የለስላሳ መጠጥ ፋብሪካዎች አከፋፋይ ቅርንጫፎች ‹‹ለደረቅ ቆሻሻ ክፍያ›› በማለት እያንዳንዳቸው ከግማሽ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር የሚሆን ክፍያ በየዓመቱ እንዲከፍሉ አዘዘ፡፡

– ወንጀሉ እስከ አሥር ዓመት እስራት ያስቀጣል በኃይሌ ሙሉ ሀሰተኛነቱ በተረጋገጠ ሰነድ ለልጃቸው 549 ሺሕ 500 ብር ዋጋ ያላቸው አክሲዮኖች እንደሸጡ በማስመሰል የፍትሐ ብሔር ክስ ሲመሰርቱ፣ ሀሰተኛውን ሰነድ ከማስረጃዎች ዝርዝር ጋር አቅርበው የተገኙት አቶ ዘመረ ጀማነህ የተባሉ ግለሰብ በ1 ሺሕ …

በሀሰተኛ ሰነድ ያጭበረበሩ ግለሰብ በ1 ሺሕ 500 ብር ቅጣት ተለቀቁ Read more »

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለፈው ዓርብ ምሽት ከስዊዘርላንድ ዳቮስ ከተመለሱ በኋላ፣ ባለፈው እሑድ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 16ኛው የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ ጉባዔም ለመጀመርያ ጊዜ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የውጭ …

የአፍሪካ ኅብረት 16ኛው የመሪዎች ጉባዔ ፋይዳ Read more »

‹‹በችሎት መዘለፍ የለብንም፤ የተደፈረው ዓቃቤ ሕግ ብቻ ሳይሆን ችሎቱም ነው›› የገቢዎችና ጉምሩክ ዓቃቤ ሕግ‹‹በፍርድ ቤት ሐሳባችንን በነፃነት መግለጽ እንችላለን፤ ይህ በልበ ሙሉነት እንዳንከራከር ማስፈራራት ነው›› የተከሳሽ ጠበቆች በታምሩ ጽጌ

በታምሩ ጽጌ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ግዮን ሆቴል አካባቢ የሚገኘውና ንብረትነቱ የወይዘሮ ሀድያ መሐመድ ጐንጂ የሆነው ሀድያ ሱፐር ማርኬት፣ ጥር 22 ሌሊት ለጥር 23 አጥቢያ 2003 ዓ.ም. እንደተዘረፈ ዋና ሥራ አስኪያጁ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

በታምሩ ጽጌ በሥልጣን ያለአግባብ በመገልገል ከአምስት ዓመታት በፊት በ86,790,000 ብር የሙስና ሙከራ ወንጀል ተከሰው የነበሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሰባት የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ትናንትና በነፃ ተሰናበቱ፡፡

– አቶ ሱፊያን ከቻይና ተስፋ ይዘው ተመለሱ በውድነህ ዘነበ ለባቡር መስመር ዝርጋታ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ ለማግኘት ባለፈው ሳምንት ቻይና የተጓዙት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አቶ ሱፊያን አህመድ በዚህ ወር በጀቱ እንደሚለቀቅ ተስፋ ይዘው መመለሳቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡

አቶ መኩሪያ ኃይሌ የቦርድ ሰብሳቢ ሆኑ በውድነህ ዘነበ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን መሥርያ ቤት የሥራ አመራር ቦርድን እንዲመሩ ለሦስት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሹመት ሰጠ፡፡

(ሪፖርተር) — ቻድሃ የተባለው የህንድ ኩባንያ በእርሻ ሥራ ላይ ለመሠማራት የአዲስ አበባን ሁለት እጥፍ የሚሆን 100 ሺሕ ሔክታር መሬት እንዲሰጠው ጥያቄ አቀረበ፡፡ ጥያቄውን በማስተናገድ ላይ የሚገኘው የግብርና ሚኒስቴር ለኩባንያው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኘው ጉጂ ዞን ካሁን በፊት 22 ሺሕ …

የህንድ ኩባንያ የአዲስ አበባን ሁለት እጥፍ መሬት እንዲሰጠው ጥያቄ አቀረበ Read more »

– የትራንስፖርትና ጋራዥ ሠራተኞች መፍትሔ የሚሰጣቸው አጥተዋል በታምሩ ጽጌ የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ስሙን ቀይሮ ኢትዮ ቴሌኮም ከመባሉ በፊት እ.ኤ.አ. ከሴብቴምበር 15 ቀን 2010 እስከ ኖቬምበር 30 ቀን 2010 ድረስ የቀን አበል በመክፈል፣ በመለስተኛ መስመር ሠራተኛነት አሠልጥኖ ያስመረቃቸው ሠራተኞች ላለፉት …

ለመስመር ሠራተኛነት የሠለጠኑ የቴሌኮም ተቀጣሪዎች ደመወዝና ምደባ መከልከላቸውን አስታወቁ Read more »

በዳዊት ታዬ ባሳለፍነው ሳምንት የለስላሳና የቢራ መጠጦች የማከፋፈያ ዋጋ ላይ የተፈጠረውን ችግር ለማቃለል ንግድ ሚኒስቴር ለየክልሎቹ የዋጋ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጠ፡፡

በምሕረት አስቻለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛውና በማታው ክፍለ ጊዜ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ሳይመዘገቡ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

በኃይሌ ሙሉ | ሪፖርተር አቶ ያዕቆብ ልኬ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በኢንጅነር ኃይሉ ሻውል መመረጣቸውን ተከትሎ፣ በመኢአድ ሥራ አስፈጻሚና በኢንጅነር ኃይሉ ሻውል መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ በኢንጅነሩና በሥራ አስፈጻሚው መካከል ውዝግቡ የተፈጠረው ታኅሣሥ 19 …

በኃይሉ ሻውልና በመኢአድ ሥራ አስፈጻሚ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ቀጥሏል Read more »

– የሊባኖስ የፖለቲካ ቀውስ በመላምትነት ቀርቧል በቃለየሱስ በቀለና በመላኩ ደምሴ የዛሬ ዓመት ጥር 25 ቀን 2002 ዓ.ም. ከሊባኖስ ርዕሰ መዲና ቤይሩት ራፊቅ ሐሪሪ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወዲያውኑ ሜዲትራኒያን ባህር ላይ ድንገተኛ አደጋ የደረሰበት አውሮፕላን የአደጋ ሪፖርት ትናንት ይወጣል …

የቤይሩት አውሮፕላን አደጋ ሪፖርት አለመውጣት እንቆቅልሽ ሆኗል Read more »

– 980 የንግድ ዘርፎች ተመርጠዋል በውድነህ ዘነበ በነፃ ገበያ ስም በአገሪቱ እየተስፋፋ የመጣውን ‹‹ሕገወጥ›› የንግድ እንቅስቃሴ ከሥሩ ማድረቅ ያስችላል በሚል፣ የንግድ ሚኒስቴር በንግድ መዝገብ መመዝገብ ያለባቸውን ነጋዴዎች በሙሉ በድጋሚ ሊመዘግብ ነው፡፡

በታምሩ ጽጌ | ሪፖርተር የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትርና የመድረክ ከፍተኛ አመራር አቶ ስዬ አብርሃ ከመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ተከራይተውት የሚኖሩበትን ቤት ከጥር 30 ቀን 2003 ዓ.ም. በፊት እንዲያስረክቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፡፡ ጥር 6 ቀን 2003 ዓ.ም. የቤት ኪራይ ከፍለው ሲመለሱ በመኖሪያ ቤታቸው አጥር …

ስዬ አብርሃ መኖሪያ ቤቱን እንዲለቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው Read more »