ነስር (Nose bleeds) (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) በአፍንጫ ደም መፍሰስ (ነስር) የምንለው አስደንጋጭ የሆነ፤ነገር ግን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ ነስር በሁለት ዓይነት ይከፈላል፡፡ 1) ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Anterior Nosebleeds) • ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይነት ከ90 …

በአፍንጫ ደም መፍሰስ (ነስር) (Nose bleeds) Read more »

✓ ለአጥንት ጤናማተትና ጥንካሬ ቴምር በውስጡ የያዛቸው ንጥረ ነገሮች እንደ ሴሌኒየም ማንጋኒዝ፣ኮፐር እና ማግኒዚየም ለአጥንት ጤናማ እድገት እና ጥንካሬ እጅግ ጠቃሚ እንዲሆን ይደርገዋል። ✓ ለሆድ ድርቀት ቴምርን መመገብ የሆድ ድርቀትን ይከላከላል። የሆድ ድርቀት የሚያስቸግርዎ ከሆነ ቴምርን በውሃ ዘፍዝፈው በማሳደር ጠዋት …

ቴምርን የመመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

 የምንመገባቸው ምግቦችና መጠጦች ለከፍተኛ ራስ ምታት (ማይግሪን) መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ። በራስ ምታት የመያዝ አጋጣሚዎች በተለያዩ ምክንያቶች (በአየር ፀባይ መለዋወጥ፣ በጠንካራ ሽታዎች፣ በከፍተኛ ብርሃን፣ በሌሎች በሽታዎች ሳቢያ፣ በካፌይን ሱሰኝነት ወዘተ) የሚያጋጥመን ቢሆንም የምንመገባቸው ምግቦችና ወደ አንጀታችን የምንልካቸው የተለያዩ መጠጦችም ለከፍተኛው ራስ …

ለማይግሪን የሚያጋልጡ ምግቦች Read more »

ቀይስርን የመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) *ለጉበት ጤናማነት ቀይስር ውስጥ የሚገኝ ቤታይን የተባለ ንጥረነገር የጉበትን አገልግሎት የማነቃቃት አቅም አለው። *ከሳንባ ጋር ተያያዥ ችግሮችን ይከላከላል ቀይስር ቫይታሚን ሲ በውስጡ ስለያዘ የአስም ምልክቶች እንዳይነሱ ይረዳል፣ በሽታ የመከላከል አቅማችን እንዲዳብርም ያግዛል። …

ቀይስርን የመመገብ የጤና ጥቅሞች Read more »

የጨጓራ ሕመምዎን ለማስታገስ የሚጠቅሙ የጤና ምክሮች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም) • ከጥጋብ በላይ አለመመገብ • ምግብን በዝግታ መመገብ • ቅባታማ ምግቦችን ማስወገድ • ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች አለመመገብ • ሲጋራ ያለማጤስ • ቡና፤አልኮል እና የለስላሳ መጠጦችን አለማዘውተር • የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል …

የጨጓራ ሕመምዎን ለማስታገስ የሚጠቅሙ የጤና ምክሮች Read more »

የድድ መድማት (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) የድድ መድማት የድ ድ ላይ ችግርን እንዲሁም ከባድ ለሚባሉ የጤና እክሎች መዳረጋችንን ጠቋሚ ምልክት ሊሆን ይችላል። ✓ የድድ መድማትን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች አንዱና ዋነኛ ምክንያት የድድ መቆጣት (inflamed gums) ወይንም ጅንጂቫይተስ (Gingivitis) ነው። በድድ መካከል …

የድድ መድማት Read more »

ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና (Ectopic Pregnancy) (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና በአብዛኛው የሚከሰተው እንቁላልን ከእንቁላል ማቀፊያ ወይም እንቁልጢ ወደ ማህፀን በሚወስደው ቱቦ (Fallopian tubes) ውስጥ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የማህፀን ውጭ እርግዝና በሆድ ውስጥ፤ በእንቁላል ማቀፊያ ከረጢት (እንቁልጢ) …

ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና (Ectopic Pregnancy) (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

የጥርስ መቦርቦር — (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ==== የጥርስ መቦርቦር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ጀርሞች (ባክቴሪያ) ጥርሳችንን የሚያበሰብሱ አሲዶችን በሚያመነጩበት ጊዜ ነው፣ ይህም በጥርሳችን ላይ የተቦረቦሩ ቀዳዳዎችን (Cavities) እንዲፈጠሩ ያደርጋል። የተቦረቦሩ ጥርሶች ህመም ከማስከተል ባለፈ ለኢንፌክሽን ያጋልጣሉ። ✔ የጥርስ መቦርቦር …

የጥርስ መቦርቦር (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

የኩላሊት ጠጠር ( KIDNEY STONES)  ==== (ዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ==== የኩላሊት ጠጠር ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ መቆየት የሚችል ሲሆን ከኩላሊት ተነስቶ በሽንት ማስወገጃ መስመር እስከ ፊኛ ድረስ ሊያደርግ በሚችለው ጉዞ ምክንያት ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡ የኩላሊት ጠጠሮች ጠጣር የሆኑ ትናንሽ …

የኩላሊት ጠጠር ( KIDNEY STONES) (ዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

የሐሞት ጠጠር —- (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ====== የሐሞት ከረጢት የሚባለው የሰውነት ክፍል ከጉበት ሥር የሚገኝ አነስተኛ ከረጢት ሲሆን ለምግብ መፍጨት ሂደት አስፈላጊ የሆነዉ የሐሞት ፈሳሽ የሚጠራቀምበት አካል ነው፡፡ የሐሞት ፈሳሽ ጨዋማ ንጥረ ነገሮችን ያዘለ ሲሆን የምንመገበዉን ቅባት እና ቫይታሚኖች …

የሐሞት ጠጠር (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

እንቅልፍ ከመተኛትዎ በፊት ማድረግ የሌለብዎን ያውቃሉ?  (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ✔ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የአካል ብቃት እቅስቃሴ ማድረግ ለጤናማ ሕይወት መሰረትና ለጥሩ እና ሰላማዊ እንቅልፍዎ ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡ ነገር ግን እንቅልፍ ከመተኛትዎ በፊት በ3 ሰዓታት ውስጥ የሚሰሩ ከሆነ የሰውነት ሙቀት …

እንቅልፍ ከመተኛትዎ በፊት ማድረግ የሌለብዎን ያውቃሉ? Read more »

በቆሎን የመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ✓ ለኪንታሮት ህመም እና ለፊንጢጣ ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል በቆሎ በፋየበር የበለፀገ ስለሆን እንደ ሆድ ድርቀት እና ተያይዞ የሚመጣውን የኪንታሮት ህመም ተጋላጭነት በእጅጉ ይቀንሳል። ✓ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ይዟል እንደ …

በቆሎ በፋየበር የበለፀገ ስለሆነ በቆሎን የመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

የኪንታሮት ህመም በታችኛ የትልቁ አንጀትና ፊንጥጣ አካበቢ ያሉ የደም መልስ( veins) የደም ቧንቧዎች በሚያብጡበትና በሚቆጡበት ወቅት የሚከሰት የህመም አይነት ነዉ፡፡ የኪንታሮት ህመም ሰገራ በሚወጡበት ወቅት ሲያምጡ፣ ወይም በፊንጥጣና በታችኛዉ የትልቁ አንጀት አካበቢ ባሉ የደም ስሮች ላይ እንደ እርግዝናና ሌሎች ጭነትን …

የትልቁ አንጀትና ፊንጥጣ አካበቢ የኪንታሮት ህመም (hemorrhoids) Read more »

ኣሳ ዘይትን የመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) *በአየር ብክለት ምክንያት የሚመጡ ችግሮችን ይከላከላል በኦሜጋ 3 የበለፀው የአሳ ዘይት በአየር ብክለት ምክንያት ሊከሰቱ ከሚችሉ የልብና ተያያዥ ህመሞች የመከላከል አቅም አለው። *የመገጣጠሚያ ህመም ስሜትን ማስታገስ የመገጣጠሚያ ህመም ካለዎት ሁለት የሾርባ …

ኣሳ ዘይትን የመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

“ሬድ ቡል”ን የመሳሰሉ ሃይል ሰጪ መጠጦች በተለይ ከአልኮል መጠጥ ጋር ተደባልቀው ሲጠጡ የጤና ችግር ሊያስከትሉ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ፡፡በአውሮፓ የተደረገ ጥናት እንዳረጋገጠው፣ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ እድሜያቸው ከ18-29 ዓመት የሚደርሱ ወጣቶች፣ እንደ “ሬድ ቡል” ያሉ ሃይል ሰጪ መጠጦችን …

ሃይል ሰጪ መጠጦች በተለይ ከአልኮል መጠጥ ጋር ተደባልቀው ሲጠጡ የጤና ችግር ያስከትላሉ ተባለ Read more »

የነጭ ሽንኩርት አስሩ ለጤንነት ያለው ጠቀሜታ ነጭ ሽንኩርት ከተለያዩ ምግቦች ውስጥ በመጨመር መመገብ ለጤንነት እጅግ ጠቀሜታ ይሰጣል::በነጭ ሽንኩርት ውስጥ አሊሲን ማለት አንቲባዮቲክ አንቲቭራል አንቲፈንገስ እንዲሁም አንቲኦክሲዳንት የተባሉት ንጥረ ነገሮች የሚገኙ ሲሆን በቫይታሚን እና በተፈጥሮ ማእድናት የበለጸገ ነው ነጭ ሽንኩርት:: በውስጡ …

የነጭ ሽንኩርት አስሩ ለጤንነት ያለው ጠቀሜታ Read more »

ለጤንነትዎ ያንብቡ : ለካንሰር ያጋልጣሉ የተባሉ እና በፍጹም ከንፈሮቻችንን መሻገር የሌለባቸው ለጤንነት እጅግ አደገኛ ንጥረ ነገሮችን የተሸከሙ አስር የምግቦች አይነቶች ከዚህ ሊንክ በዝርዝር ቀርበዋል:- http://betinews.com/?p=3818 Cancer Causing : 10 Toxic Foods That Should Never Cross Your Lips

Enjoy ! Eight Tips If Your Child Refuses To Eat

ልጆች ምግብ አልመገበም ብለው ካስቸገሩ የሚከተሉትን 8 ዘዴዎች ይጠቀሙ:: ===== ልጆች ፍቅር ናቸው የእግዝኣብሄር ስጦታዎች…ይወደዳሉ::የራስዎን ልጆች አሊያም የወንድም እህት ቤተሰብ ዘመድ ጎረቤት ልጆች በፍቅር ይወዳሉ::ልጆች በብዛት ምግብ አልበላም ብለው ሲያስቸግሩ ይታያሉ::ታዲያ ልጆች ምግብ አልበላም ብለው ሲቀውጡት እርስዎ አይጨናነቁ ቀላል ነው …

ልጆች ምግብ አልመገበም ብለው ካስቸገሩ የሚከተሉትን 8 ዘዴዎች ይጠቀሙ:: Read more »

ወደ ቢጫነት የተቀየረ ጥርስን ማከሚያ መንገዶች :-ስለ ውበት ሲታሰብና ያማረ ገጽታን ለመላበስ ሁሉም የሰውነት ክፍሎች በተመጣጠነ መልኩ አይነ ግቡ መሆን ይኖርባቸዋል።   አምሮና ደምቆ መታየት ሲታሰብ ደግሞ የፊት ገጽታ በተለይም ያማረና እና ማራኪ ፈገግታ ቀዳሚው ነው፤ ላማረ ፈገግታ ደግሞ ጤንነቱ …

ወደ ቢጫነት የተቀየረ ጥርስን ማከሚያ መንገዶች Read more »

ዘውዲቱ ሆስፒታል የመህፀን እጢ እንዳለባቸው የተነገራቸው የ 5 ልጆች እናት እጢው ወደ ካንሰር እንዳይለወጥ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና እንዲደረጉ ይታዘዛሉ ። ለዚህም ቀዶ ጥገና ሆስፒታሉ መሳሪያ ስለሌለው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የምርመራ ውጤታቸውን አባሪ በማድረግ ይልካቸዋል። የተጠቀስው ሆስፒታል እደደረሱም እናት ለህክምና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ክፍያ ሰለተጠየቁ «ያለአባት የሚያሳድጓቸው የ 5 ልጆች እናትና የቤተሰብ ሃላፊ መሆናቸውን ጭምር […]

*የደም ናሙናው ለተጨማሪ ማረጋገጫ ወደ አሜሪካ በዛሬው ዕለት ተልኳል፡፡ በትናንትናው ዕለት አንድ ከሴራሊዮን የመጣ ግለሰብ በኢቦላ ሕመም ተጠርጥሮ ምርመራ ቢደረግለትም ከቫይረሱ ነፃ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ አስታወቁ፡፡ ታማሚው በሴራሊዮን በአንድ የአለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጀት በኩል ተቀጥሮ የአካባቢ ቁጥጥር ባለሙያ በመሆን  ይሠራ የነበረ  ሲሆን፥ ከሴራሊዮን ከተመለሰ በ15ኛ ቀኑ በትኩሣት ራሱን በመሳቱ በተደረገለት የደም ምርመራ ፋልሲፓረም የተባለ የወባ በሽታ የተገኘበት በመሆኑ ለዚሁ አገልግሎት ባዘጋጀችው ላብራቶሪ ለኢባላ የደም ምርመራ ተደርጎለት ውጤቱ ከበሽታው ነፃ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በላብራቶሪ ውጤቱ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ብንሆንም ታካሚው ሴራሊዮን ደርሶ ከመመለሱ አንፃር የደም ናሙናው ለተጨማሪ ማረጋገጫ ወደ አሜሪካ በዛሬው ዕለት መላኩንና ከ48 እስከ 72 ሰዓታት ውስጥ ውጤቱ እንደሚታወቅ ነው የተመለከተው። በውጤቱ ላይ ለውጥ የሚኖር ከሆነ በቀጣይ ሚኒስቴሩ እንደሚያሳውቅ ዶክተር ከሰተብርሃን ገልጸዋል፡፡ ታካሚው በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ረፋድ ላይ ሕይወቱ ማለፉንም ነው ያስታወቁት፡፡ የተላከው ናሙና ውጤት እስከሚመጣ ድረስ ከተጠርጣሪው ጋር ቀጥታ ግንኙነት የነበራቸው ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ ላይ የባለሙያ ክትትል በመደረግ ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ኢቦላን ለመከላከል የምታደርገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ አረጋግጠዋል፡፡ ******** ምንጭ፡- ፋና – ጥር 6፣ 2007 More from Horn Affairs Amharicበአሶሳ ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ተከሰተ – ክልሉ ኢቦላ አይደለም ይላልየኬሚካል ክምችትና የአደጋ ስጋት በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶችዓለማየሁ አቶምሳ – ኪራይ ሰብሳቢነትን አምርሮ የታገለና ያታገለኢትዮ-ቴሌኮም በ75 የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኔትወርክ ችግር ፈታሁ […]

ላለፉት ሶስት ወራት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ፣ ሕዝባችን በአራቱም ማእዘናት ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ያለዉን ጥማት ለመግለጽና በሚታዩት የዜጎች የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ ያለዉን ተቃዉሞ ለማስተጋባት፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ ስር ሲንቀሳቀስ እንደነበረ በስፋት ተዘግቧል። በጂንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በወላይታ/ሶዶ፣ በባሌ/ሮቢ፣ በፍቼ፣ በአዳማ/ናዝሬት፣ በመቀሌ (በሙሉ ባይሳካም) ፣ በደሴም በባህር ዳርና ፣ በጎንደር የተደረገው የመጀመሪአዉ ዙር የሚሊየነሞች […]

ከ 318 ዓመታት በፊት ፣ እ ጎ አ በ 1705 ዓ ም መሆኑ ነው፣ ታላቁ እንግሊዛዊ የፊዚክስ ና የሒሳብ ሊቅ አይዛክ ኒውተን፤ ስለ ስበት ኃይልና ስለብርሃን ምንነት ካደረገው ምርምር ውጭ ፣ ስለ ኅልፈተ ዓለም በማንሳት፤ እ ጎ አ በ 2060 ዓ ም፣

የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አልአሳድ ጀርመን የሶሪያውን ቀውስ እንድትሸመግል እንደሚፈልጉ አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ ለአንድ የጀርመን መጽሔት እንዳሉት የጀርመን ልዑካን ሶሪያ መጥተው የሃገሪቱን አጠቃላይ ይዞታ እንዲመለከቱና በተጨባጩ ሁኔታ ላይ ከደማስቆ መንግሥት ጋር እንዲወያዩ ጠይቀዋል። ይሁንና የጀርመን መንግስት የአሳድን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

አፍሪቃ ውስጥ ሥራ እያላቸውም በልተው ማደር ያቃታቸው ጥቂቶች አይደሉም። እንደ ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ድርጅት በምህፃሩ ILO መዘርዝር ከሆነ 40 ከመቶ የሚሆን አፍሪቃዊ የሚተዳደረው በቀን ከ25 ብር በታች በሆነ ገቢ ነው።

በተመስገን ደሳለኝ

የኢህአዴግ ታጋዮች የመንግስት ‹‹ጠንካራ ይዞታ›› የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር መቆጣጠር ችለዋል፤ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት ግስጋሴም ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያምን እንቅልፍ ነስቷል፡፡ በአንዳች ተአምር ግስጋሴውን መግታት ካልቻሉ፣ በጥቂት ወራት ውስጥ ሁሉም ነገር ታሪክ እንደሚሆን በማወቃቸው፣ መላ በማፈላለጉ ላይ ተጠምደዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ነበር (የሃሳቡ አመንጪ ተለይቶ ባይታወቅም) ‹‹ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች የአጭር ጊዜ ስልጠና ሰጥቶ፣ ከገሪቱ ሠራዊት ጎን ማሰለፍና የ‹ወንበዴ›ውን ጦር መድረሻ ማሳጣት›› የሚለው ሃሳብ እንደ መፍትሄ የተወሰደው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉአሰፋ

ትላንት ምሽት። እለተ እሁድ፤ ኦክቶበር 6 2013ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮ በስልክ ያወራሉ። ንግግራቸው ከወትሮው የተለየ አልነበረም። እንደ ቀድሞው እየተቀላለዱ ይሳሳቃሉ። ታማኝ ከዴንቨርኮሎራዶ፣ ቴዲ ደግሞ ከሲድኒ– አውስትራሊያ በስራ ላይ ነበሩ። በዚህ የሶስትዮሽ የስልክ ጨዋታ ላይ እኔና ጴጥሮስ አሸናፊም ገብተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ፤ 19ኛ ዓመት ቁጥር 255፤ ነሐሴ 16 – ጳጉሜ 5 2004 ዓ.ም) ዲ/ን ታደሰ ወርቁ* ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ መንግሥታዊ አካላት የወጡ ሰነዶችና የሚሰሙ ንግግሮች ማኅበረ ቅዱሳንን የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት አክራሪዎች ማንጸርያ አድርጎ የመውሰድ አዝማሚያዎች እየታዩ ነው፡፡ ይህን የተሳሳተ አቻ ፈጠራ አፅራረ ቤተ ክርስቲያን የራሳቸውን ፍላጎት ሲያራግቡበት ይታያል፡፡ ተከታዩ ጽሑፍ መንግሥት አቋሞቹን የገለጸባቸውን …


ከቅርብ ግዜ ወዲህ ፌስቡክ የወቅቱን ጨቋኝ ሕወሓትን ጥሎ የቀድሞዎቹን ጨቋኞች እነ ምኒልክን አንስቷል፡፡ ነገርዬው ሲተቹት በመሣሪያ መልስ ከሚሰጥ አካል ጋር ከመታገል፣ በሕይወት ከሌሉት ወይም ቀጥተኛ ተወካይ የሌላቸው ላይ መዘባበት ይሻላል በሚል ይሁን ወይም የጥያቄው አሳሳቢነት ስር ሰዶ እርግጠኛ ሆኜ መናገር አልችልም፡፡ በታሪካዊ ጭቆናዎች ትርክቶች ውስጥ ‹አንዱ በማፍረስ፣ አንዱ በመካብ፣ ሌላው ደግሞ በመገላገል› ሁሉም የያቅሙን የሞት ሽረት እያደረገ ነው፡፡

እነ አብይ አቶምሳ ‹‹የታሪክ ኢ-ፍትሐዊነት ላይ መተማመኛ ላይ ሳንደርስ ወደፊት ንቅንቅ የለም› ሲሉ ሰንብተዋል፡፡ ትላንትና ዛሬ ደግሞ የኔም ወዳጆች በያዝ ለቀቅ የከረመውን ‹‹የይቅርታ ጉዳይ›› ቀለል አርገውም ቢሆን አንስተውታል፡፡ ናትናኤል ፈለቀ ‹‹የአባት ሀብት ወይም ዕዳ ለልጅ እንደሚተላለፍ ሁሉ የአባት ትውልድ በደል ለልጅ ትውልድ ይተላለፋልና፣ የበዳይ አባት ልጅ ትውልድ የተበዳይ አባት ልጅ ትውልድን ይቅር ቢል ምን አለበት?›› የሚመስል አማራጭ የመፍትሔ ጥያቄጠቁሟል፡፡ ማሕሌት ፋንታሁን ደግሞ ‹‹ነገሩን የተበዳይ ቦታ ሆኜ ብሆን ብዬ ሳስበው ከዚህ ትውልድም ቢሆን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለብኝ›› የሚል ጭብጥ ያለው የራሷን የይቅርታ መልዕክትአስነብባናለች፡፡
በኔ አመለካከት የጓደኖቼ ሐሳብ ለውይይቱ ጥሩ መንገድ ቢጠርግም፣ ይቅርታ መጠየቅ እና ምሕረት ማግኘት በአገራችን የብሔር ጭቆና ጉዳይ እንዲህ በቀላሉ በጥቂት ግለሰቦች ‹‹ይቅር ለእግዜር›› የሚፈታ አይመስለኝም፡፡ በጭቆናው ጥልቀት እና አተረጓጎም ላይ እንኳን ገና መግባባት ላይ አልደረስንም፡፡ ስለሆነም እነዚህን መጠየቅ ይቀድማል ባይ ነኝ፤
  • ይቅርታ የሚጠያየቁት አካላት (የሚጠይቀው እና የሚጠየቀው) እነማን ናቸው?
  • ይቅርታ የሚጠየቅበት በደልስ የትኛው ነው?
  • ይቅርታ የሚጠየቀውስ እንዴት ነው?
  • ይቅርታው ያለካሣ ምሕረት ያገኛል ወይ?
  • ምሕረት የሚያስገኘው የካሣ ዓይነትስ ምንድን ነው?

‹አቢሲኒያውያን (በተለይ አማራ እንዲሁም ትግራይ) በተለይ ላለፉት 130 ዓመታት በተለይ በኦሮሞ ሕዝብ (እና እንዲሁም በደቡብ ሕዝቦች ላይ) ‹‹ኢትዮጵያውነትን የመጫን›› (ወይም በሌሎች አነጋገር በኢትዮጵያ ክልል አጥሮ በማስገባት እና በጉልበት በማስገበር) ቋንቋቸውን፣ ባሕላቸውን፣ እምነታቸውን እና ጠቅላላ ማንነታቸውን የሚያጠፋ (ወይም በአማራነት የሚተካ – amharanize የሚያደርግ) በደል /ጭቆና/ አድርሰውባቸዋል› የሚለው ከሞላ ጎደል ጉዳዩን የሚገልጸው ቢሆንም በተለያዩ አካላት ግን የተለያየ አተረጓጎምና የቃላት አጠቃቀምም ጭምር ይኖረዋል፡፡

ብዙ የአማራ ልሒቃን የነበረው የማስገበር ሒደት አገር የማስፋት ነው እንጂ የብሔር ብሔረሰቦችን ማንነት ለማጥፋት የተደረገ ነገር የለም፡፡ የአማራውም የኦሮሞውም ገበሬ በነገሥታቱ ዕኩል ሲገብር፣ ሲዘረፍ እና ሲበደል ነው የኖረው ይላሉ፡፡ የኦሮሞ ልሒቃንም በበኩላቸው በሕዝባችን ላይ የደረሰው ‹የቅኝ አገዛዝ እንጂ ተራ ጭቆና አይደለም› ከሚሉት (ሌንጮ ለታ) አንስቶ ‹የነዳግማዊ ምኒልክ የማስገበር እርምጃ ነበር፤ አገር በዚያ መንገድ ነው የሚገነባው ቢሆንም የኦሮሞን ማንነት ግን ማጥፋቱ ፍትሐዊ አልነበረም… አሁንም ሒደቱ አልቆመም፡፡› እስከሚሉት (አቶ ቡልቻ ደመቅሳ) እንዲሁም ‹በኦሮሚያ የማንነት ጭቆናዎች ቢኖሩም የመደብ ጭቆናውን ያክል የከፋ አልነበረም፤ የኦሮሞ ባላባቶችም የኦሮሞ ሕዝብን በድለዋል› እስከሚሉት (ዶ/ር መረራ ጉዲና) እና ሌሎችም በከፊል የሚገናኙ እና በተለይ በአማራጭ መፍትሔዎቻቸው የሚለያዩ ማለትም ‹መገንጠል ነው መፍትሔው› በሚሉና ‹የለም ከሌሎች ጋር አብሮ በዕኩልነት ራስን ማስተዳደር› ይሻላል የሚሉ የተለያዩ አተረጓጎሞች አሉበት፡፡
ይቅርታ የመጠያየቅ አጀንዳ ሲመጣ በላይኛው አንቀጽ መሠረት አማራ በዳይ፣ ኦሮሞ ተበዳይ ለማለት የሚያስችሉ በርካታ ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልገናል፡፡ የአማራ ባላባቶች (ወይም አማርኛ ተናጋሪዎች ማለትም ይቻላል – ምክንያቱም በተለይ የሸዋ ኦሮሞዎች የሚገባቸውን ያክል እንኳን ባይሆን በሥልጣኑ ውስጥ ቦታ ነበራቸው) በማስፋፋት፣ በነፍጠኝነት (ማለትም በኦሮሞ አካባቢዎች በነፍጥ ኃይል በመስፈር እና የአካባቢውን ነዋሪዎች ጭሰኛ በማድረግ) ለሠሩት በደል አማራ በጥቅሉ ተጠያቂ መሆን ይችላል ወይ? በወቅቱ ‹‹የጨዋው ልጅ አምስት መቶም አንሞላ›› የሚሉ ባላባቶች በነበሩበት ዘመን ብዙኃኑ የአማራ ተወላጅስ ቢሆን በጭሰኝነት እየገበረ የሚኖር ተጨቋኝ አልነበረም ወይ? ከዚህ ጋር በተያያዘ የኦሮሞ መብት አራማጆች የሚያነሱት ወሳኝ መሟገቻ ‹የአማራ ብዙኃን ቢያንስ ማንነቱ አደጋ ላይ አልወደቀም፣ ይልቁንም ተስፋፍቶለት አሁንም ድረስ ስር ለሰደደው ተጠቃሚነት አብቅቶታል› የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ቢሆን ብዙኃኑ ተበዳይ በነበረበት ስርዓት ውስጥ በቋንቋ የሚመስሉት ሰዎች በደል በማድረሳቸው የእነርሱን በደል ተንተርሶ ይቅርታ መጠየቅ አለበት የሚለው ውኃ የማያነሳ መከራከሪያ ሊሆን ይችላል – አንዳንዶች ግን ‹‹ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ ሲባል ምን አለበት?›› ባዮች ናቸው፡፡
‹ይቅርታ ይጠየቅ – ጠያቂም አይጎዳም፣ ምሕረት አድራጊም አይከስርም› ቢባል ደግሞ ማነው የሚጠየቀው – በጥቅሉ የኦሮሞ ሕዝብ (እና ሌሎችም የደቡብ አካባቢዎች መኖራቸው እንዳይዘነጋ) ቢባል ማነው የሚጠይቅው – የአማራ ሕዝብ፣ የአማራ ሕዝብ ወካይ ፓርቲ (አለው?)፣ ክልላዊ መንግሥቱ (የያኔውን መንግሥት የመወከል ቅቡልነት አለው?) በርካታ ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀርም፡፡ ይቅርታ የሚጠየቅበት በደልስ የትኛው ነው፣ የመስፋፋቱ ነው? በጭሰኝነትና ማስገበሩ ነው? ‹‹በቅኝ አገዛዙ ነው››? ወይስ አገር በቀሉን ስርዓት (እንበል ‹‹ገዳ››ን) በመተካቱ ነው?
ይቅርታው ተሳክቶ ተጠያየቁ እንበልና ከዚያ በኋላ የሚመጣው ምንድን ነው? ሁሉም ባለበት ይረጋል ወይስ እንደአዲስ ዕቅድ ማውጣት እንጀምራለን፡፡ ለደረሰው በደልስ ካሣው ምንድን ነው?
ሕወሓት ሕገመንግሥቱ በራሱ በደሉን ሽሮ ወደአዲስ ምዕራፍ ተሸጋግረናል ባይ ነው፡፡ በሕገመንግሥቱ የተገኘው ነገር የብሔር ፌዴራሊዝሙ ነው፡፡ ፌዴራሊዝሙ ተበዳይ ብሔረሰቦች ያለፈው በደላቸው ባይካሥም እንደአዲስ ግን ራሳቸውን በራሳቸው መገንባት የሚችሉበትን ዕድል ይሰጣቸዋል ተብሎ ታምኗል፡፡ ሆኖም አሁንም የብሔር ጭቆናው ቀጥሏል ብለው የሚያምኑ ልሒቃን አሉ፡፡ በተለይ የኦሮምኛ ቋንቋ የፌዴራል መንግሥቱ የሥራ ቋንቋ መሆን አለበት፤ ራስን በራስ የማስተዳደሩ ሚናም በእውነተኛ የኦሮሚያ ወኪሎች እንጂ በእጅ አዙር በሚገዙ ወኪሎች መሆን የለበትም የሚሉ (ይህ እንደተመልካቹ የሚለያይ እውነት ይሆናል) እና ከዚያም ባለፈ ደግሞ የተቀማነው ‹‹ነጻነት›› (ወይም ራስን የቻለ አገርነት) ካልተመለሰ ጭቆናው ቀጥሏል የሚሉም አሉ፡፡ ካሣው እንደየልሒቁ ይለያያል ማለት ነው፡፡ ምሕረቱም ምሕረት ላይሆን ይችላል፡፡

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ባገኘው መረጃ  የጃን አሞራ፣ የማይጸብሪ አዋሳኝ፣ ራስዳሸንን ጨምሮ የአዲአርቃይን አካባቢዎች ወደ ትግራይ፣ በመተማ በኩል ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመስጠት ድርድር በመካሄድ ላይ ነው። ባለስልጣናቱ ቀደም ብለው የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ አንዳንድ የወረዳ ባላስልጣናት ጉዳዩን ወደ …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ባወጣው መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት መውደሙን ጠቅሷል። ፓርቲው እንዳለው  የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፍተኛ የአመራር ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለ10 ቀናት በአዳማ ከተማ በአክራሪነት እና ሽብርተኝነት ዙሪያ ስልጠና ሲሰጣቸው ከቆየ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ስልጠናው ወደ ታች አመራር አባላት በመውረዱ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች ለ10 ቀናት ያክል ጽህፈት ቤቶቻቸውን ዘግተው ስልጠናውን እየወሰዱ ነው። ህዝቡ  ጉዳይ ለማስፈጽም ወደ ተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲሄድ …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን ውጪ ጉዳይ ምኒስትር የሆነው ባርናባ ማርያል  እንደተናገረው ህዝበ ውሳኔ ባፋጣኝ መደረጉ በአበየ ግዛት ለሚኖሩ ነዋረዎች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሰጥና በውሳኔው መሰረት ነዋሪው ወደ ደቡብ ሱዳን ካልሆነ ወደ ሰሜን ሱዳን መቀላቀል እንደሚችል ገልፅዋል:: የደቡብ አፍረካ ሽምጋይ የሆኑት ታቦ እምቤኪይ የሚመራወ የአፍረካ ከፍተኛው አስፈጻሚው አካል የአብየ ሪፈረደም በዚህ ወር …

ዩኤስ አሜሪካ በሶማልያ እና በሊቢያ በልዩ ኮማንዶዎችዋ ባለፈው የሣምንት መጨረሻ የወሰደችው የጥቃት ርምጃ ከአብራሪ የለሽ የጦር አይሮፕላኖችዋ ይልቅ በልዩ ኃይል ላይ ያተኮረ ሥልት መከተሏን አመላካች ሆኖ ታይቶዋል።

ግዛቲቱን የሚያወድመዉ ጦርነት ለወትሮዉ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ማዕከላዊ መንግሥት እና በሩዋንዳና በዩጋንዳ ይታገዛሉ የሚባሉት የM23 አማፂያን ነበር።ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ ግን የኮንጎ መንግሥት ጦር፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጦር፥ በዉጤቱም ጦር ያዋጡት መንግሥታት እና የአማፂያን እና የአማፂያኑ ደጋፊዎች ዉጊያ ሆኗል።

የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ልዑካን በአዲስ አበባ ከአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ባለሥልጣናት ጋ ምክክር አካሄዱ። ባለሥልጣናቱ ከአንዱ ቀን ውይይት በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ አፍሪቃ በአህጉሯ ለሚታዩ ውዝግቦች መፍትሄ ለማሰገኘት በምታደርገው ጥረትዋ የዓለሙ መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ እንደማይለያት ተገልጾዋል።

ወባ ዛሬም ገዳይ በሽታ ነዉ በተለይ በአፍሪቃ። በበሽታዉ በግምባር ቀደምትነት የሚጠቁት ህጻናትና ነፍሰጡር እናቶች መሆናቸዉን የህክምና ባለሙያዎች ያመለክታሉ። በወባ በሽታ በዓለማችን በየዓመቱ ከሚያልቀዉ ህዝብ ቁጥር 80 በመቶዉ የሚገኘዉ አፍሪቃ ነዉ።

በቅርብ ጊዜ የአውሮፓ የጀልባ ስደተኞች ታሪክ እጅግ አስከፊው አደጋ ነው ። ባለፈው ሃሙስ በኢጣልያዋ የላምፔዱዛ ደሴት አቅራቢያ ወደ 500 የሚጠጉ ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ በእሳት ከተያያዘች በኋላ ሰጥማ የደረሰው አደጋ ። እንደ እድል ሆኖ 155ቱ ቢተርፉም የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 274 ከፍ ብሏል ።

የሰማዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሥለሺ ፈይሳ እንደሚሉት ደግሞ የአዲሱ ፕሬዝዳት አዲስ ነገር በራሳቸዉ ተንቀሳቅሳዉ እንግዳ መቀበል የሚችሉ መሆናቸዉ ነዉ።ዶክተር ሙላቱ ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ የተማሩ፥ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በምክትል ሚንስትርነት፥ በሚንስትርነት፥ በአፈ-ጉባኤነት፥ በአምባሳደርነት ያገለገሉ ናቸዉ።

በዚህች ቅጽበት በጣም ተናድጃለሁ፡፡ አንዳንዴና መጻፍ ስፈልግ በጣም መናደዴን ብዙም አልከፋበትም፡፡ ካልተናደድኩ የምጽፈው ነገር አለ በቂ ምክንያት ሰዎችን እንዳያስቀይም ወይም ለማስደሰት ብቻ አለ በቂ ምክንያት እንዳያስደስት በማደርገው ሀበሻዊ ይሉኝታ አዘል ጥንቃቄ ወረቀት ላይ የሚቀመጠው ነገር አንዳንዴ ለራሴም ስሜት አልባ የሚሆንብኝ አጋጣሚ አለ – ይህንን ስል ግን ተናድጄ የምጽፈው ሁሉ ቱሪናፋ ነው ማለቴ እንዳልሆነ ግንዛቤ እንድትወስዱ […]

‹ዛሬ በናትሽ ዳጎስ ያለ ሰነድ ወይም መጽሐፍ ወይም ዶሴ መብላት አማረኝ›› አለች አንዲት ነጭ አይጥ ለጓደኛዋ፡፡
‹‹ለምን አንዱ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አልወስድሽም›› አለቻት ጥቁሯ አይጥ፡፡

‹‹እኔን ለማስደብደብ ነው እንዴ ፍላጎትሽ›› አለቻት ነጯ

‹‹ማነው ደግሞ የሚደበድብሽ››

‹‹ሠራተኞቹ ናቸዋ››

‹‹ስለ ሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አታውቂም ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥኮ አንድ ነገር የሕዝብ ነው ከተባለ ሁለት ነገር ነው ማለት ነው፡፡ ወይ የማንም አይደለም፤ ወይም የጥቂቶች ብቻ ነው፡፡ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ማለት የማንም ያልሆነ ቤተ መጻሕፍት ማለት ነው፡፡ በጀት የለው፤ ተቆጣጣሪ የለው፤ ባለቤት የለው፡፡ ማዘጋጃ ቤት የባህል ቢሮ ነው ይለዋል፤ የባህል ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው ይለዋል፤ ኮሙኒኬሽን ጽ/ ቤት የወጣቶች ሊግ ነው ይለዋል፤ የወጣቶች ሊግ የሕዝብ ነው ይለዋል፡፡ ስንትና ስንት የጥንት መጽሐፍ ባለቤት ስላጣ ማንም ዘወር ብሎ አያየውም፡፡ ይልቅ ተነሽ እንሂድ››

ተያይዘው ሄዱ፡፡ ገቡ፡፡ አንድ አስነባቢ ገቢያቸውን ለብሰው ጠረጲዛ ላይ ክንዳቸውን ተንተርሰው ሸለብ አድርገዋል፡፡ አይጦቹ በበሩ ሲገቡ እንኳን አላዩዋቸውም፡፡

‹‹ያንን መጽሐፍ አውርጂው›› አለቻት ጥቁሯ፡፡ ነጯ አይጥ ሄደችና አወረደችው፡፡ ዳስ ካፒታል የሚለው የማርክስ መጽሐፍ ነው፡፡ ‹‹ለእኔ ደግሞ እዚያ ማዶ ያለውን አምጭልኝ›› አለቻት፡፡ ኦክስፎርድ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ነው፡፡ ሁለቱም ተቀምጠው መቆርጠም ጀመሩ፡፡

አስነባቢው የሆነ ድምጽ ስለሰሙ ቀና አሉና መልሰው ተኙ፡፡

‹‹እንዴ በሙሉ የድሮ መጽሐፍ ብቻ ነው እንዴ›› አለች ነጯ አይጥ፡፡

‹‹እዚህ ከተማ ለስብሰባ፣ ለድግስ፣ ለቲሸርት፣ ለኮፍያ፣ ለቢል ቦርድ፣ ለሲምፖዝየም፣ ለምናምን መታሰቢያ ቀን፣ ለምናም መመሥረቻ ቀን የሚሆን በጀት እንጂ ለዕውቀት የሚሆን በጀት የለም፡፡ አታይም ሠላሳ ሺ ሕዝብ የሚይዝ ኮንዶሚንየም ሲገነባ በግ ማረጃ እንጂ ቤተ መጻሕፍት ተገንብቷል? ለመጠጥ ቤት፣ ለጫት ቤት፣ የሚሆን ቦታ ግን ሕንጻዎቹ ሥር ተሠርቷል፡፡ ምክንያቱም ብዙዎቹ በየቢሮው ያሉት ከዕውቀት የጸዱ፣ ከሆድ የተዛመዱ ናቸዋ፡፡ ያለ አእምሮ ልማት ቁሳዊ ልማት ከየት ይመጣል፡፡ መገንባት ብቻውን አያለማምኮ፡፡ የገነባሽውን በሚገባ የሚጠቀም፣ የሚከባከብ፣ እድሜውን የሚያረዝም፣ እሴት የሚጨምርም ዜጋ ያስፈልጋል፡፡ በጎጆ አስተሳሰብ ዘጠኝ ፎቅ ላይ መኖር ትርፉ በረንዳ ላይ በግ ማረድ ነው፡፡ ከወረቀት ግብር የቢራ ግብር በሚቀንስባት ሀገር፤  ኪነ ጥበብ ከማይበረታቱ ኢንዱስትሪዎች መደብ በተመደበባት ሀገር ምን ትጠብቂያለሽ›› አለች ጥቁሯ፡፡

‹‹ባለፈው አንዲት ጓደኛዬን ለአዲስ ዓመት ወጣ ብለን እንዝናና ስላት የት እንደወሰደችኝ ታውቂያለሽ››

‹‹ዱከም ወስዳ ሥጋ ጋበዘችሽ››

‹‹ኧረ አይደለም፤ አቃቂ››

‹‹አቃቂ ደግሞ ምን አለ?››

‹‹ድሮ በደርግ ጊዜ ኩራዝ አሳታሚ እያለ ሊታተሙ የተሰበሰቡ ረቂቆች አሉ ብላ ይዛኝ ሄደች፡፡ አንድ ትልቅ የቆርቆሮ መጋዘን ውስጥ ተከምረውልሻል፡፡ እዚያ ይዛኝ ገባች፡፡ እዚህ ሀገር የታወቁ ደራስያንን ሥራ ስንከሰክስ ስንከሰክስ ዋልንልሽ፡፡ አንዳንዱ ታርሟል፤ አንዳንዱ አልፏል የሚል ተጽፎበታል፡፡ አንዳንዱ ማኅተም አለው፡፡

‹‹ዝም አሏችሁ››

‹‹ማንም ዝር አይልም ከአይጥ በቀር አሉ የለመዱትማ ሲነግሩን››

‹‹ወይ ይህቺ ሀገር፣ ከገዛ ታሪኳና ቅርሷ፣ ከገዛ መዛግብቷና ሰነዶቿ ጋር የምትጣላ ሀገር፡፡ ባለፈው የባድሜ  ጉዳይ በዓለም ፍርድ ቤት ሲዳኝ አንዱ የተጠየቅነው ሰነድ ነበር አሉ፡፡ የተቆረጠ ደረሰኝ፣ የተሰጠ ሹመት፣ ከዚያ አካባቢ የተጻፈ ነገር፣ የሐኪም ቤት ካርድ፣ ያ ቦታ የኢትዮጵያን እንደነበረ የሚያሳይ ዶሴ አምጡ ተብሎ ነበር አሉ፡፡ እዚህ ሀገርኮ ስንቱ ፋይል፣ ስንቱ ዶክመንት፣ ስንቱ ደብዳቤ፣ ስንቱ መረጃ አሮጌ ነው እየተባለ ተጥሎ በየቆርቆሮው ቤት ታሽጎበታል መሰለሽ፡፡ ለኛማ ሠርግና ምላሽ ነው፡፡ እርሱን እየበላን እንኖራለን፡፡ ሀገሪቱ ግን ታሳዝናለች፡፡››

‹‹ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት የሚባል ድርጅት አለ አይደል እንዴ››

‹‹አንድ ለእናቱ የሆነውን ነው የምትይኝ? ይኼው ሰማንያ ዓመት ሆኖታል አንድ ለእናቱ ነው፡፡ እስኪ ክልል ውረጅ አንድ የመዛግብት ማዕከል ታገኛለሽ? በተለይማ ባለፉት ሥርዓቶች የነበሩ መዛግብት የጠላት ገንዘብ ተደርገው የማንም መጫወቻ ሆነዋል፡፡ ወይ ቆርቆሮ ቤት ገብተዋል፤ ወይ ተቃጥለዋል፤ ያለበለዚያም በኪሎ ተሸጠዋል፡፡››

‹‹ይበላቸው እባክሽ፤ እነርሱ በዘመናቸው እኛ ድርሽ እንዳንል ድመት ለሚያረባ ሰው የድመት መሬት እየሰጡ አሳድደውናል፡፡ይኼው ዛሬ የሀብታም መሬት እንጂ የድመት መሬት የለ፡፡እንደልባችን ታሪክ ስንበላ እንውላለን፡፡››

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ በሽታ መቼ ተከሰተ፣ የት የት ቦታ ተከሰተ፣ ምን ያህል ሕዝብ ተያዘ፣ ምን ተደረገ፣ መቼ ጠፋ? ብለሽ ብትጠይቂ መልሱ ያለው የት እንደሆነ ታውቂያለሽ?››

‹‹ጤና ጥበቃ ነዋ››

‹‹ተሳስተሻል፡፡ እኛ ሆድ ውስጥ ነው፡፡ የሆስፒታል የድሮ ካርዶችኮ እንድንበላቸው ተፈቅደውልን የተከፋፈተ መጋዘን ውስጥ ተጥለዋል፡፡ እንደ ጓያ ነቃይ የዛሬን እንጂ የነገን የሚያስብ የለም፡፡ አሁንኮ ሀገሪቱ ስላደገች የወዳደቀ ትራፊ ሳይሆን አልፎልን ታሪክና መረጃ ነው የምንበላው፡፡ አንዳንድ መረጃዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን አሉ ጋዜጠኞች፡፡ የሚደርሰውኮ ወደኛ ነው፡፡›› 

‹‹አንድ ነገር አስታወስሽኝ፡፡ ከሆነ ዓመት በፊት አንድ ትልቅ ባለ ሥልጣን የተናገረው ነገር፡፡ ኢሕአዴግ ባሕርዳር ሲገባ እነርሱ የኢሠፓ ጽ/ቤት ነበር ያደሩት፡፡ ብርድ ስለነበር ሌሊቱን ፋይል እያነደዱ ሲሞቁ፡፡ በመካከል የአንድ ደራሲን ልቦለድ አግኝቶ እንዳነበበውና አዲስ አበባ ፈልጎ እንደሰጠው ሲናገር ነበር፡፡ አሁን ሰነድ ማቃጠል፣ ፋይል ማንደድ በቴሌቭዥን በኩራት የሚቀርብ ገድል ነው?ሰዎቹ ናቸው እንጂ ኢሠፓ ፋይሉኮ ኢሠፓ አይደለም፡፡ ፋይሉማ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው፡፡››

‹‹የኢትዮጵያን ዕቃ ገዥ ከሌላው ዓለም ገዥ የሚለየው አንዱ ነገር ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?››

‹‹አላውቅም››

‹‹ሌላው በተራ ወረቀትና ፌስታል ዕቃውን ይጠቀልላል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን በታሪካቸው ስለሚኮሩ በታሪካዊ መዛግብትና ሰነዶች፣ በታሪካዊ ደብዳቤዎችና ፋይሎች ዕቃቸውን ይጠቀልላሉ፡፡ በየሱቁ ከምትገዥው ስኳር በላይ ባለ ሱቁ የጠቀለለበት ፋይል ዋጋው ውድ ነው፡፡

‹‹ባክሽ አሁን ወሬውን ትተን እነርሱ ሙስናቸውን እኛ ታሪካችንን እንብላ፡፡››

ቆርጠም ቆርጠም ሲል አስነባቢው ቀና አሉ፡፡ እንዳጋጣሚ አንድ አንባቢ ገብቷል፡፡

‹‹አባት፣ አይጥ ሳይሆን አይቀርም›› አላቸው፡፡

‹‹ባክህ በጨረሱትና እኔም ወደሌላ ቦታ በተዛወርኩ ይሻለኝ ነበር›› አሉት፡፡

ቆርጠም፤ ቆርጠም፤ ቆርጠም

ታሪክ እንበላለን፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

በዚህች ቅጽበት በጣም ተናድጃለሁ፡፡ አንዳንዴና መጻፍ ስፈልግ በጣም መናደዴን ብዙም አልጠላውም፡፡ ካልተናደድኩ የምጽፈው ነገር አመዛዛኝ ይሆንና ሁሉንም አለ በቂ ምክንያት ላለማስቀየም ወይም አለ በቂ ምክንያት ላለማስደሰት በማደርገው ጥረት ወይም ጥንቃቄ የምጽፈው ነገር ለራሴም ስሜት ያጣብኛል፡፡ ተናድጄ ስጽፍ ግን ስሜቴን እንደወረደ ወረቀት ላይ አየዋለሁ፡፡ እርግጥ ነው – ተናድዶ መጻፍ ‹ሪስክ› አለው፡፡ ሰዎችን ልታስቆጣ ትችላለህ፡፡ በሌላም በኩል […]

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሦስተኛው  የ ኢህአዴግ ፕሬዚዳንት በመሆን በ አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ምትክ ተሾሙ። የኢህአዴግ/ኦህዴድ አባል የሆኑት  ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የዛሬ 12 ዓመት አካባቢ ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳን በመተካት ሁለተኛው ፕሬዚዳንት እንደሚሆኑ በስፋት የተወራ ቢሆንም፤”ፕሬዚዳንት ሆኖ የሚመረጠው ሰው የማናቸውም ፓርቲ አባል ያልሆነ ገለልተኛ ሰው መሆን …

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት 3 አመታት ጀምሮ በክልሉ ከመልካም አስተዳደር እና ከሰዎች መፈናቀል ጋር በተያያዘ የሚታየው ችግር እየተባባሰ በሚገኝበት ሁኔታ የክልሉን ባለስልጣናት ለመምረጥ በአዋሽ አርባ ታንከኛ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ ስብሰባ እየተካሄ ነው። ከፍተኛ የህወሀት ድጋፍ አላቸው የሚባሉት የአቶ እስማኤል አሊሴሮ ደጋፊዎች በአንድ በኩል ፕሬዚዳንቱን የሚቃወሙ ሰዎች በሌላ በኩል ሆነው በስብሰባው …