መንግሥት የሕዝብን የልብ ትርታ ያዳምጥ!
የአመራር የጥበብ መጀመርያ የሕዝብን የልብ ትርታ ማዳመጥ ነው፡፡ ችግርን ለይተው ካላወቁ ትክክለኛ መፍትሔ ለማስቀመጥና ለመስጠት ያስቸግራል፡፡ ችግርን ለይቶ ለማወቅ ደግሞ ሕዝብን ማዳመጥ ያስፈልጋል፡፡ የሚፈታው ችግር የሕዝብ ችግር ነውና፡፡
የአመራር የጥበብ መጀመርያ የሕዝብን የልብ ትርታ ማዳመጥ ነው፡፡ ችግርን ለይተው ካላወቁ ትክክለኛ መፍትሔ ለማስቀመጥና ለመስጠት ያስቸግራል፡፡ ችግርን ለይቶ ለማወቅ ደግሞ ሕዝብን ማዳመጥ ያስፈልጋል፡፡ የሚፈታው ችግር የሕዝብ ችግር ነውና፡፡
– ለግንባታው በኪሎ ሜትር 12.5 ሚሊዮን ዶላር ተጠይቋል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ መስቀል አደባባይ ድረስ (አፍሪካ ጎዳና) ያለውን 4.1 ኪሎ ሜትር መንገድ ለመገንባት የተጠየቀው የግንባታ ወጪ እጅግ የናረ በመሆኑ ፕሮጀክቱ በድጋሚ እንዲጤን መመርያ ሰጡ፡፡
የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በቅርቡ 45 በመቶ የሚሆን የማሳተሚያ ዋጋ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ ሌሎችም ማተሚያ ቤቶች ተመሳሳይ ጭማሪ በማድረጋቸው፣ በሁሉም ማተሚያ ቤቶች የሚታተሙ ጋዜጦችና መጽሔቶች የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ እንዳንዣበባቸው፣ የጋዜጣና መጽሔት አሳታሚዎች አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ ‹‹የጋዜጣና መጽሔት ሕትመት ዋጋ ጭማሪ …
‹‹የጋዜጣና መጽሔት ሕትመት ዋጋ ጭማሪ ለፕሬስ ነፃነት አደጋ ነው›› የጋዜጣና መጽሔት አሳታሚዎች አስተባባሪ ኮሚቴ Read more »
የኢትዮጵያ መንግሥት የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻሪፍ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ያቀረቡትን ጥያቄ እያጤነው እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ግብፅ በይፋ የጉብኝት ጥያቄዋን ለኢትዮጵያ ብታቀርብም፣ ጥያቄዋ እየታየ ነው፡፡
በደቡብ ክልል የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የ13 ሆቴል ባለንብረቶችን በተጨማሪ እሴት ታክስ (በቫት) ማጭበርበር በመጠርጠራቸው በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ታወቀ፡፡ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ባለሆቴሎች መካከል የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ማረጋጫ ሰርተፍኬት ያላቸው ይገኙበታል፡፡
በተጠረጠሩበት የወንጀል ክስ ላይ መቃወሚያ አቅርበው፣ በቀረበው የመቃወሚያ መልስ ላይ ብይን ለመስጠት ለትናንትና ተቀጥረው የነበሩት የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ለይኩንን ጨምሮ አሥር ተከሳሾች በድጋሚ ለብይን ተቀጠሩ፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው የወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተብለው በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ከተወሰነባቸው የግንቦት 7 ተከሳሾች መካከል፣ የብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞና የአቶ አሳምነው ጽጌ ንብረት ቤተሰቦቻቸውንና ዓቃቤ ሕግን እያከራከረ ነው፡፡
– ባለሀብቶች ላይ ጫና የሚያሳድር አሠራር እንዲኖር ይፈለጋል በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በሠራተኞች የመደራጀት መብት ላይ እየተፈጠረ ያለውን ችግር ለመቅረፍ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ከሠራተኛ ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በውይይት ላይ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታወቀ፡፡
ባህር ዳር ከተማ ከመደረሱ በፊት ከእንጅባራ ከተማ በስተግራ 100 ኪሎ ሜትር ላይ የቤኒሻንጉል ክልል ትልቁ ዞን የሆነው መተከል ይገኛል፡፡ ለዘመናት ተረስቶ የቆየው ይህ ዞን አሁን ሁለት ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል፡፡የመጀመርያው በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ታላቁ የሚሌኒየም ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ …
በውድነህ ዘነበ | ሪፖርተር በዓባይ ወንዝ ላይ ሁለት ግድቦችን ለመገንባት የሚያስችል ጥናት በማካሄድ ላይ የነበረ አነስተኛ ሔሊኮፕተር ባለፈው ሰኞ ወድቆ ተከሰከሰ፡፡ ሔሊኮፕተሩ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ቆንጮ አካባቢ ተነስቶ መንድያና ቤኮ አቦ በተባሉት ቦታዎች ላይ ለሚካሄዱ ሁለት አዳዲስ ግድቦች ጥናቶችን ሲያካሂድ፣ ድንገት …
– በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ተቃውመውታል በአዲስ አበባ ከተማ በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ውስጥ በባለሀብቶች እየተገነቡ ላሉ ግንባታዎች መከለያነት የሚታጠሩ አጥሮች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ አስተዳደሩ ጥር 27 ቀን 2003 ዓ.ም. ትዕዛዝ ማስተላለፉ ታወቀ፡፡
በየማነ ናግሽ | ሪፖርተር የሐረሪ ክልል የመሬት አስተዳደርና የካሳ ክፍያ ኃላፊ የነበሩት አቶ ሐሺም ኢድሪስ በጥይት ተመትተው አዲስ አበባ ኮርያ ሆስፒታል ከተወሰዱ በኋላ ከትናንት በስቲያ ሕይወታቸው ማለፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ረዳት ሳጅን አባስ መሐመድ …
የሐረሪ ክልል የመሬት አስተዳደር ሹም አቶ ሐሺም ኢድሪስ በጥይት ተመትተው ተገደሉ Read more »
የሐረሪ ክልል የመሬት አስተዳደርና የካሳ ክፍያ ኃላፊ የነበሩት አቶ ሐሺም ኢድሪስ በጥይት ተመትተው አዲስ አበባ ኮርያ ሆስፒታል ከተወሰዱ በኋላ ከትናንት በስቲያ ሕይወታቸው ማለፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
– ኢሬቴድ ያስተላለፈውን ማስታወቂያና የድራማውን ቅጅ እንዲያቀርብ ታዘዘ በዕለተ እሑድ ለአንድ ዓመት ሲተላለፍ የነበረውና አድናቆትን ያተረፈው የገመና ቁጥር ፩ ተከታይ ገመና ቁጥር ፪ ድራማ ላይ ቀርቦ የነበረው የእግድ ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ፡፡
በነጠላ አሀዝ ደረጃ ወርዶ በቁጥጥር ሥር ውሏል ተብሎ የነበረው የዋጋ ግሽበት በበጀት ዓመቱ መባቻ ላይ የተደረገውን የምንዛሪ ለውጥ ተከትሎ የጀመረውን የሽቅብ ጉዞ በመቀጠል፣ ባለፈው መጋቢት ወር 25 በመቶ መድረሱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ አደረገ፡፡
(ሪፖርተር) — ዱባይ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሠራተኛ የአሠሪዋን ብልት በመቁረጧ ምክንያት በቁጥጥር ሥር መዋሏን ኤማራት አል ዮም ዘግቧል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው የሰባ ዓመቱ አዛውንት ሁኔታውን ለፖሊስ ያስታወቁት ሰኞ ጧት ሲሆን፣ ኢትዮጵያዊቷም ድርጊቱን ለመፈጸሟ የእምነት ቃሏን ሰጥታለች፡፡ ‹‹በሰውዬው በሚፈጽምብኝ ማስፈራራት ተሰላችቻለሁ፤›› ነበር …
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚገባቸው የጦርነት ቋንቋ ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ ከ10 ዓመት በፊት በጠራራ ፀሐይ አሻፈረኝ ያሉትን የሰላም ሐሳብ በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ለነበሩት ኮፊ አናን እኩለ ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው ቀስቅሰው ተንበርክከው እቀበላለሁ ባላሉ ነበር፡፡
አምባሳደር ዶክተር ተውፊቅ አብዱላሂ ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ከሱዳን ጠረፍ 40 ኪሎ ሜትር ላይ በምትገኘውና ቡምባዲ በምትባለው አካባቢ የሚገነባውን ታላቁ የሚሌኒም ግድብ የመሠረት ግንባታን መርቀዋል፡፡
መንግሥት ያዘጋጀው የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ረቂቅ አዋጅ ሰሞኑን ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ረቂቅ አዋጁ በፕሮቪደንት ፈንድ ታቅፈው ላልነበረ የግል ድርጅት ሠራተኞች ዋስትና እንደሚሰጥ የማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ይገልጻል፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንድ የግል ድርጅት ተቀጣሪዎች ረቂቅ አዋጁን በበጐ ጐኑ የተመለከቱት …
በሦስት ምስክሮች ምክንያት አይጥ ዝሆን ነሽ ተብሎ ተፈረደባት›› ዝሆኖች እንዲታሰሩና ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተላለፈ፡፡ በደረሳቸው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረትም ፖሊሶች ዝሆኖችን ማሰር ጀመሩ፡፡ ዝሆኖች ሲታሰሩ በዝሆኖች እግር ሥር ተደናግጣ ስትሽሎኮሎክ የነበረችው አይጥም፣ ከዝሆኖቹ ጋር አብራ ታሰረች፡፡ ከዝሆኖቹ ጋርም ፍርድ …
– ሱዳን በቅርቡ ከግብፅ ጐራ ልታፈነግጥ ትችላለች በዘካሪያስ ስንታየሁ አዲሱ የግብፅ መንግሥት በዓባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሊነሳ በሚችል ግጭት ምክንያት ሠራዊቱን በተጠንቀቅ እንዲቆም ቢያዝም፣ የግብፅ የጦርነት እንቅስቃሴ ትኩረት ለማስቀየር መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ፡፡
በውድነህ ዘነበ | ሪፖርተር የግብፁ የማዕድን ኩባንያ አስኮም የሚሌኒየም ግድብ በሚገነባበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ባካሄደው የወርቅ ፍለጋ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ማግኘቱ ተረጋገጠ፡፡ የግብፁ ኩባንያ አስኮም ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ በክልሉ 8,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ ወርቅና የከበሩ …
በውድነህ ዘነበ የግብፁ የማዕድን ኩባንያ አስኮም የሚሌኒየም ግድብ በሚገነባበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ባካሄደው የወርቅ ፍለጋ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ማግኘቱ ተረጋገጠ፡፡
አንድነት ፓርቲ – መድረክ ዛሬ በመቀሌ ለጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይቀሰቅስ መከልከሉን ገለጸ በየማነ ናግሽ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሰሞኑን ‹‹ሽብርና አመፅን ከሚቀሰቅሱ መካከል›› ያሉዋቸውን የአንድነት የፓርቲ አባላት ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅ የሚቀሰቀስ ከሆነ የእንቅስቃሴው …
– እያንዳንዳቸው በአሥር ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ በታምሩ ፅጌ የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር ፕሬዚዳንት የነበሩትን አቶ ለይኩን ብርሃኑን ጨምሮ አሥሩም ተጠርጣሪዎች ከመጋቢት 28 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ከአገር እንዳይወጡ በፍርድ ቤት እግድ ተጣለባቸው፡፡
በአስራት ሥዩም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ቀደም ሲል በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረውን የብድር ገደብ በማንሳት የግምጃ ቤት ሰነድ ግዢ መመሪያ ካወጣ በኋላ፣ ባንኮቹ ካለፈው ሐምሌ 2002 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 2003 ዓ.ም. ድረስ ለሰጡት ብድር 27 በመቶ …
በታምሩ ጽጌ ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ሸራተን አዲስን ከመገንባታቸው በፊት በነፃ ቤት ሠርተው እንደሰጧቸውና ይዞታውም የእነሱ እንደሆነ በወቅቱ እንደነገሯቸው የሚገልጹት ሆቴሉ ከተሠራበት ቦታ ላይ ተነስተው ወደ ሲኤምሲ የተዛወሩ በርካታ ነዋሪዎች፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቱ የራሱ መሆኑን በመግለጽ ሊነጥቃቸው መሆኑን …
በውድነህ ዘነበ በዓባይ ወንዝ ላይ ለሚገነባው የሚሌኒየም ግድብ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን የተጀመረው የሚሌኒየም ቦንድ ሽያጭ በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ትኩረት እየሳበ ሲሆን፣ ግዢውን ለመፈጸም በርካታ ሰዎች የኢትዮጵያ ልማት ባንክንና የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮችን እያጨናነቁ ነው፡፡
በየማነ ናግሽ የደቡብ ኮርያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በግብርና ልማትና በማዕድን ፍለጋ ኢንቨስትመንት ሊሠማሩ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በታምሩ ጽጌ እና በለምለም ፀጋይ የአያት አክሲዮን ማኅበር ዋና ባለድርሻና ሥራ አስኪያጁ አቶ አያሌው ተሰማ፣ ዶ/ር መሐሪ መኮንንና አቶ ጌታቸው አጐናፍር መጋቢት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ካቀረቧቸው አምስት የመከላከያ ምስክሮች አራቱን አሰሙ፡፡
በየማነ ናግሽ | ሪፖርተር በመጪው ዓመት መጀመሪያ ወራት የኤርትራ ሕዝባዊ ኮንፈረንስ ለማካሄድና ከአገር ውጭ ብሔራዊ ሸንጐ ለመመስረት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ብሔራዊ ኮሚሽን፣ የኤርትራ ነፃነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በመጪው ግንቦት ዓለም አቀፍ ሠልፍ እንዲካሄድ ወስኗል፡፡ ከተመሠረተ ስድስት ወር የሆነውና በመጪው ጥቅምት ወር …
በታምሩ ጽጌ የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበርን ከ13 ዓመታት በላይ በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ለይኩን ብርሃኑን ጨምሮ፣ በባንኩ የውጭ ምንዛሪ ዲፓርትመንት ውስጥ ይሠሩ የነበሩ አሥር ከፍተኛ ኃላፊዎች መጋቢት 9 ቀን 2003 ዓ.ም. ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ከትናንት በስቲያ በዋስ ተለቀቁ፡፡
– ክልሎች ዕቅዱን በቁጥቁጥ የተዘጋጀ ሲሉ ተቹት– ለአቶ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ የቱሪዝም አባትነት ዕውቅና ተሰጠ በብርሃኑ ፈቃደና በሔኖክ ያሬድ
በውድነህ ዘነበ ኢትዮጵያ ከዓለም የስኳር ገበያ ድርሻ እንዲኖራት የተቀረጸው የስኳር ልማት ዕቅድ 75 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለታል፡፡
በታምሩ ጽጌ የሸራተን አዲስ ሆቴል ባንኩዌት በተባለው የሥራ ዘርፍ በምግብና መጠጥ አቅራቢነት ላይ ይሠሩ ለነበሩ 19 ሠራተኞች የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሆቴሉ እንዲያገኙ ፍርድ የሰጠባቸውን 11 ውሳኔዎች በመቃወም፣ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ‹‹ያስቀርባል›› በመባሉ ሊከፈላቸው የነበረውን የጥቅማ ጥቅም …
በኃያል ዓለማየሁ አዳማ በሚገኘው በኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ቅርንጫፍ መሥርያ ቤት ያገለግሉ የነበሩት አቶ ጄሉ ሁሌ የተባሉ የጥበቃ ሠራተኛ፣ ከትናንት በስቲያ ከንጋቱ 12፡30 ጀምሮ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የአዳማ ከተማን በመሣርያ ተኩስ ካሸበሩ በኋላ ሁለት ሰዎችን ገድለው እሳቸውም መገደላቸው ተገለጸ፡፡
‹‹ሒደቱ በዚሁ ከቀጠለ ሽምግልናውን ለማቆም ወስኛለሁ›› የአስታራቂ ኮሚቴው ሊቀመንበር በኃይሌ ሙሉ በእነ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በሚመራው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲና በእነፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ቡድን መካከል በአስታራቂ ሽማግሌዎች አማካኝነት ሲካሄድ የቆየው ድርድር መቋጫ ከማግኘት ይልቅ፣ ወደኋላ እየተጎተተ መሆኑን የአስታራቂ ኮሚቴው …
በብርቱካን ፈንታ ለሦስተኛ ጊዜ በአፍሪካ አስተዳደር ላይ ለሚደረገው ጥናት “ምርጫና የብዙህነት አስተዳደር በኢትዮጵያ” በሚል የኢትዮጵያን ክፍል የሚያጠኑ ታዋቂ ግለሰቦችና ምሁራኖች ታወቁ፡፡
በውድነህ ዘነበ የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን ከወጣ በዚህ ዓመት አሥረኛ ዓመቱን በማስቆጠሩና የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈ በመሆኑ በድጋሚ እንዲከለስ ካቢኔው ውሳኔ አሳለፈ፡፡
“ዋጋ የተጨመረው የቀዝቃዛ ውኃ ታሪፍ ስለጨመረ ነው” ድርጅቱ“ይህን ያህል ጭማሪ መደረጉ ተገቢ አይደለም” ተገልጋዮች በብርቱካን ፈንታ የአዲስ አበባ የፍል ውኃዎች ድርጅት በደንበኞቹ ላይ ከየካቲት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ የ35 በመቶ ጭማሪ አደረገ፡፡
በዘካሪያስ ስንታየሁ | ሪፖርተር ለመለስ ዜናዊ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ዘመናዊ ቤት በአራት ኪሎ የምኒልክ ቤተ መንግሥት ውስጥ እየተገነባላቸው ነው፡፡ አዲስ የሚገነባው ቤት እርሳቸውን የሚጐበኙ እንግዶች የሚያርፉባቸውን የእንግዳ መቀበያ ቤቶችን ያካትታል፡፡ ኢሕአዴግ የደርግን አገዛዝ በ1983 ዓ.ም ከሥልጣን ካስወገደ በኋላ …
በኃያል ዓለማየሁ በመስተንግዶ ዘርፍ ለተሠማሩ ድርጅቶች ሚኒ ባሶችን ከውጭ ለማስገባት ተፈቅዶ የነበረው የቀረጥ ነፃ መብት ተነሳ፡፡
– በ668 ሺሕ ብር የተሰጠ ኮንትራትም በ115 ሺሕ ብር እንዲሠራ ተደረገ በታምሩ ጽጌ ከተቆረቆረች 400ኛ ዓመቷን ባለፈው ዓመት በጥር ወር 2002 ዓ.ም. ያከበረችውና በሰሜን ጐንደር ዞን ውስጥ የምትገኘው የዳባት ወረዳ ከተማ የውኃ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የቴክኒክ ቁጥጥር ባለሙያና አንድ …
በውድነህ ዘነበ የጥጥ እርሻ ባለቤቶች በዚህ ሳምንት ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከኒያላ ኢንሹራንስ ጋር በሚያካሂዱት ስብሳባ ምናልባት በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በኮንትራት ስምምነት የሚቀርብ አንድ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር ሊያገኙ እንደሚችሉ የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡
– በ70 ሚሊዮን ዶላር የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ እየገነባ ነው በውድነህ ዘነበ መንግሥት ከቱርኩ ግዙፍ ኩባንያ ሴሌን ቴክስ ጋር በሽርክና አዲስ የጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ኩባንያ አቋቋመ፡፡
– ‹‹አንድ ተራ አስከባሪ በቀን ከ3,000 እስከ 5,000 ብር ያገኛል›› የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ በታምሩ ጽጌ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በከተማው የሚገኙትን 8,500 ታክሲዎችን በአምስት ቀጣናዎች ለማሠማራት ያጠናው ጥናት የተሟላና ችግርን የሚቀርፍ ሳይሆን፣ ችግሩን ይበልጥ ሊያባብስ እንደሚችል …
በየማነ ናግሽ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኒው ዮርክ ያደረጉትን ጉብኝት በማስመልከት ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የኤርትራ መንግሥት ከሽብር ተግባሩ ለመታቀብ ባለመቻሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማሳወቁን ገለጹ፡፡
– የስድስት ሚሊዮን ብር ‹‹ስዊች ጊር›› ሊወጣ ሲል ተያዘ በታምሩ ጽጌ በሸራተን አዲስ ሆቴል ለረጅም ዓመታት በከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩት የሆቴሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅና የሰው ሀብት ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ከመጋቢት 5 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራቸውን መልቀቃቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
በውድነህ ዘነበ የህንዱ ኩባንያ ኤስኤንድፒ ኢነርጂ ሶሉሽን ኩባንያ የቅባት እህሎችንና አዝርዕትን ለማልማት በቤንሻንጉል ጉምዝ 50 ሺሕ ሔክታር መሬት ተረከበ፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ-ሙን ኢትዮጵያዊቷን አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን፣ በኬንያ ናይሮቢ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው እንዲያገለግሉ ሾሟቸው፡፡