የመጠጥ ፋብሪካዎች ለአዳማ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ክፍያ ተጠየቁ

በዳዊት ታዬ

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት በአዳማ ከተማ የሚገኙ የቢራና የለስላሳ መጠጥ ፋብሪካዎች አከፋፋይ ቅርንጫፎች ‹‹ለደረቅ ቆሻሻ ክፍያ›› በማለት እያንዳንዳቸው ከግማሽ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር የሚሆን ክፍያ በየዓመቱ እንዲከፍሉ አዘዘ፡፡