– ሦስት ኮንትራክተሮች ለመጀመሪያ ጊዜ የፌዴራል መንገድ ሥራ ተረከቡ (በዳዊት ታዬ) የተለያዩ የመከላከያ ፕሮጀክቶችን ብቻ በመሥራት የሚታወቀው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ፣ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ የሚጠይቁ የመንገድ ግንባታዎችን ተረከበ፡፡ ሦስት የግል ኮንትራክተሮች ለመጀመሪያ ጊዜ በፌዴራል የመንገድ ግንባታ …

መከላከያ ኮንስትራክሽን የሁለት ቢሊዮን ብር የመንገድ ግንባታ ሥራ ተሰጠው Read more »

– ተቋማቱ በዓመት በአማካይ 35 ሺሕ ተማሪዎችን ይመዘግቡ ነበር(በምዕራፍ ብርሃኔ) በደቡብ ክልል የሚገኙ 42 የግል ትምህርት ተቋማትና ኮሌጆች ከነቅርንጫፎቻቸው በድምሩ 73 ማሠልጠኛዎች፣ ለ2003 ዓ.ም. ምዝገባ እንዳያካሂዱ ታገዱ፡፡

– መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ጠየቁ (በታምሩ ጽጌ) በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በተከሰሱበት ወንጀል እንዲከላከሉ ብይን የተላለፈባቸው የአስካሉካን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አራት ሠራተኞች፤ ቤተሰቦቻቸው አደጋ ውስጥ መሆናቸውን ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ሁለተኛ ቢፒአር ችሎት ትናንትና አስታወቁ፡፡

(በሚካኤል ተወልደ) ትናንት ረፋዱ ላይ ከኮልፌ 18 ማዞሪያ እስከ ፖሊስ ማሰልጠኛ አካባቢ ባለው ሥፍራ ሁለት ኮንቴይነሮችን የጫነ ከባድ የጭነት መኪና ባደረሰው አደጋ በሰው፣ በእንስሳትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ፡፡

(በታምሩ ጽጌ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት (መድረክ) በትናንትናው ዕለት ባደረገው 3ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ዝግ ስብሰባ የአባላቱን ሙሉ የድምፅ ድጋፍ በማግኘት ከጥምረት ወደ ግንባርነት መሸጋገሩን ምንጮች ገለጹ፡፡ በአመራሮች ላይም ለውጥ ያደረገ ሲሆን ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው የግንባሩ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ለአገሪቱ ኢንጂነሪንግ ዘርፍ አዲስ ኮርፖሬሽን በ10 ቢሊዮን ብር ካፒታል አቋቋመ (በውድነህ ዘነበ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአገሪቱ የሚገኘውን የኢንጂነሪንግ ዘርፍ ወደላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ያለውን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በ10 ቢሊዮን ብር አቋቋመ፡፡

(በውድነህ ዘነበ) የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አካሂዶት የነበረውን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በሚል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውድቅ ማድረጉን አዲስ የተመረጠው የአንበሳ ባንክ ቦርድ አጥብቆ ተቃወመ፡፡

– አዳዲስ ምርቶቹን አስተዋወቀ (በታምሩ ጽጌ) በዓለም ላይ በሴሚ ኮንዳክተር ቴሌኮሙዩኒኬሽን፣ ዲጂታል ሚዲያና ዲጂታል ሚዲያ ኮንቨርጀንስ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ሽያጭ የሚታወቀው የደቡብ ኮሪያው ሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ሊትድ፣ በሚቀጥሉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የመገጣጠሚያ ፋብሪካ ውስጥ እንደሚከፍት አስታወቀ፡፡