የቤይሩት አውሮፕላን አደጋ ሪፖርት አለመውጣት እንቆቅልሽ ሆኗል

– የሊባኖስ የፖለቲካ ቀውስ በመላምትነት ቀርቧል

በቃለየሱስ በቀለና በመላኩ ደምሴ

የዛሬ ዓመት ጥር 25 ቀን 2002 ዓ.ም. ከሊባኖስ ርዕሰ መዲና ቤይሩት ራፊቅ ሐሪሪ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወዲያውኑ ሜዲትራኒያን ባህር ላይ ድንገተኛ አደጋ የደረሰበት አውሮፕላን የአደጋ ሪፖርት ትናንት ይወጣል ተብሎ ቢጠበቅም ይፋ ሳይሆን ቀረ፡፡