በደርግ ባለሥልጣናት ጉዳይ ላይ የሃይማኖት መሪዎቹ የአቅጣጫ ለውጥ ሊያደርጉ ነው
በዘካሪያስ ስንታየሁ አራቱ የሃይማኖት መሪዎች የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የይሁንታና የይቅርታ እንቅስቃሴ ላይ የአቅጣጫ ለውጥ ሊያደርጉ መሆኑ ታወቀ፡፡
በዘካሪያስ ስንታየሁ አራቱ የሃይማኖት መሪዎች የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የይሁንታና የይቅርታ እንቅስቃሴ ላይ የአቅጣጫ ለውጥ ሊያደርጉ መሆኑ ታወቀ፡፡
በኃይሌ ሙሉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አባል ፓርቲዎች ባለፉት አራት ወራት ግንባር ለመፍጠር ሲያካሂዱት የነበረው ድርድር ባለመጠናቀቁ፣ ጉዳዩ ከአራት ወራት በኋላ ለሚካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ እንዲቀርብ ተላለፈ፡፡
በውድነህ ዘነበ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ከሁለት ሳምንት በፊት ለሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ባስተላለፈው ሰርኩላር ውድቅዳቂ ብረታ ብረት በጨረታ አውጥተው እንዳይሸጡ አገደ፡፡
በኃያል ዓለማየሁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በአገሪቱ በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነውን ከፍተኛ ቮልቴጅ መሸከምና ማሰራጨት የሚችል ተንቀሳቃሽ የማከፋፈያ ጣቢያ አስመጣ፡፡
በውድነህ ዘነበ ወይንሸት ተክሌና ቢንያም አያሌው በየጊዜው እየጨመረ የመጣው የኑሮ ውድነት አስመርሯቸዋል፡፡ ወይንሸት የሦስት ልጆች እናት ስትሆን ከባለቤቷ ጋር በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኮልፌ አካባቢ ነዋሪ ነች፡፡
በሕይወት የሌሉና ካገር የወጡ ሰዎች ተመድበዋል‹‹ምደባውን ጀመርን እንጂ አላጠናቀቅንም›› አቶ ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤልየኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በኃያል ዓለማየሁ በአዲስ መልክ በተቋቋመው ኢትዮ ቴሌኮም ከሥራ ምደባ ጋር በተያያዘ ግራ መጋባት መስፈኑን የተለያዩ የድርጅቱ ሠራተኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
በዘካሪያስ ስንታየሁ በደርግ ባለሥልጣናት የተገደሉት ስድሳዎቹ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች፣ ለደርግ መንግሥት ባለሥልጣናት ይቅርታ እንደማያደርጉ ባለፈው ሐሙስ ባወጡት መግለጫ ለአቡነ ጳውሎስ አስታወቁ፡፡
በየማነ ናግሽላለፈው አንድ ወር በግዳጅ ዕረፍት ላይ እንዲቆዩ ተወስኖባቸው የሰነበቱት የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ለይኩን ብርሃኑ፣ ከኃላፊነታቸው እንዲሰናበቱ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ወሰነ፡፡ የ10 ሺሕ ብር መቀጮ እንዲከፍሉም ተወስኖባቸዋል፡፡
– በ12 ቀናት ግምገማ ከ10 በላይ ኃላፊዎች ተነስተዋል– በክፍለ ከተማው የ10.8 ሚሊዮን ብር ሕገወጥ ግዢ ተፈጽሟልበታምሩ ጽጌ ኪራይ ሰብሳቢነት በከፍተኛ ሁኔታ በመንሠራፋቱ ልማትን ማፋጠን አለመቻሉን በማመንና ለዚህም ተጠያቂዎቹ ክፍለ ከተማውን በመምራት ላይ ያሉት ሥራ አስፈጻሚዎች መሆናቸው ስለታመነበት፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ …
በአራዳ ክፍለ ከተማ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት ተንሰራፍቷል›› በሚል ሹማምንቱ በከፍተኛ ግምገማ ተጠምደዋል Read more »
በአስራት ሥዩምና በዘካሪያስ ስንታየሁ በንግድ ማኅበረሰቡና በመንግሥት መካከል ባለፈው ዓመት የተፈረመው የጋራ የምክክር መድረክ ማቋቋሚያ የስምምነት ሰነድን መሠረት በማድረግ፣ የንግድ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የመጀመሪያ ስብሰባቸውን ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ታወቀ፡፡
በብርቱካን ፈንታየሃይማኖት ተቋማት በመንግሥት በኩል የሚጠይቋቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት የሚያስችል አዲስ የሕግ ማዕቀፍ በመዘጋጀት ላይ መሆኑን፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡
በብርቱካን ፈንታ የቀድሞው ሬዲዮ ፋና የአሁኑ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በ100 ሚሊዮን ብር የተፈረመ ካፒታል አዲስ የአደረጃጀት ለውጥ ማድረጉን ታኅሣሥ 22 ቀን 2003 ዓ.ም. በዋና መሥሪያ ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ፡፡
Joomla! 1.7 continues development of the Joomla Framework and CMS as a powerful and flexible way to bring your vision of the web to reality. With the administrator now fully MVC, the ability to control its look and the management of extensions is now …
በዘካሪያስ ስንታየሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በደርግ የተገደሉትን የስድሳዎቹን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት ቤተሰቦችን ዛሬ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ያነጋግራሉ፡፡
– ንግድ ሚኒስቴር በፍጆታ ዕቃዎች ላይ በነገው ዕለት የሚያካሂደው ስብሰባ ይጠበቃል በብርሃኑ ፈቃደ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሲሊንደር ጋዝ ዋጋ ባለፉት ሁለት ወራት ያሳየው ጭማሪ ከወትሮው የተለየ ሲሆን፣ ምክንያት የተደረጉት ደግሞ የነዳጅ ዋጋ መጨመርና የውጭ ምንዛሪ ለውጥ ናቸው፡፡
በውድነህ ዘነበ ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ለመግዛት በመወዳደር ላይ የሚገኙ ኩባንያዎች፣ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ፋብሪካውን ለእንግሊዙ ግዙፍ ኩባንያ ዲኤጎ ለመስጠት መንገዶችን እያመቻቸ ነው ሲሉ ወቀሱ፡፡
‹‹አቅሜ ስለማይችል ሱፐር ማርኬቴን ሸጬ ከከፈልኩ በኋላ አገሬ እገባለሁ›› ሚስተር ባምቢስ‹‹የፈጸሙት የግብር ስወራና ማጭበርበር ወንጀል ነው›› ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በታምሩ ጽጌ የባምቢስ ሱፐር ማርኬት ሳይከፍል የተጠራቀመበት 87 ሚሊዮን ብር ታክስ እንዳለበት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
– አውሮፕላንና ሄሊኮፕተር ያስመጣል– የሠልጣኞች ማደሪያ ሕንፃ ለመገንባት አቅዷል በብርሃኑ ፈቃደ የአቢሲኒያ የበረራ አገልግሎት የግል የበረራ ማሠልጠኛ ተቋም በተለያዩ አየር መንገዶች ተቀጥረው መሥራትና ማብረር የሚችሉ አብራሪያዎችን ለማሠልጠን የሚያስችለውን ፈቃድ ከሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አገኘ፡፡
– የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ተሾመለት በታምሩ ጽጌና በኃይሌ ሙሉ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አቶ ጌቱ ገለቴን ከተከሰሱበት የወንጀል ክስ በነፃ ያሰናበቷቸው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ዳኛ አቶ ዘሪሁን ቦዴ፣ ከፍተኛ የሥነ ምግባር ግድፈት መፈጸማቸውን በማረጋገጥ …
በሔኖክ ያሬድ በጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ በ1953 ዓ.ም. የተካሔደውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ታሪካዊ ፋይዳና ከሙከራው ስለሚገኝ ትምህርት የፊታችን ዓርብ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውይይት እንደሚካሔድ ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፡፡
በዘካሪያስ ስንታየሁ| ሪፖርተር የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሥልጣን ዘመናቸው በአገሪቱ ላይ በፈጸሙት በደልና ጥፋት ተጸጽተናል በማለት የኢትዮጵያ ሕዝብና የተጐጂ አካላትን ይቅርታ ለመጠየቅ የተቆረጠው የይሁንታ ቀን ተራዘመ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ የወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር …
በታምሩ ጽጌ | The Reporter ‹‹ቀበሌ ስሄድ የሚመለከተው ክፍለ ከተማውን ነው ይሉኛል፤ ክፍለ ከተማ ስሄድ ደግሞ እኛን አይመለከተንም፤ የሚመለከተው አስተዳደሩን ነው ይሉኛል፤ አስተዳደሩ ዘንድ ስሄድ ደግሞ ይኼማ የክፍለ ከተማው ሥራ ነው ይሉኛል፤›› ያለችው አርቲስት ሐመልማል አባተ፣ ለመንግሥትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕ …
በውድነህ ዘነበ ላለፉት 120 ዓመታት ቀስ በቀስ ሲስፋፋ ቆይቶ የዛሬውን መልክ የያዘው የአዲስ አበባ ከተማ ማዕከላዊ ክፍል ፈርሶ በድጋሚ እንዲገነባ ዕቅድ ተነድፏል፡፡
በታምሩ ጽጌ ‹‹ቀበሌ ስሄድ የሚመለከተው ክፍለ ከተማውን ነው ይሉኛል፤ ክፍለ ከተማ ስሄድ ደግሞ እኛን አይመለከተንም፤ የሚመለከተው አስተዳደሩን ነው ይሉኛል፤ አስተዳደሩ ዘንድ ስሄድ ደግሞ ይኼማ የክፍለ ከተማው ሥራ ነው ይሉኛል፤›› ያለችው አርቲስት ሐመልማል አባተ፣ ለመንግሥትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕ ማጣቷን ለማሳወቅ አንድ …
በውድነህ ዘነበመንግሥት ከጥር ወር ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች ከሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ በሸቀጦች ዋጋ ላይ ያልተገባ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ዕርምጃ መውሰድ የሚያስችለውን መቆጣጠሪያ ዘዴ ሊዘረጋ ነው፡፡
በታምሩ ጽጌ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በውኃ ላይ ታሪፍ ሊጨምር መሆኑን የባለሥልጣኑ ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
የ175 የመንግሥት መሥሪያ ቤት የፋይናንስ ኃላፊዎች ሥልጠና ይጀምራሉበውድነህ ዘነበ የአገሪቱ የበጀት ቀመር ከአሥርት ዓመታት በኋላ ከሚቀጥለው የበጀት ዓመት ጀምሮ ሊለወጥ ነው፡፡
የመታሰቢያ ሐውልት እየተሠራላቸው ነው በቃለየሱስ በቀለና በብርቱካን ፈንታ ባለፈው ዓመት በጥር ወር በቤይሩት አቅራቢያ ድንገተኛ አደጋ በደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ሕይወታቸውን ላጡ ተሳፋሪዎችና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ቤተሰቦች እስካሁን ድረስ ኢንሹራንስ እንዳልተከፈላቸው ታወቀ፡፡
በታምሩ ጽጌ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በግንቦት ወር 2000 ዓ.ም. በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በአራት የክስ መዝገብ ክስ መስርቶባቸው የነበሩት፣ የቀድሞው የኢትዮጽያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ብሩን ጨምሮ 14 ተከሳሾች በአንድ የክስ መዝገብ ከትናንት በስቲያ በዋለ …
የ286 ትምህርት ቤቶችን መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ተጠናቀቀ በምሕረት ሞገስ በግል የመጀመርያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ብቻ ሲደረግ የነበረው የትምህርት ጥራት፣ ክትትል፣ ቁጥጥርና ግምገማ ወደ መንግሥትና ሕዝብ የመጀመርያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዘለቀ፡፡
በኃይሌ ሙሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ዛሬ አዲስ ፕሬዚዳንት ይመርጣል፡፡
በታምሩ ጽጌ በደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጉዳት የደረሰበትም ሆነ ድርጊቱን በታሪክ የሚያውቀው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅር እንዲልና እርቀ ሰላም እንዲወርድ፣ አራት የሃይማኖት መሪዎች ታህሳስ 9 ቀን 2003 ዓ.ም. ያቀረቡት ጥያቄ ተቃውሞ እየገጠመው ነው፡፡
በውድነህ ዘነበ በአገሪቱ ብቸኛው የኤሌክትሪክ ኃይል አመንጪና አከፋፋይ ሆኖ ላለፉት 55 ዓመታት ሲሠራ የቆየው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በአራት ዘርፎች ተከፍሎ እንደገና ሊዋቀር ነው፡፡
– አየር መንገድ በረራ እንዳልተስተጓጎለበት አስታወቀ በብርሃኑ ፈቃደ በአውሮፓ የተከሰተው ከባድ የበረዶ ክምር የአበባ ዋጋና ገበያን ከ50 በመቶ በላይ እንዲቀንስ ማስገደዱን የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማኅበር አስታወቀ፡፡ ዝርዝሩን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ።
በዘካሪያስ ስንታየሁ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ሂውማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ መንግሥት የሚፈጽመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እስካላቆመ ድረስ፣ ለጋሾች የሚሰጡት ዕርዳታ እንዲቋረጥ የልማት አጋር ቡድንን (DAG) በድጋሚ ጠየቀ፡፡
– ‹‹35 በመቶ የቆላ አበል ክፍያ ያለአግባብ ተከልክለናል›› የጉራፈርዳ ወረዳ ሠራተኞች– ‹‹አበሉን እንደ መብት መጠየቅ አግባብ አይደለም›› አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የክልሉ ፕሬዚዳንት በታምሩ ጽጌ
በጋዜጣው ሪፖርተር ባለፈው እሑድ ከሰዓት በኋላ በደቡብ ክልል ሆሳዕና አካባቢ በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር፡፡
በብርሃኑ ፈቃደ ከአዳማ ከተማ ሦስት ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ በሚገኝ በተለይ 51 ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚችል የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት ከቻይና ባንክ ጋር የ99 ሚሊዮን 450 ሺሕ ዶላር የብድር ስምምነት ተፈጸመ፡፡
በኃይሌ ሙሉ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፌዴራሊዝም ሥርዓት ለቋንቋ ብቻ ትኩረት የሰጠ በመሆኑ፣ የሌላ ብሔረሰብ ቋንቋ የሚናገሩት የትግሪ ወርጂ ብሔረሰቦች የሥርዓቱ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን፣ የትግሬ ወርጂ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ ለሪፖርተር አስታወቀ፡፡
በታምሩ ጽጌና በዘካሪያስ ስንታየሁ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው በሞት፣ በእድሜ ልክና በዓመታት እስር እንዲቀጡ የተወሰነባቸው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለገና ሊፈቱ እንደሚችሉ ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
በኃያል ዓለማየሁ የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሸን ኮርፖሬሽን በአዲሱ አደረጃጀት ኢትዮ ቴሌኮም በሚል ስያሜ ከተዋቀረ በኋላ፣ አብዛኛዎቹ የድርጅቱ ሠራተኞች እስካሁን ባለመመደባቸው፣ የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ ቆሟል በሚያስብል ሁኔታ መዳከሙን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የድርጅቱ ሠራተኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
በውድነህ ዘነበ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በቦርድ ለሚተዳደሩ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች አዳዲስ የቦርድ ሰብሳቢዎችን ሊሾም ነው፡፡
በሚኪያስ ሰብስቤ በስድስት ሕፃናት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሟል በሚል በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመስርቶበት ከአንድ ሳምንት በፊት በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ሰባተኛ ወንጀል ችሎት ጥፋተኝነቱ የተረጋገጠበት የ16 ዓመት ወጣት፣ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ …
በሕፃናት ላይ ፆታዊ ጥቃት ያደረሰው የ16 ዓመት ወጣት በ25 ዓመት እሥራት ተቀጣ Read more »
በውድነህ ዘነበ ከአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘውን ገቢ ሙሉ ለሙሉ መሰብሰብ የተሳነው የከተማው ገቢዎች ኤጀንሲ ከፌዴራሉ ጉምሩክና ገቢዎች ባለሥልጣን ጋር ተዋህዶ እንዲሰራ ተወሰነ፡፡
በኃይሌ ሙሉ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በ100 ሺሕ ዶላር ክፍያ የጆኒ ወከር ውስኪን ማስተዋወቁ ውዝግብ አስነሳ፡፡
በኃይሌ ሙሉ በእናቱ ላይ በፈጠረው የጤንነት ችግር ምክንያት በስድስት ወር (በ27 ሳምንት እድሜው) በቀዶ ሕክምና እንዲወጣ የተደረገው ሕፃን፣ በሕይወት መቆየት ቻለች፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ28 ሳምንታት በታች የሚወለድ ልጅ እንደ ውርጃ ይቆጠራል፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል ክስ ከመሰረተባቸው ስድስት ተከሳሾች ውስጥ በአራቱ ላይ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ከ6 ዓመት እስከ 8 ዓመት ከ6 ወር በሚደርስ ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡
በብርቱካን ፈንታ ከሁለት ዓመታት በፊት ‹‹ሊከፈለኝ የተስማማሁት ክፍያ አልተፈጸመልኝም›› በማለት ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ደብዳቤ ጽፎ የነበረው እንግሊዛዊው ሚስተር አንዲ ኢቡላሚና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ውዝግብ በድርድር መፈታቱን፣ የሚኒስቴሩ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር የተከዜ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በዓለም አቀፍ ደረጃ የ2010 ምርጥ የኃይል ማመንጫ በመሆን በአንደኛ ደረጃ መመረጡን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡
በኩሩና ኮከቡ የኢትዮጵያና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋችና አሰልጣኝ የነበረው መንግሥቱ ወርቁ በ70 ዓመቱ አረፈ፡፡