የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው የገንዘብ ቅጣታቸውን መክፈል ያልቻሉ እስረኞች ጉዳይ ግራ አጋብቷል

በታምሩ ጽጌ

በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኝነታቸው በሰነድና በሰው ምስክሮች ተረጋግጦባቸው በዓመታት እሥራትና በከፍተኛ ገንዘብ የተቀጡ እስረኞች የእስር ጊዜያቸውን ቢጨርሱም፣ ገንዘቡን መክፈል ባለመቻላቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ ጠበቆቻቸው አስታወቁ፡፡