ለመስመር ሠራተኛነት የሠለጠኑ የቴሌኮም ተቀጣሪዎች ደመወዝና ምደባ መከልከላቸውን አስታወቁ
– የትራንስፖርትና ጋራዥ ሠራተኞች መፍትሔ የሚሰጣቸው አጥተዋል
በታምሩ ጽጌ
የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ስሙን ቀይሮ ኢትዮ ቴሌኮም ከመባሉ በፊት እ.ኤ.አ. ከሴብቴምበር 15 ቀን 2010 እስከ ኖቬምበር 30 ቀን 2010 ድረስ የቀን አበል በመክፈል፣ በመለስተኛ መስመር ሠራተኛነት አሠልጥኖ ያስመረቃቸው ሠራተኞች ላለፉት ሁለት ወራት ደመወዝ እንዳልከፈላቸውና ሥራ እንዳልተመደቡ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡