በሀሰተኛ ሰነድ ያጭበረበሩ ግለሰብ በ1 ሺሕ 500 ብር ቅጣት ተለቀቁ
– ወንጀሉ እስከ አሥር ዓመት እስራት ያስቀጣል
በኃይሌ ሙሉ
ሀሰተኛነቱ በተረጋገጠ ሰነድ ለልጃቸው 549 ሺሕ 500 ብር ዋጋ ያላቸው አክሲዮኖች እንደሸጡ በማስመሰል የፍትሐ ብሔር ክስ ሲመሰርቱ፣ ሀሰተኛውን ሰነድ ከማስረጃዎች ዝርዝር ጋር አቅርበው የተገኙት አቶ ዘመረ ጀማነህ የተባሉ ግለሰብ በ1 ሺሕ 500 ብር ቅጣት ተለቀቁ፡፡