የአፍሪካ ኅብረት 16ኛው የመሪዎች ጉባዔ ፋይዳ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለፈው ዓርብ ምሽት ከስዊዘርላንድ ዳቮስ ከተመለሱ በኋላ፣ ባለፈው እሑድ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 16ኛው የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ ጉባዔም ለመጀመርያ ጊዜ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ተሳትፈዋል፡፡ በምስሉ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከአቶ ኃይለ ማርያም፣ ከአምባሳደር ብርሃነና ከአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ጋር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስብሰባ ማዕከል በተደረገው ጉባዔ ላይ ሲመካከሩ፡፡በጉባዔው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ የተዘጋጀውን ዘገባ ለመመልከት እዚህ ይጫኑ!