የኢንዱስትሪ ምርቶች ወጪ ንግድ ዝቅተኛ አፈጻጸም አስመዘገበ
– ሚኒስትሩ የማካካሻ ዕቅድ እንዲዘጋጅ አዘዙ በውድነህ ዘነበ የኢንዱስትሪ ምርቶች ወጪ ንግድ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን የስድስት ወራቱን የወጭ ንግድ ዕቅድ እንዳይሳካ አደረገ፡፡
– ሚኒስትሩ የማካካሻ ዕቅድ እንዲዘጋጅ አዘዙ በውድነህ ዘነበ የኢንዱስትሪ ምርቶች ወጪ ንግድ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን የስድስት ወራቱን የወጭ ንግድ ዕቅድ እንዳይሳካ አደረገ፡፡
በዳዊት ታዬ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በባንክና ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንዳይሳተፉ የሚከለክለውን ሕግ ለማሻሻል መንግሥት ዕቅድ እንዳለው አስታወቀ፡፡
– ኢትዮጵያ ስለኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ማሰብ እንዳለባት ተጠቆመ በዘካሪያስ ስንታየሁ ግብፅ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ከአንድ ሳምንት በኋላ ጨረታ እንደምታወጣ የኤሌክትሪክና የኢነርጂ ሚኒስትሩ ሃሰን ይኑስ አስታወቁ፡፡
‹‹ሕገወጥ›› የተባሉት የሪል ስቴት አልሚዎች የክስ ጉዳይ አለየለትም በውድነህ ዘነበ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዘጠኝ ዓመት በፊት ያጸደቀው የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው አዋጅ በድጋሚ እንዲሻሻል ለፍትሕ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡
– በከተማዋ አብዛኛዎቹ ቡና ቤቶች ቢራ መሸጥ አቁመዋል በዳዊት ከበደ፣ ልዩ ዘጋቢ ከመቀሌ መንግሥት በአገር አቀፍ ደረጃ ያወጣውን መሠረታዊ የችርቻሮ ሸቀጦች የዋጋ ተመንን ተከትሎ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ጥር 6 ቀን 2003 ዓ.ም. በክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ …
በታደሰ ገብረ ማርያም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የአዲስ አበባ ላጋር ጉምሩክ ጣቢያ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ አባላት ካምፕ ላይ ጥር 13 ቀን 2003 ዓ.ም. ከእኩለ ቀን በኋላ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት አደረሰ፡፡
– ድልድዩን የሚያሠራው ድርጅት ወደ ፍርድ ቤት እሄዳለሁ አለበውድነህ ዘነበ በሲሚንቶ ጥራት መጓደል ምክንያት በጋምቤላ ክልል እየተገነባ የነበረው ድልድይ መፍረሱን ተከትሎ፣ የጥራትና ደረጃዎች ባለሥልጣን ሁለት የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ዘጋ፡፡
– ‹‹በትኬቱ ላይ ከተቀመጠው ዋጋ በላይ መክፈል የለብንም››የአገልግሎት ተጠቃሚዎች – ‹‹የነዳጅ ታሪፍ መቀያየር ትኬቱን በዋጋው እንዳንሸጥ አድርጐናል››ድርጅቱ በታምሩ ጽጌ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ ተጠቃሚዎች ከአንድ ሥፍራ ወደሌላ ሥፍራ ለሚጓጓዙበት የሚከፍሉት ክፍያ፣ ለርቀቱ ተመድቦ በአውቶቡስ ትኬት ላይ ከተጻፈው የገንዘብ መጠን ከ0.20 …
በምህረት አስቻለው የትራንስፖርት ሚኒስቴር የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል ሶፍትዌር በማሠራት ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በየማነ ናግሽ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፣ መንግሥት በቅርቡ የኑሮ ውድነቱ ችግር ለማረጋጋት የወሰደው የዋጋ ትመና ሕግንና የሕግ የበላይነት የሚጻረር መሆኑን አስታወቀ፡፡
በታምሩ ጽጌ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ከመስቀል አደባባይ እስከ ሳሪስ ድረስ እያሠራው ያለው ባለ ሦስት ረድፍ (ሌን) መንገድ መሀሉ ለባቡር መተላለፊያ የተሠራ ቢሆንም፣ የባቡር ትራንስፖርት እስከሚጀምር ድረስ ለአውቶብሶች ክፍት በመደረጉ በየቀኑ በሰዎችና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ እያደረሰ በመሆኑ ነዋሪዎች በከፍተኛ …
አቶ አህመድ ቱሳ፣ የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ መንግሥት በፖሊሲ ደረጃ ያስቀመጠው የዋጋ ዕድገት ከሰባት በመቶ መብለጥ ስለሌለበት በአንድ ጤናማ ኢኮኖሚ የዋጋ ዕድገት ከሰባት በመቶ በላይ ካለፈ አደጋ አለው ሲሉ የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አህመድ ቱሳ ከትናንት በስቲያ አስታወቁ፡፡
‹‹ካልተሳሳትኩ ግለሰቦች የፈጠሩት የሥልጣን ሽኩቻ ይመስለኛል›› አቶ አዲሱ መንግሥቱ በታምሩ ጽጌ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የኢህአዴግ አባላት ሰሞኑን ባደረጉት የአንድ ቀን ግምገማ፣ ምክትል ኮሚሽነር አዲሱ መንግሥቱን ከከፍተኛ አመራርነት ወደዕጩ አባልነት ዝቅ አደረጓቸው፡፡
– 2.7 ቢሊዮን ብር ለደመወዝ ጭማሪ ይውላል – 640 ሺሕ ጡረተኞች ጭማሪ ያገኛሉ በውድነህ ዘነበ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አቶ ሶፊያን አህመድ ባለፈው ዓርብ ያቀረቡትን የ7.5 ቢሊዮን ብር የተጨማሪ በጀት ዕቅድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወያይቶ አፀደቀው፡፡
‹‹ጥቃት እየደረሰባቸው ስለመሆኑ ማስረጃ የላቸውም›› ዩኤንኤችሲአር በኃይሌ ሙሉ የእርስ በርስ ግጭት ሸሽተው በስደተኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐ የቱትሲ (የሙኒያ ሙሌንጌ ጐሳ) አባላት በሁቱ ስደተኞች ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን በመግለጽ ሰላማዊ ሠልፍ አካሄዱ፡፡
– ከብርሃን ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጋር ለመዋሀድ ተስማማ በኃይሌ ሙሉ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ተግባራዊ የሚያደርገውን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
በታምሩ ጽጌ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለማክበር ወንጀል የተከሰሱ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሦስት ሠራተኞች፣ እያንዳንዳቸው በሁለት ወራት እስራት እንዲቀጡ ጥር 9 ቀን 2003 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
በታምሩ ጽጌ ከአገር እንዳይወጡ ገደብ የተደረገባቸውን ቅርሳ ቅርሶች ይዘው ሊወጡ ሲሉ ሕዳር 25 ቀን 2003 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሁለት የቻይና ዜጐች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
በውድነህ ዘነበመንግሥት በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ጣሪያ ካስቀመጠ ከሳምንት በኋላ የንግዱ ኅብረተሰብ ቅሬታ እየበረከተ መምጣቱን ተከትሎ፣ የንግድ ሚኒስቴር በየዘርፉ ያሉ ነጋዴዎች የሸቀጣቸውን ሙሉ መረጃ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ሰጠ፡፡ ነጋዴዎች መንግሥት ቅሬታቸውን እንዲያዳምጥ እየጠየቁ ነው፡፡
በታምሩ ጽጌየኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፣ የእስረኞችና ሰነዶች ክትትል ኃላፊና የወንጀል ምርመራ ቡድን አስተባባሪ በተከሰሱበት የፍርድ ቤት ትእዛዝ አለማክበር ወንጀል ጥፋተኛ በመባላቸው፣ ከጥር 5 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ታስረው እንዲቆዩ ትዕዛዝ …
የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የወንጀል ምርመራ ኃላፊዎች ታስረው ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ትእዛዝ ተሰጠ Read more »
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ፕሮፌሰር አንዳርጋቸው ተስፋዬ ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት በመልሶ ማቋቋምና ማኅበራዊ ችግር (Rehabilitation and Social Problem) ላይ ጥናት አካሂደው ነበር፡፡ ፕሮፌሰሩ ባቀረቡት በዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ አዲስ አበባ ውስጥ በቀን 15 የጐዳና ተዳዳሪዎች በቅዝቃዜ ምክንያት እንደሚሞቱ ገልጸዋል፡፡
በብርቱካን ፈንታሐሙስ ጥር 5 ቀን 2003 ዓ.ም. ሳሪስ ካዲስኮ አካባቢ አንድ ተሽከርካሪ በተማሪዎች ላይ ባደረሰው አደጋ የአንዲት ተማሪን ሕይወት ማለፍ ተከትሎ፣ የሠፈሩ ነዋሪዎችና ተማሪዎች አደጋ እያደረሰ ያለው መንገድ እንዲዘጋ ወይም መፍትሔ እንዲሰጣቸው ሰላማዊ ሠልፍ በመውጣት ጠየቁ፡፡
በኃያል ዓለማየሁመንግሥት ከጥር 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ከቤንዚን ጋር የሚቀላቀለውን የስኳር ተረፈ ምርት የሆነውን የኢታኖል መጠን ወደ 10 በመቶ ከፍ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን ሥራውን በበላይነት የሚመራውና የሚከታተለው የኢነርጂና የውኃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በታምሩ ጽጌበሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሐረር ከተማ ሸዋበር በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የገበያ ቦታ ጥር 4 ቀን 2003 ዓ.ም. ከምሽቱ 5 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ግምቱ ከ10 እስከ 15 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረት መውደሙን የከተማው ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡ የሱቆቹ …
በሐረር ከተማ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ያወደመው ንብረት ግምት በውል አልታወቀም Read more »
በምሕረት ሞገስመንግሥት ከታኅሣሥ 28 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ባደረገውና የዋጋ ቁጥጥር የሚደረግባቸው መሠረታዊ የንግድ ዕቃዎችን ለመወሰን በወጣው የሕዝብ ማስታወቂያ ዙርያ በታዩት ችግሮች ላይ አባላት ከሆኑና ካልሆኑ አሠሪዎች፣ ከመንግሥት አካላትና ከሸማቹ ጋር ነገ ጥር 9 ቀን 2003 ዓ.ም. በሠራተኛና ማኅበራዊ …
አሠሪዎች ፌዴሬሽን በዋጋ ቁጥጥሩ ችግሮች ዙርያ አሠሪዎችን ነገ ያወያያል – የመንግሥትን የዋጋ ተመን አምንበታለሁ አለ Read more »
በብርሃኑ ፈቃደበቅርቡ የወጣውን የሸቀጦች ዋጋ ተመን ተከትሎና በቢራ ችርቻሮ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ቅናሽ በማገናዘብ አንዳንድ የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ማስተካከያ እንደማያደርጉ ገለጹ፡፡
‹‹ወረዳው ለ25 ዓመት የቆየውን የፀበል ቦታችንን አፍርሶብናል››የጎፋ መብራት ኃይል ዑራኤል ፀበል ደብር‹‹ያፈረስኩት ሕጋዊ ፈቃድ ስለሌላቸው ነው››የወረዳው አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በብርቱካን ፈንታ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው መብራት ኃይል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው የኮንዶሚኒየም ግቢ የሚገኘው የዑራኤል …
በሚኪያስ ሰብስቤየፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የቴሌ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ብሩን ጨምሮ በ16 ተከሳሾች ላይ ‹‹የሞባይል ስልክ መስመር ለማስፋፋት የወጣውን ጨረታ ፕሮጀክት ያለአግባብ ኤሪክሰን እንዲያሸንፍ አድርገዋል›› በሚል ጥር 3 ቀን 2003 ዓ.ም. የጥፋተኝነት ውሳኔ …
በአስራት ሥዩምና ኃይሌ ሙሉየኢትዮጵያ ገቢዎችና የጉምሩክ ባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ሆቴሎች በሆቴሎቻቸው የህንፃ ግንባታዎች ወቅት ከውጪ ከቀረጥ ነፃ ባስገቧቸው የግንባታ ዕቃዎች ላይ ዝርዝር መረጃ እንዲያቀርቡ ጠየቀ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ታኅሣሥ 28 ቀን 2003 ዓ.ም. በአገሪቷ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ናቸው የተባሉ 584 ነጋዴዎችን በጽሕፈት ቤታቸው አነጋግረዋቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለኅብረተሰቡ በጣም አስፈላጊ ነው ያሏቸውን 16 ምርቶች የሚሸጡባቸውን ዋጋ ለነጋዴዎቹ አሳውቀዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የዱቄት ወተት (450 ግራም) ቀድሞ …
– አስከሬኑ ትናንት ምሽት ላይ ወደ አሜሪካ ተልኳል በታምሩ ጽጌ የገና በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር ለማክበር ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሜሪካዊ ወጣት አረፈዓይኔ ቦብ ዊን ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱ ማለፉን ቤተሰቦቹ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
• ከዳያስፖራው ጋር ሰፋፊ ውይይቶችን ለማካሄድ ተዘጋጅቷል በውድነህ ዘነበ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን (ዳያስፖራ) ወጥ በሆነ መንገድ ማስተናገድ ያስችላል ያለውን አዲስ ፖሊሲ አረቀቀ፡፡
• የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ለግንባታው ተባባሪ እንደነበረ አስታወቀ በጋዜጣው ሪፖርተር አምና በሜዲትራኒያን ባሕር ላይ ተከስክሶ በወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላለቁት ኢትዮጵያውያን በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የተገነባው ሐውልት የፊታችን እሑድ ጥር 8 ቀን 2003 ዓ.ም. ይመረቃል፡፡
በታደሰ ገብረ ማርያም የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ሰሞኑን ለእርድ የሚቀርቡ ሰንጋዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየቀነሰ በመምጣቱ ድንጋጤ ውስጥ መግባቱን አስታወቀ፡፡
በብርቱካን ፈንታ በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ በሦስት የቀበሌ ገበሬ ማኅበሮች ውስጥ ስምንት መስጂዶችን አቃጥሏል ተብሎ በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ላይ ክስ ሊመሠረት መሆኑን፣ የወረዳው እስልምና ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትና የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡
– 41.5 ሚሊዮን ብር በጀት ተይዞላቸዋል በታምሩ ጽጌ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች በልመና ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ወገኖችን፣ ዛሬ ፍቼ ከተማ ውስጥ ወደሚገኘው ማሠልጠኛ ጣቢያ እንደሚያስገባቸው በአስተዳደሩ የሠራኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ …
በብርቱካን ፈንታ ድንበር ዘለል ኩባንያዎችና ባለሀብቶች በኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ላይ እየፈጸሙዋቸው ላሉ በደሎች መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ጥሪ አቀረበ፡፡
በውድነህ ዘነበ በአገሪቱ ንግድ ውስጥ ተጽእኖ መፍጠር የሚያስችል አቅም አላቸው የተባለላቸው ነጋዴዎች ያሉባቸውን ችግሮች መግለጽ ባልደፈሩበት መድረክ፣ መንግሥት ባልተጠበቀ ሁኔታ በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የመሸጫ ዋጋ ጣሪያ ወስኗል፡፡
– መርማሪ ቡድኑ አዲስ አበባ ሊመጣ ነው– የሊባኖስ ባለሥልጣናት የተጠየቁትን መረጃዎች አልሰጡምበቃለየሱስ በቀለ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ከቤይሩት ወደ አዲስ አበባ 82 መንገደኞችን አሳፍሮ በረራ ሲጀምር በሜዲትራኒያን ባሕር ላይ ድንገተኛ አደጋ በደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ላይ በመካሄድ …
በአስፋው ብርሃኑ፣ ከሐዋሳ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መስተዳድር ሲዳማ ዞን፣ ወንዶ ገነት ወረዳ፣ በጉጂ ኦሮሞ ተወላጆችና በሲዳማ ብሔረሰብ መካከል ታኅሣሥ 24 ቀን 2003 ዓ.ም. ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ በተቀሰቀሰ ግጭት፣ የአምስት ሰዎች ሕይወት የጠፋ ሲሆን፣ ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ …
በየማነ ናግሽ በምሥራቅ አፍሪካ አዲስ አገር ይፈጥራል ተብሎ የሚጠበቀው የደቡብ ሱዳን ሕዝበ ውሳኔ ዛሬ ይደረጋል፡፡ በዛሬው ዕለት በ2,638 የምርጫ ጣቢያዎች የሚደረገው ሕዝበ ውሳኔ ዝግጅት በቂ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት አስታውቋል፡፡
በታምሩ ጽጌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ፋኩልቲ ተማሪዎች በገና በዓል አከባበር ምክንያት ከዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች ጋር ባለመስማማታቸው፣ ታህሣሥ 27 ቀን 2003 ዓ.ም. ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ ጀምረውት የነበረውን ረብሻ የአዲስ አበባ ፖሊሶችና ፌዴራል ፖሊስ በመተባበር በቀላሉ ተቆጣጠሩት፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ለሚያካሂደው 5ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ባደረገው ቅድመ ውይይት፣ ኢትዮጵያ ከሊበራል ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ጋር ሳትተዋወቅ በመቆየቷ ምክንያት ለውስብስብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች መጋለጧን አስታወቀ፡፡
በብርቱካን ፈንታ መንግሥት ባወጣው ፖሊሲ መሠረት የመምህራን ሥልጠናን በስፔሻላይዜሽን ማድረጉን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡
በታምሩ ጽጌ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በተለያዩ ሁለት የእምነት ቦታዎች ላይ ሰኔ 26 እና ሐምሌ 25 ቀን 2002 ዓ.ም ሁለት ግለሰቦችን መግደላቸው በምስክርና በማስረጃ የተረጋገጠባቸው ሁለት ወንድማማቾች፣ በሞት እንዲቀጡ ታህሣሥ 27 ቀን 2003 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
በውድነህ ዘነበ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ተገንጥሎ የሚወጣውን የኦፕሬሽን ዘርፍ በኮርፖሬሽን ደረጃ ሊያዋቅረው ነው፡፡
በዳዊት ከበደ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ በሆነችው መቀሌ ለዓመታት የዘለቀው የመጠጥ ውኃ ችግር ተባብሶ መቀጠሉን የከተማዋ ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡
በዘካሪያስ ስንታየሁ | ሪፖርተር የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ የገዛው ብሉ ናይል የተባለው ቦይንግ 777-200 LR አውሮፕላን በቆመበት በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ፣ በኤሜሬትስ አየር መንገድ አውሮፕላን ትናንት ከሰዓት በኋላ ተገጨ፡፡ የኤሜሬትስ ኤርባስ A340 አውሮፕላን ከዱባይ ተነስቶ አዲስ አበባ ካረፈ በኋላ …
በታምሩ ጽጌ | ሪፖርተር የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ኃይሉ ሻውል የመጀመሪያ ልጅ ዶ/ር ሻውል ኃይሉ ትናንትና ረፋዱ ላይ ከፍተኛ የመኪና አደጋ ደረሰባቸው፡፡ ዶ/ር ሻውል አደጋው የደረሰባቸው በቅሎ ቤት አካባቢ የሚገኘው ዳሸን ባንክ ፊት ለፊት መኪናቸውን አቁመው ወደ ባንኩ …