ጉዞ ወደ ሱዳን
ደቡብ ሱዳን በሕዝበ ውሳኔ ከሰሜኑ ክፍል መገንጠሉ እውን እንደሆነ በሚገለጽበትና የሱዳን የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም በሚባልበት በዚህ ወቅት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩና ከገጠራማ ቦታዎች የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሱዳን ኤምባሲ ሳር ቤት ከሚገኘው የሱዳን ክለብ ቪዛ ለማግኘት ሌሊቱን መንገድ ዳር እያደሩ፣ ቀኑን ተሰልፈው ይጠባበቃሉ፡፡ ሱዳን ነዳጅ ማግኘቷን ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሥራ ፍለጋ ወደ ካርቱም የሚሄዱ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሥራ ፍለጋና ለንግድ እየሄዱ ነው፡፡ በቅርቡ በተካሄደው ሪፈረንደም አዲሷ አፍሪካዊት አገር እንደምትሆን በሚነገርላት ደቡብ ሱዳን ሪፈረንደምና ውጤቱን በተመለከተ የቀረበውን ዘገባ ዝርዝር ለመመልከት እዚህ ይጫኑ፡፡