የቀድሞው የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት በነፃ ተሰናበቱ

በታምሩ ጽጌ

በሥልጣን ያለአግባብ በመገልገል ከአምስት ዓመታት በፊት በ86,790,000 ብር የሙስና ሙከራ ወንጀል ተከሰው የነበሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሰባት የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ትናንትና በነፃ ተሰናበቱ፡፡