መንግሥት ከቤንዚን ጋር የሚደባለቀውን የኢታኖል መጠን ወደ 10 በመቶ ከፍ ሊያደርግ ነው

በኃያል ዓለማየሁ
መንግሥት ከጥር 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ከቤንዚን ጋር የሚቀላቀለውን የስኳር ተረፈ ምርት የሆነውን የኢታኖል መጠን ወደ 10 በመቶ ከፍ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን ሥራውን በበላይነት የሚመራውና የሚከታተለው የኢነርጂና የውኃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡