የሚኒስትሮች ምክር ቤት 7.5 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

 

– 2.7 ቢሊዮን ብር ለደመወዝ ጭማሪ ይውላል

– 640 ሺሕ ጡረተኞች ጭማሪ ያገኛሉ

በውድነህ ዘነበ

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አቶ ሶፊያን አህመድ ባለፈው ዓርብ ያቀረቡትን የ7.5 ቢሊዮን ብር የተጨማሪ በጀት ዕቅድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወያይቶ አፀደቀው፡፡