በእምነት ቦታዎች ግድያ የፈጸሙ ሁለት ወንድማማቾ በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ

በታምሩ ጽጌ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በተለያዩ ሁለት የእምነት ቦታዎች ላይ ሰኔ 26 እና ሐምሌ 25 ቀን 2002 ዓ.ም ሁለት ግለሰቦችን መግደላቸው በምስክርና በማስረጃ የተረጋገጠባቸው ሁለት ወንድማማቾች፣ በሞት እንዲቀጡ ታህሣሥ 27 ቀን 2003 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡