ሰበካ ጉባዔውና ወረዳው እየተወዛገቡ ነው

‹‹ወረዳው ለ25 ዓመት የቆየውን የፀበል ቦታችንን አፍርሶብናል››
የጎፋ መብራት ኃይል ዑራኤል ፀበል ደብር
‹‹ያፈረስኩት ሕጋዊ ፈቃድ ስለሌላቸው ነው››
የወረዳው አስተዳደር ጽሕፈት ቤት

በብርቱካን ፈንታ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው መብራት ኃይል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው የኮንዶሚኒየም ግቢ የሚገኘው የዑራኤል ፀበል ቦታ መፍረስን ተከትሎ፣ የደቡብ ክፍለ ከተማ ሰበካ ጉባዔና የክፍለ ከተማው ወረዳ 6 አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በመወዛገብ ላይ ናቸው፡፡