በመቀሌ ከተማ በርካታ የንግድ ቤቶች እየታሸጉ ነው

– በከተማዋ አብዛኛዎቹ ቡና ቤቶች ቢራ መሸጥ አቁመዋል

በዳዊት ከበደ፣ ልዩ ዘጋቢ ከመቀሌ

መንግሥት በአገር አቀፍ ደረጃ ያወጣውን መሠረታዊ   የችርቻሮ ሸቀጦች የዋጋ ተመንን ተከትሎ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ  ጥር 6 ቀን 2003 ዓ.ም. በክልሉ ዋና ከተማ  መቀሌ የሸቀጦች የዋጋ ተመን በማውጣት በመገናኛ ብዙኅን ይፋ ማድረጉን  ተከትሎ፣ በርካታ የንግድ ድርጅቶች የወጣውን የዋጋ ተመን  በግልጽ  አልለጠፉም ከዚህም አልፈው ሕጉን አላከበሩም በሚል  እየታሸጉ ነው፡፡