የመንግሥት ዕርምጃ ገበያውን ያረጋጋው ይሆን?

በውድነህ ዘነበ

በአገሪቱ ንግድ ውስጥ ተጽእኖ መፍጠር የሚያስችል አቅም አላቸው የተባለላቸው ነጋዴዎች ያሉባቸውን ችግሮች መግለጽ ባልደፈሩበት መድረክ፣ መንግሥት ባልተጠበቀ ሁኔታ በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የመሸጫ ዋጋ ጣሪያ ወስኗል፡፡