የደቡብ ሱዳን ሕዝበ ውሳኔ ዛሬ ይካሄዳል

በየማነ ናግሽ

በምሥራቅ አፍሪካ አዲስ አገር ይፈጥራል ተብሎ የሚጠበቀው የደቡብ ሱዳን ሕዝበ ውሳኔ ዛሬ ይደረጋል፡፡ በዛሬው ዕለት በ2,638 የምርጫ ጣቢያዎች የሚደረገው ሕዝበ ውሳኔ ዝግጅት በቂ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት አስታውቋል፡፡