የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወንጀል ምርመራ ኃላፊዎች በሁለት ወራት እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ

በታምሩ ጽጌ

የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለማክበር ወንጀል የተከሰሱ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሦስት ሠራተኞች፣ እያንዳንዳቸው በሁለት ወራት እስራት እንዲቀጡ ጥር 9 ቀን 2003 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡