አሠሪዎች ፌዴሬሽን በዋጋ ቁጥጥሩ ችግሮች ዙርያ አሠሪዎችን ነገ ያወያያል – የመንግሥትን የዋጋ ተመን አምንበታለሁ አለ
በምሕረት ሞገስ
መንግሥት ከታኅሣሥ 28 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ባደረገውና የዋጋ ቁጥጥር የሚደረግባቸው መሠረታዊ የንግድ ዕቃዎችን ለመወሰን በወጣው የሕዝብ ማስታወቂያ ዙርያ በታዩት ችግሮች ላይ አባላት ከሆኑና ካልሆኑ አሠሪዎች፣ ከመንግሥት አካላትና ከሸማቹ ጋር ነገ ጥር 9 ቀን 2003 ዓ.ም. በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አዳራሽ እንደሚመክር የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ መንግሥት ያወጣውን የዋጋ ተመንም አምንበታለሁ ብሏል፡፡