በሐረር ከተማ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ያወደመው ንብረት ግምት በውል አልታወቀም

በታምሩ ጽጌ
በሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሐረር ከተማ ሸዋበር በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የገበያ ቦታ ጥር 4 ቀን 2003 ዓ.ም. ከምሽቱ 5 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ግምቱ ከ10 እስከ 15 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረት መውደሙን የከተማው ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡ የሱቆቹ ባለቤቶች ደግሞ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙንና ግምቱም ከ10 ቢሊዮን ብር እንደሚበልጥ እየተናገሩ ነው፡፡