የከተማ አውቶቡስ ትኬት ዋጋ ተጠቃሚውን ግራ እያጋባ ነው
– ‹‹በትኬቱ ላይ ከተቀመጠው ዋጋ በላይ መክፈል የለብንም››
የአገልግሎት ተጠቃሚዎች
– ‹‹የነዳጅ ታሪፍ መቀያየር ትኬቱን በዋጋው እንዳንሸጥ አድርጐናል››
ድርጅቱ
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ ተጠቃሚዎች ከአንድ ሥፍራ ወደሌላ ሥፍራ ለሚጓጓዙበት የሚከፍሉት ክፍያ፣ ለርቀቱ ተመድቦ በአውቶቡስ ትኬት ላይ ከተጻፈው የገንዘብ መጠን ከ0.20 ሣንቲም በላይ በትርፍነት መከፈሉ፣ አግባብ አለመሆኑን አንዳንድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡