በወንዶ ገነት በተፈጠረ ግጭት አምስት ሰዎች ሞቱ

በአስፋው ብርሃኑ፣ ከሐዋሳ

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መስተዳድር ሲዳማ ዞን፣ ወንዶ ገነት ወረዳ፣ በጉጂ ኦሮሞ ተወላጆችና በሲዳማ ብሔረሰብ መካከል ታኅሣሥ 24 ቀን 2003 ዓ.ም. ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ በተቀሰቀሰ ግጭት፣ የአምስት ሰዎች ሕይወት የጠፋ ሲሆን፣ ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ቆስለዋል፡፡