ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከአዲሱ የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አዋጅ ጋር ተያይዞ፣ ካፒታላቸውን ቀንሰው ለመመዝገብ የሚቀርቡ ነጋዴዎች ጉዳይ እየፈጠረ ያለውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ጥናት እንዲጠና የፍትሐ ሚኒስቴርን፣ የንግድ ሚኒስቴርንና የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን አዘዙ፡፡

አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን፣ የአስተዳደሩን መሬት ልማት አስተዳደር ቦርድና የመሬት አስተዳደርና የግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣንን፣ “የሊዝ ውል ሊሰርዙብኝ አይገባም” በሚል፣ በ27 ሚሊዮን ብር ግምት ሐምሌ 28 ቀን 2003 ዓ.ም. ክስ መሠረተ፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትንና የፖለቲካ ተሿሚዎች የሚፈጽሙትን የሙስና ወንጀል ለማጋለጥም ሆነ የሕግ ተጠያቂዎች ለማድረግ እንደሚፈራ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

የቀረጥና የታክስ መጠኑ 889,666.95 ብር የሆነ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ በቱኒዝያ ኤምባሲ ስም ከዱባይ ተጭኖ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሰ በኋላ ሊወስዱ ሙከራ ያደረጉ ግለሰቦች በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ፡፡

በረሃብ አለንጋ እየተገረፈች ላለችው ሶማሊያ ዕርዳታ እንዳታገኝ ማነቆ ሆኖባት የከረመው ጽንፈኛው አልሸባብ፣ ዋና ከተማዋን ሞቃዲሾን ለቅቆ መውጣቱ ለሶማሊያውያንም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተደበላለቀ ስሜትን መፍጠሩን የውጭ ሚዲያዎች በመዘገብ ላይ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ውስጥ በረራዎች በክረምቱ ጭጋጋማና ደመናማ የአየር ፀባይ ምክንያት በሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረጉ በረራዎች ለመሰረዝና ለማዘግየት መገደዱን አስታወቀ፡፡

አቶ ሽመልስ አዱኛ፣  የቀድሞ የዕርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን፣ ኮሚሽነርየዛሬው የቆይታ አምድ እንግዳችን አቶ ሽመልስ አዱኛ ናቸው፡፡ አቶ ሽመልስ የተወለዱት በጅጅጋ ከተማ ጥቅምት 2 ቀን 1928 ዓ.ም. ነው፡፡ እርሳቸው የተወለዱት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ ስለነበር ከእናታቸው ጋር ወደ ኬንያ ሄደው ለአምስት …

‹‹ግለሰብም ሆነ መንግሥት የራሱን ሕዝብ መመገብ እስካልቻለ ድረስ አንገቱን ቀና አድርጐ መሄድ አይችልም›› Read more »

‹‹ማንም ተሳተፈም አልተሳተፈ ሠልፉ አይቀርም›› የኢትዮጵያ አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢአዴድ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲዎች በመስቀል አደባባይ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሠልፍ በጋራ ለመጥራት ያቀረቡለትን ጥሪ አለመቀበሉን ለሪፖርተር አስታወቀ፡፡

‹‹በቅርቡ ዕጣ እናወጣላቸዋለን›› የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙና ዕጣ ያልወጣላቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ሕገወጥ ደላሎች የኪራይ ገንዘብ እየተቀበሉባቸው እንደሚጠፉ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ድርቅ በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደ ረሃብ እንደማይሸጋገር የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምትኩ ካሳ አስታወቁ፡፡ መንግሥት እያደረገ ባለው ጥረት ችግሩ ከቁጥጥር ውጭ እንዳልሆነ አቶ ምትኩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የቀድሞው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር የአሁኑ በአሜሪካ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ግርማ ብሩ፣ ከአሜሪካ ለንግድና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ሥልጠና ከመጡት አምባሳደሮች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ አጭር ቆይታ ከሪፖርተር ጋር አድርገዋል፡፡

በአፍሪካ አኅጉር ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 19ኛው የዓለም ዋንጫ ከኢትዮጵያ ተመልካቾችን ለመላክ ተብሎ በተፈጠረ ማጭበርበር ምክንያት፣ ከህዳር 3 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ በጀርመን ፖሊስ ቁጥጥር ሥር የነበሩት የአስካሉካን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤት ለኢትዮጵያ ተላልፈው ተሰጡ፡፡

– የ121 ሚሊዮን ብር ቦንድ በወለድ ለመግዛት ወስነዋል በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሪል ስቴት ኩባንያዎች በዓባይ ወንዝ ላይ ለሚገነባው የህዳሴ ግድብ ሊያዋጡ የነበረው 200 ሚሊዮን ብር ሊሟላላቸው አለመቻሉን ገልጸው፣ ቦንድ በወለድ ለመግዛት 121 ሚሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻላቸውን ገለጹ፡፡

በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ በንግድና በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መስክ በተባበሩት መንግሥታት የሥልጠናና የምርምር ተቋም (ዩኒታር) የሚሰጠውን የስድስት ቀን ሥልጠና ከነገ ጀምሮ ይከታተላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣንና የሐረርና በደሌ ቢራ ፋብሪካዎችን ለመሸጥ ያወጣውን ጨረታ ያሸነፈው ታዋቂው የሆላንዱ ሄኒከን ኩባንያ ኃላፊዎች ነሐሴ 4 ቀን 2003 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሒልተን ስምምነቱ ሊያደርጉ ነው፡፡

– እዚህ ያካሄደው ስብሰባ ዛሬ ይጠናቀቃል የምሥራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኰሜሳ) የሰሜን ሱዳን ሪፐብሊክንና በቅርቡ የተመሠረተችውን የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክን ፍጻሜ ለመዳኘት ፍላጐት እንዳለው ገለጸ፡፡

በታምሩ ጽጌ | Reporter የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ቶለሳ ተስፋዬ፣ ትናንትና ጧት የፍርድ ቤት ማዘዢያ ይዘው በቤታቸው የተገኙ ሁለት ፖሊሶችን አምልጠው መሰወራቸውን ምንጮች ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡ ‹‹ሁኔታው እስከሚጣራ ድረስ እጄን ለፖሊስ አልሰጥም፤›› ሲሉ አቶ ቶለሳ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የኦብኮ …

የኦብኮ ሊቀመንበር እጄን ለፖሊስ አልሰጥም አሉ Read more »

በአራዳ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 15/16 ክልል ልዩ ቦታው አራት ኪሎ ታላቁ ቤተ መንግሥት ውስጥ አንድ የግምጃ ቤት ኃላፊና አንድ ሾፌር በ12 እና በአምስት ዓመታት ፅኑ እስራት፣ በ20 ሺሕ ብርና በአምስት ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ዓቃቤ ሕግ ጠየቀ፡፡

‹‹አውቀን ሳይሆን ነገሮች ተገጣጥመው ነው›› የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ‹‹ድርጅቱ መፍትሔ ካላመጣ ወደ ሕግ እንሄዳለን›› የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን ማገርኮን ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ይሠሩ የነበሩ 67 የሠራተኛ ማኅበር አባላት ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ መባረራቸውን …

በሠራተኛ ማኅበር የተደራጁ የኮንስትራክሽን ሠራተኞች ከሥራ ተባረርን አሉ Read more »

የኢትዮጵያ ንግድ መርከብን፣ የኢትዮጵያ ባህርና ትራንዚት ኢንተርፕራይዝንና የኢትዮጵያ ደረቅ ወደብ ኢንተርፕራይዝ ድርጅቶችን ለማዋሀድና በአንድ ኮርፖሬሽን ሥር ለማደራጀት ጥናቱን እንዲሠራ የተዋቀረው ኮሚቴ፣ ጥናቱን አጠናቆ ባለፈው ዓርብ ለትራንስፖርት ሚኒስትሩ ለአቶ ድሪባ ኩማ አቀረበ፡፡

– ኩባንያው አራት ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ያደርጋል የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦጋዴን ቤዚን ውስጥ የሚገኙ የማሌዥያ ኩባንያ በሆነው ፔትሮናስ ተይዘው የቆዩ የካሉብና የሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችትና ሌሎች ስምንት የነዳጅ ፍለጋ ቦታዎች፣ ፔትሮትራንስ ለተባለ ተቀማጭነቱ በሆንግ ኮንግ ለሆነ የቻይና ኩባንያ ተሰጡ፡፡

በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ፣ የትምህርት ጥራት ከመምህራን ብቃት ጋር ተዳምሮ የአገሪቱ አሳሳቢ ችግር መሆኑን አስታወቁ፡፡

በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ውስጥ የሚገኘው ‹‹ብዝኀነትን ለዘላቂ ልማትና ማኅበራዊ ለውጥ መጠቀም ፕሮግራም›› የሚሌኒየሙን የልማት ግብ ለማሳካት በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) በኩል የስፔን መንግሥት በሰጠው የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ፕሮጀክት ነው፡፡

– ሁለት የብሔራዊ ባንክ ሠራተኞች በነፃ ተሰናብተዋል የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በወርቅ ማጭበርበር ተከሰው በነበሩ አንድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኃላፊና አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባልን በፅኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ትናንትና ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

–  ከዕቅዱ በ300 ሚሊዮን ዶላር ያንሳል– ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሚመሩት ኮሚቴ  ይቀርባል–  በ2004 ከወጪ ንግድ እስከ 4.5 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል መንግሥት ከወጪ ንግድ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት አቅዶ 2.7 ቢሊዮን ዶላር በማግኘት የበጀት ዓመቱን አጠናቀቀ፡፡ እንደተለመደው ቡና ከሁሉም የወጪ …

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 2.7 ቢሊዮን ዶላር ተገኘ Read more »

– በቅርቡ የዲዛይን ጨረታ ያወጣል– ነዋሪዎች ቅሬታ አላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ከ23 ዓመታት በኋላ ቦሌ መድኃኒዓለም አካባቢ የሚገኘው 65 ሔክታር መሬት በአስቸኳይ እንዲታጠርና በቦታው ላይ የሚገኙ 543 ቤቶች እንዲፈርሱ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ምንጮች አመለከቱ፡፡

አያት አክሲዮን ማኅበር በእህት ኩባንያው ጊዜ መሪ ማርኬቲንግ አክሲዮን ማኅበር ተመስርቶበት የነበረውን 5.4 ሚሊዮን ብር በላይ ዕዳ ከነወለዱ (ዘጠኝ በመቶ) ጨምሮ እንዲከፍል ውሳኔ ተላለፈበት፡፡

– ‹‹ወደ አንድነት የሄዱት ሁለት አባላት ብቻ ናቸው›› የመኢአድ ዋና ጸሐፊ– ታግደው የነበሩ 62 አባላት ፓርቲውን መቀላቀላቸው ተነገረ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ጋር አብሮ ለመሥራት ያለው ዕቅድ እንደማይደናቀፍ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ፡፡

‹‹ደቡብ ሱዳን ለሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ቤት ሠራች›› ተብሎ ባለፈው ረቡዕ የደቡብ ሱዳን ምንጮችን ዋቢ አድርጎ የተዘገበው ዜና ትክክል አለመሆኑን፣ በኢትዮጵያ የሱዳን ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

በኃይሌ ሙሉ | ሪፖርተር ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ነፃነቱን ያወጀው የደቡብ ሱዳን መንግሥት ለቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ቤት ሠርቶ ያጠናቀቀ መሆኑን የደቡብ ሱዳን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ከምንጮቻችን ለመረዳት እንደቻልነው፣ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ለኮሎኔል መንግሥቱና ቤተሰቦቻቸው መኖርያ የሚሆን ዘመናዊ ቤት እንዲሠራ ያደረገው፣ …

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ለመንግሥቱ ኃይለማርያም መኖርያ ቤት ሠራ Read more »

‹‹ጉንዳኖቹ ሲፈለጉ ቁጫጮቹ መሞት የለብንም››  አነስተኛ ነጋዴዎች‹‹የካሽ ሬጂስተር አስገቡ የምንለው ከግምት ለመውጣት ነው››   የንፋስ ስልክ ላፍቶ ገቢዎች ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 12 አነስተኛ ነጋዴዎች የቀን ገቢያችንን ያላገናዘበና ፍትሐዊ ያልሆነ የግብር ግምት ተጥሎብናል አሉ፡፡

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓቃቤ ሕግ ተከሰውና ቅጣት ተላልፎባቸው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አየለ ደበላ (አይኤምኤፍ)፣ አቶ ገብረ ኪዳን ገብረ ሥላሴ (ሞሮኮ)፣ አቶ ከበደ ተሰራ (ወርልድ ባንክ) እና አቶ ሌንጫ ዘገዬ በባንክ ያላቸው ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ባለሥልጣኑ ሒሳብ …

የእነ አየለ ደበላ (አይኤምኤፍ) ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ለባለሥልጣኑ ገቢ ተደረገ Read more »