– ኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ የአንበሳውን ድርሻ ይዘዋል ባለፈው እሑድ የተሰበሰበው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌዴራል መንግሥት ለክልሎች የሚሰጠውን የድጎማ በጀት ቀመር አፀደቀ፡፡ ምክር ቤቱ የድጎማ ቀመርና የጋራ ገቢዎች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በሆኑት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት በአቶ ሽፈራው ሸጉጤ የቀረበውን የ2004 ዓ.ም. …

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚቀጥለውን ዓመት የድጎማ በጀት አፀደቀ Read more »

ባአክሲዮኖችን ለሁለት ከፍሎ ሲያወዛግብ የሰነበተው የዘመን ባንክ የምርጫ ሽኩቻ ተጠናቆ ባለፈው ቅዳሜ ሌላ ምርጫ ተካሂዶ መሥራቹን አቶ ኤርሚያስ አመልጋን በድጋሚ ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት በመምረጥ ተቋጭቷል፡፡

– የጤና ተቋማት የተሽከርካሪ አደጋ ተጐጂዎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመርዳት ይገዳዳሉ ከያዝነው ወር ማገባደጃ ጀምሮ በመላ አገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በሙሉ የሦስተኛ ወገን የመድን ሽፋን እንዲገቡ የሚያስገድደው አዋጅ በሥራ ላይ እንደሚውል ታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የታክሲ ስምሪት በቀጣና እንዲመደብ በተደረገ በስድስተኛ ቀኑ ከታክሲ አሽከርካሪዎች ተቃውሞ ገጠመው፡፡ በዚህም ምክንያት ስምሪቱ ሰኞ ማለዳ ተስተጓጐሎ ነበር፡፡ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ የተጀመረው የቀጣና ስምሪት የታክሲ ሾፌሮችንና ረዳቶችን እንዳላስደሰተ ይነገራል፡፡

ባለፈው ሐሙስ እኩለ ሌሊት ላይ የግብፅ መንግሥትን ከፍተኛ ልዑክ አስከትለው አዲስ አበባ የገቡት የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻራፍ፣ በዓባይ ተፋሰስ አገሮች ውስጥ የነበረው የሞኖፖሊ ዘመን አክትሞ የጋራ ጥቅሞች የሚከበሩበት ዘመን ላይ መደረሱን አስታወቁ፡፡

ጊዜው ጠዋት ወደ ሥራና ትምህርት መግቢያ ሰዓት ነው፡፡ ሥፍራው ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አጠገብ በሚገኘው አስኮ መስመር ላይ ነው፡፡ በአንድ ፌርማታ ርቀት ያህል በርካታ ሰዎች የመንገዱን ጠርዝ ይዘው ቆመዋል፡፡

የግብፁ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻሪፍ ኢትዮጵያን ለመጐብኘት ሐሙስ እኩለ ሌሊት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን የሚጐበኙበት ዋነኛው ምክንያት በዓባይ ጉዳይ ለመደራደር እንደሆነም አስቀድመው ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ የተካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነትን ሽሽት፣ ከደርግ ግድያና መቅሰፍት ለማምለጥ፣ ለትምህርት እንዲሁም የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ኑሮ ለመቀየር ወይም በሌላ አጋጣሚ፣ ወደ ውጭ ወጥተው እዚያው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሚሊዮኖች እንደሚቆጠሩ ግምታዊ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ጉና ንግድ ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ላይ የ7,843,812.33 ብር ክስ ሚያዝያ 28 ቀን 2003 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት አቀረበ፡፡

– ፍርድ ቤቱ አንድ የመከላከያ ምስክርን እንዳይመሰክሩ አገዳቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በመሠረተባቸው ክስ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት እንዲከላከሉ ብይን ያስተላለፈባቸው የአያት አክሲዮን ማኅበር ዋና ባለድርሻና ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ፣ የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ዳይሬክተር ዶ/ር መሐሪ መኮንንና …

የአያት አክሲዮን ማኅበር ተከሳሶች መከላከያ ምስክሮቻቸውን ማስማት ቀጥለዋል Read more »

በከባድ የእምነት ማጉደልና መንግሥታዊ ሰነዶችን አስመስሎ በማዘጋጀትና ወደ ሀሰት በመለወጥ የሙስና ወንጀል ክስ የተመሠረተበት ተከሳሽ በሌለበት 20 ዓመት ጽኑ እስራትና በሃምሳ ሺሕ ብር መቀጮ እንዲቀጣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 2 ቀን 2003 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ውሳኔ …

በሙስና ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በሌለበት በ20 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ Read more »

– አቶ መገርሳ ምሬሳ፣ የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የማይክሮ ኢንሹራንስ ዴስክ ኃላፊ በአገራችን በአብዛኛው የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚታወቁት የመድን አገልግሎቶች ጠቅላላ ኢንሹራንስና የሕይወት ኢንሹራንስ በሚል መጠርያ ነው፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች በአብዛኛው በከተማ አካባቢ የሚሰጡ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከዳሸን ባንክ ጋር የመጋዘን ደረሰኝን በመያዝ በመጋዘኖች አካባቢ ለሚገኙ አምራቾች ብድር ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት አደረጉ፡፡ ዳሸን ባንክ ይህን መሰሉን የብድር ስምምነት ከምርት ገበያው ጋር ሲፈራረም፣ ከንብ ባንክና ከንግድ ባንክ በመቀጠል ሦስተኛው ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ‹‹ሕዳሴ›› የሚለው ቃል በየቀኑ እየተስተጋባ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሥርዓቱ ላይ የተሟላ ሕዳሴ እውን ይሆናል ተብሎ ሲስተጋባ የነበረው ቀስ በቀስ በመልካም አስተዳደር ዙርያ ብቻ ሆነ፡፡

– የቀጣና ስምሪት ዛሬ ይጀምራል በአዲስ አበባ ከተማ ሚኒባስ ታክሲዎች በሚያስከፍሉት ታሪፍ ላይ ጭማሪ እንዲደረግና ትናንሽ ታክሲዎች ደግሞ በርቀት መለኪያ እየተጠቀሙ ግልጽና ፍትሐዊ የሆነ ክፍያ የሚያሰፍኑበትን ሁኔታ ለማመቻቸት መታቀዱን፣ የአዲስ አበባ ከተማ የመንገዶችና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈለቀ ኃይሌ አስታወቁ፡፡

በቅርቡ በመካከለኛው ምሥራቅና በሰሜን አፍሪካ የተከሰተውን የፖለቲካ አለመረጋጋት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ በትርፋማነቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በትናንትናው ዕለት በለቀቀው መረጃ መሠረት የሚያዝያ ወር 2003 ዓ.ም. የዋጋ ግሽበት መጠን 29.5 በመቶ መድረሱን ሲያስታውቅ፣ አሁንም የጥራጥሬ ምርቶች ዋጋ ዋነኛው የግሽበት ምክንያት መሆኑን ጠቁሟል፡፡

– የችሮታ ጊዜን ወደ ሁለት ዓመት ዝቅ አደረገ ለግብርና ልማት መሬት የወሰዱ ኢንቨስተሮች የሚያካሂዱትን መጠነ ሰፊ የደን ምንጣሮና ቃጠሎ አቁመው መሬቱን በአግባቡ እንዲይዙ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

በመላው ኢትዮጵያ በየዓመቱ የሚደርሰውን 2,200 የሞት አደጋ፣ 8,000 የአካል ጉዳትንና ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የንብረት ውድመትን በግማሽ መቀነስ የሚያስችል፣ የ10 ዓመት የመንገድ ደኅንነት ስትራቴጂና የድርጊት መርሐ ግብር ተዘጋጅቶ ይፋ ተደረገ፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት በድርድር ማግኘት የሚፈልግ አልሚ ጥያቄውን ማቅረብ ያለበት ለከተማው ከንቲባና ለዋና ሥራ አስኪያጅ ብቻ መሆኑን የሊዝ ቦርድ ምንጮች አመለከቱ፡፡

ኢኮኖሚና ቢዝነሳችንን ለማሳደግ መፈክሩም፣ ምኞቱም፣ ዕቅዱም በየዕለቱና በየአደባባዩ ቢስተጋባም፣ በተጨባጭ ግን በኅብረተሰቡ ዘንድ የሥጋት ስሜት  እየተስተዋለ ነው፡፡ ‹‹ዕድገት አለ ይባላል፤ ተጨባጩ ለውጥ ግን የት አለ?›› የሚል ጥያቄም በየዕለቱ እየተሰማ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ሊባል በሚያስችል ደረጃ የቅሚያ፣ አንቆ (ሀንግ) ትንፋሽ በማሳጣትና በመደብደብ ዝርፊያ እየተፈጸመ ነው፡፡ የከተማው ነዋሪዎች ከጧቱ 12 ሰዓት ተነስተው ወደፈለጉበት ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይችሉም እየተናገሩ ነው፡፡

– በችርቻሮ ሱቅ የተገኘ ሲሚንቶ ይወረሳል ተባለ የሙገርና መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሲሚንቶ ዋጋ ላይ በኩንታል የ126 ብር (ከ62 በመቶ በላይ) ጭማሪ ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡ ሥራ ተቋራጮች ጭማሪው ችግር ፈጥሮብናል አሉ፡፡

ረቡዕ፣ ሚያዝያ አሥራ ዘጠኝ ቀን ሁለት ሺሕ ሦስት ዓመተ ምሕረት፣ ንጋት አስር ሰዓት ተኩል መስቀል አደባባይ ስንደርስ፣ ‹‹ማን ነው የቀረው?›› በሚያስብል ሁኔታ በርካታ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች በቦታው ላይ ተገኝተው ነበር፡፡ ብዙዎቹ ከተደረደሩት አውቶቡሶች ውስጥ ገብተው ቦታቸውን በመያዝ የጉዞውን መጀመር በጉጉት ይጠባበቃሉ፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዘረፋና ንጥቂያ እየተስፋፋ መሆኑን ወንጀልም በተደራጀ መንገድ እንደሚፈጸም የከተማው ነዋሪዎች በጭንቀት ይናገራሉ፡፡ ፖሊስ በበኩሉ ዘረፋን ጨምሮ ማንኛውም ዓይነት ወንጀል ከቁጥጥር ውጭ አለመውጣቱን ይገልጻል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 15 የቦይንግ ኩባንያ ስሪት አውሮፕላኖችን ከተለዋጭ ሞተሮቻቸው ጋር ለመግዛት የሚያስችለውን 1.45 ቢሊዮን ዶላር ብድር እያፈላለገ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ብድሩን ካገኘ አሥር B787-8 እና አምስት B737-800 ቦይንግ አውሮፕላኖችን ይገዛል፡፡

–  የግብፅ ልዑካን የዓባይን የቀድሞ ውሎች አጣጣሉ የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻራፍ በመጪዎቹ ሰባት ቀናት ውስጥ በእርግጠኝነት ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ማስታወቃቸውን አልማስሪ አልዩም የተሰኘው የግብፅ ጋዜጣ ዘገበ፡፡ አዲስ አበባን በመጎብኘት ላይ ያሉት የግብፅ ልዑካን ቡድን አባላት የቀድሞዎቹን የዓባይ ውሎች እንደማይደግፏቸው አስታወቁ፡፡

የፊታችን ማክሰኞ ሚያዝያ 25 ቀን 2003 ዓ.ም. ወይም እ.ኤ.አ. ሜይ 3 ቀን 2011 በዓለም ደረጃ የፕሬስ ነፃነት ቀን ይከበራል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት በየዓመቱ ሜይ 3 የፕሬስ ነፃነት ቀን ተብሎ እንዲከበር ደንግጓል፡፡ በመላው ዓለምም፣ በአገራችንም ጭምር ይከበራል፡፡

መንግሥት ካለፈው ወር ጀምሮ በጨመረው የነዳጅ ዋጋ ላይ ተጠቃሚው ኅብረተሰብ ግብር እንዳይከፍል በማድረግ ቀጥተኛ ያልሆነ ድጎማ በማድረግ ላይ  እንደሚገኝ የንግድ ሚኒስትር ዴኤታው አስታወቁ፡፡

    መንግሥት በተወሰኑ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ላይ የጣለው የዋጋ ተመን ዕርምጃ በጉልህ የሚታዩ ክፍተቶችን መፍጠሩን፣ የማይፈለጉ ውጤቶችንም ያስከተለ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ዘርፍ ማኅበራት አስታወቀ፡፡

‹‹ኮርፖሬሽኑ ስለታሪፍ ጭማሪ ያቀደውም፣ የሚያውቀውም ነገር የለም›› አቶ ምህረት ደበበ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚያዝያ 17 ቀን 2003 ዓ.ም. ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል በአብዛኛው የአገሪቱ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው፣ በግልገል ጊቤ ሁለት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ …

ግልገል ጊቤ ሁለት ለሰዓታት በገጠመው ችግር ኃይል ማመንጨት አቋረጠ Read more »

የዩናይትድ ስቴትስ አየር ኃይል በአፍሪካ (ዩኤስ ኤይር ፎርስ አፍሪካ) ከአፍሪካ አገሮች ጋር በጋራ ለመሥራት ፍላጐት እንዳለው አስታወቀ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው፣ በአኅጉሪቷ የሚካሄደውን የፀረ ሽብር እንቅስቃሴ ለማገዝ የአፍሪካና የዩናይትድ ስቴትስ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

– በቀጣዮቹ ዓመታት ቢሊዮን ብሮችን የሚፈልጉ ፕሮጀክቶች ይበዛሉ ከፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ትልቁ የበጀት ተጠቃሚ የሆነው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሚቀጥለው ዓመት መንግሥት 20 ቢሊዮን ብር በጀት እንዲይዝለት ጠየቀ፡፡

የአምስት ዓመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሠረት በማድረግ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብ በሚፈለገው ደረጃ የማያሳትፍ መሆኑን፣ አመራሩም ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን ተጠቅሞ ሁሉንም ወደንቅናቄ በማስገባት በኩል ሰፊ እጥረት ያለበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ፡፡

መቀሌ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ተቋም ቅርንጫፍ መሥርያ ቤት ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ኃይሌ ተስፋዬ አልጋ ከያዙበት የኢትዮጵያ ሆቴል አሳንሰር (ሊፍት) ጉድጓድ ውስጥ ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ ወድቀው ተረፉ፡፡

ኢትዮጵያ ከታላላቅ ልጆቿ መካከል አንዱ የኾኑትን የአፋሩን ሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬን በሞት አጣች፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም ከትናንት በስቲያ በትውልድ ስፍራቸውና የሱልጣንነት መቀመጫቸው በነበረችው አሳይታ ከተማ ተፈጽሟል፡፡

(ሪፖርተር) — የዘንድሮ የፋሲካ ዓውደ ዓመት ገበያ በርካታ ሸማቾችን የተፈታተነ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የሳምንቱ መገባደጃ ድረስ እንደ ወትሮው የሞቀ ገበያ አልተስተዋለም፡፡ በተለይ የቅቤ ዋጋ ከመጠን በላይ መናር ተጠቃሽ ይሆናል፡፡ የዘይት፣ የስኳር፣ በቅርቡም የዱቄት ዋጋ መወደድና የአቅርቦት እጥረት ሲያጉላላው የነበረው ሸማቾች፣ …

የዘንድሮ የፋሲካ ዓውደ ዓመት ገበያ በርካታ ሸማቾችን የተፈታተነ ነው Read more »

– ፓርቲዎቹ በገንዘቡ ክፍፍል ላይ መስማማት አቅቷቸዋል የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ምክር ቤት ለስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለመስጠት መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ዶ/ር መሰለ ኃይሌ – የቅን ኢትዮጵያ ማኅበር ሊቀመንበር ዶ/ር መሰለ ኃይሌ ቅን አስተሳሰብንና የመደናነቅን ባህል ለማስፋፋት ተብሎ በሰኔ 26 ቀን 2002 ዓ.ም.  የተቋቋመው ቅን ኢትዮጵያ ማኅበር ሊቀመንበር ናቸው፡፡ በማኅበሩ ተግባር ዙርያ ሔኖክ ያሬድ አነጋግሯቸዋል፡፡

– በኢትዮጵያ ከተመዘገቡ ፕሮጀክቶች 11 በመቶ ብቻ መተግበራቸው ተረጋገጠ የቻይና ልዑካን በኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ማኅበራት ጋር ባደረጉት ውይይት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች አንዱ የተፈጥሮ ሀብትን የተመለከተ ሲሆን፣ ሀብት ልንቀራመት አልመጣንም፣ የተሳሳተ ግንዛቤ ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡