የእነ አየለ ደበላ (አይኤምኤፍ) ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ለባለሥልጣኑ ገቢ ተደረገ

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓቃቤ ሕግ ተከሰውና ቅጣት ተላልፎባቸው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አየለ ደበላ (አይኤምኤፍ)፣ አቶ ገብረ ኪዳን ገብረ ሥላሴ (ሞሮኮ)፣ አቶ ከበደ ተሰራ (ወርልድ ባንክ) እና አቶ ሌንጫ ዘገዬ በባንክ ያላቸው ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ባለሥልጣኑ ሒሳብ እንዲዛወር መደረጉ ታወቀ፡፡