‹‹ግለሰብም ሆነ መንግሥት የራሱን ሕዝብ መመገብ እስካልቻለ ድረስ አንገቱን ቀና አድርጐ መሄድ አይችልም››

አቶ ሽመልስ አዱኛ፣  የቀድሞ የዕርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሽን፣ ኮሚሽነር
የዛሬው የቆይታ አምድ እንግዳችን አቶ ሽመልስ አዱኛ ናቸው፡፡ አቶ ሽመልስ የተወለዱት በጅጅጋ ከተማ ጥቅምት 2 ቀን 1928 ዓ.ም. ነው፡፡ እርሳቸው የተወለዱት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ ስለነበር ከእናታቸው ጋር ወደ ኬንያ ሄደው ለአምስት ዓመታት በስደት ኖረዋል፡፡