የትምህርት ጥራትና የመምህራን ብቃት እያሳሰበ ነው

በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ፣ የትምህርት ጥራት ከመምህራን ብቃት ጋር ተዳምሮ የአገሪቱ አሳሳቢ ችግር መሆኑን አስታወቁ፡፡