የዋጋ ግሽበቱ 39.2 በመቶ ደረሰ

የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበት 39.2 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ከትናንትና በስቲያ አስታወቀ፡፡ የዋጋ ግሽበቱ በሰኔ ወር 38.1 በመቶ የነበረ ሲሆን፣ የሐምሌው የ1.1 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡