‹‹አንድ ቋንቋ ሲጠፋ አብሮ ይጠፋል ተብሎ የሚታሰበው ዕውቀቱ ጭምር ነው›› አቶ አካሉ ወልደ ማርያም የፕሮጄክቱ ብሔራዊ አስተባባሪ

በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ውስጥ የሚገኘው ‹‹ብዝኀነትን ለዘላቂ ልማትና ማኅበራዊ ለውጥ መጠቀም ፕሮግራም›› የሚሌኒየሙን የልማት ግብ ለማሳካት በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) በኩል የስፔን መንግሥት በሰጠው የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ፕሮጀክት ነው፡፡