በወርቅ ማጭበርበር የተከሰሱት የብሔራዊ ባንክ ኃላፊና የፖሊስ መኮንን ተፈረደባቸው

– ሁለት የብሔራዊ ባንክ ሠራተኞች በነፃ ተሰናብተዋል

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በወርቅ ማጭበርበር ተከሰው በነበሩ አንድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኃላፊና አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባልን በፅኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ትናንትና ውሳኔ አስተላለፈ፡፡