የአልሸባብ ሞቃዲሾን ለቅቆ መውጣት ደስታንና ስጋትን ፈጥሯል

በረሃብ አለንጋ እየተገረፈች ላለችው ሶማሊያ ዕርዳታ እንዳታገኝ ማነቆ ሆኖባት የከረመው ጽንፈኛው አልሸባብ፣ ዋና ከተማዋን ሞቃዲሾን ለቅቆ መውጣቱ ለሶማሊያውያንም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተደበላለቀ ስሜትን መፍጠሩን የውጭ ሚዲያዎች በመዘገብ ላይ ናቸው፡፡