አቃቂ ብረታ ብረትን የገዛው ድርጅት የ34.9 ሚሊዮን ብር ክስ ቀረበበት
የአቃቂ ብረታ ብረት ፋብሪካን በጨረታ የገዛው ባዘቶ ኢንዱስትሪና ንግድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በገባው ውል መሠረት ክፍያ አልፈጸመም በሚል፣ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የ34.9 ሚሊዮን ብር ክስ መሠረተበት፡፡
የአቃቂ ብረታ ብረት ፋብሪካን በጨረታ የገዛው ባዘቶ ኢንዱስትሪና ንግድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በገባው ውል መሠረት ክፍያ አልፈጸመም በሚል፣ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የ34.9 ሚሊዮን ብር ክስ መሠረተበት፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለሚቀጥለው ዓመት ካፀደቀው 11.8 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ 5.6 ቢሊዮን ብር ከታክስ ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡
– መመርያውን ወርቅ አቅራቢዎች እየተቃወሙት ነው ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወርቅ በማቅረብና በመሸጥ ላይ ያሉ ወርቅ አቅራቢዎች ከዚህ በኋላ በተመረጡ የክልል ከተሞች ብቻ በሚዘጋጅ የወርቅ መቀበያ ማዕከል ብቻ እንዲያቀርቡ የሚያስገድድ መመርያ ወጣ፡፡
– የደሃ አገር በጀት ነው – ግሽበቱን የገንዘብ አቅርቦት አባብሶታል – ታንክ የገዛነው ስላረጀብን ነው – ሱዳን ውስጥ ትጥቅ እናስፈታለን
በደቡብ ክልል ከሻኪሶ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዲባቦቴ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ አንዲት ላም ከአንገቱ በላይ ሰው የሚመስል ፍጡር ሰኔ 26 ለ27 አጥቢያ 2003 ዓ.ም. ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት አካባቢ መውለዷን የአካባቢው ነዋሪዎች ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡
‹‹የሠራተኛውን መብት በሕግ ለማስከበር ዝግጅታችንን ጨርሰናል›› የሠራተኛ ማኅበሩ ‹‹የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች መሠረታዊ ማኅበር የሚባል የለም›› ኢትዮ ቴሌኮም ኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞውን ማኔጅመንት ሙሉ በሙሉ ከተረከበበት ከታኅሣሥ 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ያደረጋቸው የሠራተኛ ቅነሳና የሥራ ሁኔታ ለውጦች፣ በአገሪቱ የተደነገጉ ሕግጋትን ያልተከተለና ኢትዮጵያም የተቀበለቻቸውን …
በታምሩ ጽጌ | ሪፖርተር በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ኔትወርክ ለመዘርጋትና ለልዩ ልዩ የጥፋት ድርጊት የሚውል አደረጃጀት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተገለጸው የሁለት ጋዜጠኞችና ሌሎች የሰባት ተጠርጣሪዎች የምርመራ ሒደት አለመጠናቀቁን፣ የፌዴራል ፖሊስና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡ የአውራአምባ …
የፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሰባተኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 22 ቀን 2003 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ የ15 ዓመት ዕድሜ ያላትን ልጁን ደፍሮ ባስረገዘ የ48 ዓመት ዕድሜ ያለው ጌቱ መንዲዳ በተባለ ግለሰብ ላይ፣ የአርባ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወራት ፅኑ እስራት …
ኢትዮጵያ ጠንካራ አገር እንድትሆን የማይፈልጉ ኃይሎች አሉን? አዎን አሉ፡፡ በምኞትም ባላቸው አቅም ሁሉ በመንቀሳቀስም ኢትዮጵያ እንዳታድግ፣ እንድትወድቅ፣ እንድትበታተን የሚፈልጉ ጠላቶች አሉ፡፡
በታምሩ ጽጌ | ሪፖርት ከሰኔ 3 ቀን እስከ ሰኔ 17 ቀን 2003 ዓ.ም. ባሉት 15 ቀናት ውስጥ በቦሌ፣ በቂርቆስና በልደታ ክፍላተ ከተሞች ውስጥ በጦር መሣርያ በመታገዝ በዝርፊያ ወንጀልና በነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች፣ ሰኔ 24 ቀን 2003 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር …
በቦሌ፣ በቂርቆስና በልደታ ክፍላተ ከተሞች በጦር መሣርያ የታገዘ ዝርፊያ ተካሄድ Read more »
በታምሩ ጽጌ | ሪፖርተር የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬና ፤ አዲስ ፕሬስና ፍትህ ጋዜጦች ላይ የፖለቲካ አምደኛ የሆነችው ወይዘሪት ርዕዮት አለሙ የታሰሩት በአሸባሪነት ወንጀል ተጠርጥረው መሆኑን መንግስት አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢብዴፓ) ሊቀ መንበር አቶ ዘሪሁን …
በኃይሌ ሙሉ | Reporter የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በተሽከርካሪ እጥረት ምክንያት በባለጉዳይ መኪና ለመገልገል እየተገደዱ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አስታወቁ፡፡ የዳኞች፣ የባለሙያዎችና የተሽከርካሪ እጥረት በፍርድ አፈጻጸም ላይ መስተጓጐል እየፈጠረ ነው፡፡ ትናንት በተካሄደው የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው …
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በተሽከርካሪ እጥረት ምክንያት በባለጉዳይ መኪና እየተገለገሉ ነው Read more »
(Reporter) — በየሳምንቱ ቅዳሜ የሚታመው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እሑድ ሰኔ 12 ቀን 2003 ዓ.ም. ከመኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ኃይሎች ተወስዶ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መታሰሩን የዝግጅት ክፍሉ አስታወቀ፡፡ ጋዜጠኛ ውብሸት በመኖሪያ ቤቱ በቁጥጥር ሥር የዋለው በርካታ …
በየሳምንቱ ቅዳሜ የሚታመው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እሑድ ሰኔ 12 ቀን 2003 ዓ.ም. ከመኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ኃይሎች ተወስዶ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መታሰሩን የዝግጅት ክፍሉ አስታወቀ፡፡
– ጉዳዩን ለመከታተል የፌዴራል መንግሥት ኃላፊዎች ሄደዋል የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በትግራይ ክልላዊ መንግሥት የሽሬ እንደ ሥላሴ ከተማ መንገድ ሥራ ‹‹ደረጃውን ባልጠበቀ መንገድ ተገንብቷል›› በሚል ከከተማው ነዋሪዎች ተቃውሞ ገጠመው፡፡
ሰኔ 15 ቀን 1980 ዓ.ም. በሐውዜን ከተማ በገበያ ቀን የተካሄደውን የአውሮፕላን ጭፍጨፋ የፈጸሙ የደርግ ባለሥልጣናት የሞት ውሳኔ ወደ ዕድሜ ልክ በመቀየሩና ይፈታሉ መባሉን በመቃወም የተጠራው የተቃውሞ ሠልፍ በመንግሥት መከልከሉ ተገለጸ፡፡
መንግሥት በገና በዓል ዋዜማ በተመረጡ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ተመን ገደብ ማውጣቱ አይዘነጋም፡፡ ከአምስት ወራት በኋላም ከሦስት ሸቀጦች በስተቀር ማለትም ስኳር፣ ዘይትና ዱቄት በስተቀር፣ ያስቀመጠውን የዋጋ ተመን አንስቷል፡፡
ከ23 ዓመታት በፊት ሰኔ 15 ቀን 1980 ዓ.ም. የጦር አውሮፕላኖች ድብደባ የተፈጸመባት የሐውዜን ከተማ፣ የሰብዓዊ መብት ከተማ ተብላ እንድትሰየም ጥያቄ ቀረበ፡፡
– የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሕንፃ አዋጁን ለማስፈጸም ደንብ አውጥቷል የሕንፃ ግንባታ የሚያከናውን ማንም ሰው የገነባውን ሕንፃ ካጠናቀቀ በኋላ ሳያሳውቅና ፈቃድ ሳይሰጠው ሥራ ሊጀምር እንደማይችል አዲስ የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ አስታወቀ፡፡
– ኢትዮጵያውያኑን ወደ አገራቸው የማስመለስ ሒደቱ ቀጥሏል ከሦስት ወራት በፊት በየመን በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመፅ ቁጥራቸው ያልታወቁ ኢትዮጵያውያን ዜጐች መሞታቸውን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ሰኔ 3 ቀን 2003 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡
ለ2004 ዓ.ም. የተያዘው የመንግሥት በጀት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡ የበጀት ረቂቅ አዋጁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በዚህ ሣምንት መጨረሻ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዘር ማጥፋት ወንጀል ከተከሰሱት 23 ከፍተኛ የደርግ ባለሥልጣናት መካከል 20 ዓመት የታሠሩት አሥር ከፍተኛ የደርግ ባለሥልጣናት ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ ቀብር ትናንት በኮተቤ ገደራ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ተፈጸመ፡፡
– ውሳኔው የሸማቾች ጥበቃና የንግድ አሠራር አዋጅን የጣሰ ነው የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች በትናንትናው ዕለት ጠቅላላ ስብሰባ አድርገው በግብይይት ሥርዓቱ ላይ በሰፊው ከተወያዩ በኋላ፣ የአንድ ኪሎ ሥጋ የዋጋ ጣሪያ ቫትን ጨምሮ 90 ብር እንዲሆን ተስማሙ፡፡
– አንድ ቢሊዮን ዶላር በጀት ተይዟል ላለፉት ዓመታት ለኢትዮጵያ ማዳበሪያ ሲያቀርብ የቆየው ያራ ሆልዲንግ፣ ከህንዱ ሴፍቴክ ኩባንያ ጋር በሽርክና ባቋቋመው ኢትዮ ፖታሽ ኩባንያ ስም በአፋር ክልል የፖታሽ ማዕድን ለማምረት የፈቃድ ጥያቄ አቀረበ፡፡
– ኮንትራቱን የወሰደው ኩባንያ 33 ሚሊዮን ብር ይከፈለዋል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬትና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በዘመናዊ መረጃ ሥርዓት ውስጥ ማደራጀት የሚያስችለውን አሠራር ለመዘርጋት፣ ማኔጅመንቱን ስዌድ ሰርቬይ ለሚባል የስዊድን ኩባንያ ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም. ለሁለት ዓመት የሚቆይ ኮንትራት ሰጠ፡፡
ኃይሌ ሙሉ | ሪፖርተር ግንቦት 20 ቀን 2003 ዓ.ም. በተካሄደው የድጋፍ ሰላማዊ ሠልፍ ያልተገኙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሠራተኞች በሦስት ቀን ውስጥ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ታዘዙ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የሰው ኃይል አስተዳደር …
(ሪፖርተር) — በደርግ ዘመን የደህንነት ሚኒስትር የነበሩት ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደ ስላሴ ዛሬ ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም. (እ.አ.አ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዪ፡፡ ኮሎኔል ተስፋዬ በደርግ ዘመን በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከተከሰሱትና በቅርቡም በመንግስት ውሳኔ መሰረት የተፈረደባቸው የሞት ፍርድ ከተነሳላቸው 23 …
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ልኳንዳ ነጋዴዎች ከትናንት ጀምሮ አንድ ኪሎ ሥጋ በ90 ብር ሒሳብ እንዲሸጡ መፈቀዱን የልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበር ሊቀመንበር አስታወቀ፡፡
(ሪፖርተር) — በደቡብ ክልል ከአዲስ አበባ በ500 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኘው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ‹‹ሳይነገረን እንዴት የምግብ ፕሮግራማችን ይለወጣል?›› በሚል በፈጠሩት ረብሻ፣ ከግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት ማቆማቸውን አንዳንድ ተማሪዎች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ የተወሰኑ ቀናትን ሽሮ፣ የተወሰኑ ቀናትን …
መንግሥት ከታህሣስ 2003 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ የዋጋ ተመን ካወጣባቸው ምርቶች መካከል ቢራና ለስላሳ መጠጦች የዋጋ ተመኑ ሊነሳላቸው እንደሚችል ታወቀ፡፡
ከአምስት ወራት በፊት መንግሥት በሥጋ ዋጋ ላይ ያወጣው ተመን ካልተስተካከለ፣ የልኳንዳ ነጋዴዎች ከገበያ እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበር ለመንግሥት አስታወቀ፡፡
የተከዜ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ከማመንጨት አቅሙ አንድ ሦስተኛ የሚሆነውን ኃይል እያቀረበ እንዳልሆነ ተገለጸ፡፡
– በአምስት ወራት ውስጥ 3,969 ሠራተኞች መፍለሳቸው ይነገራል መንግሥት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማውጣት የጀመረው የተንዳሆ የሸንኮራ አገዳ ፕሮጀክት የጉልበት ሠራተኛ ፍላጐትና አቅርቦት ሊጣጣም አለመቻሉን አንድ የፕሮጀክቱ ከፍተኛ ኃላፊ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
የህንድና የአፍሪካ ጉባዔ በመዲናችን አዲስ አበባ በትናንትናው ዕለት በይፋ ተከፍቷል፡፡ ጉባዔውም ከአጀማመሩ መልካም የሆኑ ዜናዎችን እያሰማን ይገኛል፡፡
(ሪፖርተር) — ባለፈው ረቡዕና ሐሙስ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ውስጥ የተገመገቡ 600 ያህል ተማሪዎች በጠና ታመው የሕክምና ዕርዳታ ተደረገላቸው፡፡ ተማሪዎች ዓርብ ባስነሱት ተቃውሞ ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውንና ግቢው በፖሊስ ጥበቃ ሥር መዋሉ ታውቋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ ረቡዕ ተማሪዎቹ …
– ሦስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመዋል ሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝ የሲሚንቶ ሽያጭና የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የግዥ አፈጻጸም ሕገወጥ ከመሆኑም በላይ ተደጋጋሚ ችግሮችና ክፍተቶች የሚታይባቸው መሆኑን፣ የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ሰሞኑን የወጣውን የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን መመርያ ተከትሎ የንግድ ማኅበረሰቡ ግራ እየተጋባ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን የሁሉም ነጋዴዎች አስተያየት ተመሳሳይ ባይሆንም ሪፖርተር ያናገራቸው የንግዱ ማኅበረሰብ አካላት ግን በሁለት የተራራቁ ግን ተመሳሳይ የችግር ማዕቀፎች ውስጥ ይወድቃሉ፡፡
የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት በተያዘለት ዕቅድ መሠረት እየተከናወነ አለመሆኑ ተገለጸ፡፡ በአካባቢው የደረሰው የጎርፍ አደጋ ለፕሮጀክቱ መጓተት እንደ ምክንያት ቀርቧል፡፡
የኦሮሚያ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የክልሉ የመሬት አስተዳደርና የአካባቢ ጥበቃ ቢሮ ምክትል ኃላፊን አቶ መሐመድ ኢብራሂም ሙሳን ባለፈው ሳምንት በቁጥጥር ሥር አዋለ፡፡
– አውራምባና ፍትሕ ጋዜጦች ሕዝቡን ለጥፋት ያነሳሳሉ አለ ሸገር 102.1 እና ዛሚ 90.7 ኤፍኤም ሬዲዮኖች በያዝነው ዓመት ባስተላለፏቸው ፕሮግራሞች የተለያዩ ግድፈቶችን እየፈጸሙ መሆናቸውን ብሮድካስት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም የኢኮኖሚክ ፎረምን በመጪው ዓመት እንድታዘጋጅ በደቡብ አፍሪካ በተካሔደው ጉባዔ ተመርጣለች፡፡ ይህ ፎረም በዓለም ላይ ከሚካሔዱ የኢኮኖሚ ጉባዔዎች ዋነኛው ነው፡፡
– የቢራ ፋብሪካዎች አጣብቂኝ ውስጥ ነን አሉ በኢትዮጵያ ለቢራ ፋብሪካዎች ዋነኛ ግብዓት የሆነውን ብቅል በማምረትና በማቅረብ ብቸኛ የሆነው የአሰላ ብቅል ፋብሪካ፣ በአንድ ኩንታል 300 ብር ጭማሪ መደረጉን አስታወቀ፡፡ የቢራ ፋብሪካዎች አጣብቂኝ ውስጥ እየገቡ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ባለፈው ረቡዕና ሐሙስ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ውስጥ የተገመገቡ 600 ያህል ተማሪዎች በጠና ታመው የሕክምና ዕርዳታ ተደረገላቸው፡፡
የዓለማችን ግዙፍ የፋይናንስ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶሚኒክ ስትራውስ ካሃን በአስገድዶ መድፈር ሙከራ ወንጀል በመጠርጠራቸው የኒውዮርክ ፖሊስ ባለፈው ቅዳሜ በቁጥጥር ሥር አውሎአቸዋል፡፡
– ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካፒታልና በሥራ አድራሻ ምክንያት መመዝገብ ላልቻሉ ጊዜ አራዝመዋል ንግድ ሚኒስቴር ሐምሌ 17 ቀን 2002 ዓ.ም. በተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀውን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ከየካቲት 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን በመግለጽ አተገባበሩን አስመልክቶ በትናንትናው ዕለት ለኢትዮጵያ ነጋዴዎች …
የአዲስ አበባ ከተማ የታክሲ ስምሪት በቀጣና ከተመደበ ዛሬ ሳምንት ሞላው፡፡ ይህም የተደረገው የትራንስፖርት ኢንዱስትሪው ሥርዓት ባለው መንገድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሆነ ይታመናል፡፡
ከደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከሐዋሳ ከተማ በሰባት አውቶቡስ ተሰባስበው ቅሬታቸውን ለማሰማት ወደ አዲስ አበባ ያመሩት የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አገልጋዮችና የእምነቱ ተከታዮች ምዕመናን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በምትገኘው ዱከም ከተማ ላይ ሲደርሱ በፖሊስ መታገታቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
– ሰባት ኩባንያዎች የጨረታ ሰነድ ገዝተዋል በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት በኦጋዴን ቤዚን ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት የሚገኝባቸውን የካሉብና የሂላል መሬቶችን ጨምሮ፣ ፔትሮናስ በተሰኘው የማሌዥያ ኩባንያ ተይዘው የነበሩ የነዳጅ ይዞታዎችን የኢትዮጵያ መንግሥት በማጫረት ላይ እንደሆነ ታወቀ፡፡
‹‹ሕወሓት ወደ እስር ቤት ሸኘኝ፤ አንድነት ግን ወደ ትምህርት ቤት እየላከኝ ነው›› አቶ ስዬ አብርሃ የሕወሓት የቀድሞ የአመራር አባል፣ የመከላከያ ሚኒስትርና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ስዬ አብርሃ፣ በዓለም ታዋቂ ከሆኑት ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው ሐርቫርድ …