Students killed by federal police. የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተገደሉ፣ ተደበደቡአንተነህ መርዕድ

የመጀመሪያው የኬንያ ፕሬዝደንትና የነፃነት ታጋይ ጆሞ ኬንያታ ብዙ ጊዜ የሚጠቀስላቸው፣ ስለቅኝ ገዥዎች የተናገሩት እውነት ይህን ይመስል ነበር። “ሚሲዮኖች ወደ አፍሪካ ሲመጡ እነሱ መጽሐፍ ቅዱስ፤ እኛ ደግሞ መሬት ነበረን። ዐይናችንን ጨፍነን እንዴት እንደምንጸልይ አስተማሩን። ዐይናችንን ስንገልጠው ግን እነሱ መሬታችንን እኛ መጽሐፍ ቅዱሱን ታቅፈናል” አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሩት አማኑኤል

ተደጋግሞ የሚነገር አንድ ጉዳይ አለ። ዴሞክራሲ ሒደት ነው፤ መልካም አስተዳደር በሒደት የሚመጣ ነገር ነው፤ የዴሞክራሲ ተቋማትን መገንባት ሒደት ነው ወዘተ. ይባላል። ለጽሑፌ መነሻ የሆነኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በረሃብ የተጎዳው ወገን ቁጥር በእርዳታ ድርጅቶች ዳታ 13 ሚሊዮን ደረሰ:: ቀየውን ጥሎ የሚሰደደው በርክቷል:: ‪ #‎Ethiopia‬ ‪#‎EthiopiaFamine‬ ‪#‎NGO‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Drought‬ ‪#‎FAO‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በተለያዩ የሰሜን እና ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍላተሃገራት የተሰማሩ ከተለያዩ የአለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች የተገኙ ዳታዎች …

በረሃብ የተጎዳው ወገን ቁጥር በእርዳታ ድርጅቶች ዳታ 13 ሚሊዮን ደረሰ:: ቀየውን ጥሎ የሚሰደደው በርክቷል:: Read more »

በሸዋ በባሌ በሃረርጌ እና በወለጋ ክፍለሃገራት ተማሪዎች ዛሬም ቁጣቸውን ሲገልጹ ውለዋል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterPlan‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ በሙልካጡሪ ሕዝቡ ከመሃል ሃገር ወደ ሰሜን ክፍለሃገራት የሚወስደው መንገድ ዘግቶት ይገኛል:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከፎቶግራፎቹ እንደምንመለከተው የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን የሚቃወሙ የኦሮሞ ተማሪዎች …

ተማሪዎች ዛሬም ቁጣቸውን ሲገልጹ ውለዋል:: በሙልካጡሪ ሕዝቡ ከመሃል ሃገር ወደ ሰሜን ክፍለሃገራት የሚወስደው መንገድ ዘግቶት ይገኛል:: Read more »

“እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው። አሁን ግን ይኸውና ህገ-መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል… ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ ዘመናዊ ኑሮ እየኖርን ነው።” እያለ የሚናገርን አንድ ጎልማሳ የቴሌቪዥኑ መስኮት ያሳያል። የደቡብ ቅላጼና ዘዬ ባለው አማርኛ ከደቡብ የመጣ …

የብሄር ብሄረሰቦች መብት እስከመጨፈር (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ) Read more »

በአዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል እና በወታደራዊ እዞች እንዲሁም በደህንነት ቢሮ ያለው መረጃ … ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎AddisAbabaMasterPlan‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኦሕዴድ ባለስልጣናት ላይ ቁጥጥሩ ጠንክሯል::የየወረዳ ጸጥታ ሃላፊዎች ወደ ፌዴራል ደህንነት ቢሮ የተጠሩ ሲሆን በምትካቸው ከፌዴራል ፖሊስ የተመረጡ የሕወሓት …

በአዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል እና በወታደራዊ እዞች እንዲሁም በደህንነት ቢሮ ያለው መረጃ … Read more »

ጋምቤላ: የፌደራሊዝሙ ክሽፈት ማሳያ? – በዘላለም ክብረት ሐሙስ  – ጋምቤላ ከተማ፡ የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዲሱን የስራ ዘመኑን የመጀመሪያውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ በማጽደቅ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ በመዝጊያው ስነ ስርዓት ላይ በጊዜው የክልሉ ፕሬዝደንት የነበሩት ኡሞት ኡባንግ ባደረጉት ንግግር፡ ‹‹ጋምቤላን ወደ ቀድሞው …

ጋምቤላ: የፌደራሊዝሙ ክሽፈት ማሳያ? – በዘላለም ክብረት Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከዚህ ቀደም የወያኔን አንድ ለአምስት አድረጃጀት ራሱን ወያኔን ለማጥቃት ልንጠቀምበት ይገባል የሚል በመርህ ደረጃ የቀረበ ሃሳብ ቢኖርም አንዱ የአንዱ የበላይ ነኝ በሚል የፖለቲካ እደምታ እንዲሁም በፖለቲከኞች መካከል አንድነት እንዳይፈጠር እና መከፋፈል እንዲኖር በሚሰሩ ጸረ ሕዝብ …

በሕቡእ መደራጀት የወቅቱን የመብት ትግል ለድል ያበቃዋል !!! (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ኢሳት ላይ፣ የቀድሞ የወያኔ ባለስልጣን የነበረው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ሲናገር ነው ያደመጥኩት። ዮሐንስ ታደስ ተካ ይባላሉ። በመሬት ጉዳይ የመንግስት ባለስልጣን ነበሩ። መረጃዎችን ይዘው ወደ ዉጭ ከተሰደዱ በኋላ መጽሀፍ ጽፈዋል። አቶ ዮሐንስ እንደጻፉት፣ በምርጫ ዘጠና ሰባት ማግስት ፣ በቦሌ አካባቢ አንድ …

አሁን ባለው ሁኔታ ለዉጥ አንጠብቅ – ግርማ ካሳ Read more »

የህወኃት መንግስት ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን በጣም የተሳሳተ ግምት ነው ያለው፡፡ አይደለም ሌላው ነጻ ኢትዮጵያዊ የእነርሱ ተላላኪዎችና ጥቅም ተጋሪዎች በሰሩት ወንጀል ፍርሃትና በጥቅም የሚያዩትን አላየንም ፣ የሚሰሙትን አልሰማንም ብለው ይካዱ እንጂ በህዝቡ ውስጥ እስካሉ የሚሆነውን እያዩና እየሰሙ ስለመሆናቸው ቅንጣት መጠራጠር የለባቸውም፣ በእብሪት …

የህወኃት ‹‹ከሞኝ ደጅ ሞፈር የሚቆርጥበት›› “የከፋፍለህ ግዛ ” መጋዝ አርጅቷል Read more »

በደቡብ ኦሞ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙትን ተቃዋሚዎች ለማሰር የሃሰት በራሪ ወረቀት ለመበተን መዘጋቸታቸዉን የዉስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጹ፡፡በተለያዩ የሀገራቺን ከተሞች ስለአርበኞች ግንቦት 7 የተበተኑ በራሪ ወረቀቶች አይነት በዞኑ ከተሞችም ሊበተን ይችላል ከሚል ስጋትና የህዝቡን አንሰማችሁም እንቅስቃሴ ለማፈን የተቃዉሞዉ መሪ ናቸዉ የሚሉዋቸዉን …

በደቡብ ኦሞ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙትን ተቃዋሚዎች ለማሰር የሃሰት በራሪ ወረቀት ለመበተን መዘጋቸታቸዉን የዉስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጹ፡፡ Read more »

በአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ መብራት ለሀያ ሰዓታት ያህል በመቋረጡ ምክንያት በፅኑ ህክምና ክፍል (ICU) ውስጥ የነበሩ ሦስት ህሙማን ለሞት ተዳረጉ፡፡ ህዳር 20 ምሽት ላይ ለ20 ሰዓታት መብራት ተቋርጦ በመቆየቱና የሆስፒታሉ ጀነሬተር ተበላሽቶ በመቀመጡ የተነሳ በፅኑ ህክምና ክፍል የነበሩ አንዲት ወላድ እናትና ሁለት ሌሎች ህሙማን ህይወታቸው እንዳለፈ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ከይርጋለም ከተማ ወደ ሆስፒታሉ ሪፈር ተደርጋ […]

የሲሚንቶ ገበያ ተቀዛቀዘ

-የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች ፈተና መሆኑ ተነገረ

በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እየተፈተነ የሚገኘው የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ የገበያ መቀዛቀዝ አሳየ፡፡ አገር ውስጥ የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ዓመታዊ የማምረት አቅማቸው 13 ሚሊዮን ኩንታል ቢሆንም፣ ሽያጩ ግን ከሰባት ሚሊዮን ኩንታል ያልበለጠ መሆኑ ታውቋል፡፡ 

 

ከገበያ መቀዛቀዝ ባሻገር የመንግሥት የልማት ድርጅት የሆነው ሙገር ሲሚንቶ፣ ሰሞኑን አንድ ኩንታል ፒፒሲ ሲሚንቶ የሚሸጥበትን ዋጋ ከ210 ብር ወደ 190 ብር አውርዶታል፡፡ 

በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና ከቀትር በኋላ 11፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 4፡00 ሰዓት ድረስ ኃይል እንዳይጠቀሙ በመንግሥት ትዕዛዝ በመሰጠቱ የገበያ መቀዛቀዝ መፈጠሩ የተነገረ ሲሆን፣ የተለያዩ ሲሚንቶ ፋብሪካዎችም ሥራ እያቆሙ ነው፡፡ 

ሥራ ካቆሙ ፋብሪካዎች ውስጥ ሲኤች ክሊንከር፣ ሁዎንግሽን ሲሚንቶና ኢስት ሲሚንቶ ይገኙበታል፡፡ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ዘርጋው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች ትልቁ ፈተና ሆኗል፡፡ 

የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከአንድ ሺሕ ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በላይ ሙቀት ስለሚፈልጉ፣ ይህ ሙቀት ከተፈጠረ በኋላ ኃይል ሲቋረጥ በርካታ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ለብልሽት እንደሚዳረጉ፣ እንደገና ኃይል ሲመጣ ደግሞ ፋብሪካዎቹን ወደ ሥራ ለመመለስ አስቸጋሪ እንደሆነ አቶ መኮንን ገልጸዋል፡፡ 

የገበያውን መቀዛቀዝ በተመለከተ ሁሌም በክረምት ወራትና ክረምት ከወጣ በኋላ ለተወሰኑ ወራት የሲሚንቶ ገበያ መቀዛቀዙ የተለመደ እንደሆነና ከመብራት ጋር እንደማይገናኝ ገልጸዋል፡፡ ይሁንና በዚህ ሐሳብ የማይስማሙ አሉ፡፡ 

ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የአንድ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ መንግሥት በአንድ ጊዜ በርካታ ፕሮጀክቶችን ያስጀመረ በመሆኑ፣ ለሚያሠራው ሥራ ክፍያ ለመፈጸም እየተቸገረ ነው፡፡ 

መንግሥት የበጀት እጥረት ስላለበት መንግሥት ክፍያ እየፈጸመ ባለመሆኑ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በመቀዛቀዙ የሲሚንቶ ገበያውም ሊቀዛቀዝ እንደቻለ አመልክተዋል፡፡ ባለፉት በርካታ ዓመታት የዋጋ ንረት ሲያጋጥመው የቆየው የሲሚንቶ ገበያ፣ በአሁኑ ጊዜ መቀዛቀዝ ስለታየበት፣ ሁሉም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከ190 ብር እስከ 210 ብር ድረስ ባለው ዋጋ በመሸጥ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት ሲሚንቶ ገበያው ውስጥ በኩንታል እስከ 400 ብር ይሸጥ ነበር፡፡ 

አቶ መኮንን ሙገር የሲሚንቶ ዋጋ ሊቀነስ ከቻለባቸው ምክንያቶች አንዱ ሲጠቀም የቆየውን ጥቁር ናፍጣ ትቶ፣ በድንጋይ ከሰል እንዲጠቀም በመወሰኑ ነው ብለዋል፡፡ 

በ15 ቀናት ውስጥ በድንጋይ ከሰል መጠቀም እንደሚጀምር የተናገሩት አቶ መኮንን፣ ከጥቁር ናፍጣ ይልቅ የድንጋይ ከሰል ርካሽ በመሆኑ ሙገር ዋጋ ለመቀነሱ አንዱ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 

 

ዛሬ (Dec. 7) ፕሮግራማችን ባለመደመጡ ይቅርታ እንጠይቃለን። በዚህ እለት 44ቱም የአሜሪካ ድምፅ ራድዮና ቴሊቪዥን እንዲሁም በኢንተርነት የሚሰራጩ ፕሮግራሞች ያልተደመጡበት ምክንያት በሕንፃው የኤሌትሪክ ሓይል ሥርጭት በመግጠሙ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን። ፕሮግራማችን በነገው እለት ይደመጣል።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅና የግዢና ንብረት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በአሥር ሚሊዮን ብር ሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታወቀ፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ኤፍሬም ደሳለኝና የግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ንጉሤ ታደሰ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ኅዳር 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ሲሆን፣ ኅዳር 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ 

ተጠርጣሪዎቹ በድርጅቱ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ተመድበው ሲሠሩ የመንግሥትንና የሕዝብን ጥቅም ማስጠበቅ ሲገባቸው፣ አቶ ገብረ አምላክ በርሄ ከሚባሉ ግለሰብ ጋር በመመሳጠር ግምቱ 8,974,000 ብር የሆነ የመንግሥት ንብረት (ምንነቱ አልተገለጸም) አውጥተው በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ መርማሪ ፖሊስ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት አስረድቷል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በተጨማሪ ያለምንም ስምምነትና ውል ከ1.9 ሚሊዮን ብር በላይ ከድርጅቱ ካዝና በማውጣት ለልኳንዳ ነጋዴዎች እንዲከፈል በማድረጋቸው፣ ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል መጠርጠራቸውን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ በመሆኑም መርማሪ ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ እንዲፈቀድላቸው ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄም ታልፏል፡፡ 

 

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

• ችጋር ምንድን ነው? ሰፊ ቦታንና ብዙ ሕዝብን የሚሸፍን፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ እንስሳት (ሰውንም ጨምሮ) ዕለት በዕለት የራሳቸውን አካል እስኪያልቅ ድረስ “እየበሉ” በመጨረሻም የሚሞቱበት ሁኔታ ነው፤ ረሀብ አካል ሲዳከም አካልን ለመገንባት የሚደረግ ጥሪ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Vacance ማስታወቂያጌቱ ኃይሉ

አቶ ዠ ደብዳቤ ጻፉ። 40 ዓመት ሙሉ መፈክር ሲጽፉ ኖረው፣ ኖረው፣ ኖረው አሁን አርቲስት ለመሆን የሚያበቃውን ዝግጅት የጨረሱ መስሎ ተሰማቸው። ሰሞኑን ለወጣው ማስታወቂያ “ብቁ ነኝ” ብለው አሰቡ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

PM Hailemariam Desalegn. ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝሩት አማኑኤል

ሕዝብ አዋቂ ነው። የፖለቲካ ሶሲዮሎጂስቷ ቴዳ ስኮፖል በሚያሳምን ሁኔታ እንደገለጸችውና በአገራችን በተግባር እንደሚታየው ሕዝብ ዝም ቢልም አፈናን ተቀብሏል ማለት አይደለም። በአፈና ውስጥ ያለ ሕዝብ ዝም ሲል እንድም ብናገርም ለውጥ አላመጣም ማለቱ ነው፤ አንድም ማኩረፉንና መከፋቱን መግለጹ ነው፤ አንድም የተመቻቸ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ አድብቶ መጠበቁ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Prof. Mesfin Woldemariam ፕ/ር መስፍን ወልደማርያምፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

በፌስቡክ የምንሰባሰበው ለመወያየት፣ አንዱ ከሌላው እንዲማር፣ መረጃዎችን በነጻነት እንድንለዋወጥ፣ ይህንን ሁሉ በማድረግ ራሳችንን ለማሻሻል፣ የእኛ መሻሻል እየተራባና እየተባዛ የአገርና የሕዝብ መሻሻል እንዲሆን፣ ከተቻለንም ከአገራችንና ከሕዝባችን አልፈን የምንታይ የዓለም አካል እንድንሆን መስሎኝ ነበር፤ ሳየው በዚያ መንገድ ላይ ያለንና ፌስቡክን ለበጎ ዓላማ እየተጠቀምንበት ያለን አይመስለኝም፤ ስለዚህ ወይ መታረም፣ አለዚያም በፌስቢክ ጊዜ ማጥፋቱን መተው ምርጫ ሊሆንብን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopia and the World Bank of Lies, Damned Lies and Statislies, by Prof. Almariamፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

ጆን ሚልተን ገነትን ማጣት/Paradise Lost በሚለው መጽሀፋቸው “የቱም ዓይነት ቅጥፈት ቢሆን ዘለቄታዊነት የለውም የሰማይ ቁጣንም ይስባል።” በማለት ጽፈዋል። በእርግጥ ሚልተን ሊጨበጥ ሊዳሰስ ስለማይችለው ባዶ ምናብ ስለሚፈጥረው ስለሰይጣን እና ስለዕኩይ ምግባሩ ነበር የጻፉት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አዲስ አበባን የማስፋት ኢትዮጵያን የማጥበብ አላማው ጥቅሙ ለሕወሕቶች ብቻ ነው:: (እንዴት?) ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AddisAbabaMasterplan‬ ‪#‎Ethiosudanborder‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሕወሓት አገዛዙን በእጁ ካደረገ ጀምሮ ለሃገርም ይሁን ለሕዝብ የፈየደው ምንም ነገር የለም::በልማት ስም እየሰራን ነው በሚል ሃሰተኛ የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ ሃገሪቷን …

አዲስ አበባን የማስፋት ኢትዮጵያን የማጥበብ አላማው ጥቅሙ ለሕወሕቶች ብቻ ነው:: (እንዴት?) (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

በማረሚያ ቤት አለመኖራቸው በተገለጸው አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ

በሽብር ድርጊት ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሥርቶባቸው ማረሚያ ቤት በሚገኙት በእነ ዘመኑ ካሴ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት በተቆጠሩት የግንቦት ሰባት አመራር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣

በመከላከያ ምስክርነት እንዳይቀርቡ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ይግባኝ ኅዳር 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ውድቅ ተደረገ፡፡

ተከሳሾቹ ከተመሠረተባቸው ክስ አንዱ የግንቦት ሰባት አመራር ከነበሩትና ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ከየመን ወደ አስመራ ሊሄዱ ሲሉ ከሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ከተሰጡት አቶ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተው መመርያ መቀበላቸውን የሚመለከት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም አቶ አንዳርጋቸው በፌዴራል ማረሚያ ቤት ስለሚገኙ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው፣ ክሱን እየመረመረ ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት አመልክተው ፍርድ ቤቱም ተቀብሏቸዋል፡፡

የተከሳሾቹን አቤቱታ በመቃወም ለፍርድ ቤቱ ያመለከተው ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ፣ አቶ አንዳርጋቸው በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብና በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የክስ መዝገብ የዕድሜ ልክና ሞት ፍርደኛ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ምስክርነት ለመስጠት እንደማይችሉና መብታቸው የተገፈፈ መሆኑን አስረድቶ ተቃውሞ ነበር፡፡ ነገር ግን ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን አቶ አንዳርጋቸው መብታቸው የተገፈፈው ስለራሳቸው እንጂ ስለሌሎች ምስክርነት መስጠት ስላልሆነ ሊመሰክሩ እንደሚገባ ገልጾ፣ የዓቃቤ ሕግን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ ቀርበው እንዲሰሙ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡

አቶ አንዳርጋቸውን በመከላከያ ምስክርነት እንዲያቀርብ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ታዞ የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት ሳያቀርባቸው ቢቆይም፣ ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ደብዳቤ ግን ‹‹አቶ አንዳርጋቸው ማረሚያ ቤት የሉም፤›› ብሎ መግለጹ ይታወሳል፡፡

ተከሳሾቹ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ በመቃወም አቶ አንዳርጋቸው አገር ውስጥ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር እንደሚያውቁ በመጠቆም፣ ለእነሱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ተመካክሮ እንደሚያሳውቃቸው ገልጾ በቀጠሮ ላይ እንዳሉ፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ አቶ አንዳርጋቸው በመከላከያ ምስክርነት ሊቀርቡ እንደማይገባ ለሥር ፍርድ ቤት ያመለከተበትን ምክንያት ጠቅሶ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ መርምሮ በሰጠው ብይን በፍርድ ቤት እንዲቀርብ የታዘዘ ምስክር ‹‹ይቅረብ አይቅረብ›› ተብሎ ይግባኝ ሊባል እንደማይቻል በመግለጽ፣ የዓቃቤ ሕግን ይግባኝ እንዳልተቀበለው አስታውቋል፡፡ 
የጠቅላይ ፍርድ ቤትን ውሳኔ የተቃወመው ዓቃቤ ሕግ፣ መሠረታዊ የሕግ ጥሰት መፈጸሙን በመጥቀስ ለሰበር ሰሚ ችሎት ማመልከቻ ማቅረቡን ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡  

በገዛ አፈ-ሙዙ መቃብሩን የሚቆፍር የሽንፈትን ጽዋ ይጎነጫል ! ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎SemayawiParty‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ @SemayawiParty ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማንና ዙሪያን ለማከለል ከወጣው የማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ፤ ገቢራዊነትና ሃሳቡን የተቃወሙ የኦሮሞ ተወላጆች እና …

በገዛ አፈ-ሙዙ መቃብሩን የሚቆፍር የሽንፈትን ጽዋ ይጎነጫል ! – ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ Read more »

በእንደርታ ወረዳ ለሚገኙ በድርቅ ለተጎዱ ተብሎ የመጣው ኣንድ እስካንያ መከኒ ከነተጎታቹ የእርዳታ እህል በወረዳው ባለስልጣናትና ነገዴዎች በመመሳጠር የተራገፈ ኣስመስለው በሌላ መኪና ገልብጠው ጭነው ሲወስዱ የኲሓ ህዝብ እጀ ከፈንጅ ይዞ ለፖሊስ ኣስረክበዋል። እነዚ የወረዳ ባለ ስልጣናትና የኲሓ ነጋዴዎች የዘረፉት በኣራት መኪኖች …

በእንደርታ ወረዳ ለሚገኙ በድርቅ ለተጎዱ ተብሎ የመጣው የእርዳታ እህል እየተዘረፈ ነው። Read more »

የቡራዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፌደራል ፖሊሶች የተከበቡ ሲሆን ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ::በሃሮማያ ዩንቨርስቲ በር ላይ አንድ ወጣት ተማሪ ተገሏል::የሃሮማያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ በአከባቢው በዳሞታ ባቴ ፊንቂልጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል::ይህን ተከቶ ከሆርሶ ወታደራዊ ካምፕ በርካታ ወታደሮችን የጫኑ …

የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ በመላው ሃገሪቷ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። Read more »

ከኦነግና ኦነጋውያን ጋር ሰልፍ ስለመውጣት? ኦነግና ኦነጋውያንን ወያኔንና የወያኔን ፖሊሲ ሲተቹ ስመለከት ይገርመኛል! ኦነግም ወያኔም አንድ ጡት የጠቡና ዛሬም የሚጠቡ የኢትዮጵያና የአማራ ጥላቻ ውላጆች የሆኑ የአንድ «ርዕዮተ አለም» መንትያ ልጆች ናቸው። የሁለቱ ልዩነት ወያኔ መሰሪነቱን አሟጦ በመጠቀም ለስልጣን ቋምጦ ሲቅበዘበዝ …

ከኦነግና ኦነጋውያን ጋር ሰልፍ ስለመውጣት? Achamyeleh Tamiru Read more »

Prof. Getatchew Haile ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

መግቢያ፤

መጀመሪያ ለመግቢያ ያህል፥ “ዘመድ” የሚለውን ቃል እንዴትና ለምን እንደተጠቀምኩበት ላስረዳ። “ዘመድ” ማለት “ወገን” ማለት ነው። በእንግሊዝኛ “kin, family, tribe” ማለት ነው። በየሊቃቸው የሚመሩ የተለያዩ የመላእክት ሠራዊት “ዘመድ” ወይም “ነገድ” ነው የሚባሉት”–ዘመደ መላእክት፣ ነገደ መላእክት። ሌሎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው መጠሪያዎች “ቤት” (ቤተ አምሐራ)፣ “ጎሳ” (የጉጂ ጎሳ)፣ “ዘር” ናቸው። ዛሬ ደግሞ “ብሔረ ሰብ” የሚለው መጠሪያ ነግሧል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሰሞኑን በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች በኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ማውጣት ባለመቻላቸው፣ በአጭር የመልዕክት ጽሑፍ ገንዘብ ማውጣታቸውን በሚገልጸው መልዕክት ከፍተኛ መደናገጥ እየተፈጠረባቸው ነው፡፡

ባንኩ በበኩሉ በጊዜያዊ ገንዘብ ዝውውር የኔትወርክ ችግር ያጋጠመ ቢሆንም፣ የገንዘብ ኪሳራ እንደማይገጥማቸው ገልጿል፡፡

በከተማዋ የተለያዩ የባንኩ ቅርንጫፎችና በንግድ ተቋማት አካባቢ በተተከሉ የኤቲኤም ማሽኖች ደንበኞች ገንዘብ ለማውጣት ቢሞክሩም፣ ሙከራቸው አለመሳካቱን ከማሽኑ የመረጃ ሰሌዳ እየተገለጸላቸው መሆኑንም እየገለጹ ነው፡፡ ሪፖርተርም ይኼንኑ ችግር በተለያዩ ቦታዎች ተዟዙሮ አይቷል፡፡ በተለይ ደንበኞች ሙከራው እንዳልተሳካላቸው ዓይተው ከሄዱ በኋላ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ሞክረው ያልተሳካላቸውን የገንዘብ መጠን ማውጣታቸውን የሚገልጸው መልዕክት ሲደርሳቸው፣  ድንጋጤና ግራ መጋባት ተፈጥሮባቸዋል፡፡ 

ነገር ግን ከቆይታ በኋላ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ወደ አካውንታቸው መመለሱን የሚያሳይ መልዕክት ከባንኩ እንደሚደርሳቸውም ለመረዳት ተችሏል፡፡ ይኼንን በተመለከተ መገናኛ፣ አራት ኪሎ፣ ካዛንቺስና ቦሌ አካባቢዎች የሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች ሪፖርት በሚያደርጉ ደንበኞች ተጨናንቀው መሰንበታቸውን ለማየት ተችሏል፡፡ በአንዳንዶቹ ቅርንጫፎች ደንበኞች በምሬት ከባንኩ ሠራተኞች ጋር ሲጨቃጨቁም ተስተውለዋል፡፡

የባንኩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በተወሰኑ ቅርንጫፎች አካባቢ ባሉ ማሽኖች ችግሩ መስተዋሉን አምነው ችግሩ ከኔትወርክ መቆራረጥ ጋር የተያያዘ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ከቴክኖሎጂው ጋር ለመራመድ በሚደረገው ጥረትም ችግሮች እንደሚከሰቱ ጠቁመዋል፡፡

ችግሩ የተከሰተው በዝውውር (Transfer)  አለመሟላት ምክንያት ቢሆንም፣ በማዕከል ቋት አማካይነት የሚተላለፍ በመሆኑና ጥብቅ ክትትል ስለሚደረግበት፣ ደንበኞች ሥጋት ላይ ሊወድቁ እንደማይገባና በፍጥነት ሊስተካከል እንደሚችል አቶ ኤፍሬም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ደንበኞች እንዲህ ዓይነት ችግር በሚገጥማቸው ወቅት በአቅራቢያቸው በሚገኙ ቅርንጫፎች ወይም ኤቲኤም ካርዱን ያወጡበት ቅርንጫፍ በመሄድ ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የባንኩን ነፃ የስልክ መስመር በሆነው በ950 በመደወል ጥያቄ ሊያቀርቡ ይገባልም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላው አገሪቱ ከ650 በላይ የኤቲኤም ማሽኖች  አሉት፡፡ በአዲስ አበባ ብቻ ከ250 በላይ መትከሉን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

 

ለኢትዮጵያ ተማሪዎችና ሁሉም ወጣቶች ሀገራዊ ጥሪ ….. ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምፅ ሬዲዮ: በአሁኑ ጊዜ ያለውን የሀገራችን አሳሳቢ ሁኔታ በማጤን ለወሳኝ የህብረሰብ ክፍሎች ሁሉ የትግል ጥሪን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ በቅድሚያ ለለውጥ አምጪዎችና የሰፊው ህዝብ ወገኖች ለሆናችሁት ወጣቶች የትግል ጥሪ …

ለኢትዮጵያ ተማሪዎችና ሁሉም ወጣቶች ሀገራዊ ጥሪ : ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምፅ Read more »

– ተጨማሪ የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ኃይል አባላት አመጽ ወደተቀጣጠለባቸው አካባቢዎች እንዲሰማራ የታዘዘ መሆኑ ታወቀ፤ አመጹ አሁንም ተፋፍሞ ተቀጣጥሏል – የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጤና ተቋም በድርቁ ምክንያት በበሽታ የሚሰቃዩትን ህጻናትና ድካሞች ለመታደግ ወደ ኢትዮጵያ የህክምና ቡድን የላከ መሆኑን አስታወቀ -በናይጄሪያ ሰሜን …

ተጨማሪ የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ኃይል አባላት አመጽ ወደተቀጣጠለባቸው አካባቢዎች እንዲሰማራ የታዘዘ መሆኑ ታወቀ፤ አመጹ አሁንም ተፋፍሞ ተቀጣጥሏል Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ምንም ያህል ልዩነት ቢኖረው የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው፡፡የአንድ ‹‹ህዝብ›› የእምነት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ…መብቱ በግለሰብ ደረጃ ካልተጠበቀለት በስተቀር የ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› መብት ሊጠበቅ አይችልም፡፡ ችግሩ የ‹‹ብሄርና›› ሌሎች ማንነቶችን የሚጠቀሙ የፖለቲካ ቡድኖች ከግለሰብ ማንነት …

በተማሪዎች ደም የደመቀው አገዛዝ የግለሰብ መብት እስካላከበረ የብሄር ብሄረሰቦች መብት ሊያከብር አይችልም:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በመከላከያ ምስክርነት ይቅረቡ አይቅረቡ ዙሪያ የተነሳው ክርክር ሰበር ሰሚ ችሎት ደረሰ::የጠቅላይ ፍርድ ቤትን ውሳኔ የተቃወመው ዓቃቤ ሕግ፣ መሠረታዊ የሕግ ጥሰት መፈጸሙን በመጥቀስ ለሰበር ሰሚ ችሎት ማመልከቻ ማቅረቡን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በሽብር ድርጊት ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሥርቶባቸው ማረሚያ ቤት …

በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በመከላከያ ምስክርነት ይቅረቡ አይቅረቡ ዙሪያ የተነሳው ክርክር ሰበር ሰሚ ችሎት ደረሰ:: Read more »

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅና የግዢና ንብረት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በአሥር ሚሊዮን ብር ሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታወቀ፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ኤፍሬም ደሳለኝና የግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ንጉሤ ታደሰ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ኅዳር 21 …

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅና የግዢና ንብረት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በአሥር ሚሊዮን ብር ሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታወቀ፡፡ Read more »

ልማታዊ አርቲስት የሚባለው ሰራዊት ፍቅሬ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 50ኛ አመቱን ለማክበር ባወጣው ጨረታ ከባለስልጣኑ ኃላፊዎች ጋር ባደረገው መመሳጠር የቀረበውን የይስሙላ ጨረታ እንዳሸነፈ ተደርጎ የ9 ሚሊየን 411 ሺህ 600 ብር ጨረታ ያሸነፈበት ስራ በጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዲሰረዝ ተደረገ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን …

ጸረ ሙስና ኮሚሽን አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ከኢትዮጲያ ቴሌቪዥን ባለስልጣናት ጋር ተመሳጥሮ ሊሰራው የነበረውን ሰራ ሰረዘው። Read more »

– በተለያዩ ከተሞች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚያደርጉት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ቀጥሏል –  በጎንደር ውጥረቱ ተባብሷል –  በካይሮ በአንድ ሬስቶራንት ውስጥ በደረሰ ቃጠሎ በርካታ ሰዎች ህይወታቸውን አጡ – የጣሊያን ጠረፍ ጠባቂዎች ስደተኞችን አዳኑ – በሶማሊያ አንዲት ጋዜጠኛ በፈንጅ ተገደለች = – የካጋሜን ለሶስተኛ …

በጎንደር ውጥረቱ ተባብሷል : በተለያዩ ከተሞች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚያደርጉት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ቀጥሏል Read more »

የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላንን በተመለከተ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ያለውን ዝርዝር አቋም በተመለከተ የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን አዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ በፅ/ቤታቸው ተገኝቶ አነጋግሯቸዋል፡፡ መንግሥት ማስተርፕላኑ ከተሞችን በመሰረተ ልማት በማስተሳሰር እድገትን ለማምጣት …

“ወደ እውነተኛው ፌደራሊዝም እንመለስ” የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ Read more »

የመጨረሻዋ የለውጥ ሂደት ላይ ነን መሆናችንን አውቀን ጊዜውን እንጠቀምበት::(ምንሊክ ሳልሳዊ) ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianOppostionParties‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከ1997 ምርጫ ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ወያኔን በሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለመጣል የነበሩ እድሎችን በአንድነት ቆመን ስላልተጠቀምንበት አገዛዙ እድሜውን ሊያስረዝም ችሏል::ልብ በሉ ሕዝቡ …

የመጨረሻዋ የለውጥ ሂደት ላይ ነን መሆናችንን አውቀን ጊዜውን እንጠቀምበት::(ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

– 1500 ጥበቃዎች ተመድበዋል – ለጥበቃ በወር 3ሚ. ብር ያወጣል የኢትዮ – ጅቡቲ የሃዲድ መስመርን የሚዘረጋው ቻይና ኩባንያ ከስርቆት ጋር በተያያዘ 20 ሚሊዮን ብር ገደማ ኪሳራ እንደደረሰበት የታወቀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ስርቆቱን ለመከላከል ከ1500 በላይ ጥበቃዎች  በሀዲድ መስመሩ ላይ ተመድበዋል፡፡ …

በስርቆት 20ሚ. ብር አጣሁ አለ የኢትዮ-ጅቡቲን የሃዲድ መስመር የሚገነባው ኩባንያ Read more »

ከቡድኑ ጋር ወደ አገራቸው እንዳይመለሱ፣ ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው ነበር በሴካፋ ዋንጫ ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ የመጣውን የኬንያ ብሄራዊ ቡድን ልኡካን የመሩት የክለቡ ማናጀር ዊሊስ ዋሊያውላ፤ ስድስት የቡድኑ ልኡክ አባላት ለአስር ቀናት አርፈውበት ለቆዩት “እንዳለ እና ቤተሰቡ ቸርቺል ሆቴል መከፈል የነበረበትን 41 ሺህ …

በአዲስ አበባ በ41 ሺህ ብር የሆቴል ዕዳ የተያዙት የኬንያ ብሔራዊ ቡድን መሪ ተለቀቁ Read more »

የፍ/ቤት ክርክሩ ከ3 ዓመት በላይ ፈጅቷል የሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ሚካኤል፤ በነሐሴ ወር 2003 ዓ.ም ከሞቱ በኋላ ነው፤ “የሊቀ ጳጳሱ ልጅ ነኝ” የሚል የወራሽነት አቤቱታ ለፍ/ቤት የቀረበው፡፡ “የሟች ልጅ ነኝ” የሚል አቤቱታ ያቀረቡት አቶ ዮሐንስ ተክለሚካኤል፤ …

“የሊቀ ጳጳሱ ልጅ ነኝ” በሚል የቀረበን ጥያቄ ፍ/ቤቱ ውድቅ አደረገ Read more »

በአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ መብራት ለሀያ ሰዓታት ያህል በመቋረጡ ምክንያት በፅኑ ህክምና ክፍል (ICU) ውስጥ የነበሩ ሦስት ህሙማን ለሞት ተዳረጉ፡፡ ህዳር 20 ምሽት ላይ ለ20 ሰዓታት መብራት ተቋርጦ በመቆየቱና የሆስፒታሉ ጀነሬተር ተበላሽቶ በመቀመጡ የተነሳ በፅኑ ህክምና ክፍል የነበሩ አንዲት …

በአዋሣ ሪፈራል ሆስፒታል መብራት በመቋረጡ 3 ህሙማን ህይወታቸው አለፈ Read more »

“ማስተር ፕላኑ ልማትን ያሻሽላል፤ በረብሻ የተሳተፉ ይከሰሳሉ” – መንግሥት “የአዲስ አበባና የፊኒፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን” ላይ፣ ሰሞኑን በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች  በተቀሰቀሰው ተቃውሞ፣ ከፖሊስ ጋር ግጭት ተፈጥሮ፣ ሶስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፤ መንግስትን ተጠያቂ አድርጓል፡፡ የክልሉ …

መንግሥት፣ ማስተር ፕላኑን ካልሰረዘ፣ ሰላማዊ ሰልፍ እጠራለሁ” – ኦፌኮ Read more »

የባቡሩ ጦስ!! በዘሪሁን ገሠሠ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ሴትና የሰው ጉልበት እርካሽ ነው፡፡›› ውድ አንባቢያን በዚህ ፅሁፌ የአዋሽ ኮምቦልቻ ወልድያ /ሀራ/ የባቡር መስመር ግንባታን ተከትሎ ግንባታውን ለመስራት አሸናፊ ሆኖ በቀረበው ያፒ መርከዚ የተሰኘ የቱርክ ኩባንያ ወደሀገራችን በገቡ ቱርካውያን ሰራተኞች እየተፈፀመ ስላለው ባህልና …

የባቡሩ ጦስ!! – ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ሴትና የሰው ጉልበት እርካሽ ነው፡፡›› – በዘሪሁን ገሠሠ Read more »

– በርካታ የጫንጮ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ባልታወቀ በሽታ ታመሙ – የጎንደር እስር ቤት ቃጠሎ በተነሳበት ወቅት በወያኔ ፖሊስ የተገደሉት ከሰላሳ በላይ ናቸው ተባለ – በዩናይትድ ስትቴስ ሶስት ሰዎች አስራ አራት ሰዎችን ገድለው አስራ ሰባት ሰዎች አቆሰሉ – የሩሲያ ፕሬዚዳንት ፑቲን …

በርካታ የጫንጮ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ባልታወቀ በሽታ ታመሙ:: Read more »

ዝናቡ በመቅረቱ የተዘራው ጤፍም ሆነ ስንዴ ምርት አለማፍራቱን የምዕራብ አርሲ አርሦ አደሮች ገልፀዋል።

በአፍሪቃ ሕብረት መቀመጫ መዲና አዲስ አበባ ላይ ስድስት አስርተ ዓመታትን ያስቆጠረዉ የጥበብ አድባር፤ በርካታ የጥበብ ፈርጦችን አፍርቷል። በኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብ ጉልህ ድርሻ ያበረከቱት አንጋፋ አርቲስቶች ያላቸዉን እዉቀት ለአዲሱ ትዉልድ እያሻገሩ ብሔራዊ ቲያትር ዳግም 60ዓመታት እንዲጨምር የሞያ ትግል የሚያደረጉ ባለሞያዎች ምሥጋና ይገባቸዋል።

በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ መዝግብ ተከሰው የነበሩት 4 የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አብርሃም ሰለሞን ነፃ ቢባሉም በይግባኝ ታግደው ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እየተመላለሱ እንደሆነ ይታወቃል። አሁንም ለቃል ክርክር ሕዳር 29, 2008 ተቀጥረዋል። ቀሪዎቹ፣ ማለትም ዘላለም ወ/አገኘሁ፣ ዮናታን ወልዴ፣ ባሕሩ ደጉ፣ ሰለሞን እና ተስፋዬ ከሕዳር 13–16, 2008 ድረስ ከፊል መከላከያዎቻቸውን ያስደመጡ ሲሆን ቀሪውን ዛሬ (ሕዳር 24, 2008) ያስደምጣሉ።
እነዘላለም ተከላከሉ የተባሉት በፀረ–ሽብር ሕጉ አንቀፅ 7/1 መሠረት የግንቦት 7 አባል በመሆን ሠርታችኋል በሚል ነው። በ5ቱም (ዘላለም፣ ዮናታን፣ ባሕሩ፣ ሰለሞን እና ነፃ ተብሎ በይግባኝ የተያዘው አብርሃም ሰለሞን) ላይ የመሰከሩት 3ተኛ የዐ/ሕግ ምስክር አቶ እዮብ ሲሆኑ፣ የምስክርነታቸው ጭብጥ በጥቅሉ ‘ዘላለም ወ/አገኘሁ መልምሏቸው ለግንቦት 7 ወታደርነት 3 ሰዎችን መልምለው ከወሰዱ በኋላ ጎንደር ላይ ባለመስማማታቸው እንደተመለሱ። ከ3ቱ አንዱ እዚሁ መዝገብ ላይ 8ኛ ተከሳሽ የሆኑት አቶ ሰለሞን መሆናቸውን። አቶ ዘላለም በባሕሩ እና ዮናታን ሥር የተደራጀ ቡድን መኖሩን እንደነገሯቸው’ የሚያስረዳ ነው።
አቶ ሰለሞን፣ ዮናታን እና ዘላለም ከፊል ምስክሮቻቸውን ያስደመጡ ሲሆን አቶ ተስፋዬ (10ኛ ተከሳሽ) ጉዳያቸው ከነዘላለም የተለየ ቢሆንም አንድ መዝገብ በመሆናቸው ምስክሮቻቸውን አስደምጠው ጨርሰዋል።
አቶ ሰለሞን ሁለት ምስክሮችን አቅርበው እዮብ “የተሻለ ሥራ አገናኝሃለሁ በሚል አቶ ሰለሞንን ወደጎንደር ከወሰዷቸው በኋላ ጎንደር ሲደርሱ ለግንቦት ሰባት ወታደርነት እንደሆነ ሲነግሯቸው” መመለሳቸውን አስመስክረዋል። ራሰቸውም በሰጡት ቃል እዮብ እየወሰዳቸው እያለ መቶ አለቃ እያለ ከሚጠራው ሰው ጋር በስልክ ይነጋገር እንደነበርና የዘላለምን ስም ጨርሶ እንዳልሰሙ ተናግረዋል። 
ዮናታንም በበኩሉ እስካሁን 4 ምስክሮችን አስደምጧል። የመጀመሪያው አብሮ አደግ ጓደኛው ሲሆን፣ ዮናታን ውጭ አገር ለሚደረግ የሰብኣዊ መብትና ሚዲያ ነክ ሥልጠና ሊሄድ መሆኑን ነግሮት እርሱም ከፈለገ ሲቪውን እንዲሰጠው ጠይቆት መስማማቱን፣ ነገር ግን ሥልጠናው ባልታወቀ ምክንያት መስተጓጎሉን ለችሎቱ አስረድቷል። በሁለተኝነት የቀረበው ምስክር አቶ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ ስለእነዚህ ዓይነት ሥልጠናዎች ሠላማዊነት እና ሰጪዎቹም ዓለምዐቀፍ ዕውቅና የተቸራቸው ስለመሆኑ የባለሙያ ምስክርነቱን ሰጥቷል። በሦስተኝነት የቀረበው ምስክር አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ እዮብ ማዕከላዊ እያለ አናግሮት እንደነበር፣ ዮናታንን ፍፁም እንደማያውቀው፣ በኋላ ግን በድብደባ ብዛት እግሩ ተጎድቶ ማንከስ ሲጀምር እና ሥራ የሌላት ሚስቱና ልጁ ዕጣ ሲያሳስበው ተስፋ በመቁረጥ ሌሎቹ ላይ መስክሮ ሊፈታ መሆኑን እንደነገረው ለችሎቱ ነግሯል። በአራተኝነት ዘላለም ወ/አገኘሁ ቀርቦ እዮብ “ዘላለም በዮናታን ሥር ቡድን አለ ብሎ ነግሮኛል ያለው ሐሰት ነው” ብሏል።
ዘላለም ወርቅአገኘሁም ለራሱ እስካሁን 4 መከላከያ ምስክሮችን ያስደመጠ ሲሆን በቀዳሚነት የቀረበው ጥበቡ የተባለው አብሮ አደግ ጓደኛው ነበር። ጥበቡ፣ በክሱ ላይ የግንቦት 7 አመራር ተብሎ የተጠቀሰው ተድላ ደስታ አብሮ አደግ ጓደኛቸው እንደሆነና፣ እንግሊዝ አገር ከሄደ በኋላም ተማሩ እኔ ገንዘብ እልክላችኋለሁ ብሎ ገንዘብ ለሁለቱም እንደላከላቸውና ዘላለም ከመያዙ በፊት ማስተርሱን መማር እንደጀመረ ተናግሯል። የዘላለም እናት ወ/ሮ የኔእናትም በበኩላቸው ተድላ ደስታን ከልጅነቱ ጀምሮ የሚያውቁት የልጃቸው ጓደኛ በመሆኑ መሆኑን ጠቅሰው በ2005 ብር ልኮለት እሳቸው ጨምረውበት ዘላለም ትምህርት መጀመሩን ለችሎቱ ገልጸዋል። ቀሪዎቹ ሁለት ምስክሮች ሙዘሚል እና አዲሱ የተባሉ በክሱ ላይ በዘላለም ለግንቦት 7 የተመለመሉ እንደሆኑ የተገለጹ ወጣቶች ናቸው። ሁለቱም ወጣቶች በየተራ ከዘላለም ጋር ያላቸው ዕውቂያ በሰፈር ልጅነት እንደሆነና ምንም ዓይነት የሚያውቁት ቡድን እንደሌለ እና በቁም ነገር ቁጭ ብለው ያወሩበት አጀንዳም እንደሌለ ተናግረዋል።
ዘላለምና ዮናታን በሰጡት መከላከያ ቃላቸውም ላይ ወደውጪ ለሰብኣዊ መብትና ሚዲያ ነክ ሥልጠናዎች ለመሄድ ክሱ ላይ የግንቦት ሰባት አመራር ተብሎ የተጠቀሰው እና እነርሱ በጋዜጠኝነቱ እንደሚያውቁት የተናገሩት አርጋው አሽኔ ጋር ከመነጋገራቸው በቀር ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። ዘላለም፣ ሌሎችን ላለማስፈራራት ሲል ዝርዝሩን እንደማይናገር ነገር ግን በሐምሌ ወር፣ በቀዝቃዛ እና ዘጠና ሳንቲሜትር በሆነች ጨለማ ክፍል ውስጥ 41 ቀን መቆየቱንና ጠባሳ የማይተው ነገር ግን የነርቭን ስርዓት በሚያዛባ ምት እየተመታ መመርመሩን ተናግሯል።
በጥቅሉ ዐ/ሕግ ያቀረበው ክስ እና ማስረጃ ጠቅላላ ምስል፣ «ከውጭ አገር ገንዘብ በሚላክለት ዘላለም አማካኝነት የተመለመለው እዮብ ለግንቦት ሰባት ወታደሮችን እየላከ፣ ዘላለምም በሠላማዊ ትግል ሥም ቡድኖችን እያዋቀረ እንደሆነ» ለማሳየት ሲሞክር፣ እነዘላለምም በመከላከያቸው «ከውጭ አገር የተላከው ገንዘብ የዘላለም አብሮ አደግ ጓደኛ ለዘላለም የግል ፍላጎት የላከው መሆኑን፣ እዮብ ለግንቦት ሰባት ወታደርነት [እያታለለ] በወሰዳቸው ሰዎች ውስጥ ዘላለም እጁ እንደሌለበት፣ ቡድን እየተባለ የሚጠራ ነገር እንደሌለ እና ዜጎች ሁሉ ቢወስዱት የሚመከር ሥልጠና ለመውሰድ መጻጻፋቸውን በዚያ መንገድ እንደተተረጎመባቸው» የሚያስረዳ የመከላከያ ምስል ለመፍጠር እየሞከሩ ነው።

ቁርጠኝነት – አዲሱ የወያኔ የማዘናጊያ እና የማጭበርበሪያ ዲስኩር – ጊዜው የስር ነቀል ለውጥ ነው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Ethiopianoppositionparties‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የውስጥ አጣብቂኟ ሲበረታ ወያኔ አዲስ ፋሽን ይዛ መታለች -ቁርጠኝነት- የሚሉት::በሃሰተኝነት እና በፕሮፓጋንዳ ማጭበርበር ወያኔን የሚችለው የለም::ወያኔ እያወቀ …

ቁርጠኝነት – አዲሱ የወያኔ የማዘናጊያ እና የማጭበርበሪያ ዲስኩር – ጊዜው የስር ነቀል ለውጥ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

የማለዳ ወግ…. የዛሬው ደም የነገ እዳችሁ ሆኖ ይፋረዳችኋል ! ===================================== * ከጎንደር ባዕታ ወህኒ እሰከ ኦሮሚያ ተማሪዎች የጎንደር የባዕታ ወህኒ ቤት መቃጠሉን ተከትሎ ሰው ቆስሏል ፣ ሰው ሞቷል … የጎንደር ከተማ ነዋሪ ባዕታ ወህኒ ቤት እያለ በሚጠራው ማረሚያ ቤት በተከሰተ …

የማለዳ ወግ…. የዛሬው ደም የነገ እዳችሁ ሆኖ ይፋረዳችኋል ! ነቢዩ ሲራክ Read more »