ይገረም አለሙ

ስለ አሃዳዊና ፌዴረላዊ ሥርዓት ምንነትና እንዴትነት በአጭሩና በጥቅሉ የመጀመሪያው ሥልጣን የተማከለበት ሁለተኛው ሥልጣን የተከፋፈለበት ብሎ መግለጽ ይቻላል። ዛሬ በኢትዮጵያ ያለው ግን ሁለቱንም ያልሆነ ሥርዓት ነው። በወያኔ የትግል ብስራት ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የተጎናጸፉበትን ፌዴራላዊ ሥርዓት ለማግኘት በቅተዋል ተብሎ ቢነገረንም መሬት ላይ የሚታየው እውነታ ግን ይህን አያሳያም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አብርሃም በየነ

ሞት ለሰው ልጆች ፀጋም ዕዳም የሚሆንበት ጊዜ አለው። ዜጎች መብታቸው ሲደፈር፣ ነፃነታቸው ሲገፈፍ፤ ማንነታቸው ሲፋቅና የመኖራቸው ህልውና በሞት ጥላ ስር ሲወድቅ ሞት ዕዳውን ያከብድባቸዋል። የክፍያውንም ዋጋ በሕይወት ይመነዝረውና መተኪያ የሌለውን ሕይወት በሞት ወለድ አገድ ያስይዘዋል። ህዝብም የታገቱትን መብቶቹን ለማስፈታት ሞትን ይኖሩታል እንጂ አይሞቱትም ብሎ ይንቀሳቀሳል። ሰው የተፈጠረው ለመሞት ነውና ሞትን ሙቶ ሊያቸንፈው ዕምቢኝ ለሀገሬ ሲል በሞት ላይ ያምፃል። ብሎም ጅግና ይፀነሳል። ሰማዕት ይወለዳል። ህዝብም ከመቃብር በላይ የሚውል ስም በደሙ ጽፎ ለማለፍ ሆ ብሎ ይነሳል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

“Hate Begets Hate; Violence Begets Violence” and Lawlessness Begets Anarchyፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

በዚህ ባለፈው ሳምንት አሜሪካውያን መንፈሳቸውን በሚፈታተን ክስተት ውስጥ ወድቀዋል። አሜሪካውያን አጅግ በጣም አዝነዋል። አሜሪካውያን በጥንቃቄ በማሰብ ስቃይ ውስጥ ተዘፍቀው ይገኛሉ።

ሁለት አፍሪካ አሜሪካውያን ዜጎች በሁለት እምነተ ቢስ የፖሊስ ኃላፊዎች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ መገደላቸውን ተመልክተናል። እምነተ ቢስ የፖሊስ ኃላፊዎች የሚለውን ሀረግ ላሰምርበት እፈልጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

TPLFተሻለ መንግሥቱ

በብሂለ ግዕዝ “ትንቢትሰ ይቀድሞ ለነገር” ይባላል። አንዳንድ ነገሮችን በአፍ ወለምታም ይሁን በቴሌፓቲክ የነገሮች አፈጻጸም ሂደት ቀድመው ይጠቀሳሉ። መለስ ዜናዊ ስለአክሱም ሐውልት የይገባኛል ጥያቄና የባለቤትነት ይዞታ ሲናገር መረንን በማያውቀው ስድ አንደበቱ በርዕሴ ላይ የጠቀስኩትን ከፋፋይ ሃሳብ በገሃድ ተናግሯል። ለነገሩ መለስ ያልተናገረው ጠያፍ ነገር የለም። የአንዲት ሀገር መሪ ሆኖ ራሱን ሾሞ ሲያበቃ ሌሎችን እንደጨርቅ እርሱ የወጣትበን ጎሣ ግን እንደወርቅ መመሰሉን በአደባባይ ገልጾ እርሱና እርሱን መሰሎች ሀፍረትን ባያውቁም እኛ ስለነሱ አፍረናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ታረቀኝ ሙጬ ([email protected])

“ልፋ ያለው በልሙ ዳውላ ሲሸከም ያድራል” እንዲሉ ሆኖብን ሰሚና አድማጭ ያለ እየመሰለን የምንጮህ ብዙዎች ነን። ግን ያው እነመምሩ “ነባይ ነባይነ ከምዘይባይነ ኮነ” (ጮህን፣ ጮህን ግና እንዳልጮህን ተቆጠርን (ሰሚ አጣን)” እንዳሉት ዘመናችን የጥንቶቹ ባቢሎናውያን ዓይነት የመደነቋቆሪያ ጊዜ ሆነና እንዲሁ በከንቱ እንደቁራ እንጮሃለን። ቢሆንም ካለመጮኽ መጮኽ ይሻላል – ዝምታም አንዳንዴ ከሞት አንድ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነቢዩ ሲራክ

“… በሕብረት መኖር አለብን ብሎ የሚመክር የሚዘክር ድንቅ ሰው ነበር፣ አቡኬ”

Abukee Alex, አቡኬ አሌክስ

በያዝነው ሣምንት … በአብዛኛው የሐበሻ መገናኛ መንደር፣ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ዋንኛ መድረክ በFacebook መስኮት አንድ መሪር መርዶ ተሰምቷል። የትሁት፣ አስተዋይና አርቆ አስተዋዩ በጎ ሰው፣ የጎልማሳው የአቡኬ አሌክስ ህልፈት። የአቡኬ አሌክስ በድንገት መለየት ጥልቅ ኀዘናን ሁላችንንም አንገብግቦናል። “ከሞቱ አሟሟቱ” እንዲሉ አቡኬ ባንድ ጀንበር ታይቶ በርቶ፣ ባንዱ ጀንበር ሳይታሰብ ጠፍቶብናል። እናም በቅርብ ከሚያውቁት፣ ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ጓደኞች እኩል በሥራው በዝና የምናውቀው በኀዘኑ አዝነን ከፍቶናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Habtamu Ayalewነቢዩ ሲራክ

የማለዳ ወግ … የሀገሬ ዲሞክራሲያዊ የበቀል ፖለቲካ

የሰሜኑ ኮከብ አብርሃ ደስታ እንኳንም ተፈታህ!

የሰሜኑ ኮከብ ወንድም አብርሃም ደስታ ከእስር እንደሚፈታ ቢገመትም ዘንድሮ ሲሆን እንጅ ሲባል ለማመን ተቸግሬያለሁና ዛሬን መቆየት ነበረብኝ ። እናማ የሰሜኑ ኮከብ ደፋሩና ለእውነት ግንባሩን የማያጥፈው የመቀሌው አብርሃም ደስታ “እውነት ተፈታ” ሲባል ሰማሁ፣ ደስ አለኝ! አብርሽ፤ እንኳንም ከቤተሰብ፣ ከዘመድ አዝማድና ወዳጅ አፍቃሪ ወገንህ ጋር ተቀላቀልክ እልሃለሁ፣ አብርሽ!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ምሕረቱ ዘገዬ

ወዳጅን ቢከፋውም ጠላት ግን ደስ ይበለው – ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ለይቶላት ጨርቋን ጥላ ዐብዳለች። ዕብደት እንዴት ይገለጻል? የሀገርና የሕዝብ ዕብደት እንደኔ አስተሳሰብ በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊገለጽ ቢችል የሚያስማማ ይመስለኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አንዱዓለም ተፈራ

Brexit የእንግሊዝ ከአውሮፓ ሕብረት መውጣት

የዓለም የንዋይ ስምሪት አውታር ክንፎች አጥናፋቸውን ሲያሰፉ፣ የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ቁልልፍ እየተወሳሰበ ሲሄድ፤ ግለሰቦች ከራሳቸው ከባቢ ውጪ ያለውን ክንውን፤ በንቃት መከታተል ግድ ይሆንባቸዋል። ምክንያቱም በዚህ በተወጠረ የዓለም ትስስር ሕልውና፣ አንዱ አካባቢ የሚነጥረው ጠጠር ሌላውን አካባቢ ያረግባልና! ለዚህ ነው ከኢትዮጵያ በስደት አሜሪካ ተቀምጬ፤ አውሮፓ የሚካሄደውን የእንግሊዝ ከአውሮፓ ኀብረት መውጣት በንቃት የተከታተልኩት። እናም እነሆ ግንዛቤዬ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

እንዲያውም ርእሱን ካህናትና ስደት ብለው ይሻላል፤ ካህናት የሁሉንም ሃይማኖቶች መሪዎችን ይመለከታል፤ ዓላማዬም ሁሉም የኃይማኖት መሪዎችን የሚነካ ነው፤ ነገር ግን የእኔ እውቀት በክርስትናው ላይ ጎላ ያለ በመሆኑ የክርስቲያኖቹ መሪዎች ላይ ያተኮርኩ ቢመስልም ሁሉንም ይመለከታል፤ በተለይ መነኩሴዎች ላይ የማነጣጥርበትም የተለየ ምክንያት አለኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

አቶ ግርማ ሠይፉ ማሩ / Girma Seifu Maru

ከ2002 ዓ.ም. እስከ እስከ 2007 ዓ.ም. ድረስ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ “ለዴሞክራሲ ሥርዓት ምን ዓይነት ፓርቲ ያስፈልገናል?” በሚል ርዕስ ያቀረቡትን ጽሁፍ ለማንበብ የጓጓሁት የአንድነት ም/ሊቀመንበር ነበሩና ከተግባር ተሞክሮአቸው በመነሳት ድክመት ጥንካሬን መለስ ብለው ቃኝተው መሆን ያለበትን ያመላክታሉ በሚል ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ (በግራ) ዶ/ር መረራ ጉዲና (በቀኝ) / Prof. Beyene Petros (Left) & Dr. Merera Gudina (Right). (AP Photo/Mulugeta Ayene)ግርማ ሠይፉ ማሩ

በሀገራችን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማኅበራት እንዲሁም የሚዲያ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ እንደሆነ ሁሉም ይረዳዋል ማለት ባይቻልም፤ በተለይ የፖለቲካ ፓርቲ አባል አመራር የሆኑ ሰዎች ይጠፋቸዋል ብሎ የሚገምት ላይኖር ይችላል። እውነቱ ግን ከዚህ የተለየ ነው። በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ሰዎች የሚሳተፉት በዋነኝነት በሀገራችን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን መዋጮ በማስላት ሳይሆን፤ ገዢውን ፓርቲ በማስወገድ ላይ ብቻ ያጠነጠነ ይመስላል። ይህንንም ማድረግ የሚፈልጉት ደግሞ በትርፍ ጊዜያቸው ከሥራ መልስ ወይም በጡረታ ጊዚያቸው ነው። ይህን ሲያደርጉ ደግሞ የብዙ ወጣቶች ጊዜና ጉልበት መስመር ባልያዘ አቅጣጫ እንደሚመሩ አይረዱም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የአፍሪካ ቀንድ ተስፋ ሊኖረው ይችላልን? Horn of Africaፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2014 “ለአፍሪካ ተስፋ ሊኖረው ይችላልን?“ በሚል ርዕስ አንድ ትችት ጽፌ ነበር። ያንን ትችት የጻፍኩት ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ ተንሰራፍቶ በሚገኘው እና ማቆሚያ በሌለው በአፍሪካ ሰው ሰራሽ ቀውስ ምክንያት ምንም ዓይነት ተስፋ የሌለኝ በመሆኑ ነበር። እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2014 የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ (መአሬ) አውዳሚ በሆነ የጎሳ-ኃይማኖት የዘር ማጥፋት ዘመቻ እልቂት ውስጥ ተዘፍቃ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

ሰሞኑን በሰሜኑ የሀገራችን ግዛት ጦርነት ተቀስቅሷል። አስመራም፣ አዲስ አበባም ያሉ ገዢዎች ጦርነት መደረጉን ማመን ብቻ ሳይሆን “ይሄን ደመሰስን፣ ይሄን ያህል ገደልን” እያሉ በመማጸደቅ ላይ ናቸው። ዓለም የትናየት ደርሳለች፣ ትላንናት እኛ እየረዳናቸው ነጻ የወጡ የአፍሪካ ሀገራት እንኳን የትናየት ደርሰዋል፣ እኛ አሁንም መግደልን እንደ ጀብዱ አድርገን እናወራለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ማስተዋል በለጠ (ከአዲስ አበባ)

የወያኔ ውድቀት የአደባባይ ምሥጢር መሆኑን የሚያመላክት አጋጣሚ

ከደቂቃዎች በፊት ከአንዱ የመሥሪያ ቤቴ ቅርንጫፍ ወደ ዋናው መ/ቤት ስመጣ እንዲህ ሆነ። መኪናዋ ውስጥ በተላላኪነት የምትሠራ አንዲት ወጣት፣ ሹፌራችንና እኔ ብቻ ነን የነበርነው። የዛሬው ቀን የከተማችን ወሬ የሆነውን የማትሪክ ፈተና መሰረቅ አነሳሁና የተለጎመውን የሦስታችንንም አንደበት በጋራ የሀገር ጉዳይ ከፈትኩት። በዚህን ዓይነት ሁኔታ እኔ ብዙውን ጊዜ ነገር እለኩስና ዋና ሥራየ ማዳመጥ፣ ማዳነቅና ማውጣጣት ነው። ቀዳሚው ሥራየ ግን የማዋራቸው ሰዎች በኔ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ጥረት ማድረግ ነው፤ ሰው ከተጠራጠረህ የልቡን አይናገርም። ዝም ሊል ወይም ሊዋሽህና ሊያታልልህም ይችላል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

Ginbot 20, 25th anv. ግንቦት 20፣ 25ኛ ዓመት

በእርስ በርስ ጦርነት ከሁለቱም ወገን የሚሞተው የአንድ ሀገር ልጅ ነው። አባትና ልጅ፤ ወንድምና ወንድም ከዛና ከዚህ ተሰልፈው የሚገዳደሉበት አጋጣሚም ይኖራል። ይህም በ17 ዓመቱ የርስ በርስ ጦርነት በግልጽ ታይቷል። ወያኔዎች ለድል የበቁት የኢትዮጵያን ሠራዊት ብቻ ሳይሆን ደርግን ተቃውመው ብረት ያነሱ፤ ነገር ግን ከዋሉ ካደሩ ለህወሓት ህልውና አስጊ ይሆናሉ ያሉዋቸውን ድርጅቶች ጭምር (ለምሳሌም ኢህአፓ፣ ኢዲዩ፣ …) ተዋግተው፤ ከዚህም አልፎ በህወሓትም ውስጥ የተለየ አስተሳሰብ ያራመዱ ወይንም ለሥልጣን ያሰጋሉ የተባሉትን እያሰቃዩና እየገደሉ በመሆኑ፤ መገዳደሉ በአንድ ሀገር ልጆች መካከል ከመሆን አልፎ በቤተሰብ መካከል ጭምር እንደነበር አሌ አይባልም። ለዚህ ደግሞ ሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ በኢህአፓነቱ በወያኔ እንደተገደለ የሚነገረውን የአቶ በረከት ስምኦን ወንድም መጥቀስ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሄኖክ የሺጥላ

ስደት

ወዳጄ እና ጓደኛዬ በቅርቡ በሱዳን አሳብሮ፣ በሊቢያ በረሃ አቋርጦ፣ በባህር አሳልጦ ጣሊያን፣ ከጣሊያን ደሞ ጀርመን እንደደረሰ አጫወተኝ። እርግጥ የተጓዘው መንገድ፣ ያየው መከራ፣ የቀመሰው ችግር እንዲህ በሁለት መስመር በሱዳን አድርጎ በሊቢያ አቋርጦ ጣሊያን ደረሰ ብሎ እንደማለት ቀላል አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግንቦት 20 እንዲህ መቀለጃ ሆና ትቅር?ታዛቢ (ከአዲስ አበባ)

ሥራየ መምህርነት ነው። በአንድ የመንግሥት የ2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ውስጥ አስተምራለሁ። ሰሞኑን ታዲያ የግንቦት 20 የኢትዮጵያ የነፃነት ቀን እንደመሆኑ የበዓሉን መቃረብ አስታክኬ በየምገባባቸው በርካታ ክፍሎች ትምህርቱን ከመጀመሬ በፊት “እንኳን አደረሳችሁ” እላለሁ። ይሀንን የምለው ኢህአዲግ መራሹ ዴሞክራሲያዊው መንግሥታችን ጨቋኙን የደርግ መንግሥት ደምስሶ ህዝባዊ መሠረት የተላበሰና በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የቆመ የዴሞክራሲ ሥርዓት በመትከሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopiaይገረም ዓለሙ

በ1982 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆነ አይደለም የት ላይ እንዳለች አንኳን መናገር በማይቻልበት ወቅት፤ ከአንድ ባልንጀራየ ጋር እየሄድን፤ እኔ ከማላውቀው የእርሱ ጓደኛ ጋር መንገድ አገናኘን። እናም ሠላምታ ተለዋውጠው፤ ታዲያስ እንዴት ነህ፣ እንዴት ናችሁ ሲለው፤ ምን እባክህ ሰውም አለን ሰውም የለንም ሲል መለሰለት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር (ኦዴግ). Oromo Democratic Front (ODF)

አንዳንድ በተለይም በውጭ ያሉ የኦሮሞ ብሔረተኞች፣ የአክራሪውን እና የብዙ ወገኖች ደም በእጁ ያለበትን የኦነግን ባንዲራ እያውለበለቡ፣ የጭቁን ኦሮሞ ወገኖቻችንን ተቃውሞ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እና እንቅስቃሴውን ሃይጃክ በማድረግ፣ የኦሮሚያ ሪፑብሊክን ለመመስረት ያላቸውን ሕልም ለመተግበር ደፋ ቀና እያሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በፍቅር ለይኩን*

Ethiopian patriots. ጀግኖች አርበኞቻችን

“… When he saw a poster, Mussolini Invades Ethiopia, he was immediately seized by a violent emotion. At the moment, he writes, it was almost as if the whole of London had suddenly declared war on me personally. For the next few minutes I could do nothing but glare at each impassive faces, wondering if these people could realize that wickedness of colonialism, and praying that the day might come when I could play my part in bringing about the downfall of such a system. … I was ready to go through hell itself, if need be, in order to achieve my object.”

ዕውቁ ፓን አፍሪካኒስትና የ”ጋና የነጻነት አባት” በሚል ቅጽል የሚጠራው ዶ/ር ክዋሜ ንኩርማ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ በሚያደርገው ጉዞው በለንደን ከተማ ባደረገው አጭር ጊዜ ቆይታ ያስተዋለው፣ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት ምልክት፣ የጥቁር ሕዝብ ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ ቅርስና ማንነት መገለጫ፣ የነጻነት የተስፋ ምድር- ከነዓን ተደርጋ የምትቆጠረው ኢትዮጵያ በፋሽስት ኢጣሊያ በግፍ የመወረር አስደንጋጭ ዜና፣ መርዶ በውስጡ ያሳደረበትን ስሜትና ቁጭት “ጋና” በሚል ርዕስ በጻፈው የሕይወት ታሪኩ መጽሐፍ ያሰፈረውን በጥቂቱ የቀነጨብኩት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይሄይስ አእምሮ

Tigrinya. ትግርኛ

መምህር ልዑለቃል አካሉ የተባሉ ኢትዮጵያዊ በቅርቡ በኦሮምኛ ቋንቋ የላቲን ፊደል አጠቃቀም ዙሪያ የጻፉትን መጣጥፍ ቆየት ብዬም ቢሆን ዛሬ አነበብኩት፤ ግሩም ነው። እሳቸው የሚሉት “ለኦሮምኛው ከላቲን ይልቅ የግዕዙ ፊደል አይቀርብም ወይ?” ነው። ይሄን ያህል ለምን ሩቅ ተሄደ ነው ጥያቄያቸው። ላቲኑን ለመጠቀም ለምን ያን ያህል ሩቅ መንገድ መጓዝ እንዳስፈለገም መልሱ በመጣጥፉ ውስጥ አለ – ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች በወያኔ በመታገዝ ሀገሪቱን ለመበታተን ከሸረቡት ሤራ አንዱ መሆኑ በስፋት ተጠቅሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከኢትዮጵያዊ ማንነት አንጻር ለውይይት መነሻ እንዲሆን የቀረበ ጽሁፍ

መምህር ልዑለቃል አካሉ (ሲያትል፣ ዋሽንግተን)

መግቢያ

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፈ ቅዳሴዋን ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተርጕማ አሳትማለች። መሆን ያለበትና መደረግም የነበረበት ነው። በምርቃቱ መርሐ ግብርም የቀድሞውን ፕሬዝደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ ብዙ እንግዶች ተገኝተው እንደ ነበር ታውቋል። ይሁን እንጂ ከግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በቀር የላቲንን ፊደል በቅዳሴው ላይ መጠቀሟ ትክክል አለመሆኑን ያስታወሰ እና ለወደፊትም ቤተ ክርስቲያን እንድታስብበት የጠየቀ የለም ተብሎአል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሄኖክ የሺጥላ

የሀገራችን ፖለቲካ፣ ትችት እና ዘለፋ እንደ ርችት እያብረቀረቀ የሚዘንብበት የነገር ሸራተን ነው። ትናንት ወዳጅህ የነበረ፣ ዛሬ እንደ አማዞን እባብ ቆዳውን ሸልቅቆ ሙልጭ አድርጎ ሊሰድብህ ይችላል፤ ሃሳብህን ሳይሆን ሱሪህን ሊያወልቅ ይፈልጋል። እሱ ራሱ የወጣለት ጠንጋራ ብሔርተኛ ሆኖ፣ ዓይኑን በጨው አጥቦ «ለምን ስለ አንድነት አትሰብክም» ይልሃል፤ የሌሎችን ቁመና ሲያፍረጠርጥ ከርሞ፣ የሱ ቁመና ሲነካ፣ አደለም ቁመናዬን እዳሪዬን እንኳ መተቸት (መንካት) መብትህ አይደለም ሲል አያፍርም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፍርዱ ዘገዬ

Mega books plc. ቋንቋን በጄኔቲክ ከአባትህ አትወርሰውም

ዳዊት በመዝሙሩ፣ “አቤቱ ጌታ ሆይ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወዳንተ ይድረስ፣ በመከራየም ቀን ፊትህን ከኔ አታዙር” ሲል ፈጣሪውን ተማጽኗል። እኛስ? ከልበ ድንጋዮቹ ወንድሞቻችን ግፍና በደል የሚታደገንን ሙሤ እንዲልክልን እንደዳዊት እየጮኽን ነው ወይንስ እንደኖኅና እንደሎጥ የቅጣት ዘመናት በአሥረሽ ምቺው የኃጢኣት ባሕር ከተዘፈቁት ጋር አብረን ፈጣሪን ረስተናል?

ሙሉውን አስነብበኝ …

Bekele Gerba. በቀለ ገርባፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

በአሜሪካ የሕግ አፈ ታሪክ የስኮፐስ የዝንጀሮ (የይስሙላ) ፍርድ ቤት ነበር

እ.ኤ.አ በ1925 ጆን ስኮፐስ ተብሎ የሚጠራ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር በቴኔሲ ግዛት ድንጋጌን በመጣስ በአንድ የሕዝብ ትምህርት ቤት ውስጥ ስለሰው ልጆች ዘገምተኛ ለውጥ/human evolution ሲያስተምር ተገኝቶ እንደወንጀለኛ ተቆጥሮ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር። የስኮፐስ የፍርድ ሂደት ጉዳይ ልጆቻቸው በዘመናዊ ትምህርት እንዲታነጹ በማይፈልጉ ምንም በማያውቁ ደንቆሮዎች እና ሌሎች ደግሞ ዘመናዊውን የአሜሪካ የሳይንስ ትምህርት እንዲገበዩላቸው በሚፈልጉ ሰዎች መካከል የሚደረግ ትግል ስለነበር የፍርድ ሂደቱ በመላው ዩኤስ አሜሪካ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሲታይ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ለይኩን እሸቱ. Leyikun Eshetu(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከሚኖርበት ሆላንድ ወደ ትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ የገባው ወጣት ለይኩን እሸቱ፤ በፋሲካ በዓል ዋዜማ ስምንት ቦታ በስለት ወግተው የገደሉት ወንጀለኞች እስካሁን አልተያዙም። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ገዳዮቹ ባለጊዜዎች ስለሆኑ ሟች ደመ ከልብ ሆኖ ቀርቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopian Airlines. የኢትዮጵያ አየር መንገድይሄይስ አእምሮ

የ2008ን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ አንድ የኢትዮጵያ ይሁን የትግራይ ውሉ ባልታወቀ አየር መንገድ ውስጥ የሚሠራ ሰው በቤቱ ምሣ ጋበዘኝ። ተራ ጎረቤቱ እንጂ የሰማሁትን በሆዴ የማላሳድር ወሬ አራጋቢ መሆኔን አያውቅም። በሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት በቀድሞው አጠራር ስለኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ደግሞ ስለ”ትግራይ አየር መንገድ” እየተንገፈገፈ ሲናገር እንደማንኛውም ተጋባዥ አደመጥኩ። የምፈልገውን ወሬ ከጨበጥኩ በኋላ የተከፈተልኝን ቢራ እንኳን በቅጡ ሳልጨርስ ወደቤቴ አመራሁ – እንደልማዴ ልጫጭር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Geezedit. ግዕዝኤዲት

ዋና መሥሪያ ቤቱ ብራይተን ኮሎራዶ የሆነው የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ቁጥሩ ዘጠኝ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ኃምሳ ሰባት የሆነ የዩናይትድ ስቴትስ የባለቤትነት መታወቂያ (ፓተንት) መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. (አፕሪል 7 ቀን 2016 እ.ኤ.አ.) ማግኘቱን አስታወቀ። ፓተንቱ የተሰጠው ለፈጠራውና የኩባንያው ባለቤት ለዶ/ር አበራ ሞላ ሲሆን፤ ኩባንያው የእርሳቸውንና የባለቤታቸው የወ/ሮ ሠናይት ከተማ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Prof. Messay Kebede. ፕ/ር መሳይ ከበደግርማ ካሳ

ማርች 26 እና ማርች 27 ቀን 2016፣ በቪዥን ኢትዮጵያ አማካኝነት አንድ ኮንፍራንስ ተካሄዶ ነበር። በዚህ ኮንፍራንስ ላይ ብዙ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች አቅርበዋል (“የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ”)። ከነዚህ መካከል ፕ/ር መሳይ ከበደ አንዱ ነበሩ። ንግግራቸውን በሦስት ነበር የከፈሉት። የመጀመሪያው ክፍል ስለዘውግ (ethnicity) አንዳንድ ጽንሰ ሃሳቦች ለማሳየት የሞከሩበት ነው። ብዙም የማያከራክር ለጠቅላላ እውቀት የሚሆን ፍልስፍናዊና ቴዎረቲካል ትንተና በመሆኑ እዚያ ላይ ብዙ ጊዜ አላጠፋም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘውግና ብሔራዊ አንድነት እንዴት ይታረቃሉ?

Prof. Messay Kebede. ፕ/ር መሳይ ከበደገለታው ዘለቀ

ይህን ርዕስ የወሰድኩት በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ፕሮፌሠር መሳይ ከበደ “የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ” በሚል ርዕስ ስር ካቀረቡት መሳጭ ጥናታዊ ጽሁፋቸው ስር ካነሷቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መሃል አንዱን መዝዤ ነው። ፕሮፌሠር መሳይ ከበደ በዚህ ፕሮግራም ላይ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፋቸው በርግጥ ደረጃውን የጠበቀና በሚገባ የተደራጀ ነው። ፕሮፌሠሩ ፈላስፋም ስለሆኑ አሳባቸውን በሚገባ ገልጸዋል። አስበውበት ተፈላስፈውበት በመሆኑ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል። በእንዲህ ዓይነት ስብሰባዎች ላይም እንዲህ ዓይነት ትንተና መኖሩ መልካም ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር መሳይ ከበደ

Prof. Messay Kebede. ፕ/ር መሳይ ከበደ

ይህ ጽሁፍ በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ ያቀረብኩት ነው።

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት በሠላም ወይም በኃይል ከሥልጣን ለማውረድ ቢችሉም እንኳን፤ ባለፉት 24 ዓመታት የተዘረጋውን ዘውጋዊ ክፍፍል ለማብረድና ብሔራዊ አንድነትን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል ራዕይና ፖለቲካዊ መፍትሔ ያስፈልጋቸዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ከሚስተዋሉት ችግሮች ሁሉ ተቀዳሚና እጅግ አስቸጋሪ የሆነው ዘውጋዊ ፖለቲካ በመሆኑ ያለውን መንግሥት ለመጣልና አዲስ ሥርዓት ለመመስርት ስለ ዘውግና ዘውጋዊ ፖለቲካ ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘትን ይጠይቃል። ወያኔ ከተሸነፈ የዘውግ ፖለቲካ በራሱ ይጠፋል ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት ነው። ይህ ጽሁፍም “የዘውግ ፖለቲካ ዋና ዓላማ ምንድን ነው? ከብሔራዊ አንድነት ጋር በምን ሁኔታ ሊጣጣም ይችላል?” የሚሉትን ጥያቄዎች በአጭሩ ይዳስሳል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዩሱፍ ከዲ

AA traffic police. በደመነፍስ የሚነዱ ትራፊክ ፖሊሶችና የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር

የቅዳሜ ሚያዝያ 1 2008 አጭር ገጠመኝ

ከሜክሲኮ በባልቻ አድርጎ በአብነት ወደ አውቶቡስ ተራ የሚወስደውን በተለምዶ ዶልፊን የሚባለውን ታክሲ ስሳፈር፣ ሰዓቱ ገና አንድ ሰዓት ከሃያ አካባቢ ነበር። ታክሲውም አንድ ወይም ሁለት ሰው ቀርቶት ባልሞላበት ሁኔታም ነበር መንቀሳቀስ የጀመረው። ይህ ድርጊቱ የሾፌሩን “ለሰዓት/ለጊዜ እንዲሁም ለጫናቸው ተሳፋሪዎቹ ያለውን አክብሮት” ያሳየኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁና እንዳከበርከን ክበር እያልኩኝ በውስጤ መልካም እየተመኘሁለት ነው የተጓዝኩት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

Crooked forest and TPLF.

የቀድሞው ጠቅላይ ምኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በአብዮታዊ ዴሞክራሲያቸው ድል ማግስት መቀሌ ተገኝተው በትግርኛ ባደረጉት የአደባባይ ንግግር፤ “እኛ ከሥልጣን ብንወርድ፤ ነፍጠኞች አንድ ቀን አያሳድሩዋችሁም” ማለታቸውን የዓይን እማኝነታቸውን የሰጡ ሰዎች በወቅቱ አስነብበውናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ምሕረቱ ዘገዬ

Merkato, Addis Ababa. መርካቶ

በተለይ ካለፉት 25 ዓመታት ወዲህ ዓለምን የሚያስደምም ወንጀል በሀገራችን ውስጥ እየተሠራ ይገኛል። በዓለማችን የእስካሁንም ይሁን የወደፊት ታሪክ በፍጹም ያልታየና ሊታይም የማይችል ወንጀል ወያኔዎች እንደልባቸው እየሠሩ ናቸው። እነዚህ በጣት የሚቆጠሩና የዋናው ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ቡድን አባላት የሆኑ ጥቂት ወያኔዎች እየሠሩት ያለውን የከፋና የከረፋ ወንጀል ሁለቱም መሪዎቻችን በሚገባ ያውቃሉ። ነገር ግን ሁለቱም መሪዎቻችን እልህ የተጋቡና አንዳቸው በአንዳቸው ጣልቃ ላለመግባት የወሰኑ ይመስላል፤ በድርድርም ይሁን በመሸናነፍ ቅራኔያቸውን አስወግደው እኛን ሠላም ሊሰጡን አልቻሉም ወይም ምናባልት ጊዜው ገና ነው። የዝኆኖች መራገጥ ለሣር እንደማይበጅ ሁሉ እኛም በነሱ ሰበብ እየተደቆስን አለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Artist Getachew Mekuria. አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. April 4, 2016):- በ1927 ዓ.ም. የተወለደው አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ ጥበብን የተቀላቀላት በመንገድ ላይ ታንቡር መቺ በመሆን ነው። ይህ የሆነው በ1940 ዓ.ም. ነበር ። በኋላም ጥበብን እየተከተላት እሷም ወዳለችበት እየጠራችው በ1948 ዓ.ም. በመዘጋጃ ቤት ተቀጥሮ በፊት ከሚያደንቃቸው በኋላም ለረጅም ዓመታት አብረውት ከሠሩት ከአርቲስት ተፈራ አቡነወልድና ከአርቲስት ወዳጄነህ ፍልፍሉ ጋር ተቀላቀለ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

Ethnic apartheid in Ethiopia. የጎሣ ዘረኝነት (ክልላዊነት) በኢትዮጵያ

የጸሐፊው ማስታወሻ፡- ይህ “የጎሣ ዘረኝነት/አፓርታይድ በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ መደበኛ በሆነ መልኩ እያዘጋጀሁ የማወጣው ተከታታይ ትችት ሁለተኛው ክፍል ነው። የዚህ ተከታታይ ጽሑፍ ጥንድ ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው።

1ኛ) በአሁኑ ጊዜ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ–ህወሓት) አድራጊ ፈጣሪነት ተመስርቶ እየተቀነቀነ ያለው አውዳሚ የፖለቲካ ሥርዓት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሰፊው የጥቁሮች ህዝብ የበላይ አገዛዝ ሥርዓት ከመፈጠሩ በፊት በጥቂት ነጮች የዘረኝነት የበላይ አገዛዝ ከነበረው የአፓርታይድ ዘረኛ አገዛዝ ተሞክሮ ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን ከምንም ጥርጣሬ በላይ ለማመላከት እና

2ኛ) ጥልቀት እና ስፋት ያለው ክርክር እና ውይይት በማካሄድ ከጎሣ ዘረኝነት የጸዳች አዲሲቷን ኢትዮጵያ የመገንባቱን አስፈላጊነት ለመፍጠር እንዲቻል የኢትዮጵያን የአቦ ሸማኔ ወጣት ትውልድ ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተስፋዬ ገብረዮሐንስ (ከጀርመን)

Ethiopian federalism map. የወያኔ የጎሣ ፌደራሊዝም ሲፈተሽ

የወያኔ አስተዳደር የማዕከላዊውን የመንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በሀገሪቱ ተግባራዊ ያደረገው የፌደራል ሥርዓት ጎሣን መሠረት ማድረጉ የሚታወቅ ነው። እንደ ወያኔ አገላለጽ ይህ የጎሣ ፌደራሊዝም በኢትዮጵያ ደም መፋሰስን ያስቀረና ሀገሪቱንም ከመበታተን አደጋ የሚታደግ ነው ይላል። ይሁን እንጂ በተግባር እየተፈፀመ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ስንፈትሽ ይህ ወያኔ-ሰራሽ የሆነው የጎሣ ፌደራሊዝም ዓላማም ሆነ እያስከተለ ያለው ውጤት ከዚህ በተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ገለታው ዘለቀ

በመጀመሪያ ደረጃ መተማመን (Trsut) ስንል የአንድ ሕብረተሰብ የጋራ ሀብት ወይም የማኅበራዊ ካፒታል ዋና አካል መሆኑን እናንሳ። በአጠቃላይ ማኅበራዊ ካፒታል ስንል ደግሞ ልክ እንደሌሎቹ የሰው ልጆች ካፒታል የሚታይ ነው። ለምሳሌ የገንዘብ ካፒታል፣ የሰው ካፒታል (Human capital) እንደምንለው ማኅበራዊ ካፒታልም ካፒታል ይባላል። ካፒታል ነው እንደንል የሚያስችለን ምክንያት አንድም ልክ እንደሌሎቹ ካፒታሎች የሚመረት (Produce የሚደረግ) መሆኑና ለተለያዩ የማኅበረሰብ ልማቶች ኢንቨስት የምናደርገው ሀብት በመሆኑ ነው። እነዚህ ተፈጥሮዎቹ ከሌሎች ካፒታሎቻችን ጋር ያመሳስሉታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

Blue party. ሰማያዊ ፓርቲ

የፖለቲከ ስህተትና የሳንባ ነቀርሳ ጠንቆች የተመሳሳይነት ባህርይ አላቸው። ሁለቱም ችግሮች በለጋነታቸው ወቅት ከተነቃባቸው ችግሮቹን የማስወገድ ዕድል ከፍተኛ ነው። ችግሮቹ ሥር ከሰደዱ በኋላ የሚደረገው መሯሯጥ ግን ፈውስ የማስገኘቱ ሁኔታ አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን የማይቻልም ሊሆን ይችላል። (ማርጋሪት ታቸር የእንግሊዝ ጠ/ሚ የነበሩ)

ሙሉውን አስነብበኝ …

አሊ ጓንጉል

Daniel Kibret. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ይህ ጽሁፍ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በቅርቡ ‘“ሀገር ማለት ሰው ነው”! እስቲ ሙት በለኝ!’ ሲል ለለቀቀው ጽሁፍ መልስ ነው። … እስካሁን ድረስ “ሀገር ማለት ሰው ነው” የሚባል ዘፈን መኖሩን ሰምቼም አይቼም አላውቅም። በዚህ ስም የሚጠራ ዘፈን ኖሮ እኔ ያላወቅሁ እንኳን ቢሆንም፣ “ሀገር ማለት ሰው መሆኑን” ሊያስክድ የሚችል አንዳችም ነገር ያለ አይመስለኝም። በዚህ ስም የሚጠራ ዘፈን ጨርሶ ሳይኖር፣ የበድሉ ዋቅጅራን “ሀገር ማለት የኔ ልጅ … ሰው ነው …” በሚል ርዕስ የሚታወቀውን ታላቅ ግጥም እንዲሁ “ዘፈን” በማለት ለመተቸት ወይም ለማውረድ ከሆነ ደግሞ፣ ዲያቆኑን የባሰ የታሪክ፣ የኃይማኖት እና ከሁሉም በላይ የስነ-ጽሁፍ ድህነቱን ይናገርበት ይመስለኛል። ምክንያቱም ሀገር ማለት ሰው ነው! ላስረዳ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነፃነት ዘለቀ

Panda

የታያቸውን አላውቅም ከምን ጊዜውም በላይ ወያኔዎች ሰሞኑን ክፉኛ ተጨንቀዋል። እነሱና እኔ ከጥንት ጀምሮ የተለዬ “ዝምድና” ያለን በመሆናችን ነገረ ሥራቸውን በደንብ አውቀዋለሁ። ሲጨነቁና ሲጠበቡ እንዴት እንደሚሆኑና ምን እንደሚያደርጉ በረሃ ሳሉ ጀምሮ በሚገባ እንተዋወቃለን። ከዱሮው ለማጣቀስ ያህል አንዳች አደጋ አንጃቦባቸው ሲጨነቁ ትላልቅ ባለሥልጣኖቻቸውን በቃለ-መጠይቅ መልክ እያቀረቡ ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል ጀሌያቸውን ያጽናናሉ፤ ያበረታታሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

“ወያኔ የራሱን መቃብር እየቆፈረ ሞቱን ሲያፋጥን፤ ተቃዋሚዎች ገንገንዘው ሳጥን ለመክተትም ሆነ ከቀብር ስፍራ አድርሰው አፈር ለመመለስ የሚችሉ አልሆኑም”

TPLF funeral. "ወያኔ የራሱን መቃብር እየቆፈረ ሞቱን ሲያፋጥን፤ ተቃዋሚዎች ገንገንዘው ሳጥን ለመክተትም ሆነ ከቀብር ስፍራ አድርሰው አፈር ለመመለስ የሚችሉ አልሆኑም"

እኔ ከምኑም የለሁበት ተቀዋሚም ደጋፊም አይደለሁም በሚል ጭንብል ተሸፍኖ የሚኖረው ክፍል ሲቀር ሌላው በሁለቱ ጎራ ይመደባል። በወያኔ ጎራ ያለው ወገን ለአባልነትም ይሁን ለደጋፊነት ያበቃው ምክንያት ምንም ይሁን ባለው አቅም በሚችለው መንገድ የወያኔን ዕድሜ ለማራዘም ያስችላል ብሎ ያመነበትን ይሠራል። እንደውም አንዳንዱ ያለ ወያኔ መኖር እንደማይቻል ራሱን አሳምኖ ሞቴን ከወያኔ ጋራ ያለ ነው የሚመስለው። በዚህ ጎራ የተሰለፉ ሰዎች ሆነ ብለው አቅደው ሊገኝ የሚችለውን ውጤት ናፍቀው የወያኔን ዕድሜ በሚያሳጥር ተግባር ላይ አይሰማሩም። የውስጥ አርበኞች ካልሆኑ በስተቀር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የማለዳ ወግ …

* በኀዘን የሚላወስ እንስፍስፍ የእናት አንጀት

* የኮንትራት ሠራተኛዋን እህት ቤዛን አፋልጉኝ!

ነቢዩ ሲራክ

ሆዴን ያላወሰው የእማማ ሎሜ አደራ

Beza Ashenafi Engida and her mother Lome Regass. እህት ቤዛ አሸናፊ እንግዳ እና እናት ሎሜ ረጋስ

የእናትን መሪር ኀዘን ሰምቼ ሆዴ ተላውሷል፣ የእናትን ጥልቅ ጭንቀቷ፣ ያለ አባት በአሳር በመከራ ያሳደገቻት የእናትን ሎሜ መሪር ኀዘን ተረድቼ ሕመም መታመሜ እውነት ሳለ፤ በዝምታ እየቆሰልኩ ማስረጃና መረጃ ፍለጋ መዋተቴ ሕመሜን አክብዶታል። ከጉያዋ ወሽቃ፣ በትንፋሿ አሙቃ፣ ስታገኝ በደስታ፣ ስታጣ ተከፍታ፣ ድሃ አደግ ቤቷን አሟሙቃ፣ ነገ ልጆቿን ለወግ ለማዕረግ የማድረስ ምኞት ተስፋን ሰንቃ፤ ተስፋዋን የተነጠቀች እናት እንባ ውስጤን አድምቶ አቃጥሎታል። እናት ዛሬ ማለዳ በላኩልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል “የልጄን ነገር አደራ! እባክህ ነፍሴን አሳርፋት” …

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

Quo Vadis Ethiopia: Where Are You (not) Going?

(እ.ኤ.አ መጋቢት 27/2016 በማሪዮት ጆርጅታዎን ከተማ (ዋሽንግተን ዲሲ) ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለው ድርጅት አስተባባሪነት “ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛው ቅጅ ከቀረበው ንግግር የተወሰደ ነው።) …

“ስለወዲፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ ስለተዘጋጀው ጉባኤ ቪዥን ኢትዮጵያን እና የጉባኤውን አስተባባሪዎች በሙሉ ለማመስገን እፈልጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አስፋ ጫቦ

Ato Assefa Chabo. አቶ አስፋ ጫቦ

ትዝታ ነው የሚርበን

ላናገኘው ላይጠግብን ብሏል ወዳጄ የነበረው ጸጋዬ ገብረ መድኅን

ለመሆኑት ትዝታ ምንድነው? ዘፈፍን ነው? እንጉርጉሮ? ኩርኮራ? ማላዘን?ሐሳብ ልጓም የለውምና እንዳሻው ወደላይ ወደታች፤ ወደውስጥ ወደውጭ፤ ወደፊት ወደኋላ፣ ወደየሚታይ ወደሊታይ ወደማይቻል ይሔዳል፤ ይጓዛል፤ ይተናል፤ ይበናል፤ ይመላለሳል፣ ይመለሳልም። “ማን አለኝ ከልካይ!” መሆኑ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉ አሰፋ

Heineken ethiopia

የሆላንድ ዜምብላ[1] ጋዜጠኞች የኦሮሞ ፀሐፊው የሆነውን ያሶ ካባባን ይዘው ወደ ጊንጪ ያመራሉ። እግረመንገድ ላይ የሚያገኟቸው ገበሬዎችም ሲጠይቋቸው በምስሉ ይታያል። እነዚያ በቀያቸው ማረፍያ እንኳን የሌላቸው ገበሬዎች የጋዜጠኞቹን መኪና ከብበው እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ። “መሬታችንን ቀምተው ለነጮች ሰጡብን። እኛንም በታተኑን …”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

Prof. Getachew Hahile. ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

የክርስቲያኖቹ መጽሐፍ “ግብር ለሚገባው (ሹም) ግብር ገብሩ” ይላል። ግብር ለማይገባው እንደወያኔ ላለ ገዢ ግን ግብር ስለማይገባው አንዲት ቀይ ቤሳ አታቅምሱት ማለቱ ነው። ጊዜ ስለሰጠው ቀምቶ ይወስዳል። ግን ብዕሬ ስቦኝ ነው እንጂ ለማለት የፈለግሁት እንኳን “አድናቆት ለሚገባቸው የኦሮምኛ ተናጋሪ የጎሣ ፖለቲከኞች አድናቆት ስጧቸው” ለማለት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

በአጋዚ ጦር በአምቦ ከተማ የተገደለው የግርማ ረጋሳ ቤተሰቦች

ሁለት ወንድማማቾች ናቸው። ቃየን እና አቤል ይባላሉ። በዘፍጥረት ምዕራፍ 4 ላይ የተጻፈው ነው። “ቃየን አቤልን ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ አቤል ላይ ተነሳበት። ገደለውም” ይለናል ቃሉ። ደም ፈሰሰ። የወንድም ደም በወንድም እጅ። እግዚአብሔር በሆነው ነገር አዘነ። ለቃየንም ጥያቄ አቀረበለት። “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” አለው። ቃየንም መለስ “ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” አለ።

ሙሉውን አስነብበኝ …