“ወደ እውነተኛው ፌደራሊዝም እንመለስ” የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ
የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላንን በተመለከተ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ያለውን ዝርዝር አቋም በተመለከተ የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን አዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ በፅ/ቤታቸው ተገኝቶ አነጋግሯቸዋል፡፡

መንግሥት ማስተርፕላኑ ከተሞችን በመሰረተ ልማት በማስተሳሰር እድገትን ለማምጣት ከፍተኛ ጥቅም አለው ይላል፡፡ ፓርቲያችሁ ደግሞ ማስተር ፕላኑን አልቀበልም ብሏል፡፡ በምን ምክንያት ነው የማትቀበሉት?
እኛ ማስተር ፕላኑን የማንቀበለው በትክክል የህዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የተዘጋጀ ነው የሚል እምነት ስለሌለን ነው፡፡ መንግሥት በዚህ አሳቦ ወደ ኦሮሚያ አጎራባች ከተሞች ዘልቆ እየገባ ለባለስልጣናትና ለስርአቱ አገልጋዮች ተጨማሪ ገቢ ማስገኛ፣ የሀብት መዝረፊያ፣ በህዝብ ላይ ደግሞ ሌላ የጭቆና ቀንበር መጫኛ፤ ማንነቱን፣ ቋንቋውን፣ ባህሉን የማጥፋት ዘመቻ ነው ብለን ነው የምንወስደው ይሄን ለምን አልን? ስርአቱ ሲመሰረት,ኧ በህገ መንግሥት ተደንግጎ እንደሚገኘው ፌደራል ስርአት ነው፡፡ ማዕከላዊ መንግሥት ራሱን ችሎ የተሰጠው የስራ ድርሻ አለ፡፡ ክልሎች በዋነኝነት ራሳቸውን የማስተዳደር፣ ግብር የመሰብሰብ፣ የሰበሰቡትን ግብር ደግሞ እቅድ አውጥቶ በስራ ላይ የማዋል፣ በአካባቢያቸው የሚገኙ ማናቸውንም ነገር የማስተዳደር ስልጣኖች አሏቸው፡፡ ስለዚህ በአካባቢያቸው ሊፈፅሙት ያሰቡትን ልማት ለየትኛው ቅድሚያ እንደሚሰጡ በትክክል በገቢያቸው ላይ ተመስርተው ማርቀቅ ያለባቸው ራሳቸው ናቸው እንጂ ሌሎች ክልሎች ወይም ማዕከላዊ መንግሥት ሊያቅዱላቸው አይችሉም፡፡
አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ላሉ ከተሞች እቅድ የማውጣት አቅሙም ስልጣኑም የላትም፡፡ በህገ መንግሥቱ በምንም መንገድ አዲስ አበባ ለነዚህ ከተሞች እቅድ የማውጣት ስልጣን አልተሰጣትም፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ቻርተርም፣ በኦሮሚያ ክልል ህገ መንግሥትም፣ በሀገሪቱ ህገ መንግሥትም ቢሆን ይሄን ስልጣን አልሰጠም፡፡ የፌደራል መንግሥትም በከተሞች ፕላን ውስጥ ጣልቃ የመግባት ስልጣን አልተሰጠውም፡፡ እንደዚህ ከሆነ ከተሞች ራሳቸውን አስተዳደሩ ማለት እንዴት ይቻላል? ህዝቡ ምኑ ላይ ነው ራሱን አስተዳደረ የሚባለው? እንደዚህ ከሆነ ትናንት ከ25 ዓመት በፊት ወደነበርንበት ተመልሰን እየገባን ነው ማለት ነው፡፡
አሁን ለተነሳው አይነት ጥያቄ የፓርቲያችሁ ፕሮግራም ምን አይነት ምላሽ ነው የሚሰጠው?
እኛ አሁን በአገሪቱ ውስጥ እየተተገበረ ያለው የፌደራል ስርአት ነው አንልም፡፡ ምክንያቱም በአንድ ክልል ውስጥ የሚደረግን ነገር ሌላ ክልል ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ይገኛል፡፡ ይሄ ማለት እቅዶች ሁሉ ከላይ ወደታች የሚፈሱ፣ በትዕዛዝ መልክ የሚተላለፉ ናቸው ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ በአንድ የትግራይ ወረዳ ውስጥ ያለ የመንግሥት አሰራር በኦሮሚያ ውስጥ ወይም በደቡብ ውስጥ ይገኛል፡፡ ይሄ የሆነው ምንጩ ማዕከላዊው ስለሆነ ነው፡፡ ፌደራሊዝም ግን ፅንሰ ሀሳቡ ይሄ አይደለም፡፡ ለምሳሌ አሜሪካን ብንወስድ በአንዱ ስቴት በህግ የሚከለከል ነገር ሌላኛው ጋ ይፈቀዳል፡፡ አንዱ ስቴት የሞት ቅጣት ተግባራዊ ሊያደርግ ይችላል፤ ሌላው ጋር ፈፅሞ የተወገዘ ይሆናል፡፡ ይሄ የሆነው እንግዲህ ስቴቶች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብታቸው ሳይሸራረፍ በመተግበሩ ነው፡፡ በአንፃሩ እኛ ጋ ግን ክልልና ፌደራሉ የሚለያዩበትን ነጥብ አናገኝም፡፡ አንድ ክልል የራሱ እቅድ ማውጣት ቢችልም አሁን ባለው አሰራር ይሄ የለም፡፡ አንድ ክልል ስንት ት/ቤቶች ስንት የጤና ኬላ እንደሚያስፈልጉት አያውቅም። ያንን የሚያቅድለት ማዕከላዊ መንግሥት ነው፡፡ ይሄ ከፌደራሊዝም ፅንሠ ሀሳብ ጋር ይቃረናል፡፡ የፓርቲያችን የፌደራል ስርአት ግን እነዚህን በትክክል አቃንቶ የሚተገብር ነው፡፡
በአንድ በኩል አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማም ነች። ከዚህ ቀደምም የኦሮሚያ ነች የሚል ጥያቄ ተነስቷል፡፡ በሌላ በኩል የኦሮሞ ነች የምትባለው ይህቺ ከተማ ከሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ጋር እንድትተሳሰር መንግስት ያወጣውን እቅድ ትቃወማላችሁ፡፡ እነዚህን ነገሮች እንዴት ነው የምታስታርቁት?
እኛ ጥያቄያችን ህገ መንግሥቱን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ህገ መንግሥቱ ላይ ኦሮሚያ ከፌደራል መንግሥቱ መቀመጫ አዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ታገኛለች፤ ዝርዝሩም በሌላ ህግ ይገለፃል የሚል አለ፡፡ ዝርዝሩ ግን ሳይገለፅ 20 ዓመት አለፈ፡፡ በኦሮሚኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ ት/ቤቶችም የሉም፡፡ አሁን ያለው አሰራር ህጎች የሚተረጎሙት በባለስልጣናቱ ምቾት ላይ ተመስርተው ነው፡፡ ለራሳቸው እስካልጠቀመ ድረስ በህገ መንግስቱ እንደተጠቀሰው፤ ከከተማዋ የኦሮሞ ህዝብ የተለየ ጥቅም እንዲያገኝ አልፈለጉም፡፡ በተቃራኒው ግን የአዲስ አበባን ቆሻሻና ሌሎች ችግሮች የመሸከሙ ኃላፊነት ያለው ኦሮሚያ ላይ ነው፡፡
በ1997 ምርጫ ጊዜ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሌላ አካል የሚረከብ ስለመሰለው፣ የኦሮሚያ መቀመጫ አዲስ አበባ እንዲመስል አደረገ። በዚያ ምክንያት በፊት የተከለከሉ ጥቅሞችን ክልሉ እንዲያገኝ አንድ ፕሮፖዛል እንዲሰራ አደረገ፡፡ አዲስ አበባ ከምታገኘው ገቢ ምን ያህሉ ወደ ኦሮሚያ መግባት እንዳለበት፣ በኬላችን ላይ ቀረጥ እንዲከፈልና ኦሮሚያ ገንዘብ እንድታገኝ፣ በአዲስ አበባ ውስጥ ካሉት የምክር ቤት መቀመጫ ውስጥ ደግሞ ኦሮሚያ ያለ ውድድር የተወሰኑ መቀመጫዎችን እንድታገኝ የመሳሰሉ ፕሮፖዛሎች ቀርበው ነበር፡፡ የተባለው ድርጅት ከተማዋን ሳይረከብ ሲቀርና መልሶ ኢህአዴግ ከተማዋን ሲይዝ የተዘጋጀውን ፕሮፖዛል መልሶ ጣሉት አላቸው፡፡ ስለዚህ ኦሮሚያ በፊትም ማግኘት የነበረበትን ጥቅም አላገኘም፤ ይባስ ብሎም አዲስ አበባ ውስጥ ያለው መሬት በማለቁ ሌላ ጥቅም ፍለጋ ወደ ኦሮሚያ መሬት እጃቸውን መዘርጋት ጀመሩ ማለት ነው፡፡
ፓርቲያችሁ በአዲስ አበባ ጉዳይ ያለው አቋም ምንድን ነው?
በቻርተሩ ጊዜ በተደረገው ስምምነት መሰረት፤ አዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ የምትገኘው በኦሮሚያ ውስጥ ነው በሚል ነው የታለፈው፡፡ የኦሮሚያ ናት የሚል አልተቀመጠም፡፡ ነገር ግን በጣም ወሳኝ የሆነ ቁጥር በዚህች ከተማ እንዳለ ይታወቃል፡፡ መጀመሪያም ትንሽ የኦሮሚያ መንግስት ከመሆን ጀምራ ነው አሁን ወዳለችበት ደረጃ ያደገችው፡፡ ይህ እድገቷ ዛሬም እንዲቀጥል እንፈልጋለን፡፡ እዚህ ውስጥ የኦሮሞ ፍላጎትም እንዲንፀባረቅ እንፈልጋለን፡፡ የሌሎችን ህዝቦች ጥቅም በማይጎዳ መንገድ አንዳንድ የኦሮሞ ተቋሞች እንዲከፈቱ እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን አሁን ከያዘችው ወሰን አልፋ ወደ የትኛውም የኦሮሚያ ክልል የመስፋፋት ህጋዊ የሆነ መሰረት ስለሌ ያንን እንቃወማለን፡፡
ማስተር ፕላኑ መሰሪ ነው የምንለው፣ መሬትን የመሻማትና የመቀራመት ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡ ማንነትን በማጥፋት ሌሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስለሆነ ነው፡፡
ፕላኑ ማንነትን ያጠፋል የምትሉትንና ሌሎች ለተቃውሞ መነሻ የሆኗችሁን ጉዳዮች በተጨባጭ ማስረጃ አስደግፋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ?
አንደኛ ነገር ፕላኑ ሉአላዊነትን ይፃረራል፡፡ አንድ ገበሬ ከመሬቴ አልነሳም ሲል የግድ ትነሳለህ ማለት የመብት መደፈር ነው፡፡ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። ሌላ ሙያ የሌለው ካፒታሉ መሬት ብቻ የሆነን ህዝብ ማፈናቀል፣ የኢኮኖሚ መሰረቱን ማሳጣት ብቻ ሳይሆን ማንነቱን፣ ቋንቋውን፣ ባህሉን የሚያሳጣ ነው፡፡ በእነዚህ አካባቢ የዛሬ 25 ዓመት ኦሮሚኛ ሲነገር ነበር፡፡ ዛሬ አንድ የኦሮሚኛ ቋንቋ የማይሰማባቸው ቦታዎች ሆነዋል፡፡ በዚህ ነው ማንነትን ያጠፋል የምንለው፡፡ ህዝቦች ማንነታቸውን እንደጠበቁ አብሮ በመኖር እናምናለን፤ ነገር ግን አንዱ የአንዱን ማንነት እያጠፋ አይሆንም፡፡ አሁንም ይሄን አካሄድ መቃወማችንን እንቀጥላለን፡፡
መንግሥት አሜሪካንን በመሳሰሉ የሰለጠኑ ሀገራት የክልል ከተሞችን በእንዲህ ያለው ፕላን የማስተሳሰሩ ጉዳይ የተለመደ መሆኑን በመጥቀስ፣ የከተሞች በልማት መተሳሰር ምን ክፋት አለው ይላል፡፡ ለዚህ የናንተ ምላሽ ምንድነው?
አንደኛ ነገር የአሜሪካንን ተሞክሮ እዚህ የምናመጣ ከሆነ አይሰራም፡፡ ህዝቡ ተመሳሳይ አይደለም፡፡ ተመሳሳይ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለ ህዝብ፣ ከሞላ ጎደል አንድ ቋንቋ የሚናገር ህዝብ፣ ተመሳሳይ ስነ ልቦና ያለውና ቢቀላቀል ማንነቱ በምንም አይነት ሁኔታ የማይበረዝስ ነው የአሜሪካው፡፡ በኛ ሁኔታ ግን መጀመሪያውኑ ፌደራል ስርአቱ መሰረት አድርጎ የተነሳው የተለያዩ አይነት ህዝቦችን ነው፡፡ የተለያየ ቋንቋ፣ ባህልና ስነ ልቦና ያላቸው ህዝቦች ተጋርተው የሚኖሩባት ሀገር በመሆኑና እያንዳንዱ ህዝብ ማንነቱን፣ ቋንቋና ባህሉን የሚፈልግ በመሆኑ ነው ፌደራሊዝም ያስፈለገው፡፡
አሁን በተኬደበት አቅጣጫ ግን እነዚህ ከተሞች በምን ቋንቋ ሊጠቀሙ ነው? አስተዳደሩስ ምን ይሆናል? አሁን ለምሳሌ ቡራዩና ላይ ት/ቤቶች ቢሰሩ፣ መሰረተ ልማቶች ቢስፋፉ እኛ እንደግፋለን ነገር ግን የኛ መሰረታዊ ጥያቄ ለቡራዩ አዲስ አበባ ልታቅድ አትችልም ነው፡፡ ፌደራል መንግሥትም ቢሆን ለከተሞች የማቀድ ስልጣን በህገ መንግሥቱ አልተሰጠውመ፡፡
ይሄ በፌደራል መንግሥት የሥልጣን እርከን ውስጥ አይደለም፡፡ እንደዛ ከሆነ ከተሞች ለምን የራሳቸው አስተዳደር አስፈለጋቸው?
የኛ አጠቃላይ አቋም አንዱን ካንዱ መቀላቀል የሚለው ለምዕራባውያን እንጂ እንደኛ አይነት የተለያየ ቋንቋ፣ ባህል ያለው ማህበረሰብ ውስጥ ሊሰራ አይችልም ነው፡፡ መንግሥት በፌደራል ደረጃ የሚሰራቸው ሀገራዊ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች አሁንም መሰራት አለባቸው ነገር ግን ከተማ ነክ የሆኑትን ከተሞች አንዱ ካንዱ እየተቀበለ ነው መስራት ያለበት፡፡
ለምሳሌ የአሜሪካ ከተሞች እነ ዋሽንግተን ዲሲን ስንመለከት፣ ዲሲ ራሷ የተመሰረተችው ከተለያዩ ስቴቶች በተቆራረጠ መሬት ላይ ነው፡፡ በኋላ ግን አንዱ ስቴት የተወሰነን የዲሲ መሬት የራሴ ነው ብሎ ወስዷል፡፡ እርግጥ ነው አሁን በዲሲና በቨርጂኒያ መካከል ልዩነት ላይታይ ይችላል፤ ነገር ግን ሁለቱ ከተሞች የተሰመረ ድንበርና የየራሳቸው አስተዳደር አላቸው፡፡
ወደኛ ሁኔታ ስንመጣ ግን አሁን የአዲስ አበባ ኮንዶሞኒየም ቤቶች የሚሰሩት የኦሮሚያ ግዛት ውስጥ ነው፡፡ ይሄን የኦሮሚያ ክልል አያውቀውም። ገላን ላይ ያወጣውን ውሃ የአዲስ አበባ ህዝብ ሲጠጣ፣ ገላን ላይ ያለው ህዝብ ግን ውሃ እየተጠማ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ይሄ የተቀናጀ አይደለም፡፡ አንዱን ወገን ጎድቶ አንዱን የሚጠቅም አይነት ነው፡፡ ይሄን ዓይነት በህዝቦች መካከል ያለውን አብሮ የመኖር ባህል የሚንድ እንቅስቃሴ መቆም አለበት እንላለን፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ ያሉ ማናቸውም ህዝቦች፤ ከኦሮሞ ህዝብ እኩል መብታቸው ሊከበርላቸው እንደሚገባ እናምናለን፡፡ የኛ ጥያቄ ወደ እውነተኛው ፌደራሊዝም እንመለስ ነው፡፡
ለኒህ ሰውየ ትልቅ ክብር አለኝ ለአቶ በቀለ ገርባ።በተናገሩትም ሁሉ እስማማለሁ ግን ወያኔ ለሱዳን ቆርሶ ስለሰጠው መሬት አንዲት አረፍተ ነገር እንኩዋ ተሳስቶዋቸው አልውጣም ! ! ! በዚህ በጣም አዘንኩኝ ! ! ! ለባዕድ የተሰጠውን መሬት ጎንደሬ ብቻ ይጨነቅበት አያገባኝም ያሉ ይመስላል።የአሰብንስ ለሳውድ አረቢያ መሸጥ አይገዳቸውም ? ? ? ወያኔ ልክ ኤርትራን እንዳስገነጠለው ሁሉ ለሱዳን የሰጠውን መሬት ለአለም መንግስታት ካሳወቀ ብሁዋላ ማንም ሰው የመጠየቅም የመናገርም መብት አይኖረውም። እኒህ ሰውየ ይኽንን የሚያክል national issue ignore ማድረጋቸው በጣም ቅርር ያሰኛል።ልብ በሉልኝ ስለ አዲስ አበባ master plan የሰጡት አስተያየትና መልስ እጅግ በጣም ትክክል ነው ከክልል ያለፈ አስተያየታችውን እጠብቃልሁ።
This guy I think needs
attention . Why not they
throw him like Iskender.
and the rest.
ይችህ ናት ሀገሬ አንቀፄ 39
ወያኔዎች እንኳን ደሥ አላችሁ ያሠባችሁት ተሣክቷል ግን ዙሩ የኛ ነው ትደመሠሣላችሁ።
ato bekele gerba erso bekrbu be esat yalutn lastawsot oromo bzu slehone ende asefaferu yerasu yehone tewekay yasfelgewal neber yalun erso yeyazutn kartama amharawlaym hone lilaw ethiopiyalay begdaj yetechane yezer fideralizm new lemehonu erso yemilun oromo sisefr amhara yelem neber oromo yeseferebet bota hulu yeoromonew yalew manew? bzu yeoromo lezer lhikanoch yemilut yalefut sratoch yeamhara geziwoch slenebere oromo teweronew alachu betam yemigermew erso bzunen ende asefaferachn eyalu endit new oromo eyetewerere ezih liders yechalew ? ena eNa zari be21Naw kfle zemen yeoromo zeroch yeseferubetn hulu lezerochachew bezerrochachew sm slemikellu lilaw agerun menetek alebet ? slezih sijemer weyanin bechakam hone 25 amet eyankebekebachu bezer mannet ager felegachu gn zer bematfat zer bemasdat ager memesret ena neSanet mamtat ychalal wey? yeasi woch sreat be ethiopiya mililik aydelum yefeterut mililik oromowochn krstiyan hun blew ahun yeyazachhutn karta kemtew ethiopiyawi endthonu alaregachum oromo be ethiopiyawst sisefr asi tedros asi yohans yegezubet zemen wstm neberu mililik abatochachew ayatochachew kene tarikachew yeshewa ngus nachew gonderi aydelim weym gojami weym weleyi bezer beamharanet tederajtew oromon zer yatefubet tarik yelem be ethiopiya wst lemejemeriya neft yetenesaw grN mahmed yeshewa nguse negst mengst afersalew ethiopiyan ye eslam ager adergalew balebet zemen awo krstiyanoch agerachewn wedeneberechbet lemasmeles haymanotachewnm lemasmeles tglewal kezam befit ethiopiya yemttawekew yeshwa nguse negset mengst muslimochn yastega yemejemeriyawa ethiopiya sdeteNochn yetekebelech tarik yalat nech yh hilu siwerd siwared ahun lalenbet mannetachn hononal zari bezer eyetederajachu ager lemekefafel ethiopiyanoch bezerachew mknyat bagerachew sisededu lemn ersona teketayochot altekawemum ? leweyani yetekemachut amharan atfto wero siyabeka ,gabilan mewrer matfat sumalin afarun ….eyale adis abeban bwerea tekotatro sichrs wede oromo meta bibal yasdenkal wey siserabet yeneberew 25 amet mulu bewerera yezer lhikanochn eyepeweze etiopiyanochn eyatefa ye ethiopiyan habt wederasu bemasgebat lemotelet tgri zer endit ye ekonomi balebit endemiyaderg betegbar asaytal zarim begonder yetesetew merit oromon aynekamblew asbew kehone tesastewla weyani amharawn wero gabilan alekekem ….blo zari oromiya yemtlatn kll (ager) alfelegemen? slezih bezer astesaseb ethiopiyanoch neSa aywetum be ethiopiyawinet gn hak new
This is very nice comment ! We have to understood and struggle !!!
I wonder if Bekele Gerba is a CIA agent. He should better drop tribalism and fight for Ethiopianism. There is only Ethiopian land in Ethiopia, and the land is only for Ethiopians. There has never been a so-called Oromia. Oromos by the way came to Ethiopia since the 16th century, and most people who speak oromigna today are not ethnic oromos.
” temelkach says:December 5, 2015 at 1:35 pm
ለኒህ ሰውየ ትልቅ ክብር አለኝ ለአቶ በቀለ ገርባ።በተናገሩትም ሁሉ እስማማለሁ ግን ወያኔ ለሱዳን ቆርሶ ስለሰጠው መሬት አንዲት አረፍተ ነገር እንኩዋ ተሳስቶዋቸው አልውጣም ! ! ! በዚህ በጣም አዘንኩኝ ! ! ! ለባዕድ የተሰጠውን መሬት ጎንደሬ ብቻ ይጨነቅበት አያገባኝም ያሉ ይመስላል።የአሰብንስ ለሳውድ አረቢያ መሸጥ አይገዳቸውም ? ? ? ወያኔ ልክ ኤርትራን እንዳስገነጠለው ሁሉ ለሱዳን የሰጠውን መሬት ለአለም መንግስታት ካሳወቀ ብሁዋላ ማንም ሰው የመጠየቅም የመናገርም መብት አይኖረውም። እኒህ ሰውየ ይኽንን የሚያክል national issue ignore ማድረጋቸው በጣም ቅርር ያሰኛል።ልብ በሉልኝ ስለ አዲስ አበባ master plan የሰጡት አስተያየትና መልስ እጅግ በጣም ትክክል ነው ከክልል ያለፈ አስተያየታችውን እጠብቃልሁ።”
No, you are wrong.
The guy is a tribalist, we must reject tribalism.
Oromos migrated to Ethiopia only since 16th century. Oromos are not native to Ethiopia, so Bekele would be a fool if he is tribalist since oromo tribal land is not in Ethiopia.
ሁለት ነገሮችን ለያይተን እናቅርብ፤
አንደኛ፣ የኢትዮጵያው ሕገ መንግስት ስለ ፌዴራል አወቃቀር ምን ይላል ብንል፣ ሁሉም ክልሎች ራሳቸውን ያስተዳድራሉ፤ በመቀጠልም በሀገሪቱ ትልቁ የስልጣን መዋቅር ወረዳ ነው ይላል።
እንግዲህ ትልቁ ስልጣን ለወረዳዎች ሰጥቶ እያለ ነው የፌዴራሉ መንግስት ያለ ስልጣኑ ገብቶ ይቅርና የወረዳዎችን ስልጣን ሊያከብር፣ የየክልሎችን ስልጣንና መብትን ደፍጥጦ ያለው።
ስለዚህ ሕገ መንግስቱን የጣሰው ማነው ነው የሚሆነው ጥያቄው? ምንም እንኳ ህገ መንግስቱ ራሱ ብዙ ህጸጾች ያሉት መሆኑንና ብዙ መስተካከል ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ ግንዛቤ በማስገባት ጭምር ነው።
ግን ይህንን ህግ አክብሩ ብሎ ያለው መንግስት ራሱ ላወጣው ሕግ እንኳ ተገዢ ሳይሆን ሲቀር ሌላውማ ከነግሳንግሱ ይሁን ብሎ ለተቀበለው(ለጊዜውም እስካሰራን ብሎ)፣ ቢጥሰው ተወቃሽ የሚያደርገው ያለ አይመስለኝም።
ሁለተኛ፣
ከለልተኝነት እለዋለሁ ጎጠኝነት ከማለት ይልቅ። ምክንያቱም በክልል አጥር አጥረውን እርስ በርሳችን እንዳንተያይ፣ የተጎዳነው ካለም እንዳንመካከርበት ወዘተ በክልል እስር ቤት ውስጥ አስገብተው ካስቀመጡን ቆይተናል። እንደሚታወቀው ሁላችንም አልተመቸንም፣ ቃል የተገባልንም እንዲሁ በሰማይ ያለ ዳቦ ነው የሆነብን ወዘተ።
ታዲያ ይህንን ችግራችንን አውቀን በጋራ ታግለን የተሻለ አስተዳደር እንደምፍጠር፣ ወንድማችንና የምናከብራቸው አቶ በቀለ ገርባ አሁንም የቀድሞ መዝሙራቸውንና ዕርባና ያላስገኘልንን የክልል መሬት አትንኩብኝ ጥያቄ ላይ ሙጭጭ ማለታቸው ትግላችን ገና ረዥም እንደሆነ አመላካች ነው።
በተለያዩ የ አገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች ይህንን አስመልክቶ ተማሪዎች ጥያቄዎቻቸውን እያቀረቡ ነው። ለነዚህም ድጋፋችንን እንድንቸራቸው ጥያቄ ቀርቧል። ነገር ግን ጥያቄው ክልልን የሚመለከት ብቻ በመሆኑ፣ በበኩሌ ተነሳሽነቴን ቀንሶታል። ዝም ብዬም መንግስቱን ተቃዉመዋልና የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚለው ተገፍቼ ድጋፍ ለመስጠት ይቸግረኛል።
አስተውለን ከሆነ ወያኔ ሁላችንንም በየተራ ሲቀጠቅጠን ዝም እያልን፣ ተራው የኛ በሆነ ጊዜ ነው ጩኸታችን የሚበረታው።
ስለዚህ ጥያቄው ሃገራዊ አንድነታዊ አድርጉት አብረናችሁ እንሰለፍ። አለበለዚያ ያህያ መናጆ ሆኜ መጸጸትን አልፈልግም። የበፊቱም ደርግ ይውደቅ እንጂ፣ የሚመጣው ከርሱ የባሰ አይሆንም የሚለው ግምቴ ቁጭትን ፈጥሮ ዋጋ እያስከፈለን በመሆኑ ነው።
የሀገሬ የኦሮሞ ልጆችም ቆም ብላች ሁ የፖለቲከኞችን ቁማር ተመልከቱ፣ ለብሔር ነጻነት ተብሎ ስንት የትግራይ ልጆች አለቁ፨ ያ የህልም እንጀራ ይቅርና ለሌሎች ነጻነት ሲሉ የከፈሉት መስዋዕትነት እንኳን ለራሳቸውም አላገኙትም።
በዚያ ሁሉ መስዋዕትነት የተገኘው ቢኖር፣ በብሄር ስም አገሪቷ ለጥቂት ከዳተኞች እንድትዳረግ ሆናለች።
ስለዚህ አሁንም በስማችሁ እየተነገደ እንዳይሆን አስተውሉ።
የሁላችንም ችግር ክብደቱና መጠኑ ሊለያይ ቢችልም አንድ ስለሆነ በጋራ በአንድ ሃገር ማዕቀፍ ስር ተመልክተን መፍታቱ ነው የሚሻለን።
በቸር እንሰንብት።