ሰሞኑን በአምቦ ፣ በሐረማያ ፣ በወለጋ ፣ በቡራዩ እና ወዘተ ቦታዎች ኢትዮጵያውያኖች ዛሬም በዘረኛው ወያኔ ትግሬ እየተገደሉ እንደሆነ ሰምቻለሁ ። በጎንደር ኢትዮጵያውያኖች እየተገደሉ እንደሆነ ሰምቻለሁ ። ህዝበ ሙስሊሙ የእምነት ነጻነቱን እንደተነጠቀም አውቃለሁ ። አስራምስት ሚሊዮን ሕዝብ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ በሚሻበት …

ይህ መንግስት ምን ይዞ ቆመ ( ኄኖክ የሺጥላ ) Read more »

Amdom Gebreslasie – “ልማታዊ መንግስት” ነኝ ብሎ ራሱ የሚያወድሰው ኢህኣዴግ ኣዲስ ኣበባን የሚያለማ ኣዲስ ማስተር ፕላን ኣዘጋጀው ብሎ ኣወጀ።የልማቱ ዋነኛ ትኩረቱ ደግሞ በኣዲስ ኣበባ ዙርያ የሚገኙ ከተሞችና ገጠር ወረዳዎች ሲሆን የኦሮምያ ልዩ ዞን ተብሎ የሚታወቅ ነው። ልማት የሚጠላ ሰው ያለ …

“ልማታዊ መንግስት” ነኝ ብሎ ራሱ የሚያወድሰው ኢህኣዴግ ኣዲስ ኣበባን የሚያለማ ኣዲስ ማስተር ፕላን ኣዘጋጀው ብሎ ኣወጀ። Read more »

በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም በተማሪዎች የሚካሄድ ሰልፍ ዛሬም መቀጠሉ ታዉቋል።
በተቃዋሚዎች ላይ የጸጥታ አስከባሪዎች በሚወስዱት እርምጃም የሰዉ ሕይወት እንደጠፋ፥ የቁሰሉና የታሰራ እንዳሉ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ቃለ ምልልስ የሰጡ ነዋሪዎችና የተቃዋሚ ፓለቲካ ተወካዮች ተናግረዋል። በነሞ ዳንዲ የተጠናቀረዉን ዘገባ ዝርዝር ትዝታ በላቸዉ ታቀርባለች።

የብሪታንያ የጦር አይሮፕላኖች ሶርያ ውስጥ የአየር ድብደባ ጀምረዋል። ድብደባውን የጀመሩት የብሪታንያ የምክር ቤት አባላት እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለውን ጽንፈኛ ቡድን ለማሸነፍ እንዲቻል የሀገሪቱ ስትራተጂ እንዲሰፋ ዴቪድ ካምሩን ያቀረቡትን ሃሳብ ካጸደቀ በኋላ ነው – VIDEO ↓

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

በጎንደር ዩንቨርስቲ ከፍተኛ ተቃውሞ በተማሪዎች ተነስቷል:: ‪#‎Gonder‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎GonderProtests‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የጎንደርን ህዝባዊ አመፅ የቋራ ገበሬዎች እና የጎንደር ዮኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቀላቀሉ። ዛሬ ከሰአት በሃላ ጀምሮ የቆራ ገበሬዎች የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግሬ ይጠቀምባቸዉ የነበሩትን የእርሻ መሳሪያ በማዉደም …

በጎንደር ዩንቨርስቲ ከፍተኛ ተቃውሞ በተማሪዎች ተነስቷል:: Read more »

ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ምስክር ሆነው እንዳይቀርቡ ያቀረበውን ይግባኝ ዛሬ ህዳር 23/2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውድቅ አደርጎታል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ …

ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ምስክር ሆነው እንዳይቀርቡ የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ Read more »

የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን … መሬት.. ካሳ.. ነጠቃ.. ጎዳና … አደጋ ( ምንሊክ ሳልሳዊ ) ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AddisAbabaMasterPlan‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎EPRDF‬ Minilik Salsawi– ሃገር ቢያድግ ከተሞች ቢስፋፉ ማንም የሚጠላ የለም::በልማት ስም የሚደረጉ ድምጽ አልባ ሽብሮች ግን ለዜጎች ሕልውና አደጋ ስለሆኑ ሊተኮርባቸው ይገባል:: …

የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ትላንት በዘረኝነት በጥላቻ የተባበሩበት ጉዳይ ዛሬ ራሳቸውን ነጥሎ እያጠቃ ነው:: Read more »

ኦሮሚያ ውስጥ እየታየ ላለው የተማሪዎች ተቃውሞና መዘዝ ተጠያቂው መንግሥት እንደሆነ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ – ኦፌኮ ክሥ አሰምቷል፡፡ አዲስ አበባ — የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ – ኦፌኮ በአሁኑ ጊዜ የሃገሪቱ አንድነት ያለው “አጠያያቂ ሁኔታ ላይ ነው” ብሏል፡፡ እስከአሁን ለተፈጠሩ ችግሮችና ወደፊትም ሊከተሉ ለሚችሉ …

ኦሮሚያ ውስጥ እየታየ ላለው ተቃውሞና መዘዝ ተጠያቂው መንግሥት እንደሆነ ኦፌኮ ክሥ አሰምቷል፡፡ Read more »

የ-ማስታወቂያ አላማ አዲስ ነገርን ለብዙ ዘመን የምታውቀው ፣ የምታውቀውን ደሞ አዲስ አስመስሎ ማቅረብ ነው ይላል አንዱ ፈረንጅ ፣ በራሱ በፈረንጁ ቋንቋ አባባሉ እንዲህ ተጽፎ ነበር ( Advertisement is making the new familiar and the familiar new )። አዎ አንዳንድ የፖለቲካ …

ድሃው የትግራይ ገበሬ ( ኄኖክ የሺጥላ ) Read more »

ቢቢኤን በዛሬው እለተ እሮብ ዝግጅታችን http://goo.gl/alb6ny መንግስት በኦሮሞ ተወላጆች በተማሪዎች ላይ የሚፈጸመውን የሃይል እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሏል ዝርዝረ መረጃዎችን ይዘናል በጉዳዩ ላይ ጋዜጠኛ በፍቃዱም ሞረዳን አወያይተናል በመርሳ ከተማ የሚፈጸመው የመስጅድ ነጠቃና አፈና ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ ለወጣቱ ጥሪ ቀርበዋል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ …

መንግስት በኦሮሞ ተወላጆች በተማሪዎች ላይ የሚፈጸመውን የሃይል እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሏል::ዝርዝረ መረጃዎችን ይዘናል Read more »

ያሳፍራል፤ ያሳዝናል፤ እውነተኛ ገጠመኝ //Girma Bekele አንድ ኦሮሞ ወዳጄ –እንዲውም በጣም ቢቆይም ቀድሞ የኦሮሚያ ባለሥልጣን የነበረ፣ የመንግስት ሥራ ትቶ በግል ሥራ ኦሮሚያ ውስጥ ለዚያውም በተወለደበት አካባቢ ኢንቨስት ለማድረግ ፕሮፖዛሉን ይዞ ወደ ዞኑ ኢንቨስትመንት ቢሮ ይሄዳል፣ ያስገባል፡፡ የጠየቀውም ቦታ በማንም ተይዞ …

ሰውን በቀዬው ባይተዋር ማድረግና የትግራይ ተወላጆችን የኢኮኖሚ አቅም መገንባት – እውነተኛ ገጠመኝ Read more »

የኃይል ማመንጫዎች ብልሽት በመላ አገሪቱ የኃይል አቅርቦት እያስተጓጎለ ነው

በጣና በለስና በጊቤ አንድ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በደረሰ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና የኤሌክትሮኒክ መቆጣጠሪያ ብልሽት፣ በመላ አገሪቱ የኃይል አቅርቦ ተስተጓጉሏል፡፡ ቅዳሜ ኅዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በአገሪቱ ትልቁና 460 ሜጋ ዋት

የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ላይ በሚገኘው ጣና በለስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ  የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መቆጣጠሪያ ተበላሽቷል፡፡

ይህንን ብልሽት ለማስተካከል እየተሞረከ ባለበት ወቅት በነጋታው እሑድ ኅዳር 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ደግሞ በጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ተመሳሳይ ብልሽት አጋጥሟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተነስቶ ከሰኮሩ ከተማ ወደ ጌዶ የተዘረጋው የኃይል መስመር አደጋ ደርሶበታል፡፡

በእነዚህ ምክንያቶች ኅዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት፣ ኅዳር 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ደግሞ ከ9፡30 ሰዓት ጀምሮ በመላ አገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል፡፡ በዚህ የኃይል መቋረጥ ነዋሪዎች በሚያካሂዱት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ፣ ከጥቃቅንና ከአነስተኛ አምራቾች እስከ ግዙፍ ማምረቻ ተቋማት ችግር ገጥሟቸዋል፡፡ በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ በሁለት አቅጣጫዎች አገልግሎት መስጠት የጀመረው የቀላል ባቡር ትራንስፖርትም መስተጓጎል ገጥሞት ነበር፡፡

የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ባለሥልጣን ባለሙያዎች ወደ ሥፍራው ተንቀሳቅሰው ችግሩን ለመፍታት እየሞከሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ምስክር ነጋሽ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

460 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ያለው ጣና በለስና 184 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የማመንጨቅ አቅም ያለው ጊቤ አንድ፣ በብሔራዊ የኃይል ቋት ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው በአገሪቱ ችግር ተፈጥሯል፡፡

በዚህ ምክንያት በመላ አገሪቱ ኃይል ከመቋረጡም በላይ፣ ችግሩ እስካሁን ባለመፈታቱም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም የኃይል መቆራረጥ እያጋጠመ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ እነዚህ ችግሮች  በአሁኑ ወቅት የጎላ ደረጃ ይድረሱ እንጂ ችግሮቹ ያልተፈቱባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡

ከእነዚህ ውስጥም የመለዋወጫ ዕቃዎች በወቅቱ አለማዘጋጀት፣ በግድቦች አስተዳደር የባለሙያ እጥረት፣ አሮጌ የማሰራጫና ማስተላለፊያ መስመሮች በአዲስ አለመተካትና አሻጥረኛ ሠራተኞች መኖራቸው ለችግሩ መባባስ እንደ ምክንያት ያስቀምጣሉ፡፡

አሁን በተፈጠረው ችግር ብቻ አዲስ አበባ ከ120 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት መከሰቱን መረጃዎች አመልክተው፣ በአንዳንድ መንደሮች ኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት ቅንጦት እየሆነ ነው፡፡

አሁን ያጋጠመውን ችግር ለመቅረፍ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን፣  በመስኩ ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር ግንኙነት በማድረግ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሠራ እንደሆነ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

 

 

 

 

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን ላይ ተቃውሞ አሰሙ

‹‹አረጋግተን እንዴት ትምህርት መጀመር እንዳለባቸው እየተነጋገርን ነው›› የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላንን በመቃወም፣ ኅዳር 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሠልፍ ወጡ፡፡ 

ተማሪዎቹ በማስተር ፕላኑ ውስጥ ማንኛውም የኦሮሚያ ቦታ መወሰድ ወይም መካተት እንደሌለበት የሚያንፀባርቁ መፈክሮችን ይዘው ከዩኒቨርሲቲው ግቢ በመውጣት፣ ወደ ሐረማያ ከተማ ለመሄድ ባደረጉት ሙከራ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር መጋጨታቸው ታውቋል፡፡ 

ተማሪዎቹ እንቅስቃሴውን የጀመሩት ኅዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ምሽት ላይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ እንቅስቃሴውን በመስማቱ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ ለፀጥታ ኃይሎች መረጃው በመድረሱ የዩኒቨርሲቲው ፖሊሶች፣ የክልሉ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት መከላከል፣ የተማሪዎቹ ሠልፍ በቅጥር ግቢው መገታቱን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ተማሪዎች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ 

የተቀናጀ ማስተር ፕላኑን በሚመለከት ባለፈው ዓመት ተነስቶ በነበረው ተቃውሞ የመንግሥት አካላት ትኩረት በመስጠት በተለይ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ ነዋሪዎችና ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ተፈጥሮ የነበረውን ውጥረት ከማርገባቸውም በተጨማሪ ስምምነት ላይ እንደደረሱ መገለጹ ይታወሳል፡፡ 

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ነገሩን እንደ አዲስ እንዴት ሊያነሱት እንደቻሉ ተማሪዎቹ ተጠይቀው እንደገለጹት፣ ኅዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም. የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስብሰባ አዳራሽ ጉባዔ ጠርቶ ነበር፡፡ ከስብሰባው አጀንዳዎች አንዱ የከተማ ማስተር ፕላኖችን ማስተካከል ነው፡፡ በመሆኑም ባለፈው ዓመት ተቃውሞ ተነስቶበት በቂ ማብራሪያ ሳይሰጥበትና ስምምነት ላይ ሳይደረስ በዝምታ ታልፎ፣ አሁን ሊፀድቅ እንደሆነ በመገመት ሳይሆን እንዳልቀረ፣ የተቃውሞውን ምክንያት መገመታቸውን ተማሪዎቹ አስረድተዋል፡፡ 

ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ እየተዟዟሩ መፈክር በማሰማት ላይ እያሉ፣ ለተቃውሞው መነሳት ምክንያት ናቸው የተባሉ ቁጥራቸው የማይታወቁ ተማሪዎች መታሰራቸውንና የተወሰኑ ተማሪዎች ተደብድበው ጉዳት እንደደረሰባቸው ተማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በወቅቱ ጥይት የተኮሰ ቢሆንም የተጎዳም ሆነ የሞት አደጋ እንዳልደረሰ አክለዋል፡፡ ቁጥራቸው የማይታወቅ ተማሪዎች ሠልፉ ከመደረጉ አስቀድመው ከግቢው በመውጣት ከዘመዶቻቸው ጋር መቀላቀላቸውንና ከተለያዩ ክልሎች የመጡም ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ በተለያዩ ቦታዎች ተደብቀው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ 

ኅዳር 20 እና 21 ቀን 2008 ዓ.ም. (ኅትመት እስከገባንበት ምሽት ድረስ) በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሒደት መቋረጡም ታውቋል፡፡ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ተማሪዎች ስላነሱት ተቃውሞ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጨመዳ ፊኒንሳ፣ ተማሪዎቹ ተቃውሞ ማንሳታቸውን አረጋግጠው ‹‹አረጋግተን እንዴት ትምህርት መጀመር እንዳለባቸው እየተመካከርን ነው፤›› ብለዋል፡፡ 

ተማሪዎቹ ኅዳር 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ረፋዱ 2፡30 ሰዓት ድረስ፣ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ሰላማዊ ሠልፍ ማድረጋቸውን የተናገሩት ፕሮፌሰሩ የአካባቢው አስተዳደር፣ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስና ፌዴራል ፖሊስ ወደ ውጭ እንዳይወጡ ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ 

የተማሪዎቹ ተቃውሞ ከማስተር ፕላኑ ጋር ብቻ የተገናኘ መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰሩ፣ እንዴት ስለማስተር ፕላኑ ሊያነሱ እንደቻሉ እሳቸውም እንዳልገባቸው አስረድተዋል፡፡ በሠልፉ ግርግር ትንሽ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ሕክምና የተደረገላቸው መሆኑን ጠቁመው፣ ሦስት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ክሊኒክ እየታከሙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

ፖሊስ ወደ ሰማይ ከመተኮስ ባለፈ ተማሪዎችን የሚጎዳ ድርጊት አለመፈጸሙን፣ ለረብሻው ምክንያት ናቸው የተባሉ ተማሪዎች ተይዘው በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ከፖሊስ፣ ከዩኒቨርሲቲውና ከተማሪዎች የተውጣጣ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ምርመራ እያደረገባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የተወሰኑ ተማሪዎችም መለቀቃቸውን አክለዋል፡፡ 

ተማሪዎቹ ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ እሳቸውን ጨምሮ መምህራኑ እየመከሩ መሆኑን ፕሮፌሰር ጨመዳ አስታውቀዋል፡፡ ለትምህርት ሚኒስትሩ ለአቶ ሽፈራው ሽጉጤና ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማሳወቃቸውንም አረጋግጠዋል፡፡ 

 

የመንግስት ሃይሎች የሱሉልታ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ጉዳት አደረሱ ። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎Oromo‬ ‪#‎AddisababaMasterplan‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ የመንግስት ሃይሎች በዛሬው እለት የሱሉልታ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የመብት ጥያቄ በመጠየቃቸው በጫንጮ ከተማ ተማሪዎች ላይ ጉዳት አደረሱ ።የኦሮሞ ተማሪዎች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ተቃውሞዋቸውን …

የመንግስት ሃይሎች የሱሉልታ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ጉዳት አደረሱ ። (Photos) Read more »

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News የህዳር 21 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (December 01, 2015 News) – የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች በቂ ውሃ ባለማጠራቀማቸው ምክንያት የኤሌክትሪክ አገልጎት በየቦታው የሚቋረጥ መሆኑ ተነገረ –  የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም እየተካሄደ ያለው …

የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች በቂ ውሃ ባለማጠራቀማቸው ምክንያት የኤሌክትሪክ አገልጎት በየቦታው የሚቋረጥ መሆኑ ተነገረ Read more »

News Ethiopia Wetatoch Dimts መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም የስፖርት ዘገባዎች መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ ። [youtube http://www.youtube.com/watch?v=x4ZqSwhWzYU]  

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)– የወያኔን ጉጅሌ አገዛዝ ጭካኔ እና እኩይ ተግባር ብናወራው አያልቅም::በሕግ እና በሕዝብ ስም ሽፋን በርካታ አደገኛ ወንጀሎች በተደጋጋሚ እየተፈጸሙ ነው::በለውጥ ሃይሉ መካከል በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት እስካሌለ ድረስ ወያኔ ይህንኑ ክፋቱን ከሰይጣን የበለጠ ተግባሩን አስፋፍቶ ይቀጥላል::ሕዝብ እምነት …

ቀን እየቆጠሩ ከማስጨፈር የግለሰብ ከዚያ የብሄረሰቦችን መብት ማክበር ይቅደም:: Read more »

በትናንቱ ዕለት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደው ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት ሕይወታቸው ያለፈና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች እንደነበሩ ተገለጸ። በተለይም ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ (Haramaya University) በደረሰ ግጭት የመንግሥት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ሁለት ተማሮች መሞታቸው ታውቋል።

ጎንደር ከተማ ዉስጥ የሚገኘዉ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እስር ቤት በእሳት እየተቃጠለ ነዉ። ከማሰቃያ ቤቱ የነበሩ እስረኞች አምልጠዋል። የድንበሩ ጉዳይ ህዝብን አስቆጥቶ መላ ጎንደርን እያናወጣት ነዉ።

የዲላ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ስለሺ ኮሬ በቀረበባቸው ከፍተኛ ክስ በሙስና ሴቶችን በማማገጥ እና ሌሎች የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከስልጣናቸው መነሳታቸው ሲታወስ ይህን አስታኮ ፕሬዚዳንቱ አስቀድመው ያዘጋጁትና በዘር የተደራጁ ደጋፊዎቻቸው ጥቅማችን ተነካ ወገናችን የጌድዎ ልጅ ተባረረ በማለት በምክትል ፕሬዚዳንቱ በአቶ ሰለሞን …

የተባረሩት የዲላ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደጋፊዎች በጎሳ ተደራጅተው ለአመጽ እየተዘጋጁ ነው:: Read more »

በባሌ ሮቤ የፌዴራል ፖሊስ እና የአግኣዚ ጦር አባላት በከተማው ደርሰው በመፍሰስ እንዲሁም ከገጠሩ ወደ ከተማው የሚያስገቡ መንገዶችን በመዝጋት ከተማዋን ውጥረት ውስጥ ከተዋታል::የሮቤ መምህራን ኮሌጅን የሁለተኛ ደረጃ እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምሕርት ቤቶችን ከበዋል::የመዳወላቡ ዩንቨርስቲ ከከተማው የሚያገናኘው መስመር በወታደሮችኡ ተቆርጦ የታጠረ ሲሆን …

ባሌ ሮቤን መደወላቡ ዩንቨርስቲ ውጥረት ላይ ናቸው::የመዳወላቡ ዩንቨርስቲን ከከተማዋ የሚያገናኘው መስመር ታጥሯል:: Read more »

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር አቅራቢያ ስናር መቅሪ ጨው ላይ ሰፍሮ የቆየው የህወሓት ልዩ ኃይል ጦር በወረርሽኝ በሽታ በመጠቃቱ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ተገደደ፡፡ ህወሓት የልዩ ኃይል ጦሩን ስናር ላይ ያሰፈረው በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ሲሆን በጦር ካምፑ ውስጥ ወረርሽኝ በመግባቱ እና ሁሉም አባላት …

በኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር የህወሓት ልዩ ኃይል ጦር በወረርሽኝ በመጠቃቱ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ተገደደ፡፡ ‪ Read more »

የምሥራቅና የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ተረጂዎች ቁጥር ከ50 በመቶ በላይ ጨምሯል

ከኤልኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች የተከሰተው ድርቅ እያሳረፈ ያለው ተፅዕኖ እየሰፋ መምጣት የተረጂዎችን ቁጥር እንዲጨምር እያደረገ ነው፡፡

ሰሞኑን በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመቃኘት የተንቀሳቀሰው የጋዜጠኞች ቡድን ከተመለከታቸው አካባቢዎች መካከል፣ የምዕራብና የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ውስጥ ከወራት በፊት የነበሩት ተረጂዎች ቁጥር ከ50 በመቶ በላይ ጨምሯል፡፡በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሃረን አልዪ እንደገለጹት፣ እስካሁን¬ 549,000 ተረጂዎች ተለይተው ዕርዳታ ሲሰጣቸው ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ድርቁ አሁንም ለውጥ ሳያሳይ በመቀጠሉ የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ብቻ ከ320 ሺሕ በላይ ተጨማሪ ተረጂዎች የመንግሥትን ዕርዳታ የሚሹ በመሆናቸው፣ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ የተረጂዎች ቁጥር 900 ሺሕ ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል፡፡ ለእነዚህ ተረጂዎች የሚሆን ተጨማሪ የምግብ ዕርዳታ የተጠየቀ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በምዕራብ ሐረርጌ ዞንም በተመሳሳይ በድርቅ የተጎዱ ተረጂዎች ቁጥር እንደጨመረ፣ የዞኑ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቶፊቅ አብዱላሂ ገልጸዋል፡፡ እንደ አቶ ቶፊቅ ገለጻ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብለው ሲሰጣቸው የነበሩት ከ500 ሺሕ በላይ ተረጂዎች ነበሩ፡፡ በጥር ወር ግን የተረጂዎች ቁጥር ከ720 ሺሕ በላይ እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል፡፡ 

የሁለቱም ዞኖች የሥራ ኃላፊዎች የተረጂዎቹ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን ሥጋት ገልጸዋል፡፡ በሁለቱም ዞኖች እስካሁን ዕርዳታ ሲሰጣቸው የነበሩት የባሰ ችግር የነበረባቸው ናቸው፡፡ ድርቁ እየተራዘመ በመምጣቱ ግን የተሻሉ ናቸው የተባሉትንም ጭምር ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው እየሆኑ መጥተዋል፡፡

በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳም ባለፈው ዓመት 14,404 የነበሩ ተረጂዎች ቁጥራቸው ከ51 ሺሕ በላይ ሆኗል፡፡

እንደ ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ፣ በ2007 የምርት ዘመን ይገኛል ተብሎ የታቀደው 12 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ነበር፡፡ በቅርቡ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ግን ሊገኝ የሚችለው ከሦስት ሚሊዮን ኩንታል ያነሰ ነው፡፡ በምዕራብ ሐረርጌም የሚጠበቀው ምርት ቀድሞ ከተገመተው በእጅጉ ያነሰ እንደሚሆን ታምኗል፡፡

በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የድርቅ ተጎጂዎች ከሆኑ ወረዳዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የሚደጋ ቶላ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ሳርቱ ሙክታር እንደሚሉት፣ መንግሥት ዕርዳታ እየሰጣቸው ቢሆንም ዕርዳታው በቂ አይደለም፡፡ በአንድ ቤተሰብ 15 ኪሎ ስንዴ እየተሰጣቸው መሆኑንና ሦስት ጊዜ መውሰዳቸውንም ተናግረዋል፡፡

ከስንዴው ጋርም አንድ ሊትር ዘይት ቢሰጣቸውም ይህ ግን በቂ አይደለም ይላሉ፡፡ የውኃ ችግሩ ግን እጅግ የከፋ መሆኑን የሚገልጹት የሚደጋ ቶላ ወረዳ ነዋሪዎች፣ በአጋጣሚ በዘነበው ዝናብ በአንድ ኩሬ ላይ የተጠራቀመ ውኃ ለከብቶቻቸውም ለራሳቸውም ይጠቀሙበታል፡፡

ቀድሞ ለመጠጥ ይጠቀሙበት የነበረው ኩሬ በመድረቁ መንግሥት በቦቴ የሚያመጣውና የሚያሠራጨው ውኃ የማይዳረስ ስለሆነ፣ አንዳንድ ነጋዴዎች አምጥተው የሚሸጡትን አንድ ሊትር ውኃ በአንድ ብር እየገዙ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ይህም ቢሆን በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡

አቶ ሃሮን አሊዪ እንደሚሉትም በአካባቢው ያለው የውኃ እጥረት ከፍተኛ ነው፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፣ ካለው ሁኔታ አንፃር በዞኑ የከፋ ችግር ላለባቸው ወረዳዎች 30 የውኃ ማመላለሻ ቦቴዎች እንደሚያስፈልጉ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹17ቱን አግኝተን በእነዚሁ ቦቴዎች እያከፋፈልን ነው፡፡ የጠየቅናቸው የውኃ ቦቴዎች ከመጡ የውኃ ሥርጭቱ መጠን ይጨምራል፤›› ይላሉ፡፡

በምዕራብ ሐረርጌ ሚኤሶ ወረዳ ሪፖርተር ያገኛቸው አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች፣ እንዲሁም በምሥራቅ ሐረርጌ በድርቅ የተጎዱ ነዋሪዎች እንደሚናገሩት የሚደረግላቸው ዕርዳታ በቂ ያለመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ጨርሶ ዕርዳታ እየተሰጣቸው ያለመሆኑን ነው፡፡ የሚሰጣቸው ዕርዳታ ባለመኖሩም አንዳንዶቹ ወደ ጂቡቲና ወደተለያዩ አካባቢዎች ለመሰደድ መገደዳቸውን ይናገራሉ፡፡

እንደነ አቶ ዓሊ ኢንድሪስ ያሉት ደግሞ ከአዲስ አበባ – ጂቡቲ በተዘረጋው የባቡር ፕሮጀክት ላይ በቀን ሠራተኝነት ተቀጥረው በቀን 30 ብር እየተከፈላቸው ሕይወታቸውን ይመራሉ፡፡ ከዚህ ሲብስም በደህናው ጊዜ ያደለቧቸውን ከብቶች እየሸጡ ነው፡፡

በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎችም ከብቶቻቸው በድርቁ ምክንያት ስለተጎዱና ከችግር ለማምለጥ ለመሸጥ ወደ ገበያ ሲያወጧቸው ዋጋ እየወደቀባቸው መቸገራቸውን፣ ሲብስም ቀድሞ እስከ 20 ሺሕ ብር ይሸጡ የነበሩትን ከብት ከአምስት ሺሕ ብር ባልበለጠ ዋጋ ለመሸጥ መገደዳቸውን ይናገራሉ፡፡

በዚህ ወረዳ ከ77 ሺሕ በላይ ከብቶች አስቸኳይ የመኖ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ቢገልጹም፣ እስካሁን ግን ምንም ዓይነት ምላሽ እንዳልተሰጣቸው የወረዳው የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጣሂር ፊኒኖ ተናግረዋል፡፡ መንግሥት በቶሎ መኖውን ካላቀረበላቸውም በከብቶቹ ላይ የሚደርሰው ጉዳት የከፋ እንደሚሆን ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡ 

አቶ አብደላ መሐመድ የሚኤሶ ወረዳ ነዋሪ ናቸው፡፡ በአካባቢያቸው ያለው ድርቅ የከፋ እንደሆነና በአጭር ጊዜ ውስጥ ዕርዳታ ካላገኙም ችግር ውስጥ የሚወድቁ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ችግሩ ለከብቶቻቸው ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡ እስካሁን በ2007 የምርት ዘመን ፍሬ ያላፈራውን የበቆሎና የማሽላ አገዳ እየመገቡ ያቆዩዋቸው ቢሆንም፣ ከብቶቻቸው አሁን ምንም መኖ የላቸውም፡፡

አቶ አብደላ ያሏቸውን ከብቶች ከሚኖሩበት መንደር ውኃ ወዳለበት አካባቢ ማምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ በ2007 የምርት ዘመን የዘሩት በቆሎና ማሽላ ሙሉ በሙሉ በመጥፋቱ፣ በእጃቸው የቀሩትን ከብቶች በአነስተኛ ትንሽ ኩሬ ውኃ እያጠጡ ከኩሬ ዳር ማደርና መዋል ከጀመሩ ሦስት ቀናት አልፏቸዋል፡፡

ይህችም ኩሬ ብትሆን ከአንድ ሳምንት በላይ የሚቆይ ውኃ የሌላት መሆኑን የገለጹት አቶ አብደላ፣ ሦስት ልጆቻቸውን ጥለው እሳቸው ከብቶቻቸውን ለማዳን ሲወስኑ ከከብቶቻቸው ሦስቱን ሸጠው ለቀለብ የሚሆን ገንዘብ ለቤተሰቦቻቸው በመተው ነው፡፡ 

እንደ አቶ አብደላ ገለጻ እስካሁን አምስት ከብቶቻቸውን አርደዋል፡፡ ከሚሞቱ ብለው የወሰዱት ይህ ዕርምጃ በቀሪዎቹ ከብቶቻቸው ላይ እንዳይደርስም የቻሉትን ያህል ውኃ ወዳለበት መጓዝ ግዴታቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በሁሉም ወረዳዎች ትልቁ ችግር ውኃ ሲሆን፣ በአንዳንዶቹ አካባቢዎች ሰዎችም ሆኑ ከብቶች ውኃ ለማግኘት በእጅጉ ተቸግረዋል፡፡ ድርቁ ያስከተለው ጉዳት ከዚህም በኋላ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

በዚህችው አነስተኛ ኩሬ ዳርቻ ሪፖርተር ያገኛቸው ሌላው አርሶ አደር እየደረሰ ያለውን ጉዳት በማየት ዕርዳታ ያልተደረገላቸው መሆኑን በሐዘኔታ ይገልጻሉ፡፡ ‹‹በተደጋጋሚ ወደ አካባቢው የሚመጡት የመንግሥት ኃላፊዎች ችግሩን ሰምተው ይሄዳሉ እንጂ ዕርዳታ እያደረጉልን አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ 

‹‹የልጆቻችን ሰውነት ቀንሷል፡፡ ከትምህርት ቤትም እየቀሩብን ነው፤›› የሚሉት እኚሁ አርሶ አደር፣ ለውኃ ችግር መፍትሔ ካልመጣ አካባቢውን ለቆ መሄድ ግድ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

‹‹ይህ የፈጣሪ ጉዳይ ስለሆነ ከዘራነው አላገኘንም፡፡ ከፈጣሪ በታች ያለን መንግሥት ነውና ዕርዱን ብለናል፤›› ያሉት አርሶ አደሩ፣ አሁንም ይህ ጥያቄያቸው ምላሽ እንዲያገኝ ይማፀናሉ፡፡ 

በሚኤሶ ወረዳ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ዕርዳታ እየተሰጣቸው አለመሆኑን ቢገልጹም፣ የሚኤሶ ወረዳና የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ኃላፊዎች ዕርዳታ እየተሰጠ ነው ይላሉ፡፡

የሚኤሶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ከማል፣ ‹‹በአጋጣሚ ያነጋገርናቸው በወረዳው ሊረዱ ይገባል ተብለው ከተያዙት ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ፤›› በማለት የአልተረዳንም ጥያቄ ለሚያነሱት አርሶ አደሮች ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ የተሻሉ ናቸው የተባሉትም ዕርዳታ የሚሹ እየሆኑ በመምጣታቸው፣ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ዕርዳታ ሊሰጣቸው ይገባል ከሚባሉት ውስጥ ይካተታሉ ብለዋል፡፡

ከዕርዳታ ሥርጭት ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስተያየቶችም ይሰነዘራሉ፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች በቂ ዕርዳታ እየተሰጠ አለመሆኑን ሲገልጹም ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ያላካተተ አሠራር እንዳለ ያመለክታሉ፡፡

የዕርዳታ አሰጣጡ ፍትሐዊ ነው ብለው የሚያምኑ እንዳሉም የሚናገሩ አርሶ አደሮች አሉ፡፡ የሁለቱ ዞኖች አስተዳዳሪዎች ግን የዕርዳታ አሰጣጡ በግልጽነት የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት፡፡ በዚህ ዕርዳታ አሰጣጥ ላይ ችግር ቢፈጠር ወዲያው ዕርምጃ የሚወሰድበት አሠራር ተዘርግቷል ይላሉ፡፡ 

የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን አስተዳደር እንደገለጸው ለቁጥጥር ከአስተዳደር፣ ከዓቃቤ ሕግና ከሕዝብ አደረጃጀት የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡ 

በሚኤሶ ወረዳ ዲርባ ቀበሌ ደግሞ ከዕርዳታ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የቀበሌው የሥራ ኃላፊና የጎጥ አመራሮች እንዲታሰሩ መደረጉን፣ የወረዳው አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡

የቀበሌው ሊቀመንበርና የጎጥ አመራሮች የታሰሩት በዕርዳታ ዕደላው ወቅት የአንዳንዱን ቤተሰብ ቁጥር በማሳነሳቸው፣ የአንዳንዶቹን ደግሞ ቁጥራቸውን በመጨመር የተሻለ መጠን ያለው ዕርዳታ እንዲሰጣቸው በማድረጋቸው ነው፡፡ 

ወረዳው ይህንን መረጃ በሕዝብ ጥቆማ ካገኘ በኋላ ባደረገው ማጣራት፣ ድርጊቱ መፈጸሙ በመረጋጡ ዕርምጃው ለመውሰድ መቻሉን ነው የተናገሩት፡፡

በሁለቱም ዞኖች ያለው የከፋ ድርቅ በሰው ሕይወት ላይ ሞት አላስከተለም ተብሏል፡፡ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ ብቻ እስካሁን ከ2,200 በላይ ከብቶች መሞታቸውን የወረዳው የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገልጸዋል፡፡

ድርቁ ባስከተለው ችግር የተሰደዱ አሉ የሚባለውን ያስተባበሉት የወረዳው አስተዳዳሪ፣ በዚህ አካባቢ ያለ ነዋሪ ወደ ጂቡቲ መሄድና መምጣት የተለመደ በመሆኑ በድርቁ የተሰደዱ ናቸው ሊባል እንደማይችል ገልጸዋል፡፡ ‹‹ይሁን እንጂ እንዳይሰደዱ በቂ ዕርዳታ እየተሰጣቸው ነው፡፡ ነገር ግን አንፈልግም ብለው የሚሄዱ አሉ፤›› ብለዋል፡፡ በወረዳቸው ደረጃ የበለጠ ዕርዳታ የሚያስፈልገው ተረጂ ቁጥር ከአንድ ወር በኋላ ስለሚጨምር ለዚህ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን አስተዳዳሪ አሁን ያለውን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ‹‹ድርቁ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን በሁለቱም ዞኖች መንግሥት ከሚያደርገው ጥረት ባለፈ፣ የመንግሥት ሠራተኞች ከደመወዛቸው ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ በፈቃዳቸው አዋጥተው ለድርቁ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መጠባበቂያ ፈንድ ውስጥ ተይዟል፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ድርቁ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን መንግሥት ተከታታይ ዕርዳታዎችን እንደሚያደርግ በእርግጠኝነት አስታውቀዋል፡፡

 

 

ለመጀመርያ ጊዜ ለሳቅ ዉድድር ጀርመን ሀገር እንደመጣ የሚናገረዉ ለዓለም የሳቅ ንጉሱ ለበላቸዉ ግርማ፤ ሳቅ ፍቅር ነዉ፤ ሳቅ መላ አካላትን የሚያንቀሳቅስ ስፖርት ነዉ፤ ሳቅ ሰላምን መፍጠርያ መሣርያ ነዉ፤ ሳቅ ጤና ነዉ፤ ሳቅ ደስታ ነዉ፤ ሳቅ ሕይወት ነዉ፤ ሳቅ የሰላም መሣርያ ነዉ፤ ሳቅ የፍቅር መሣርያ ነዉ፤ ሳቅ ወጣት የሚያደርግ ነዉ።

ድምፃችን ይሰማ ድል ‹‹እምቢ!›› ማለት መቻል ነው! ድል ለጭቆና እጅ አለመስጠት ነው! የአላህ (ሱ.ወ) የምንዳ ሚዛን ጥረትን እንጂ መዳረሻን ያማከለ አይደለም!!! የመንግስትን ረጃጅም እጆች በሀይማኖታዊ ጉዳዮቻችን ጣልቃ ከመግባት ተቆጥበው አያውቁም ነበር፡፡ በሀምሌ 2003 እነዚህ ጣልቃ ገብነቶች የእምነት አስተሳሰብን ወደመምረጥና ወደማጥመቅ …

ድል ‹‹እምቢ!›› ማለት መቻል ነው! ድል ለጭቆና እጅ አለመስጠት ነው! ድምፃችን ይሰማ Read more »

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከተማዋ ውጥረት ነግሶ መሰንበቱን የገለጸው ወኪላችን፣ መንስኤውም አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል ተደብድቦና በጥይት ተመትቶ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን ተከትሎ ነው። ውጥረቱን ተከትሎ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ትራፊክ ዋና አዛዥ ኮማንደር አብዲ ኢብራሂም የተሰወሩ ሲሆን፣ በመከላከያ ሰራዊት አባላት በጥብቅ እየተፈለጉ ነው። ጉዳዩን ለማጣራት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳና የፌደራል ፖሊስ …

Minilik Salsawi – በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዳይሆን የተቃውሞ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ከነበሩ የኦሮሚያ ተወላጅ ተማሪዎች መካከል የፊዴራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ወደ ዪኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በመግባት ሶስት ተማሪዎችን መግደላቸውንና ብዙዎችን ማቁሰላቸው እየተሰማ ነው ።

በኢህአዴግ የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ በድርቅና በድህነት ምክንያት በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው ከፍተኛ ችግር መጠን ሊድበሰበስ አይገባም!! (ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ) ሀገራችንን ላለፉት 25 ዓመታት ሲገዛ የቆየው ኢህአዴግ ባለ2 አሀዝ ፈጣን እድገት እያስመዘገብኩ ሀገራችን በምግብ ራሷን እንዲትችል፣ ከስንዴ …

በኢህአዴግ የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ በድርቅና በድህነት ምክንያት በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው ከፍተኛ ችግር መጠን ሊድበሰበስ አይገባም!! – መድረክ Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ ባል ድፍን አዲስ አበባ ጭለማ ውጧታል። ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ የሃይል መቆራረጡ እየተባባሰ የመጣ ሲሆን የመንግስት ሹማምንት አንዴ ችግሩ የመልካም አስተዳደር ብልሽት ውጤት ነው፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የመስመር እርጅና ነው እያሉ ፣ እርስበርሱ የተምታታ መግለጫ ከመስጠት ባለፈ ሁነኛ መፍትሄ ሳያበጁለት ቀርተዋል። ችግሩ …

ፖሊስ መምህር ግርማን በነፍስ ግድያ በመጠርጠሩ በዋስ አልተፈቱም

በተጠረጠሩበት የማታለልና ሐሰተኛ ሰነድ መጠቀም ወንጀሎች የ50 ሺሕ ብርና የ40 ሺሕ ብር ዋስትና የተፈቀደላቸው [መምህር] ግርማ ወንድሙን፣ ፖሊስ በነፍስ ግድያ እንደሚጠረጥራቸው በማመልከቱ አለመፈታታቸው ታወቀ፡፡

ፖሊስ [መምህር] ግርማ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ሳያገኙ ፈቃድ እንደተሰጣቸው በማስመሰል ሐሰተኛ ሰነድ እንደተጠቀሙ በመግለጽ፣ ሰነዱን እያስመረመረ መሆኑን ገልጾ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ኅዳር 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ ተጠርጣሪው በ40 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ፖሊስ እሳቸውን በነፍስ ግድያ እንደሚጠረጥራቸው በመግለጽ ለፍርድ ቤቱ ማመልከቻ በማቅረቡ፣ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ሰነዶችን እንዲያቀርብ ለኅዳር 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ተጠርጣሪው  ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ የሚኖሩ ግለሰብን ቤት በማሸጥና ገንዘቡንም ‹‹ይፀለይበት›› በማለት መውሰዳቸውን በሚመለከት ፖሊስ ካቀረበባቸው ክስ፣ በ50 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ነገር ግን በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ቅር የተሰኘው ፖሊስ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያለ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ኅዳር 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የፖሊስን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ የሥር ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አፅድቆ በ50 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ አዟል፡፡ ነገር ግን ተጠርጣሪው በነፍስ ግድያ በመጠርጠራቸው ከእስር አልተፈቱም፡፡ 

ይህ በዚህ እንዳለ በሪፖርተር ቅጽ 21 ቁጥር 1622 ዕትም፣ ‹‹በ50 ሺሕ ብር ዋስ ይፈቱ የተባሉት [መምህር] ግርማ ይግባኝ ተጠየቀባቸው›› በሚለው ዜና ውስጥ ‹‹ከቤተ ክህነት እንደተሰጣቸው የገለጹት ሰነድ በፎረንሲክ ተመርምሮ ሐሰተኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል፤›› የሚለው አገላለጽ በስህተት ስለሆነ፣ ‹‹ሰነዱን ለምርመራ ለፎረንሲክ ሰጥቶ እየተጠባበቀ መሆኑን አስረድቷል፤›› ተብሎ ተስተካክሎ እንዲነበብ አንባቢያንን ከይቅርታ ጋር እንጠይቃለን፡፡

 

IN MEMORY of Mr. Belay Wendafrash From Voice of Ethiopian youth በጀርመን ሃገር እና በመላው አውሮፓ ኢትዮጵያውያንን በማሰባሰብ ለታፈኑትና ድምጽ አልባ ለሆኑት ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ሲሟገት የኖረው ወንድማችን አቶ በላይ ወንዳፍራሽ ቅዳሜ ኖቬምበር 28፣ በፍራንክፈርት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት …

በኢትዮጵያ ፍትሕ፣ እኩልነትና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ሲታገል የኖረው አቶ በላይ ወንዳፍራሽ (እንደዜጋ/ሰላምሁን PalTalk name)በጀርመን ሃገር አረፈ። Read more »

Amdom Gebreslasie “የእርዳታ እህሉ ወደ ተረጂው ህዝብ ልናደርሰው ኣልቻልንም” ወይዘሮ ያለም ፀጋይ የምስራቃዊ ዞን ዋና ኣስተዳዳሪና የማእከላይ ኮሚቴ ኣባል። ወይዘሮ ያለም ፀጋይ ያፍረጠረጠችው ሓቅ ” የእርዳታ እህሉ ወደ ተራበው ህዝብ ልናደርሰው ኣልቻልንም ከዚህ የተነሳ ድርቁ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል። …

በትግራይ ለተከሰተው ረሃብ የመጣው እርዳታ ለተጎጂዎች ኣይደርስም ሲሉ ኣንድ ባለስልጣን ተናገሩ። Read more »

– በአምቦ አመጹ አልበረደም፤ የወያኔ አድማ በታኝ ፖሊስ በውድቅት ሌሊት አምቦ ገባ፤ – በማዕከላዊ ምርመራ በየቀኑ በምርመራ ጉዳት የሚደርስባቸው ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተባለ፤ – ሁለተኛ የአባይ ግድብ ግንባታ ሥራ እንዲቆም ግብጽ በይፋ ወያኔን ትጠይቃለች ተባለ፤ – የሮማው ጳጳስ፣ ኬኒያውያን …

በአምቦ አመጹ አልበረደም፤ የወያኔ አድማ በታኝ ፖሊስ በውድቅት ሌሊት አምቦ ገባ:: Read more »

ኤጀንሲው የአቶ በረከት ስምዖንን መኖሪያ ቤት ለባለቤቱ እንዲያስረክብ ታዘዘ

ቤቱ ለባለቤቱ እንዲመለስ ከተወሰነ 17 ዓመታት አልፎታል

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 17 ቀበሌ 19 ውስጥ የሚገኘውን፣ የቤት ቁጥር 119 የሆነውንና የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ በረከት ስምዖን እየኖሩበት የሚገኘውን መኖሪያ ቤት፣ ታኅሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዲያስረክብ ታዘዘ፡፡ 

 

ኤጀንሲው ቤቱን ለባለ ንብረቱ አቶ መሐሪ ተወልደ ብርሃን እንዲያስረክብ፣ የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ከ17 ዓመታት በፊት ሚያዝያ 28 ቀን 1990 ዓ.ም. ትዕዛዝ ያስተላለፈ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን አለማስረከቡ ተጠቁሟል፡፡

የቤቱ ባለቤት አቶ መሐሪ ጥቅምት 5 ቀን 1988 ዓ.ም. ለፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ባቀረቡት አቤቱታ እንዳስታወቁት፣ ቤቱ የተወረሰው ከአዋጅ ውጪ በመሆኑ እንዲመለስላቸው መጠየቃቸውን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡ ኤጀንሲውም ባደረገው ምርመራ የአመልካቹ ቤት በአዋጅ ቁጥር 110/87 አንቀጽ 2(3) መሠረት ከአዋጅ ውጪ የተወረሰ መሆኑን እንዳረጋገጠ ጠቁሞ፣ ኤጀንሲው ለቤቱ ማሠሪያ የዋለ የባንክ ዕዳ ካለ ተሳስቦ ለባንክ እንዲከፍልና ምንም ዓይነት የዕዳ ጥያቄ ሳያቀርብ ቤቱን ለአቶ መሐሪ እንዲያስረክብ አዞት እንደነበር ሰነዱ ያሳያል፡፡ ነገር ግን ቤቱ ተጨማሪ ማጣራት እንደሚያስፈልገው ተገልጾ፣ ከሰኔ 12 ቀን 1990 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ ታግዶ የቆየ ቢሆንም፣ ቤቱ እንዲመለስላቸው የተሰጠው ውሳኔ ትክክል መሆኑ ስለተረጋገጠ፣ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ኤጀንሲ ቦርድ እግዱ እንዲነሳ ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም. በመወሰኑ፣ ቤቶች ኤጀንሲ ቤቱን ለአቶ መሐሪ እንዲያስረክብ በድጋሚ ማዘዙን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡

ቤቶች ኤጀንሲ እንዲያስፈጽም ለተላለፈለት ትዕዛዝ በሰጠው ምላሽ፣ ‹‹ቤቱ ለባለቤቱ እንዲመለስ ውሳኔ ያስተላለፈው ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ነው፡፡ ውሳኔው የሚፈጸመው በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት በውክልና ነው፡፡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለማስፈጸም ሥልጣን የለውም፤›› በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን እንዳብራራው፣ ኤጀንሲው ፍርድ ቤቱ ሥልጣን እንደሌለው ቢገልጽም ማስረጃ አላቀረበም፡፡ ኤጀንሲው ጊዜ እንደሚያስፈልገው ቢገልጽም፣ እንዲያስፈጽም ከስምንት ወራት በላይ ስለተሰጠው በቂ ጊዜ እንደሆነና በቤቱ ውስጥ የሚኖሩት ከፍተኛ ባለሥልጣን ናቸው የሚለው ተቀባይነት እንደሌለው በመዘርዘር፣ ቀደም ብሎ ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ፣ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ አቶ በረከት ስምዖን የሚኖሩበት መኖሪያ ቤት ለባለቤቱ አቶ መሐሪ ተወልደ ብርሃን እንዲያስረክብ፣ የቤቶች ኤጀንሲ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ኅዳር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ትዕዛዝ ተላልፎለታል፡፡     

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ ለከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ፣ በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ባለሥልጣን የሚመጥን ቤት ስላልተገኘ ለግ

‹‹ሌብነት የለመደ በአንድ ሳምንት ውስጥ ቴሌቪዥን ላይ ወጥተን ስለጮህን እጁን ይሰበስባል ማለት አይደለም›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሐሙስ ኅዳር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሪፖርተር ጋዜጣ ዋና አዘጋጆች ዘካሪያስ ስንታየሁና አሥራት ስዩም ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ቆይታ አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ዓይነት ቆይታ ከግል የኅትመት ሚዲያ ጋር ሲያደርጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸውም ወቅታዊ በሆኑ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በቅርቡ ከተከሰተው ድርቅ አንስቶ ስለመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ እንዲሁም በኤርትራ ጉዳይ ላይ ያደረጉት ልዩ ቃለ ምልልስ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡  

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ኅዳር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ብሔር ተኮርና ልማትን መሠረት ያደረጉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በኢትዮጵያ እየተባባሱ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡ የአገር ውስጥና የውጭ የመገናኛ ብዙኃን አባላት፣ የተለያዩ ኤምባሲ ተወካዮችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት …

ሰመጉ ብሔር ተኮርና ልማትን መሠረት ያደረጉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በኢትዮጵያ እየተባባሱ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡ Read more »

አቶ በረከት ስምኦን ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የነጠቁትን መኖሪያ ቤት እንዲመልሱ ተጠየቁ:: -ቤቱ ለባለቤቱ እንዲመለስ ከተወሰነ 17 ዓመታት አልፎታል::ለ17 አመት አቶ በረከት ስምኦንን የሚመጥን መኖሪያ ቤት አልተገኘም ማለት በሕዝብ ላይ እንደ ማሾፍ ነው:: የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 17 …

አቶ በረከት ስምኦን ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የነጠቁትን መኖሪያ ቤት እንዲመልሱ ተጠየቁ:: ለባለቤቱ እንዲመለስ ከተወሰነ 17 ዓመታት አልፎታል Read more »

ማስተር ፕላኑን መቃወማቸው የገበሬው መፈናቀል አሳስቧቸው ነዉን ? – ግርማ ካሳ ሰሞኑን በምእራብ ኦሮሚያ ተማሪዎች ተቃዉሞ አሰምተውል። የአሜሪክ ድምጽ በዚህ ዙሪያ ዘገባ አጠናክሯል። አንዳንድ ወገኖች ተማሪዎች ተቃዉሟቸውን ያሰሙት በዋናነት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም እንደሆነ ይናገራሉ። “የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን …

የኦሮሞ ተማሪዎች ማስተር ፕላኑን መቃወማቸው የገበሬው መፈናቀል አሳስቧቸው ነዉን ? – ግርማ ካሳ Read more »

ቀኑ ዓርብ ሚያዝያ 16/2001 ዓ.ም ነበር ። ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌድራል ልብስ የለበሱ ፖሊሶች መሳሪያቸውን አቀባብለው ወደቤት በመግባት <<ስልካችሁን አጥፉ ወደማንም እንዳትደውሉ >> በማለት ለወ/ሮ እማዋይሽ ቤተሰቦች ትእዛዝ ይሰጣሉ ። ቀጥሎም ቤቱን ለመፈተሽ የተፈቀደላቸውን ወረቀት እያሳዩ << ቤት ለመፈተሽ …

ያልተዘመረላቸው ጀግና ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ! Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በሓገራችን የተከሰተውን ድርቅ እና ያስከተለውን ረሃብ ለመቋቋም በሚደረጉ ጥረቶች በአቅርቦት እና በፍላጎቶች መካከል እጅግ ሰፊ ልዩነት ከመኖሩም በላይ ግልጽነት የጎደለውና በፖለቲካ ላይ የተመሰረተ አድልዎ እንዲሁም ከፕሮፓጋንዳ ውጪ ፈጣን እና የተቀናጀ ስራ በተግባር ስለማይታይ በድርቅ የተጠቁ …

በብድር እና እርዳታ የተገኙ የውጪ ምንዛሬዎች የት እንደገቡ አይታወቅም::ረሃቡ የኢኮኖሚ ቀውስ ፈጥሯል::‪ (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

      Written by  ዮሐንስ ሰ.  • ‘ግድብ-መስኖ አትስሩ’ የሚል ዘመቻ፣ እና ተመፅዋች ረሃብተኛ 1. ከሃያ የዓለማችን ድሃ አገራት አንዷ! በየዓመቱ 10 ሚ. ችግረኞች፣ እርዳታና ድጎማ ይቀበላሉ። ዘንድሮ ግን፣ የተረጂዎቹ ቁጥር ወደ 15 ሚሊዮን ጨምሯል። 2. አስቸኳይና የሚያዛልቁ መፍትሄዎች! …

የረሃብ አደጋውን፣ ‘ዱብዕዳ’ ወይም ‘ጊዜያዊ’ አናስመስለው! Read more »

አንጋፋው ተዋናይ አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም በሽርክና የሚያሳትመውን የመረጃና የስልክ አድራሻ ማውጫ ዳይሬክተሪ፤ አመሳስለው በማዘጋጀት ለገበያ አቅርበውብኛል ባላቸው አካላት ክስ መስርቷል “እንደ ልጄ የማየውን ሥራዬን ነው የወሰዱብኝ” ብሏል – አርቲስቱ፡፡ በአቃቤ ህግ የቀረበው የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው፤ ዌብ ፕላኔት አይቲ ሶሉሽን እና …

አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ከሳሽም ምስክርም ሆኖ ፍ/ቤት ቀረበ Read more »

በየሳምንቱ ረቡዕ ምሽት በኢቢኤስ ቴሌቭዥን የሚቀርበው የ“ሞጋቾቹ” ተከታታይ ድራማ ደራሲ በሆነው ኃይሉ ፀጋዬና በፕሮዱዩሰሯ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተለያዩ ሲሆን ድራማው በታዋቂው ፀሐፌ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ ይቀጥላል ተብሏል፡፡ የድራማው ደራሲ አንጋፋው የተውኔት ፀሐፊ ኃይሉ ፀጋዬ ለአዲስ አድማስ እንደተናገረው፤ ከዚህ ቀደም በተለያዩ …

የ“ሞጋቾቹ” ድራማ ደራሲና ፕሮዱዩሰሯ ባለመግባባት ተለያዩ Read more »

Written by  ዮሐንስ ሰ.=== በኢትዮጵያ የረሃብ አደጋ ላይ ያተኮረው የቢቢሲ ዘገባ፣ ይሄውና ብዙዎችን እያወዛገበ ሁለተኛ ሳምንቱን ይዟል። የጋዜጠኛውን ዘገባ፣ በአድናቆት የሚያሞግሱ በርካታ ሰዎች፣ ‘መንግስት፣ የረሃብ አደጋውን ችላ ብሏል፤ መረጃም ደብቋል’ በማለት መራራ ትችት አውርደውበታል። መንግስት በበኩሉ፣ በቢቢሲ ዘገባ ተቆጥቶ፣ በየአቅጣጫው …

ድርቅ ባይኖርም በየቀኑ፣ከ500 በላይ ሕፃናት ይሞታሉ; የኢትዮጵያ ችግር፣ ከቢቢሲ ዘገባም ይብሳል! Read more »

በአባይ ወንዝ አጠቃቀምና በህዳሴ ግድብ ግንባታ ሳቢያ ለ5 ዓመት እየከረረና እየረገበ የዘለቀው የኢትዮጵያና የግብፅ ግንኙነት፤ ከሰሞኑ ትኩሳት አገርሽቶበታል፡፡ የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲዘገይ ማድረግ እንችላለን በማለት እንደተናገሩ ሰኞ እለት የዘገቡ አልጀዚራና ምስር ጆርናል፤ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …

በአባይ ወንዝ አጠቃቀምና በህዳሴ ግድብ ግንባታ ሳቢያ ለ5 ዓመት እየከረረና እየረገበ የዘለቀው የኢትዮጵያና የግብፅ ግንኙነት፤ ከሰሞኑ ትኩሳት አገርሽቶበታል፡፡ Read more »