የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ በመላው ሃገሪቷ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።

Minilik Salsawi's photo.

የቡራዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፌደራል ፖሊሶች የተከበቡ ሲሆን ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ::በሃሮማያ ዩንቨርስቲ በር ላይ አንድ ወጣት ተማሪ ተገሏል::የሃሮማያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ በአከባቢው በዳሞታ ባቴ ፊንቂልጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል::ይህን ተከቶ ከሆርሶ ወታደራዊ ካምፕ በርካታ ወታደሮችን የጫኑ ካምቢዮኖች ወደ ሃሮማያ ከተማ ገብተዋል::በምእራብ ሸዋ ጮቤ ከተማ ተቃውሞ ተነስቷል::በወለጋ አርጆ በሱሉልታ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ በመላው ሃገሪቷ እንደቀጠለ ነው። በአዲስ አበባ እና በ Mekelle ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎች የዝምታ ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ::

ቀይ ሽብር በኢትዮጵያ ታሪክ ሆኗል ብሎ የሚያስብ ካለ ተሳስቷል። ዛሬ በመላው ኦሮሚያ ክልል ቀይ ሽብር በመፋፋም ላይ ነው። የኦሮሞ ወጣቶች በሰላማዊ ሰልፍ በመሳተፋቸው ብቻ በአደባባይና በጠራራ ፀሀይ የጥይት እራት እየሆኑ ነው። የኦሮሞ ገበሬዎችን በልማት ስም ማፈናቀል አሁኑኑ ይቁም! የሚለው መፈክራችን አሁንም ደጋግሞ እየተሰማ ነው።

ዱግዳ ዳዋ አውራጃ በጅማ፣ አምቦ፣ ቡሌ ሆራና ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞዎች ሲያደረጉ፣ በብዙ ከተሞች ነዋሪዎችም ሰልፈኞችን ተቀላቅለዋል። በዛሬው እለት አንድ የ 9ኛ ክፍል ተማሪ በ ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ፊትለፊት የተገደለ ሲሆን፤ መንግሥት በሁሉም አካባቢዎች መደበኛ የመከላከያ ሰራዊት በማሰማራት ላይ ነው። በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቋሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ ስሙ ሰመራ ግቢ ተብሎ በሚጠራው ግቢ ክፍተኛ ብጥብጥ ተነሰቷ ልዩ ሀይሎች በጥብጡን ለማብረድ በግቢው አካባቢ ከበዋል ተማሪዎች በአሁኑ ስዓት ዲንጋይ መወርወር ጀምረዋል Minilik Salsawi

Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.

Minilik Salsawi የሃሮማያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ በአከባቢው በዳሞታ ባቴ ፊንቂልጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.

 

7 Comments on “የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ በመላው ሃገሪቷ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።”

  1. “ዘብሄረ ኦህዴድ”

    ከበደኖ የጠለቀ ከአፄው የከፋ ግዜ መቼውንም የማይረሣ ጠባሣ የኦሮሞ ህዝብ
    መሥዋእት እየከፈለ ይገኛል ግን ይህ ህብረት አትንኩኝ ባይነት ላጣነው ነፃነት የወያኔን
    መንግሥት በቀጣይ የምናሥወግድበት መንደርደሪያ እንደሚሆን አልጠራጠርም እንደኔ
    ኦህዴድ አሁን ነው ሠአቱ ጫካ የመግቢያው ግዜ ይህን ሥል በሀሠት ታገልን ሥትሉለት
    የነበረውን ወያኔ አሁን ነፃነታችሁን በአፈሙዝ ደፍኖ እርሥ በእርሥ ፊንፊኔ ዙሪያ ገለመሌ
    እያለ አማራ ነፍጠኛ ከመሬትህ አሥወጣ እያለ ህገወጥ የማባላት ሥልት በመከተል
    ከጥንት ተከባብረን ተዋልደን ያለነውን ሥርአት በዚህ ከፍተኛ የብሄር ክምችት ባለበት
    ክልል የራሡን የሣጣን ግዜ ለማራዘም እንዲሁም ኦሮሞ ህዝብ ከተነሣ ወያኔ
    እንደሚያበቃለት ጭምር ሥለሚያውቅም ይህን የማባላት የማናከሥ የብሄር ፌድራሊዝም
    ሥርአት እንደጭቃ ሾክ እየወጋን ይገኛል ክቡር የኦሮሞ ህዝብ ሆይ ወያኔን ለማሥወገድ
    እርሥ በእርሥ በመቀናጀት ተግባራዊነቱን እናሣይ።

    ለምሣሌ የብሄሩ ተወላጆች ከሚበዙበት የሥራ መሥክ አንፃር

    1 ግብርና
    2 ምድር ጦር
    3 ፖሊሥ
    4 ትራፊክ ፖሊሥ
    5 ቴሌኮም
    7 ሜቴክ
    8 ገቢዎች
    9 ውሀ ሥራዎች
    10 አዋሽ ባንክ
    11 ኦሮሚያ ባንክ

    ታድያ ይህ ሁሉ ሀይል እያለን እንዴት 10 የማይሞሉ የህወሀት አባሎችን መደምሠሥ
    አቃተን?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*