የወያኔ ሰርጎ ገብ ካድሬዎች የኦሮሞ ተማሪዎችን ተቃውሞ ተገን አድርገው በአመያ የአማሮችን ቤት አቃጥለዋል:: ማንምም ለወገኑ የሚቆረቆር ሊያረጋግጠዉ የሚችል ሃቅ:: በአመያ ወረዳ በሮሙረያ ቀበሌ ቤታቸው ከተቃጠለባቸው አማራዎች መካከል 1 አባበይ ታዬ 2 ጌታቸው ክር 3 አስጨናቂ ታዬ 4 ጌታቸው መንግስት 5 …

የወያኔ ሰርጎ ገብ ካድሬዎች የኦሮሞ ተማሪዎችን ተቃውሞ ተገን አድርገው በአመያ የአማሮችን ቤት አቃጥለዋል:: Read more »

ሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን እሁድ ታህሳስ …

ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ ማስተር ፕላኑ እና ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ያቀደውን መሬቱ እንዳይሰጥ ለመቃወም በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ:: Read more »

ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃረር ከተማ ህዝቡ የመንግስትን እርምጃ ሙሉ በሙሉ አውግዟል። በሌላ በኩል መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተከትሎ እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም በጋራ ሰልፍ ጠርተዋል። የሰልፉ አላማ በዋነኛነት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ መንግስት …

የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ባህርዳር ላይ እስረኞች ተቃውሞ አሰሙ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎BahrDar‬ ‪#‎Ethiopiaprotests‬ ‪#‎NegereEthiopia‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ባህርዳር ከተማ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ከትናንት ታህሳስ 9/2008 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ቤቱ የሚዘጋጀውን ምግብ እንደማይበሉ ማሳወቃቸውንና ጩኸት በማሰማት ተቃውሟቸውን መግለፃቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች …

ባህርዳር ከተማ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ተቃውሞ አሰሙ Read more »

የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ከዚህች ከኣዲስ ኣበባዋ የመሬት ነጠቃ ጥያቄ በጅጉ ገዝፎ የሄደ ነው። ከፍተኛው ጥያቄ የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄ ነው። በመጀመሪያ ህወሃት ይህን ዘረኛ ፖለቲካውን ተሸክሞ ኣዲስ ኣበባ ከገባ በሁዋላ በተለይ ኦሮሞንና ኣማራን ጸጥ ኣድርጎ ለመግዛት የተጠቀመው ዘዴ በነዚህ ክልሎች ውስጥ ከታች እስከ ላይ ያሉትን ባለ ስልጣናት በኣልተማሩና የማስተዳደር ችሎታ በሌላቸው ነገር ግን ታዛዥ ብቻ በሆኑ […]

የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ብዙ ፈተናዎችን ያሳለፈች ወጣት ናት። ከልጅነቷ አንስቶ የቤት ሰራተኛ ሆና አገልግላለች ፤ኃላም የጎዳና ተዳዳሪ ነበረች። እዛው ጎዳና ላይም ነፍሰ ጡር እና እመጫት ሊስትሮም ሆና ሰርታለች።

ሰላማዊ ተቃውሞ፣ ከፖሊስ ጋር ግጭት፣ ከዚያ ረብሻና እስር፣ ቃጠሎና ግድያ… ከዚህ አሳዛኝ የጥፋት ሰንሰለት መላቀቅ ያቃተን፤ መውጫ የሌለው አዙሪት የሆነብን ለምንድነው? እንዲህ አይነት ቀውስ በተፈጠረ ቁጥር፤ መንግስት እየደጋገመ የሚናገረው ነገር አለ። ቅሬታዎችን ማቅረብ፣ ተቃውሞን በሰላም መግለፅ፣ ተፈጥሯዊ መብት ነው ይላል …

“የተረገመ አዙሪት” – አገሬውን በአፈናና በጉልበት ዝም ለማሰኘት መሯሯጥ Read more »

የትግራይ ህዝብ ውርደት = Amdom Gebreslasie ************ በኣሁኑ ሰዓት በድርቅ ምክንያት 1.2 ሚልዮን ህዝብ ኣስቸኳይ እርዳታ የሚጠባበቅ ሲሆን 1.5 ደግሞ በሴፍትኔት እርዳታ( ሰርቶ ለምግብ) በድምሩ 2.7 ሚልዮን ህዝብ ጥገኛ ሆኖ እንደሚገኝ የትግራይ ክልል ኣደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፅህፈት ቤት ሰነዶች ይገልፃሉ። …

የትግራይ ህዝብ ውርደት :- 1.2 ሚ. ህዝብ ኣስቸኳይ እርዳታ የሚጠበቅ -1.5ሚ. ሰርቶ ለምግብ በድምሩ 2.7 ሚልዮን ህዝብ ጥገኛ Read more »

    ባለፈው መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ታመው ተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል ከገቡትና ለ10 ቀናት በህክምና ላይ ቆይተው ጥቅምት 6 ቀን ህይወታቸው ካለፈው ወይዘሮ አየለች ደግፌ ጆሮ ላይ የጠፋው 5 ግራም የጆሮ ወርቅ፤ ሆስፒታሉንና የሟች ቤተሰብን እያወዛገበ ነው፡፡ የሆስፒታሉ የፅኑ ህሙማን ክፍል ኃላፊ ሲስተር አስናቀች ተጠይቀው ሲመልሱ፤ “ወርቁ ከአስከሬኑ ጋር አብሮ የተገነዘ በመሆኑ መቃብሩ ይቆፈርልኝ” ማለታቸውን የሟች ልጅ አቶ ሰለሞን ጌታቸው ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
እናቴን “ለመጨረሻ ጊዜ ፅኑ ህሙማን ክፍል ገብተን ስናያት ወርቁ ጆሮዋ ላይ መሆኑን ተመልክቻለሁ” ያለው አቶ ሰለሞን፤ “ከሞተች በኋላ ወርቁን ስጠይቅ ከአስከሬኑ ጋር ተገንዟል ተባልኩኝ፤ እውነቱ እንዲወጣ ስለምፈልግ መቃብሩ እንዲቆፈር ብፈቅድም እስካሁን ምንም ምላሽ አላገኘሁም” ብሏል፡፡
“ዛሬ ነገ እያሉኝ በመመላለስ ብዙ ተንከራተትኩ፤ እኔ ጉዳዬ ከወርቁ አይደለም፤ ነገር ግን መቃብሩ ተቆፍሮ እውነቱ እንዲወጣና ለሌሎችም ትምህርት እንዲሆን እፈልጋለሁ” ይላል አቶ ሰለሞን፡፡ ሆኖም ሥራዬንና ጊዜዬን ከማባከን በቀር እስካሁን አጥጋቢ ምላሽ ማግኘት አልቻልኩም ሲል አማርሯል የሟች ልጅ፡፡
የሆስፒታሉን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ስዩምን አነጋግሬ ነበር ያለው አቶ ሰለሞን፤ “ኃላፊዋ ወርቁን እንድትከፍል ወስነው ነበር፤ ነርሷ ዋጋውን ከጠየቀችኝና ከነገርኳት በኋላ ነው መቃብሩ ይቆፈር ያለችኝ” ብሏል፡፡ እኔ ከራሴ ጋር እየታገልኩም ቢሆን እውነት እንዲወጣ፣  ወጪውን ሸፍና ቁፋሮውን እንድታካሂድ ብፈቅድም ኃላፊዋ የተለያዩ ምክንያቶች እየፈጠረች ጊዜዬን እያባከነች ነው ያለው አቶ ሰለሞን፤ ሆስፒታሉ ለጉዳዩ እልባት የማይሰጠኝ ከሆነ ማስረጃዎቼን ይዤ ወደ ፍርድ ቤት አመራለሁ ብሏል፡፡
አንድ ህመምተኛ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል (ICU) ሲገባ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ የጠይቀናቸው የህክምና ባለሙያ እንደነገሩን፤ ህመምተኛው “እንኳን ጌጣጌጥ ከቤቱ ያመጣውን ፒጃማ እንኳን መልበስ አይችልም፤ ብዙ ጊዜ ፅኑ ህሙማን በማሽን ስለሚተነፍሱና የልብ ምታቸው በየጊዜው ስለሚታይ በአብዛኛው ደረታቸው ክፍት መሆን አለበት፤ ስለዚህ በአንሶላና በብርድልብስ ብቻ ይሸፈናሉ” ከዚህ አንፃር ህመምተኞች ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል ሊገቡ ሲዘጋጁ ማናቸውም ጌጣጌጥና ብራስሌት ወላልቆ ለቅርብ ቤተሰባቸው እንደሚሰጥ የጠቆሙት ባለሙያዋ፤ ይህም የፅኑ ህሙማን ክፍል ኃላፊዎች ሥራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡  
“የጆሮ ጌጡ ከአስከሬኑ ጋር ተገንዞ ቢሆን እንኳን የፅኑ ህመምተኛ ክፍል ኃላፊዋ ስራቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ከተጠያቂነት አያመልጡም” ብለዋል – ባለሙያዋ፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ስዩም ምላሽ እንዲሰጡን ጥረት ብናደርግም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

የሕዝብን ተቃውሞ ማፈን ቀውስን አያስወግድም !!! ( የኢሕአፓ መግለጫ ) ባለፉት ጥቂት ቀናት የወያኔን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሲቃወሙ የነበሩ በርካታ ዜጎችን ወያኔ በግፍ ጨፍጭፏል።ኢሕአፓ አምባገነኑ የወያኔ ቡድን በዜጎች ላይ ያካሄደውን አረመኔያዊ ድርጊት እየኮነነና እያወገዘ ይህን አጥፊ ቡድን ለማስወገድ የሚካሄደው …

የሕዝብን ተቃውሞ ማፈን ቀውስን አያስወግድም !!! ( የኢሕአፓ መግለጫ ) Read more »

የጥርስ መቦርቦር — (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ==== የጥርስ መቦርቦር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ጀርሞች (ባክቴሪያ) ጥርሳችንን የሚያበሰብሱ አሲዶችን በሚያመነጩበት ጊዜ ነው፣ ይህም በጥርሳችን ላይ የተቦረቦሩ ቀዳዳዎችን (Cavities) እንዲፈጠሩ ያደርጋል። የተቦረቦሩ ጥርሶች ህመም ከማስከተል ባለፈ ለኢንፌክሽን ያጋልጣሉ። ✔ የጥርስ መቦርቦር …

የጥርስ መቦርቦር (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

ላለፉት ሦስት ሳምንታት የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ተማሪዎች የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ሲቃወሙ ሰንብተዋል። የተቃውሞን ጅምር የሚያትተውን የማርታ ፋን ደር ቮልፍ የአዲስ አበባ ዘገባ ጨምራ፤ ጽዮን ግርማ የዛሬውን የተቃውሞ ሰልፍ ውሎ የተመለከት ርእሶችን ይዛለች፡፡

የደንነት መስሪያ ቤቱ በሚንስትሮች ምክር ቤት በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያ የሰባት ቀን የጌዜ ገደብ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ማስተላለፉ ታውቆአል። የደህንነት መስሪያ ቤቱ በሀገሪቱ ውስጥ ሳይታሰብ የፈነዳውን አመፅ ለመቆጣጠር ምን አይነት እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ አልችል ብሎ ሲወዛገብ መሰንበቱ ሲታወቅ ዛሪ ከጥዋት ጁምሮ ሲአካሂድ በዋለው ውይይት ላይ ግን ማንኛውንም አይነት ሀይል ተጠቅሞ አመፁን ለመቆጣጠር […]

መንግሥት ሁከት በሚፈጥሩት ላይ የማያዳግም እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል

   በጎንደር ጭልጋ አካባቢ ቅማንትና አማራ በሚል በተደራጁ ቡድኖች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካቶች ለሞት መዳረጋቸው የተገለፀ ሲሆን ነዋሪዎች በስጋት ከቤታቸው ሳይወጡ እንደሰነበቱ ምንጮች ገለፁ፡፡
ግጭቱ ስር የሰደደ እንደነበር የጠቆሙት የአካባቢው ምንጮቻችን፤ ከመስከረም ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርታቸውን መከታተል እንዳልቻሉ፣ ከሳምንት በላይ ባስቆጠረው አደገኛ ግጭትም ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡
ቅማንት በሚል የተደራጀው ቡድን፣ “የቅማንት ጥያቄ እስኪመለስ ትምህርት የለም፤ እናንተም አትማሩም” በሚል ት/ቤቶች ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ እንደነበር የጠቀሱት ምንጮች፤ በዚህም የተነሳ የአካባቢው ልጆች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል ይላሉ፡፡ የቅማንቶች የማንነት ጥያቄ ምላሽ ካገኘ በኋላ ከሰሞኑ ለተፈጠረው ግጭት መነሻ የሆነው “ዞን ይዋቀርልን፣ ድንበር ይከለልልን” በሚል በተነሳ ጥያቄ ነው ተብሏል፡፡
ቅማንቶች የማንነት ጥያቄ ማቅረብ ከጀመሩበት ከ3 ዓመት በፊት አካባቢው ውጥረትና ግጭት ተለይቶት እንደማያውቅ የሚጠቅሱት ነዋሪዎች፤ ከሁለት አመት በፊት ሚያዚያ ወር ላይ በአይከል ከተማ ከፍተኛ ረብሻ ተነስቶ ሰዎች መጎዳታቸውንና በርካታ ሱቆችና መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ያስታውሳሉ፡፡
ባሳለፍነው ሐሙስ ህዳር 30 ቀን 2008 ዓ.ም ግጭቱ በከፍተኛ ደረጃ መቀስቀሱን የጠቀሱት ምንጮቻችን፤ በእለቱ አንድ የቅማንት ወጣት መገደሉን ተከትሎ ቅማንት በሚል የተደራጁ ቡድኖች፤ ዳቦ ቤት ማቃጠላቸውንና ሱቅ ማውደማቸውን ይጠቅሳሉ፡፡ ይህን ተከትሎ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሚል የተደራጁ ወገኖች በቋራ፣ ሺንፋ፣ ነጋዴ በሃርና ገንዳ ውሃ በተባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ቅማንቶችን እያባረሩ ቤት ንብረት ማቃጠል እንደጀመሩ ይገልፃሉ፡፡
ከእነዚህ አካባቢ የተባረሩ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ጭልጋ ውስጥ በየድንኳኑ ተጠልለው የአካባቢው ህብረተሰብ የእለት ጉርስ እያቀረበላቸው እንደሚገኝና ሰሞኑን ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የክልሉ ባለስልጣናት ህዝቡን ሰብስበው እንዳወያዩ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
በዚህም የተነሳ በአካባቢው ውጥረት መንገሱን የሚጠቅሱት ምንጮች፤ ሰዎች ከቤት መውጣት እንደተሳናቸውና በየመንገዱ ጦር፣ ገጀራ፣ ቢለዋ፣ መጥረቢያና የጦር መሳሪያዎች የያዙ ሰዎች እንደሚዟዟሩ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ ትናንት በአንፃሩ ሠላማዊ እንቅስቃሴ እንደነበር ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
በገጠር አካባቢዎች ተደራጅተው ለጠብ የተዘጋጁ የቅማንት ተወላጆችን መበተን እንዳልተቻለ የሚጠቅሱት የሚናገሩት ምንጮች፤ የመንግስት ባለስልጣናት ከህዝቡ ጋር ባደረጉት ውይይት ግን ከዚህ በኋላ በግጭቱ ተሳታፊ የሚሆኑና ፀብ የሚጭሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ መናገራቸን ጠቅሰዋል፡፡ ህብረተሰቡም የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ላለመግባት ተስማምቷል ተብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፤ ከቅማንት ብሄረሰብ የማንነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ግጭቶች በመንግስት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመው የአካባቢውን ሰላም በሚያውኩት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ንቅናቄያችን የተቋቋመበት ዋነኛ አላማ የአማራን ህዝብ ህልውና መታደግ ነው።በመሆኑም አሁን በመላው ኢትዮጵያ በአማራው ላይ የሚደርሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል ሽፋን እየተሰጠው ከመቼውም በላቀ ሁኔታ ተጠናክሮ በመቀጠሉ የሚከተሉትን አቋም እንድንይዝ አስገድደውናል። ፩- በመላው ኢትዮጵያ የሚገኝ የአማራ ተወላጅ እራሱን ከጥቃት ለመከላከል እርምጃ ቢወስድ …

ከአማራ‬ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ Read more »

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሒውማን ራይትስ ዎች ትናንት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰውና ሣምንታትን ባስቆጠረው ተቃውሞ ቢያንስ 75 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን አስታወቀ።

የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞውን እንደቀጠለ ነው::በዲሾች ላይ የተጀመረው ነቀላ/ጦርነት ቀጥሏል::ጃኪ ጎሴ የወያኔን ስራ በመቃወም በ2 ሃገራት የሚያካሂደውን ኮንሰርት ሰረዘው::‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterPlan‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ከአዲስ አበባ 60 ኪሎሜትር ላይ በምትገኘው ጫንጮ ከተማ ሕዝቦ አደባባይ በመውጣት ወያኔን ሲያስጨንቀው ታይቷል::በተለያየ ክፍለሃገራት የተሰማሩ የወያኔ ሰራዊት ልብስ …

የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞውን እንደቀጠለ ነው::በዲሾች ላይ የተጀመረው ነቀላ/ጦርነት ቀጥሏል::ጃኪ ጎሴ የወያኔን ስራ በመቃወም በ2 ሃገራት የሚያካሂደውን ኮንሰርት ሰረዘው: Read more »

Minilik Salsawi – የመከላከያ ሚኒስቴር እና የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ድረ-ገጾች (ዌብሳይቶች) ተጠለፉ:: የመከላከያ ሚኒስቴር እና የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ዌብሳይቶች መጠለፋቸውን በማህበራዊ ድህረገጽ የተለቀቁ መረጃዎች ጠቁመዋል:: ድረ ገጾቹ ከተጠለፉ በኋላ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን የሚቃወሙ እና የኦሮሞ ተማሪዎች እና ገበሬዎች የአዲስ አበባ ማስተር …

የመከላከያ ሚኒስቴር እና የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ድረ-ገጾች (ዌብሳይቶች) ተጠለፉ:: Read more »

ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ እሳት ራሱ ይቃጠላል::ሕወሓት ተረት ተረት የሚሆንበት ቀን ደርሷል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Unity‬ Minilik Salsawi – የኢትዮጵያን ሕዝብ በጎሳ እና በጎጥ ከፋፍሎ ለመግዛት የሞከረው ሕወሓት በተደጋጋሚ የሕዝቡ አንድነት እሳት እየሆነበት መጥቷል::ለስልጣኑ መስረዘሚያ የተለያዩ መርዘኛ የግጭት …

ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ እሳት ራሱ ይቃጠላል::ሕወሓት ተረት ተረት የሚሆንበት ቀን ደርሷል:: ‪ Read more »

         በሀገሪቱ የሚታየው የእርስ በእርስ ግጭትና ህዝባዊ አመፅ ሀገር ከመበታተኑ በፊት የሃይማኖት አባቶች ተሰሚነታቸውን ተጠቅመው የሰላም ጥሪ እንዲያቀርቡ ተጠየቁ፡፡
የመግባባት አንድነትና ሰላም ማህበር (ሰላም) ባወጣው መግለጫ፤ በሌሎች ሀገራት የሚታየው የእርስ በእርስ ግጭት ያስከተለው ጉዳትና ቀውስ በአገራችን እንዳይፈጠር የሃይማኖት አባቶች የሽምግልና ሸንጎ በማቋቋም፣ በሀገሪቱ ከጫፍ እስከ ጫፍ የብሄራዊ እርቅ ጥሪ እንዲያቀርቡ ተማፅኗል፡፡
ሀገርና ዜጎች ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት ጭንቀት ውስጥ የገቡበት አጋጣሚ አለመከሰቱን የጠቆመው ማህበሩ፤ የሃይማኖት አባቶች በሀገሪቱ የሚታየው በዘር፣ በጎሣ፣ በሃይማኖትና በቀዬ የመከፋፈል አባዜ እስራትና ስደት እንዲሁም፣ ግጭትና ጦርነት መፍትሔ ይበጅለት ዘንድ እንዲተጉ ጠይቋል፡፡ በሃይማኖት አባቶች መካከል ያለው ግጭትም እልባት እንዲያገኝ ማህበሩ ተማፅኗል፡፡
ኢትዮጵያ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖባት መቆየቷ ባይካድም ያልተቋረጠ ግጭት እያስተናገደች ባለበት በአሁኑ ሰዓት “ፍፁም ሰላም የሰፈነባት አገር ናት” በሚል ከእውነታው መሸሽ ተገቢ አይደለም ያለው ማኅበሩ፤ “በሀገሪቱ የበቀል እርምጃ እየሰፋና እየከፋ በመምጣቱ ምክንያት ማብቂያ ወደሌለው የጥፋት ጎዳና እያመራን እንገኛለን” ብሏል፡፡
“አስከፊ የእርስ በእርስ ግጭትና ህዝባዊ አመፅ እንደሚመጣ አስቀድመን ስጋታችንን ተናግረን ነበር” ያለው ማህበሩ፤ ሆኖም ለእርቀ ሰላም ስንማፀን “በሀገሪቱ ፍፁም ሰላም ሰፍኗል” በሚል ሰሚ ጆሮ ሳናገኝ ቀርተናል ብሏል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት በመተባበር ሀገሪቱ አሁን ከገባችበት አስጊ ሁኔታ ትወጣ ዘንድ እንዲፀልዩና የሀገር ሽማግሌዎች ሸንጎ ለማቋቋም ለሚደረገው ጥረትም እገዛ እንዲያደርጉ ማኅበሩ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡


የሆነ ጊዜ የሰማኋት ቀልድ ትዝ አለችኝ፤ አንዳንድ የተቃዋሚ ተወካዮች ፓርላማ ውስጥ በነበሩበት በዚያ በደጉ ጊዜ ነው አሉ፡፡ አንድ ተወካይ የሻዕቢያ መንግሥት ላይ ሊደረግ ስለሚገባው እርምጃ ሲናገሩ እንዲህ አሉ፤ “አሁኑኑ ገብተን ድምጥማጣቸውን ማጥፋት አለብን፡፡ አለበለዚያ ካደሩ አይቆረጠሙም፤ እነዚያ ወያኔዎችም ያኔ ሲመሠረቱ ሳንጨፈልቃቸው ዝም ብለናቸው ነው ዛሬ አናታችን ላይ…” አሉና ያሉበት ቦታ ትዝ ሲላቸው ድንግጥ ብለው ወደአቶ መለስ መቀመጫ አማተሩ፡፡ አቶ መለስ በጥሞና ያዳምጣሉ፤ ተወካዩ እንደደነገጡ “…ልጨርሰው ወይስ ትጨርሰኛለህ?” አሉ ይባላል፡፡
የሕወሓት/ኢሕአዴግ ወታደሮች አዲስ አበባ ደርሰው “ሲቪል” መንግሥት ከመመሥረታቸው አስቀድሞ “እኩይ” ናቸው በሚል ሲቃወማቸው የነበረ እና እስካሁንም ስክነቱ ያልተለየው አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው፡፡ የታማኝ የአክቲቪስትነት ሪከርድ ከኮሜዲያንነቱ የሚመዘዝ ነው፡፡ በቀልዶቹ ቢጀምርም አሁን ግን በጣም ‹ሲሪዬስ› ነው፡፡ አሁን እነቪኦኤ፣ ዶቸ ቬሊ፣ ኢሳት በየቤቱ እንደሚደመጡት ከደርግ ማክተሚያ ቀደም ብሎ ብዙ ሰው በየቤቱ ‹ድምፂ ወያነ›ን በድብቅ ያደምጥ ነበር፡፡ የፕሮፓጋንዳ ሚዲያዎች አመል ነውና ያው ውሸታቸው አይጣል ነው፡፡ ታዲያ ታማኝ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቀርቦ የምሩን ሲቀልድ ‹እዚህ ቦታ ይሄን ያክል ሻለቃ ጦር፣ እዚያ ቦታ ደግሞ ይሄን ያክል ሻለቃ ጦር ደመሰስን ይላሉ፡፡ ሲደመር ግን ይሄን ያክላል፡፡ ቆይ እኔ የምለው ወያኔዎቹ የሚደመስሱት ጦር ከጠቅላላ ጦሩ በለጠ እኮ፤ ከየት እያመጡ ነው የሚደመስሱት?› ዓይነት ቀልድ ተናግሮ አላገጠባቸው፡፡ ከዚያ በድምፂ ወያነ መልስ ተሰጠው፤ “ቁጥሩን አዲስ አበባ ስንደርስ እናወራርዳለን” የሚል፡፡ ዛቻ የሽፍትነት ዘመንም አመል ነበረች፡፡
ግንቦት 20/1983 – ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ሲረግጥ፣ ሲ ኤን ኤን ካነጋገራቸው ሰዎች አንዱ ታማኝ በየነ ነበር፡፡ “በመሣሪያ ተከበናል፣ ምንም ሠላም የለም…” የሚል ነገር ለጋዜጠኛው ሲነግረው ይታያል፡፡ ታዲያ ታማኝ ሁኔታውን በቀልድ ሲያስታውስ “ጓደኞቼ ከውጪ ደውለው ‹ሲ ኤን ኤን› ላይ አየንህ ሲሉኝ፣ ወዲያውኑ እንግሊዝኛዬ እንዴት ነበር?” አልኳቸው ይላል፡፡
ታማኝ ከአዲሱ ስርዓት ጋር አብሮ መኖር በማይችልበት ሁኔታ የተቀያየመው፣ ካልተሳሳትኩ የወቅቱ ባለሥልጣናት፣ እነታምራት ላይኔ በተገኙበት ስታዲዬም ውስጥ በቀለደው ቀልድ ነው፡፡ እንደማስታውሰው ቀልዱ በማንነት ላይ የተመሠረተ እና ለኢሕአዴግ የማንነት ብያኔ የማይበገር ዓይነት ቀልድ ነው፡፡

ፍቃዱ ማሕተመወርቅ፣ የቀድሞዋ ዕንቁ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነበር፡፡ በመጽሔትና ጋዜጦች አከፋፋይነትም ይታወቃል፡፡ አሁን መጽሔቱ ተዘግቶ “በታክስ ስም” ፍርድ ቤት እየተመላለሰ ይገኛል፡፡ ፍቃዱ ነጻው ፕሬስ ሲጀመር ጀምሮ ምኅዳሩን ያውቀዋል፤ እናም “እናንተ በደጉ ጊዜ ነው የመጣችሁት” እያለ ይቀልድብኛል፡፡ ያኔ (ማለትም የመጀመሪያው አንቀጼ ላይ ‹ደግ› ባልኩት፣  ለፍቃዱ ግን ‹ክፉ› ግዜ) አንድ ሰው ስርዓቱን የሚያስቀይም ንግግር ሲናገር፣ እንዳሁኑ በሕግ ሥም ፍርድ ቤት አይመላለስም፣ የደረሰበት ይጠፋና ከአራት አምስት ወር በኋላ ተመልሶ ይመጣል፡፡ እንዳይሞት እንዳይሽር ተቀጥቅጦ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ከዚያ ወዲህ ያሻሻልነው ነገር ቢኖር ፍርድ ቤት የመቅረብ ዕድል መፈጠሩ ነው ማለት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ይህን ያነሳሁት ታማኝ ላይ የደረሰውም እንዲህ ያለው ነገር ነው ለማለት ነው፡፡
ታማኝ ተሰደደ፡፡ ብዙዎች ሲሰደዱ አቅላቸውን ያጣሉ፡፡ የሀገር ቤት ናፍቆት መመለስ ካለመቻሉ ጋር ተደማምሮ ይሁን፣ የሄዱበት አገር ኢሕአዴግ የማይደርስባቸው ከመሆኑ በተጨማሪ የሚያዩት ነጻነት ስለሚያስቀናቸው አላውቅም ብቻ ጠርዝ ይይዛሉ፡፡ ጥቂቶች ብቻ ሚዛናቸውን በጥፍራቸው ቆንጥጠው ይቆማሉ፡፡ ታማኝ ለኔ ከጥቂቶቹ አንዱ ነው፤ ያውም በረዥም ቆይታ ይህንን ማስመስከር የቻለ፡፡ ታማኝ አሁን አክቲቪዝሙን የሚሠራው ብዙ ጊዜ የቪዲዮ ማስረጃዎችን እያቀረበ ነው፡፡ ቪዲዮዎቹን ዩቱዩብ ላይ ሳያቸው በክምችቱ እቀናለሁ፡፡ ለረዥም ጊዜ የአገር ቤት ጉዳይን እየተከታተሉ፣ ማስረጃዎችን እየሰበሰቡ የመቆየት ፅናት የገቡበትን ጉዳይ ርዝመት እና ክብደት ከመረዳት ይመነጫል፡፡
የማስረጃ ነገር ከተነሳ አይቀር፣ አሁን እነ ታማኝ ማስረጃ ዶት ኮም (masreja.com) የተባለ ድረአምባ ፈጥረዋል፡፡ ድረአምባው በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ የበላይነት ፈንታ ራሳቸው ከሕግ የበላይ ሆነው ወንጀል የሚፈጽሙ ሰዎች ላይ ማስረጃ የሚሰበሰብበት ነው፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ እኔ በይቅርታ አምናለሁ፤ እስከዛሬ አዲሱ ያለፈውን እየቀጣ የመጣበት ዑደት ቢያንስ የእኛ ትውልድ ላይ ቢቆም እያልኩ እመኛለሁ፡፡
ይህንን በተመለከተ ጓደኛዬ ሶሊያና “ይቅርታ ከፍትሕ ጋር መጋጨት የለበትም” ብላ ሞግታኛለች፡፡ ልክ ነች፤ በወቅቱ የሰጠችኝን ምሳሌ ከወቅታዊው ሁኔታ ጋር አዋህጄ ልናገር፤ “#OromoProtests ላይ ልጇ የተገደለባት እናት የስርዓት ለውጥ ቢመጣ እና ለገዳዩ ወታደር ይቅርታ አድርጊለት ብትባል ፍትሕ ተደረገልኝ ብላ ታምናለች?” በወቅቱ፣ ሶሊም እኔም ጥያቄውን ከመጠየቅ በቀር መልስ መስጠት አልቻልንም፡፡ እርግጥ ነው ልጁ የሞተው የመጣው ለውጥ እንዲመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በምሳሌያችን መሠረት አወዛጋቢው ማስተር ፕላን ቢሰረዝ እንኳን ልጁ የለውጡ እሸት ተጋሪ ላይሆን አልፏል፡፡ ይቅርታ ለአገሪቱ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ያስፈልግ ይሆናል፤ የቤተሰቡን አባል ወይም ወዳጁን ላጣው ግለሰብ ግን ፍትሕ ሆኖ ይሰማዋል ማለት አይቻልም፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ለይቅርታውም ቢሆን ማስረጃውን መሰብሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ አጥፊው ጥፋቱን እንዳይክድ፣ ይቅርታ ጠይቁኝ ባዩም በማስረጃ እንዲሞግት፡፡
ማስረጃ መሰብሰብ ሕገ-ወጥ መስሏችሁ የምትፈሩ ካላችሁ አትሳሳቱ፡፡ ሕጋዊ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥት ራሱ በፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኩል አላግባብ የተገኘ ሀብት ካለ በሚል የባለሥልጣናቱን ሀብት ምንጭ ሳይቀር የማጣራት ማንዴት አለው፡፡ ቁርጠኝነቱ ስለሌለ አልተሳካላቸውም፤ እኛ ግን ይሳካልናል፡፡ በየቀኑ ከታችኛው እርከን (ወረዳ) እስከ ላይ ድረስ የምንጠየቃቸውን ጉቦዎች፣ ባለሀብቱና ባለሥልጣናቱ (ሁለቱም አንድ ናቸው) ኢ-ርትዓዊ በሆነ መንገድ የሚያካብቱትን ሀብት፤ ከትላልቆቹ እስከ ትናንሾቹ ሹመኞች በሕዝብ ላይ የሚፈፅሙትን ግፍ፤ ትንንሽሽም፣ ትልልቅም ሠላማዊ ተቃውሞዎች በተነሱ ቁጥር በንፁሐን ዜጎች ነፍስ ላይ የሚሰነዘሩትን የኃይል እርምጃዎች የሚያጋልጡ ማስረጃዎች ባገኘን ቁጥር ለማስረጃ ዶት ኮም በመላክ ለኢትዮጵያችን የወደፊት መልካም ዕጣ ፈንታ ሲባል እንዲከማቹ የበኩላችንን እናድርግ፡፡ ማስረጃዎቹን መሰብሰቡ ሌላው ቢቀር አጥፊዎቹን ስለሚያስፈራቸው በደላቸውን ሊያላሉልን ይችላሉ፡፡

ቪቫ ላ ታማኝ!!!

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተማሪወችም መንግስት በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖችና ወረዳዎች የፈፀማቸውን ግድያዎች በምልክት መቃወማቸው ታወቀ ። በትላንትናው እለት መንግስት አዳአ በርጋ ሙገር ከተማ በወሰደው እርምጀሰ ከሐያ ሰዎች በላይ መግደሉንና ብዛት ያላቸውንም ማቁሰሉን : ተጎጂዎችም በኢንጪኔ ሆስፒታል እንደሚገኙ ታውቋል። በዛሬው እለት በቀለም …

የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተጀመረው ተቃውሞ ተፋፍሞ ቀጥሏል Read more »

የዘር ፖለቲካ መዘዝ – ግርማ ካሳ የአሜሪካን ዽምጽ ራዲዮ ዘገባ አደመጥኩ። ከ50 በላይ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎች እንደተዘረፉና ጥቃት እንደደረሰባቸው ነው ዘገባው የሚገልጸው።በጣም አዝኛለሁ። ዜጎች ከዚህ ወይም ከዚያ ብሄረሰብ በመሆናቸው ብቻ ጥቃት ሲፈጸምባቸው መሰማቱ እንደ አገር አሁን ሕወሃት/ኢሕአዴግ እያራመደው …

የዘር ፖለቲካ መዘዝ – ግርማ ካሳ Read more »

የመንግሥት ኃይሎች ኦሮሚያ ውስጥ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ “እጅግ አስከፊ” ወይም በእንግሊዝኛው ቀጥተኛ አባባል “ብሩታል” ናቸው ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አውግዟል፡፡

መንግስታዊ ሽብርና ትንኮሳ ይቁም! ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማሸማቀቅ እና ለማሳቀቅ ፍተሻ በሚል በተለያዮ መስጅዶች የማዋከብ ተግባራት በሰፊው ተስተውለዋል ይህም ሆን ተብሎ የህዝቡን አቴንሺን ለመስረቅና ለማሳቀቅ የሚፈፀም መንግስታዊ ሽብር ነው። በሙስሊሙ ማህበረሰብ ከ1987 ጀምሮ የሽብርና የግድያ ተግባራትን ማን እንደፀመ ህዝቡ በሚገባ ጠንቅቆ …

ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማሸማቀቅ እና ለማሳቀቅ ፍተሻ በሚል በተለያዮ መስጅዶች የማዋከብ ተግባራት በሰፊው ተስተውለዋል Read more »

የአዴሃን ዋነኛ አላማ የሚያስረዳና ለትግል የሚቀሰቅስ ፁሁፎች በአዋሳ በሰፈረ ሰላም: ገብሬል: ዋርካ :ፒያሳ: አላሙራ: አቶቴ ሞቢል አረብ ሰፈረ እና በማስታወቂያ ቦርዶች በሻሸመኔ ሰማኒያ አንድ ሰፈር አሮጌ መነሃሪያ አዲሱ መነሃሪያ ሞቢል ሰፈር በበቂ ሁኔታ ተሰራጭተዋል:: የህወሃት መንግስት አጥብቂኝ ዉስጥ በመዉደቁ ህዝባዊ …

በአዋሳ እና በሻሸመኔ በእኩለ ቀን በአማራ ዴሞክራሲዊ ሃይል( አዴሃን) የትግል ጥሪ በያዙ በራሪ ወረቀቶች እና ፖስተሮች ተጥለቀለቀች:: Read more »

በሰሜን ጎንደር እና አካባቢው በቅማንት ብሔረሰብ አባሎችና በአማሮች መካከል ግጭት መከሰቱና የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ትላንት ባስተላለፍነው ዝግጅት ማሰማታችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የችግሩ ሰላባ ከሆኑት መካከል አንድ ሰማቸን ለመግለጽ ያልፈለጉ የትግራይ ተዋላጅን አነጋግረናል።

ውጭ ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ከሃገር ውስጥ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ሁከት አስመልክቶ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ።

የኩላሊት ጠጠር ( KIDNEY STONES)  ==== (ዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ==== የኩላሊት ጠጠር ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ መቆየት የሚችል ሲሆን ከኩላሊት ተነስቶ በሽንት ማስወገጃ መስመር እስከ ፊኛ ድረስ ሊያደርግ በሚችለው ጉዞ ምክንያት ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡ የኩላሊት ጠጠሮች ጠጣር የሆኑ ትናንሽ …

የኩላሊት ጠጠር ( KIDNEY STONES) (ዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

የሐሞት ጠጠር —- (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ====== የሐሞት ከረጢት የሚባለው የሰውነት ክፍል ከጉበት ሥር የሚገኝ አነስተኛ ከረጢት ሲሆን ለምግብ መፍጨት ሂደት አስፈላጊ የሆነዉ የሐሞት ፈሳሽ የሚጠራቀምበት አካል ነው፡፡ የሐሞት ፈሳሽ ጨዋማ ንጥረ ነገሮችን ያዘለ ሲሆን የምንመገበዉን ቅባት እና ቫይታሚኖች …

የሐሞት ጠጠር (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

ሕዝብን በፍቅር እንጂ በኃይል ማንበርከክ አይቻልም – ግርማ ካሳ ሁልጊዜ እንደምናደረገው ብሄራዊ እርቅን፣ ሰላምን እንሰብካለን። እስከአሁን ሰሚ አላገኘንም። ቢሆንም ለአገርና ለህዝብ ይበጃል የምንለዉን የሰላም ጥሪ እየደጋገምን፣ ሰሚ ኖረም አልኖረም እንጻፋለን። እንናገራለን። የጥበብና የማስተዋል መንፈስ ይለቀቅልን ዘንድ፣ በተለይም ሌላውን ጋኔን የሚሉ …

ሕዝብን በፍቅር እንጂ በኃይል ማንበርከክ አይቻልም – ግርማ ካሳ Read more »

ከጥቂቅ ደቂቃዎች በፊት ለዘ-ሐበሻ በደረሰው ዜና መሠረት በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ነውጥ ነበር:: የዚህ የተኩስ መነሻ ከልደታ ፍርድ ቤት እስረኞች ስላመለጡ ነው ተብሏል፡፡የአይን እማኞች እንደሚገልጹት ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም እስረኞች ያመለጡ ሲሆን አክባቢው ተረብሾ ይገኛል፡፡ የአይን እማኞች እንደሚገልጹት እስረኞች አምልጠዋል በሚል ከሃያ በላይ የጥይት ድምጾችን ሰምተዋል፡፡ በተለይም በዛሬው ዕለት በዚሁ ፍርድ ቤት መምህር […]

አዲስ አበቤዎች ካልደፈረሰ አይጠራም::ፈሪውን ወያኔን ገፍትሮ ለመጣል አፋፍ ላይ ስለሆንን እንግፋው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterplan‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ወያኔ እኔ ካሌለው የሃገር አንድነት ይፈርሳል የሚል አጉል የማይሆን ዲስኩር እያሰማ ይገኛል:: የትኛውን አንድነት ነው ወያኔ የገነባው?ከደርግ የወረሳት ኢትዮጵያን እኮ …

አዲስ አበቤዎች ካልደፈረሰ አይጠራም::ፈሪውን ወያኔን ገፍትሮ ለመጣል አፋፍ ላይ ስለሆንን እንግፋው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

የሳውዲ አረብያ የተፈጥሮ ሃብት፣ ሃገሪቱን ባለፀጋ እና ተሰሚነት ያላት አገር እንድትሆን አድርጓል ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን የሳውዲ የሃብት ምንጭ የሆነው የነዳጅ ዘይት ዋጋ መውረዱና የየመኑ ጦርነት እንዲሁም በአካባቢው ከኢራን ጋር የሚካሄደው ሽኩቻ እስካሁን በገንዘብ አቅም የያዘችውን ቦታ ሳያሳጣት አይቀርም ።

የኦሮሞ ጀግኖች ተቃውሞ በየከተሞች እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ቀጥሎ ሱሉልታ ላይ መንገድ ተዘግቷል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterPlan‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi – የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ እና የሕዝብ ብሶት የወለዳቸው በራሱ በሕዝቡ መሪነት የሚካሄዱ ተቃውሞዎች ቀጥለዋል::በዛሬው እለት እየተደረገ ባለው ተቃውሞ የጎጃም …

የኦሮሞ ጀግኖች ተቃውሞ በየከተሞች እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ቀጥሎ ሱሉልታ ላይ የባህርዳር መንገድ ተዘግቷል:: Read more »

የወልቃይት ማህበረሰብ ከአዲስአበባ በ977 ኪሎሜትር ላይ በትግራይ ክልል ስር በሁመራ ዞን አድረመጭ ወረዳ የሚገኝ ነው። በ11ሺ 149 ስኩዌር ኪሎሜትር ላይ ሰፈረውና 413ሺ564 ሕዝብ እንዳለው የሚነገርለት የወልቃይት ማህበረሰብ ባለፉት 24 ዓመታት የአማራ ብሄር ነን በሚል በአማራ ክልል ለመካለል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ሲቀርብ …

‘አማራ ነን‘ የወልቃይት ሕዝብ ያልተመለሰ ጥያቄ – የወልቃይት ሕዝብ አቤቱታ እንደሚከተለው ቀርቧል። Read more »

ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመው በሀሰተኛ ሰነዶች በመታገዝ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ በፌዴራል ከፍተኛ እና በጠቅላይ ፍርድ ጥፋተኛ ተብለውና ይግባኛቸው ውድቅ ሆኖ በእስር ላይ የሚገኙ 11 ሰዎችን ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ በጥቅም ተሳስረው ረድተዋል የተባሉ 16 ተከሳሾች እንዲከላከሉ ሲል የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ …

ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመው በሀሰተኛ ሰነዶች በመታገዝ ከማረሚያ ቤት የወጡና ያስወጡ ተከሳሾች እንዲከላከሉ ተበየነ Read more »

እነ በረከተ መርገምት እና እነ ደመቀ መኮነን እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣናት የሚመራ ብዛታቸው ሰባት የሚሆኑ ልዑካን ወደ መተማ ከተማ ትናንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ሂደዋል በስምንት የፌዴራል ፓሊስ ፓትሮል እየታጀቡ አቅንተዋል ። ከሱዳን ጋር በተሸጠው መሬት ሊመክሩ እንደሆነ የውስጥ አዋቂ በሆኑ ሰዎች መረጃው ደርሶኛል ። በዚህ ጉዳይ ላይ የመተማ ከተማ እና የሸህዲ ከተማ ነዋሪዎች በግፍ በጭነት […]

በቋራ፣በመተማና በሸንፋ በአካባቢዉ ታጣቂ አማጺያንና በመንግስት ታጣቂዎች መካከል ሳምንቱን ሙሉ የተኩስ ልዉዉጥ አለመቋረጡን፣ የሞቱ ሰዎች መኞራቸዉ፣መንገድ መዘጋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢኤን ገልጸዋል። በምእራብ ትግራይ ወልቃይት ጠገዴን ወደ አማራዉ መስተዳድር ለመመለስ የሚደረገዉ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ይህንንኑ በመስጋት ብአዴን የወልቃይት ህዝብንና ኢህአዴግን ለማሸማገል የሚያደርገዉ ጥረት ተቀባይነት እንዳላገኘ ታዉቋል። የወልቃይት ተወላጆች ለቢቢኤን እንደገለጹት ሽምግልና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የህዝብ […]

የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ያገረሸው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ፡፡የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለሰጡት አስተያየትም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የኬንያ ፖሊስ በሕገ- ወጥ አገሪትዋ ዉስጥ የሚኖሩ ያላቸዉን 54 ኢትዮጵያዉያን ማሰሩ ተመለከተ። እንደ ፖሊስ ገለጻ፤ በኬንያ ናይሮቢ ካሳራኒ በሚባል አካባቢ ሦስት ክፍል ዉስጥ ሲኖሩ የነበሩ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን የተያዙት ፖሊስ በደረሰዉ ጥቆማ እንደሆነ ገልጾአል።

በጎንደር ክፍለሃገር የሰሜኑ ክፍል ውጥረቱ አይሏል::በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Gonder‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በጎንደር ክፍለሃገር የሰሜኑ ክፍል ባለፉት ሳምንታት ሞቅ ቀዝቀዝ ሲል የነበረ የወያኔ አገዛዝ እና የሕዝቡ ግጭት ወደ ለየለት መስመር መቀየሩን እና …

በጎንደር ክፍለሃገር የሰሜኑ ክፍል ውጥረቱ አይሏል::በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በምስክርነት እንደማያቀርብ አሳወቀ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሰውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በምስክርነት እንደማያቀርበው ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ማረሚያ ቤቱ ታህሳስ 4/2008 ዓ.ም ለልደታ ፍርድ ቤት በላከው …

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በምስክርነት እንደማያቀርብ አሳወቀ Read more »

በዘላለም ክብረት


ሐሙስ 20 – 01 – 2003፣ ጋምቤላ ከተማ፡

የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዲሱን የስራ ዘመኑን የመጀመሪያውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ በማጽደቅ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ በመዝጊያው ስነ ስርዓት ላይ በጊዜው የክልሉ ፕሬዝደንት የነበሩት ኡሞት ኡባንግ ባደረጉት ንግግር፡

‹‹ጋምቤላን ወደ ቀድሞው ክብሯ እንመልሳታለን፡፡ ያችን አኙዋዎች፣ ኑዌሮች፣ መዠንገሮች፣ ኦፖዎች፣ ኮሞዎችና ደገኞች አንድ ላይ በሕብረት የሚኖሩባትን – ጋምቤላ፡፡ ሁላችንም አፍሪካዊያኖች ነን፡፡ ጥላቻና ልዩነት ለማናችንም አይበጁንም…››


በማለት የሁሉንም ተሰብሳቢዎች ልብ የሚነካ ሃሳብ አቀረቡ፡፡ 156 መቀመጫዎች ያሉት የክልሉ ምክር ቤትም በጭብጨባ ተናጋ፡፡ ኡሞት ይሄን ታሪካዊ ንግግር ሲያደርጉ ከኡሞት ጎን የተቀመጡት የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አሽኔ አስቲን ተከትለው ስለ ልማትና መከባበር ተናግረው አሁንም አዳራሹን በሌላ ጭብጨባ አናጉት፡፡ ከሚያጨበጭቡት የምክር ቤት አባላት መካከል ቁመተ ሎጋው የ50 ዓመቱ ከአኙዋ ዞን የተወከሉት አቶ በኳች ማሞ ይገኙበታል፡፡ 

እሁድ፡ 06 – 07 – 2007፣ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ፡

የቀድሞው የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ሆኑት አቶ አሽኔ አስቲን በኬኒያ ናይሮቢ አኝዋ ሰርቫይቫል፣ Bread for All እና GRAIN በተባሉ ዓለማቀፍ ተቋማት የተዘጋጀውን ዓለማቀፍ የምግብ ኮንፈረንስ ላይ ለመሳተፍ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከሌሎች አራት ግለሰቦች ጋር (የዓለም ባንኩን አስተርጓሚ ፓስተር ኡሞት አግዋን ጨምሮ) ተገኙ፡፡ ነገሮች እንዳሰቡት ሳይሆን ቀረና አምስቱም ግለሰቦች በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ተይዘው ወደ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ተወሰዱ፡፡

ከአንድ ቀን በኋ ሰኞ፣ 07 – 07 – 2007፡ 

‹ምርጫ 2007› ሊደረግ ስልሳ ሰባት ቀናት ይቀሩታል፡፡ ‹አፈ-መንግስቱ› ኢቢሲ ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን  ባወጣው የፖለቲካ ፓርቲዎች የቅስቀሳ የአየር ጊዜ መሰረት የዕለቱ (በቴሌቪዥን ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ዜና በኋላ) ተረኛ በጋምቤላ የኢሕአዴግ አጋር ፓርቲ በመሆን ክልሉን እያስተዳደረ ያለው የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕአዴን) ነው፡፡ ጋሕአዴን በዕለቱ እየቀሰቀሰበት የነበረው ጉዳይ የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ሲሆን፤ በዚሁም መሰረት የክልሉ ህዝብ በዴሞክራሲያዊ መንገድ በተመረጡ የፓርላማ አባላት በፌደራል እና በክልል ደረጃ እንደተወከለና የውክልና ዴሞክራሲም በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደላቀ ደረጃ እንደደረሰ ጠቅሶ ይቀሰቅሳል፡፡ በቅስቀሳው መሃል ከሚታዩት ምስሎች መሃል ግን አንዱ ጉዳዩን ለሚያውቅ ሰው ወይ ያስቃል አለያም ያስደነግጣል፡፡ አስቂኙ/አሳዛኙ ጉዳይ በ2002 ምርጫ የክልሉ ምክር ቤት ካለው 250 መቀመጫዎች መካከል አንዱን የያዙት የአኙዋ ዞን ተወካዩ አቶ በኳች ማሞ በክልሉ ፓርላማ ውስጥ የድምፅ አሰጣጥ ስርዓት ላይ እጃቸውን ሲያወጡ መታየታቸው ነው፡፡ ምክንያቱም አቶ በኳች ማሞ በቀን 07 – 07 – ’07 ‹‹መቀመጫውን ሀሬና፣ ኤርትራ ካደረገው ራሱን የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋህነን) ብሎ ከሚጠራ የሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት ፈጥረሃል፣ በሃላፊነትም እያገለገልክ ነው›› ተብለው በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ  አንቀፅ 7 (2) መሰረት ከ 20 ዓመት እስከ እድሜ ልክ ሊያስቀጣ የሚችል ክስ ቀርቦባቸው ያለመከሰስ መብታቸው እንኳን ሳይነሳ በእስር ላይ ይገኛሉና፡፡ በኳች ታስረዋል፡፡ ጋሕአዴን ደግሞ የውክልና ዴሞክራሲ መጎልበት ተምሳሌት አደርጎ ይቀሰቅስባቸዋል፡፡

ሰኞ፣ 17 – 09 – 2007፡ ጋምቤላ፣ ማጃንግ ዞን፡

በአስገራሚ ሁኔታ የቀድሞው የጋምቤላ ክልላዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል አቶ አሽኔ አስቲን በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን መንድሽ የምርጫ ክልል በተካሔደው የክልል ምክር ቤት ምርጫ  ጋሕአዴንን በመወከል ምርጫውን በማሸነፋቸው የምርጫ ክልሉ ምርጫ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ማቴዎስ ኤፍሬም የተፈረመ የተመራጭነት መታወቂያ የተዘጋጀላቸው ሲሆን ‹የተመራጩ ፊርማ› የሚለው ቦታ ላይ ግን ፊርማቸውን አላሳረፉም፡፡ 

ለምን? ምክንያቱም አቶ አሽኔ አስቲን ከመጋቢት 06 – 2007 ጀምሮ ‹‹መቀመጫውን ሀሬና፣ ኤርትራ ካደረገው ራሱን የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋህነን) ብሎ ከሚጠራ የሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት ፈጥረሃል›› ተብለው በፀረ-ሽብርተኝነት አቆጁ መሰረት ተከሰው በእስር ላይ ስለሆኑ፡፡ እንግዲህ አቶ አሽኔ አስቲን ምርጫ የተወዳደሩትም ያሸነፉትም በሌሉበት ሲሆን፤ በመጨረሻም በሌሉበት የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት  ተመራጭ ስለመሆናቸው በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ የተመራጭነት መታወቂያ ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡

***

ኡሞት ኡባንግ በ2002 ምርጫ አሸንፎ ስልጣን የያዘውን የጋምቤላ ምክር ቤት አራተኛ የስራ ዘመን በ2003 መጀመሪያ ላይ ሲከፍቱ አሽኔ አስቲን በአፈ ጉባኤነት ከጎናቸው የነበሩ ሲሆን በኳች ማሞ ደግሞ የምክር ቤት አባል ሁነው ከፊት ለፊታቸው ተቀምጠው ነበር፡፡ አምስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ኡሞት ኡባንግ ከክልሉ ፕሬዝደንትነታቸው ተነስተው በፌደራል ደረጃ ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ቢሾሙም የያዙትን ይዘው ከሀገር ኮበለሉ፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አፈ ጉባኤና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል አሽኔ አስቲን በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ታስረው ይገኛሉ፣ የምክር ቤት አባሉ በኳች ማሞም እንዲሁ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

እውነት ይህ ሁሉ የሚሆነው ህግና ስርዓት ባለበት ሀገር ነው? ብሎ መጠየቅ እዚህ ጋር ተገቢ ነው፡፡ የጋምቤላ አበሳ ግን ከዚህም ይልቃል፡፡

1. ጋምቤላ

የኢፌዴሪ ሕገ – መንግስት በአንቀፅ 47 ካቋቋማቸው ዘጠኝ የክልል መስተዳደሮች አንዱ ነው፡፡ የሕዝብ ብዛቱ ትንሽ ከሚባሉ ክልሎች አንዱ ሲሆን (የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን የሃምሌ 2007 ግመታ የክልሉ ሕዝብ ብዛት ሶስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ እንደሆነ ያሳያል)፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙት አስር ክፍለ ከተማዎች ውስጥ ‹በየካ ክፍለ ከተማ› ብቻ የሚኖረው ነዋሪ በአጠቃላይ በጋምቤላ ክልል ከሚኖረው ነዋሪ በእጅጉ ይበልጣል እንደ ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በጋምቤላ ክልል የሚኖረው ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ 0.4 በመቶውን ብቻ ይሸፍናል፡፡ (የሕዝብ ቁጥሩ ላይ የተለያዩ የክልሉ ልሂቃን ጥርጣሬ አላቸው) የሕዝብ ብዛቱ ከቆዳ ስፋቱ አንፃር ሲታይ ግን በኢትዮጵያ እንደ ጋምቤላ ህዝብ ሰፊ መሬት ላይ የሰፈረበት (sparsely populated) ክልል የለም፡፡ በንፅፅር ሲቀርብም ሃምሳ ከሚሆኑት የአውሮፓ ሀገራት ጋምቤላ አስራ ሶስት የሚሆኑትን በቆዳ ስፋት ይበልጣል፡፡ ጋምቤላ መሬቱ ሰፊ፣ የሕዝብ ብዛቱ ትንሽ እና እጅግ ለም ክልል ቢሆንም እንደ ጋምቤላ ጭቆናው፣ የመብት ጥሰቱ፣ ስደቱና መከራው የበዛበት ክልል የለም ማለት ደግሞ ስህተት ነው አያስብልም፡፡ 

በ1980ዎቹ አጋማሽ Cultural Survival በጋምቤላ የሚኖረውን የአኙዋ ዘውግ ‹አደጋ ላይ ያሉ ቡድኖች› ዝርዝር (endangered groups list) ውስጥ ካስገባው ጊዜ ጀምሮ ስለ ጋምቤላ ስቃይና መከራ እንደ Genocide Watch, Survival International, Oakland Institute, Inclusive Development, Human Rights Watch, Amnesty International, International Consortium of Investigative Journalists (ICIJ) የመሳሰሉ ፖሊሲ አፍላቂዎች (think tanks)፣ የመብት ተከራካሪዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች ብዙ ሪፖርቶች፣ መግለጫዎችና ዘገባዎችን በተለያዩ ጊዜያት አውጥተዋል፡፡ የግጭት ተንታኞች (conflict analysts) የፌደራል ኢትዮጵያን የግጭት መንስኤና መፍትሄ ሲተነትኑ ከጋምቤላ የተሻለ ምሳሌ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ እዚህም እዛም ጋምቤላ ነው በምሳሌነት የሚቀርበው፡፡ ለምን ጋምቤላ?

2. ጋምቤላና: ‘የፌደሬሽኑ ፈተና’?

ኢትዮጵያ የዘውግ ፌደራሊዝምን (ethnic federalism) በሕገ መንግስት ደረጃ ተቀብላ ተግባራዊ ማድረግ በጀመረችበት ወቅት ሂደቱ ዘውግ ፌደራሊዝምን በሕግ ደረጃ ከከለከሉትና ዘውጌ ፖለቲካ ፓርቲዎችን በሕግ ደረጃ ከሚያግዱት ከአብዛኖቹ የአፍሪካ ሀገራት የተለየ (divergent) በመሆኑ ትችትና ውዳሴ ከተለያዩ አካላት ይቀርብለት ነበር፡፡ ተችዎች ይህ ለአፍሪካዊያን መጥፎ ምሳሌ (precedent) ነው በማለት ከፋፋይ ነው ሲሉ ሲያጣጥሉት፤ አወዳሾቹ ደግሞ አፍሪካ ከተዘፈቀችበት የግጭት አዙሪት ለመውጣት ጥሩ መፍትሔ ነው በማለት ሲያሞግሱት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ዘውጌ ፌደራሊዝም ከሃያ ዓመታት በኋላ እንደ ተችዎቹ ሆነ ወይስ እንደ አወዳሾቱ የሚለው ኦዲቲንግ የዚህ ፅሁፍ ዓላማ ባለመሆኑ በዚህ ፅሁፍ ለማየት አልተሞከረም፡፡

‹የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ብዙ ውይይት ሳይደረግበት ነው አሁን ባለው ደረጃ ሕገ መንግስታዊ የሆነው› የሚለው የምሁራን ትችት እንዳለ ሆኖ ዘጠኝ ክልሎችንና ሁለት የከተማ አስተዳደሮችን (ድሬዳዋን በኋላ ሕገ መንግስቱን እንኳን ማሻሻል ሳያስፈልገው በአዋጅ የከተማ አስተዳደር አድርጎ ተቀብሏታል) ይዞ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ ይህ በዋነኛነት ዘውግን መሰረት ያደረገው ፌደራሊዝም ግን የግጭትና መንስኤ መሆን የጀመረው በተግባራዊነቱ ማግስት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፌደሬሽን ዋነኛ የግጭት መንስኤ የሆነባቸው ክልሎች ደግሞ አራቱ ብዙሃኑን የሚወክል ‹አውራ ዘውግ› (dominant ethnic group) የሌለባቸው ክልሎች ማለትም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል፣ በጋምቤላ ሕዝቦች ክልል እና በሀረሪ ሕዝብ ክልል ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት አራት ክልሎች ተፎካካሪ ዘውጎች (competing ethnic groups) ያሉባቸው በመሆናቸው የሃብትና የስልጣን ፉክክሩ ነገሮችን በቀላሉ ወደ ግጭት እንዲያመሩ ያደርጓቸዋል፡፡ እንግዲህ ጋምቤላም ከነዚህ አራት ክልሎች አንዱ ነው፡፡
2.1. ‘አኙዋ’  ከ‘ኑዌር’

በአሁኑ ወቅት ያሉት ሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የፌደራሉን ሕገ መንግስት መሰረት በማድረግ (በአብዛኛው ከፌደራሉ ሕገ መንግስት ቃል በቃል የተቀዳ) ራሳቸው የክልል ሕገ መንግስት አላቸው፡፡ የጋምቤላ ሕዝቦች ክልልም የራሱ የሆነ ሕገ መንግስት አለው፡፡ የጋምቤላ ሕዝቦች ሕገ መንግስትን ከሌሎች ክልሎች ሕገ መንግስትም ሆነ ከፌደራሉ ሕገ መንግስት በተለየ ‹የክልሉ መስራች አባላት› (titular groups) የሚል ሀሳብ ማካተቱ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልል ሕገ መንግስት አንቀፅ 46 መሰረት የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስራች ብሔር ብሔረሰቦች አምስት ሲሆኑ የአኙዋ ብሔረሰብ፣ የኑዌር ብሔረሰብ፣ የመዠንገር ብሔረሰብ፣ የኦፖና ኮሞ ብሔረሰቦች ናቸው፡፡ ከነዚህ መስራች ብሔረሰቦች› መካከል የአኙዋና የኑዌር ብሔረሰቦች በድምሩ ከዘጠና በመቶ በላይ የሚሆነውን የህዝብ ቁጥር ሲይዙ ከአጠቃላይ የክልሉ ነዋሪዎች መካከል ደግሞ እነዚህ ሁለት ብሔረሰቦች ከሁለት ሶስተኛ የሚልቀውን ይይዛሉ፡፡ በመሆኑም የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል ዋነኛ እጣ ፋንታ የሚወሰነው በሁለቱ ‹መስራች ብሔረሰቦች› ተፎካካሪ (competing) ግንኙነት ነው ማለት ነው፡፡

የተለያዩ የክልሉን ፖለቲካ ያጠኑ ግለሰቦች/ተቋማት ጋምቤላን ሰላም ካሳጧት ችግሮች አንዱና ዋነኛው በውስጡ ያሉት ዘውጎች የዕርስ በርስ ፉክክርና ግጭት (inter-ethnic conflict) ነው፡፡ ይህ ግጭትም የሃብት፣ የመሬት እና የስልጣን ፍክክር ነው በማለት ያብራራሉ፡፡ የግጭቶቹ መንስኤ በአጭሩ ይሄ ነው ማለት ከባድ ነገር ቢሆንም በዋናነት ግን ግጭቱና ቁርሾው በአኙዋና ኑዌር ዘውጎች መካከል እንደሆነ ጥናት ያደረጉ ቡድኖች ይገልፃሉ፡፡ የአኙዋ ዘውግ ልሒቃን ጋምቤላ በታሪክ የአኙዋ ምድር እንደሆነች ሌሎች ዘውጎች ከአሁኗ ደቡብ ሱዳንና ከአጎራባች ክልሎች በተለያዩ ጊዜያት እንደመጡ በመግለፅ የጋምቤላ ሃብትና ስልጣን ለባለታሪኩ (historical right) እንደሚገባ በመግለፅ ይሟገታሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ አብዛኛው የዘውጉ አባላት በደቡብ ሱዳን የሚኖሩት የኑዌር ብሔረሰብ ልሂቃን ጋምቤላ የሁላችንም ናት ከሚል መነሻ “መጤ” የሚለው ስያሜ አይገባንም በማለት ሃሳባቸውን ያቀርባሉ፡፡ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ መድሃኔ ታደሰ በተለምዶ የአኙዋ -ኑዌር ግጭት በኑዌሮች ‹ተስፋፊነት›ና በአኙዋዎች ከመሬታቸው ጋር ባለ ጥብቅ ቁርኝት መካከል የተፈጠረ አለመጣጣም እንደሆነ ሲገልፁ ‹‹Traditionally, the Anuak- Nuer conflict can be explained by the incompatibility (antithesis) of the expansionist nature of the Nuer and the Anuaks’ strong emotional ties with their land›› በማለት ነው፡፡

ይህን የተፎካካሪ ዘውጎች ውዝግብ ለመፍታት ተወሰደው ርምጃ ጋምቤላን የኑዌር፣ የአኙዋና የማጃንግ ዞኖች ብሎ በዘውግ መስመር በሶስት ዞኖች መክፈል ነው፡፡ ይህ መፍትሔ የበለጡ የድንበር ጥያቄዎችንና ከመፍጠር ባለፈ፣ የክልሉን ስልጣን ለመያዝ የሚደረገውን ፍክክር የበለጠ አጡዞ የባሰ ችግር ከማምጣት ባለፈ ለጋምቤላ ሕመም መድሃኒት ሊሆናት አልቻለም፡፡

2.2. ‘መስራቾቹ’ ከ’መጤዎቹ

ፖለቲካል ዲሞግራፊ በአካዳሚያው ውስጥ እንደ ጥናት መስክ ተቆጥሮ መጠናት ከጀመረ ከአንድ አስርት ዓመት ብዙም አላለፈም፡፡ ሳይንሱ በዋናነት የሚያጠናው በአንድ ፖለቲካል-ኢኮኖሚ ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ ሰዎች (ወጣቶች፣ ሽማግሌዎች፣ &#4660

Everything is destroyed or burned at Sola Grow, a company that grows seedlings. When protests in Ethiopia, three Dutch agricultural businesses as well as destroyed. A rose grower, a seed company and a grass and livestock farm were targeted by violent protesters. “Our guards have their guns empty shot in the air, but the attack was […]

ትናንት በባኮ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሶ ከተማይቱ በተኩስ ስትናጥ ቆይታለች ። ወደ ነቀምት ያመሩ የነበሩ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በባኮ ለማለፍ ተቸግረው ባኮ መግቢያ ላይ ለመገተር ተገደዋል ። በባኮ ተቃውሞ የፖሊስ መኪኖችና ድርጅቶች ተቃጥለዋል ።የአጋዚ ልዩ ኃይሎች ባኮ ከገቡ በኋላ የግብርና ኮሌጁን በመቆጣጠር ከመቶ በላይ ተማሪዎችን በኦራል መኪና ጭነዉ ከከተማዋ ውጪ በመውሰድ ፎቶግራፍና እና ቪድዮ ቀርፀዋቸዋል፡፡ ተማሪዎቹን […]

ከአዲስ አበባ ጎንደር የገቡት የአገዛዙ ባለስልጣናት የህወሓቱ አባይ ፀሀዬ፣ የህወሓት ተላላኪ የሆነው ብአዴን ቁንጮዎች በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ ናቸው፡፡ የክልሉ ሹም ገዱ አንዳርጋቸውም በአጃቢነት ተገኝቷል፡፡ አባይ፣ በረከትና አዲሱ በትናንትናው ዕለት የዞኑን ካቢኔ አባላትና ጥቂት የስርዓቱ ደጋፊ የሆኑ የከተማው ነዋሪዎችን በጎሃ ሆቴል ሰብስበው በጎንደር ስለሰፈነው አለመረጋጋት፣ አመፅና ጦርነት ለማነጋገር ሞክረው “ይህ ሁሉ ችግር ከደረሰና ሁኔታው ከቁጥጥር […]

በዮሐንስ ደሳለኝ (ጀርመን – ፍራንክፈርት)
በየዓመቱ ዲሰምበር 10 የሚከበረው የሰብዓዊ መብት ቀን ሐሙስ December 10,2015 በፍራንክፈርት የዋናው ባቡር ጣቢያ አካባቢ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ አመሸ። ከተለያዩ አገሮች የመጡ ተገን ጠያቂዎች የተገኙበት ይህ አከባበር ለየት ያለና የወቅቱ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚገባው ብርድ ያልበገረው ነበር።

 

frankfort 

ሙሉውን አስነብበኝ …