የምግብ እጥረት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በርትቷል፡፡
ሁለት አነስተኛ ድንኳኖች በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ ሐሩርና ንዳድ ለመከላከል ያስችሉ ዘንድ ተዘርግተዋል፡፡ በአንደኛው ድንኳን ውስጥ አራት ፍራሾች ተዘርግተው፣ ኢልኒኖ ባስከተለው ከፍተኛ ድርቅ የተነሳ የምግብ እጥረት የገጠማቸውን ሕፃናትና እናቶች ለመንከባከብ እንዲያስችሉ አንሶላ ለብሰው ተዘጋጅተዋል፡፡ በእነዚህ ድንኳኖች ውስጥ ደግሞ ‹‹ሴቭ ዘ ቺልድረን›› …