የህወኃት ‹‹ከሞኝ ደጅ ሞፈር የሚቆርጥበት›› “የከፋፍለህ ግዛ ” መጋዝ አርጅቷል
የህወኃት መንግስት ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን በጣም የተሳሳተ ግምት ነው ያለው፡፡ አይደለም ሌላው ነጻ ኢትዮጵያዊ የእነርሱ ተላላኪዎችና ጥቅም ተጋሪዎች በሰሩት ወንጀል ፍርሃትና በጥቅም የሚያዩትን አላየንም ፣ የሚሰሙትን አልሰማንም ብለው ይካዱ እንጂ በህዝቡ ውስጥ እስካሉ የሚሆነውን እያዩና እየሰሙ ስለመሆናቸው ቅንጣት መጠራጠር የለባቸውም፣ በእብሪት ታውረው እንጂ፡፡ ታዛዥ ጀሌዎቻቸው እየተፈጸመባቸው ያለውንና የሚታዘዙትን ያውቃሉና ነጻ ቢሆኑ ምን ያህል በህወኃት ጭቆና ስር እንዳሉና የህወኃት የበላይነት የቱን ያህል እንደሆነ በነገሩን ነበር፤ ግን የሚነግሩን ቀን የቀረበ ስለመሆኑ የሚያጡት አይመስለኝም ፡፡
ለመገዛትና ራሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት ቢወስኑም የሚሠጠውና የሚለወጠው እጃቸውና ሆዳቸው እንጂ ከአደባባይ መልስ ከእነርሱ ጋር ብቻ ለብቻ የሚቀረው ኅሊናቸው እንደሚያፋጥጣቸው የፈጣሪ ትዕዛዝ ነውና ጨርሰው ሊሸጡትም ሆነ ሊሸሹት አይቻላቸውም፡፡ ለዚህም ነው ራሳቸውን ከኅሊናቸው ለማሸሽ በተለያየ መደበቂያ ( አልኮል ፣ ሴት ጭን ፣ ….) ውስጥ የሚሸጉጡት፡፡ ህወኃቶቸ የገተሩት ህንጻ በእኛ/ህዝብ መሃል መሆኑን ብቻ ሳይሆን እያንዳንዷ ቁራሽ መሬት ሳትቀር የማን እንደነበረች ፣እንዴት እጃቸው እንደገባችና እንደተዘዋወረች … ከዬት በመጣ ገንዘብ እንደተገነባና የሸሸው ዶላርና ፓውንድ እንዴትና ከየት እንደተገኘ ሁሉ የተነጠቀውም፣ የተሰጠውም ከህዝብ ነውና ከህዝብ ሊሰወር አይችልም፡፡ የት እንደተደበቀም ሆነ እንደተቀመጠ -ከቁም ሣጥን እስከ ባንክ ይታወቃል፤ የቀን ጉዳይ ነው ከተደበቀበት ሲወጣ፣ከተጫነበት ሲወርድ ጊዜ አሳይቶናል፣ ነገም ያሳየናል ፡፡ ጊዜ ለኩሉ//
የድንጋይ ክምሩንና ገንዘቡን ብቻም አይደለም የሰዎቹን ማንነት፣ መነሻና የደረሱበትን ሁሉ ህዝብ ያውቀዋል፡፡ በ1983 ጠላ ቤት የምንተዋወቃቸው ዛሬ እኛ ወደተወደደብን የቧንቧ ውኃ ስንወርድ እነርሱ ‹‹ ሽቅብ ተምዘግዝገው›› ሸራተን አንሷቸው ዱባይና ታይላንድ ለጭንና ለአረቄ ሲጓዙ እንዳላየን የምንሆነው በጊዜ ምክንያት ‹‹የቀን እንጂ የሰው ጀግና የለውም›› ብለን እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡ በመሳሪያ፣ በገንዘብና በሥልጣን ጊዜውና ሁኔታው ለያየን እንጂ ሁሉም የተፈጸመውም ያለውም በዚህቺው አገር ሲያልፍም ፕላኔት ነው፡፡ በታሪክ ከህዝብ የተደበቀ ምስጢር የለም፡፡ ህዝብ ሁሉንም ያውቃል፡፡ እኛም የሚያስቡንን ያህል ሞኝና ተላላ አይደለንም፣ ለጊዜውም ቢሆን ጀግናው ጊዜ ጀግኖብን ‹‹ማወቁን እናውቃለን ፣ብንናገር እናልቃለን ›› በሚል አንገታችን ደፍተን ነው፤ አሁን ግን አንገታችን ቀና የምናደርግበት ደወል ድምጽ ከአራቱም አቅጣጫ እየተሰማ ነው፡፡ ህወኃት ‹‹ከሞኝ ደጅ ሞፈር የሚቆርጥበት›› የመከፋፈያና ማናቆሪያ መጋዝ ‹‹ተበልቶ ›› እያለቀ ነው፣ አልቋል ማለትም ያስደፍራል፡፡ ከፋፍሎ ማሸማቀቅ፣የህወኃትና ጀሌዎቹ የአንገት ማስደፋትና ማጨራረስ ፣የእብሪትና ማን አለብኝነት …. ጀንበር አዘቅዝቃለች፡፡ ቀሪዋ አጭር ጊዜ የሱባኤ፣ ኑዛዜና ንስሃ ናት፣ያውም በመጨረሻም ቢሆን የፈጣሪን- የእውነትን አሸናፊነት ለመረዳት ለታደሉት፡፡ የእኛ ቀጣይ ተግባር የደወሉ ድምጽ በእኩል ከዳር እስከዳር እንዲሰማ ማድረግና ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ የኅብረት ድምጹን እንዲያሰማ ማስተባበርና ማቀናጀት ነው፡፡ በቸር ያገናኘን// 27/03/08 Girma Bekele
gobez tkkl neh ethiopiyanoch be ethiopiya astesasebachn enji ende fashishit kefafleh gzaw bezer mesebaseb lemanachnm neSanet aymetam weyanin ena degafi ashkerochu begLs yawkutal gn eni yemaymechen neger ahunm weyani yemetabetn menged degfew tekawami bemahon lezerochachn yemilu keweyani yetekorekomu hayloch yeweyani menged ena astesasebachew bota endelilew amnew ke ethiopiyawiyan gar mekelakel alebachew lemsali medrek malet arena letgri ofeko leoromo degmo man endehone balawkm leamhara , ledebub eyalu weyani yekefafelewn lemasketel yemitagelut bemn mesfert new yh yezer kll zer bematfat zer mebechefchef yetederege yewerera sistem new slezih tglachn agerachn lemekefafel weym yezer fediralizm memesret mhon yelebetm weyani ye eethiopiya telat ena geday bihonm betekawaminet komew yeweyanin mewdek hlmachewn lemasakat yemimeNu bezer mannet dimokrasi ager mekemat kll mefter new yemilutnm atbko meleyet mawgez yasfelgal weyani eni kalgezawu blo yaskemetachew bonboch ena ethiopiya enikelilehu serdo aybkel blo yezerachew nachew
!!!!
Endet resahew, the Amhara governments neglected by
all the other ethnic groups.
EPRDF allows those neglected by your previous governments to take part in the change introduced.
We wittness a very fast economic growth as confirmed by IMF, among others.
Anonymus _ የሞኝ ዘፈን ሁል ጊዜ አበባዬ ሆነና ነገሩ የቀድሞ ስርአት ናፋቂዎች እያልክ ታላዝናለህ እንጂ ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኦሮሞን፣ሲዳማን፣ሶማሌውን፣አፋሩን፣ጉራጌውን፣አኙዋኩን፣አገውን፣ሃድያውን፣ወላይታውን፣ከፋውን፣አማራውን፣ኢትዮጵያኢትዮጵያየሚለውን ትግሬ___ወዘተ፤ በጠራራ ፀሀይ እገደለ፣እያሰቃዬ፣እያሰረ፣እያሳበደ__ወዘተ ያለው ማን ሆነና? ብቻ አንተን ያላቀን እንጂ የቀን ጅብ ይብላን።።።
በደርግ ጊዜም ደርግ ይውደቅ እንጂ ከሱ የከፋ አይመጣብንም ተብሎ እዚህ ደርሰናል።
የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ እንዳይሆን አሁንም በደመ ነፍስ ከምንጓዝ፣ ከማን ጋር ነው እየተጓዝኩ ያለሁት ብለን ራሳችንን እንጠይቅ።
የኦሮሞ ወገኖቻችን የደረሰባቸውንና እየደረሰባቸው ያለው በደል ግልጽ ነው፤ ይሁን እንጂ ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተለየ በደል አልደረሰባቸውም ብዬ ነው የማምነው።
መቼም ያለፈውን እየረሳን እንጂ ስንቶቹ የአማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ናቸው በገዛ አገራቸው ግፍ የተፈጸመባቸው። በተናጠል እየተመታን ስላልተባበርን አሁንም ባንድነት ቆመን ጥያቄያችንን የጋራ አድርገን እስካልተነሳን ድረስ መከራችን ይቀጥላል።
የኦሮሞዎቹ መሬት ወደ አዲስ አበባ ሊሄድብን ነው ተብሎ የተነሳው ተቃውሞ ለሌላ ማነሳሻ ይጠቅም እንደሆነ እንጂ፣ በጎንደርና እስከ ጋምቤላ ድረስ ለሱዳን ስለተሰጠብን መሬት ግን ኦሮሞዎቹም አላነሱትም እኛም ቀሪዎቹ ኢትዮጵያውያን የረባ ተቃውሞ ስናደርግ አልታየንም።
አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ እንዳይሆን፣ አንድን ነገር ስንደግፍ ጥርት ብሎ መሆን አለበት። ዝም ብሎ ለጊዝያዊ ጥቅም ተብሎ የሚደረግ ሆይ ሆይታ የኋላ ኋላ ዋጋ እንዳያስከፍለን አስተዉለን ለዘለቄታዊ መፍትሄ ነው መስራት ያለብን።
ሙስሊም ወገኖቻችን ተበደልን ብለው በጽናት አሁንም ድረስ ሲታገሉ፣ ምን ያህሎቻችን ነን እነርሱን ደግፈን አብረናቸው የተሰለፍነው? ጋምቤላዎች ያ ሁሉ ጭፍጨፋ ሲደርስባቸውስ? በጉራ ፈርዳ፤ በቤንሻንጉል ግፍ የተፈጸመባቸውስ? ስንቱ ተቆጥሮ ይዘለቃል።
አዳሜ፤ ዘርን ሳይሆን የሰው ልጅ በመሆኑ ብቻ ለሚደርስበት ግፍና በደል አብረን እስካልቆምን ድረስ መከራችን ገና የሚቀጥል ነው የሚሆነው። አገዛዙን ዘረኛ እንላለን እንጂ ራሳችን ነን በዘር ልክፍት ተዉጠን መዉጫ ያጣነው።
እግዚአብሄር አገራችንን ይጠብቅ።