በትናንትናው ዕለት በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሃይቅ ለመከበር በዝግጅት ላይ የነበረውና ከኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ የሆነው ኢሬቻ በዓል ላይ ለዘገባ ተገኝተው የነበሩ ጋዜጠኞች የተከታተሉትን በዝርዝር ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ጽዮን ግርማ የተወሰኑትን አነጋግራ ተከታዩን አጠናቅራለች። ያድምጡ ↓

colonel-demeke-zewde
የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ተጨማሪ የሽብር ምርመራ በፌደራል ፖሊስ ሊካሄድባቸው የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቋል፡፡ ኮ/ል ደመቀ አሁንም ክሥ ያልተመሠረተባቸው ሲሆን ጉዳያቸው ከትናንት በስተያ፤ መስከረም 18/2009 ዓ.ም የታየው በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት መሆኑን ጠበቃቸው አቶ መክት ካሣሁን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በግድያ ወንጀል የጠረጠራቸው ፖሊስ የምርመራ መዝገብ በዕለቱ ተዘግቶ አቃቤ ሕግ ክሥ ይመሠርት ወይም ሌላ ሃሣብ ያቀርብ እንደሆነ የ15 ቀናት ጊዜ ያለው መሆኑን አቶ መክት ገልፀው አዲስ ለተከፈተው ምርመራ ፖሊስ የሃያ ስምንት ቀን ቀጠሮ ጠይቆ እንደነበር አመልክተዋል፡፡

እርሣቸውና ደንበኛቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 2/2009 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኮሎኔል ደመቀ ጉዳይ የአካባቢው ሕዝብ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት እዚያው ጎንደር ከተማ ውስጥ እንዲታይ መወሰኑን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ንጉሡ ጥላሁን አመልክተዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ →listen

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ዲግሪ በተለያየ ሙያ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እረፍታቸውን ጨርሰው የ2009 የትምህርት ዘመን ለመጀመር ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ወደየ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ።


የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ነበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በመንግሥት የሥልጣን አመራር ዘመናቸውም የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) የፓርቲ አባልና ሥራ አስፈጻሚ አባልና ከፍተኛ አመራር ነበሩ። በኦህዴድ ውስጥ የተደረገው ሹም ሹር ምን እንደምታ እንዳለው አስተያየር እንዲሰጡ ተጠይቀዋል። ጽዮን ግርማ አነጋግራቸዋለች → LISTEN

የፀጥታ ኃይሎች ጨዋ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ይተኩሳሉ፣ ይገድላሉ ያሉት ተቃዋሚዎች ተጠያቂዎቹም የመንግሥት የፖለቲካ መሪዎች እንደሆኑ አስታውቀዋል።

ከዋሽንግተን ዲሲና ከአካባቢው እንዲሁም ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የመጡ ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ በዋይት ሃውስ እና በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ደጃፎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።

ሕጻናት የያዙ እናቶችና አዛውንቶች ጭምር የነበሩበት እጅግ የበዛ ቁጥር ያለው ሰላማዊ ሰልፈኛ ከማለዳው አንስቶ ነው “በዚያች አገር እየተካሄደ ነው” ያለውን ግድያ “በአፋጣኝ አስቁሙ!” እና “ለመንግስቱ የምትሰጡትንም እርዳታ አቋረጡ” የሚሉ ጥያቄዎችን ላቀረበላቸው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባለሥልጣናትና የምክር ቤት አባላት ሲያሰማ የዋለው።

ሳያቋርጥ ቀኑን በዘለቀው ካፊያ ውስጥ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መሥሪያ ቤት ወደ በዋይት ሃውስ አልፎ ከምክር ቤት የሚያደርሱትን የከተማይቱን ጎዳናዎች ሞልቶ…

በትናንትናው ዕለት በነቀምት ከተማ ደርጊ ወይም ቀበሌ ሁለት በተባለ ቦታ ባልታወቁ ሰዎች በኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮች ካምፕ ላይ የፈነዳ ቦምብ ጉዳት ማድረሱ ተገለጿል። ከጉዳቱ በኋላ በአካባቢው የተገኘው ሰው ሁሉ ድብደባ ደርሶበታል ሲሉ ነዋሪዎች ያማርራሉ።

የአገር ፈተናዎች፥ የመውጫ መንገዶችና ተሥፋ፤ አንጋፋው የኢትዮጵያ ጉዳይ አዋቂ፥ ደራሲና የመብት ተሟጋች ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማሪያም ትላንትናችንን፥ ዛሬንና ነገን፤ መንታ መንገድ ላይ ያለች በምትመስለው ሃገር ሰሞንኛ ይዞታ ውስጥ ይቃኛሉ።

በምዕራብ ሃረርጌ መሰላ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ሰሞኑን የፀጥታ ኃይሎች ወሰዱ በተባሉ እርምጃዎች ሁለት ሰው መገደሉን የወረዳው አስተዳዳሪ ገልፀዋል፡፡ ዝርዝሩን ያዳምጡ → listen

በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ በተቀሰቀ ግጭት የሰው ሕይወት ጠፋ። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እስካሁን የአራት ሰው ሕይወት ጠፍቷል ሲሉ የክልሉ መንግሥት እስካሁን ባለን መረጃ የጠፋው የአንድ ሰው ሕይወት ነው ብሏል። ዘገባውን ያዳምጡ → listen


ሐምሌ አራት ለሐምሌ አምስት አጥቢያ የፌደራል ልብስ ለብሰው ጭንብል ያጠለቁና ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማነንት ጥያቄ ኮሚቴ አራት አባላትን አፍነው በመውሰዳቸና፤ አንዱን የኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በግዳጅ ለመውሰድ በተደረገ ግብግብ በጎንደር ከተማ ግጭት መጫሩ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ የኮሚቴው ፀሐፊ አቶ አደራጀው ናኘው ተናግረዋል።

ከረጅም ዓመታት በፊት በፖለቲካ ምክንያት በሶማሊያ መኖር እንዳልቻሉ በመግለጽ በኖርዌይ ያቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይንት አግኝቶ ፤ የመኖሪያ ፈቃድ እና ዜግነንት ተሰጥቷቸው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ። ለዚህ ሁሉ የዳረጋቸው ደግሞ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ስለራሳቸው የሚያወጡት መረጃ …

በፌስቡክ ምክንያት በርካታ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ – VOA Read more »

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ ውስጥ በመካከለኛ ርቀት 800 ሜትር ተወዳዳሪ የነበረችውና በብሔራዊ ቡድን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ተመራጭ በመሆን የምትታወቀው የ19 አመትዋ አትሌት ኩለኒ ገልቻ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በአትሌት ጓደኛዋ እጅ ህይወቷ በስለት ማለፉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፌዴራል …

አትሌት ኩለኒ ገልቻ በወንድ ጓደኛዋ ተወግታ ተገደለች – VOA Read more »

ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ጥቃት ያደረስኩት እኔ ነኝ ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ኃላፊነቱን ወስዷል። የድርጅቱ ሊቀ መንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ፥ ”ትግላችንን የምናካሂደው እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆነን ነው” ብለዋል። ያዳምጡ → listen

በደቡብ ኦሮምያ፤ ቦረና ዞን ውስጥ ትናንት፣ ዓርብ ምሽት ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ ቢያንስ የ13 ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሆስፒታል ምንጮች አስታወቁ፡፡ አደጋው የደረሰው አንድ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከልክ በላይ አሳፍሮ ሜጋ ወረዳ ውስጥ ካለችው የዓርብ ገበያ ከሚቆምባት ዱቡሉቂ ከተማ ወደ …

በያቤሎ የአውቶቡስ አደጋ አሥራ ሦስት ሰው ሞተ – VOA Read more »

በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ውስጥ ባለፈው ዕሁድ ሌሊት ከፖሊስ ድብደባ ጋር በተያያዘ አንድ ተማሪ መሞቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኦሮምኛ ፕሮግራም ክፍል ባልደረባ ለጃለኔ ገመዳ ተናግረዋል። የነጆ ከተማ አስተዳደር ግን ተማሪው የሞተው በሕመም ምክንያት መሆኑን ሐኪም አረጋግጧል ይላል። ​በሌላ በኩል፥ ቤተሰብ …

በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፖሊስ ድብደባ ጋር በተያያዘ አንድ ተማሪ መሞቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ይገልጻሉ – VOA Read more »

“በኢትዮጵያ ያለው የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ምን ይመስላል?” ስትል ጽዮን ግርማ የሂዩማን ራይትስ ዎች የጥናት ባለሞያ ፍሊክስ ሆርንና የደህንነት ጥናት ተቋም የጥናትና ምርምር ባለሞያ ሃሌሉያ ሉሌን ጠይቃለች። ሁለቱም ባለሞያዎች በኢትዮያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት እጦት ተባብሷል ይላሉ። ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ → listen

የኢትዮጵያው ፌዴራል ዐቃቤ ህግ 33 ሰዎችን በአገር ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን (የኦነግን) ድርጅታዊ ህዋስ በመመሥረት፣ በመምራትና አባላት በመሆን የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል ሲል በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መሠረተባቸው። ፍርድ ቤቱም፣ ተከሳሾቹ መልስ እንዲሰጡ በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ …

33 ሰዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ድርጅታዊ ህዋስ በመመሥረትና በአሸባሪነት ተከሰሱ – VOA Read more »

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ የአመራር አባል አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 በሽብር የተጠረጠሩ ተከሳሾች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ። እነ አቶ በቀለ በማረሚያ ቤት ስድብ ማስፈራራትና ሌሎችም ከፍተኛ ተጽኖዎች እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ …

የኦፌኮ ከፍተኛ የአመራር አባላት በማረሚያ ቤት ከፍተኛ በደል ይደርስብናል አሉ – VOA Read more »

የኢትዮጵያን ቋንቋ፣ ታሪክና ባህል ለበርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን በማስተማር ላይ ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል በሜሪላንድ የሚገኘው የደብረ ገነት መድሃኒያለም ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አንዱ ነው። በዚሁ ቤተክርስቲያን በምክትል አስተዳዳሪነትና በቅዳሴ በማገልገል ላይ የሚገኙት መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ገብረወልድ አገዝ ወደ …

የቆሎ ተማሪ በአሜሪካ – VOA Read more »

በትግራይ ክልል የእምባስነይቲ ህዝብ ቀድሞ የነበረውን ወረዳ እንዲመለስለት ከ20 ዓመታት በላይ ጠይቆ አወንታዊ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት የተሰማውን ቅሬታ ትላንት በሰላማዊ ሰልፍ ገልጿል።

መንግስት የቆየውን ወረዳችን የማይመልስልን ከሆነ ከወረዳ እስከ ተወካዮች ምክር ቤት የወከልናቸውን ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ ውክልናችን ማንሳታችን እንገልፃለን ብሏል ህዝቡ።

“ጠዋት ቂሊንጦ ስንሄድ አራቱ ሰዎች የሉም። ያሉበትን የሚነግረን አላገኘንም።” ወ/ሮ ዓይናለም ደበሎ፤ ላለፉት አራት ወራት በማዕከላዊ እሥር ቤት የነበሩትና ካለፈው አርብ አንስቶ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዛውረዋል፤ ከተባሉት የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባላት ቤተሰብ አባላት አንዷ ናቸው። ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ → …

እስር ላይ የሚገኙትን አራት የኦፌኮ አመራር አባላት መጠየቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ – VOA Read more »

ከአራት መቶ በላይ የሚሆኑ አሶሳ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች በፌደራል ትምሕርት ሚኒስቴርና በቤንሻጉል ክልል ምክር ቤት ላይ የፍትሐቤር ክስ መመስረታቸው ታወቀ። ለክክልሉ ምክር ቤት መጥሪያ ሊሰጡ የሄዱት የአርሶ አደሮቹ ተወካይ ተይዘው መታሰራቸውም ይሰማል። የክልሉን ምክትል አስተዳዳሪ እና የቤንሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች …

ከ400 በላይ የሚሆኑ አሶሳ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ክስ መመስረታቸው ታወቀ – VOA Read more »

እስከአሁን ባደረግነው ክትትል በትናንትናው ዕለት 14 ኢትዮጵያውያን በደቡብ ሱዳን ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውንና አስከሬኖቻቸው ተለይተው ዛሬ ለዘመድ አዝማድ መላካቸውን ለሆስፒታል ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል። አስክሬን ፍለጋው መቀጠሉ ተነግሯል። ዝርዝሩን ያዳምጡ → listen

የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰብ ላይ እያካሄደ ነው ያሉትን አፈና እንደሚያወግዙ አሥራ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ለምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ አቅርበዋል። የውሣኔ ሃሣቡን የያዘው ሰነድ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ሲቪሎችን መግደላቸው በተገለፀበት በአሁኑ ሁኔታ የአሜሪካው …

የአሜሪካ ሴናተሮች “ኢትዮጵያ ውስጥ አለ” ያሉትን አፈና አወገዙ – VOA Read more »

የበሽታዎቹን መከሰት ከወዲሁ የሚጠቁሙ አስቀድመው የሚታዩ ምልክቶች ይኖሩ ይሆን? የስኳር ሕሙማን በራሳቸው ሊወስዱ የሚችሏቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ይኖሩ ይሆን? የስኳር በሽታን ተከትለው የሚከሰቱት አሳሳቢዎቹ የዓይን ሕመም ዓይነቶች የትኞቹ ናቸው? ተከታታይ ቅንብሮቹ የሕክምና አማራጮቹን ጨምረው ሕሙማንና የቤተሰብ አባላት ሊጠይቁና ሊመልሱ የሚሿቸውን ጭብጦች ይዳሳሳሉ።

ሚስትና ልጁን ያጣ፣ እናትና ወንድሞቹን ውሃ የበላበት፣ እህቱን እና 28 ጓደኞቹን ያጣ ናቸው። ስላሳለፉት ጉዞ አስቸጋሪነትና ለመሄድ ስለተዘጋጁ ስደተኖች የሚነግረን ወጣትም ከግብጽ አነጋግረናል። ባለፈው ሳምንት ማብቂያ በሜዲትራንያን ባህር ላይ ጀልባ ተገልብጦ 500 ስደተኞች ሰጥመው ሕይወታቸው ማለፉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲ …

ከመስመጥ የተርፉት ኢትዮጵያውያን 11 ብቻ ናቸው፤ ሦስቱን አነጋግረናቸዋል – VOA Read more »

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ባለፈዉ ሳምንት በሰጠዉ ዉሳኔ ነጻ ያሰናበታቸዉ ሁለት ሰዎች እንዳልተፈቱ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ፖሊስ ማእከላዊ የወንጀል ምርመራ እንደወሰዳቸዉም ተገልጿል። የፖሊስ እርምጃ ምክንያት ግን አልታወቀም። ዝርዝሩን ከመለስካቸዉ አመሃ ዘገባ ያድምጡ → listen

በ120ኛው የቦሰተን ማራቶን በሴቶቹ ተከታትለው በመግባት ያሸነፉት፥ አፀደ ባይሣና ትርፊ ነገሪ ናቸው። የወንዶቹን ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ሥፍራ የወሰዱትና ታሪክ የሠሩት የኢትዮጵያ ሯጮች ደግሞ፥ ለሚ ብርሃኑ፥ ያለፉት ሁለት ዓመታት ሻምቲዮኑ ሌሊሣ ዴሢሣና ፀጋዬ ናቸው። listen

በኦሮሚያ ክልል አልፎ አልፎ በተማሪዎችና በነዋሪዎች የሚካሄደዉ ተቃዉሞና የጸጥታ ሃይሎች የሃይል እርምጃ ምላሽም ቀጥሏል። በጉጂ ዞን ኦዶሻኪሶ ወረዳ መጋደር በተባለ መንደር ባለፈዉ ማክሰኞ በዳዳ ጋልቹ የሚባል ወጣት በመንግስት ሃይሎች መገደሉን የአካባቢ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ገልጸዋል። በወረዳዉ የሻኪሶ ከተማ አስተዳዳሪዎች …

በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ በዳዳ ገልቹ የሚባል ወጣት በመንግስት ታጣቂዎች መገደሉ ተነገረ – VOA Read more »

በኦሮሚያ በየደረጃው የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ሃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉ ከ 800 በላይ አመራሮች ከደረጃ ዝቅ ብለው እንዲሰሩ የማድረግና ከሀላፊነት የማንሳት እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። በክልሉ የተጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን የኦሮሚያ ክልልና የፌደራሉ መንግስት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ዘጋብያችን እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ የላከው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል።

በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ውስጥ ሰኞ እና ማክሰኞ በተማሪዎችና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭት መፈጠሩን ነዋሪዎች ገለጹ። ከግጭቱም በኋላ ከሰላሳ ሰው በላይ መታሰሩን ተናግረዋል። የከተማው ፖሊስ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ይላል። የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ቱጁቤ ኩሳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ …

በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከ30 በላይ ሰዎች መታሠራቸውን ተማሪዎች ተናገሩ – VOA Read more »

በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ ካለፈው አርብ ጀምሮ ውሃ መቋረጡን፣ መብራት ከዕረቡ ጀምሮ መጥፋቱን እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከሠላሳ በላይ ሰዎች መታሠራቸው በዚህ ዘገባ ተካቷል።

በሕክምናው አጠራር “ኮሌስትሮል” በመባል በሚታወቀው፤ በአንድ በኩል ለጤና በእጅጉ አስፈላጊ፤ መጠንና ዓይነቱ ሲለወጥ ደግሞ ጎጂ በሚሆነው በደማችን ውስጥ የሚዘዋወረው ስብ መሠል ንጥረ ነገር ምንነትና የሕክምናው ዓለም ምልከታዎች ዙሪያ የሚያተኩር ተከታታይ ቅንብር ነው። ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን የልብና የውስጥ ደዌ ከፍተኛ አማካሪ …

ኮሌስትሮልን ተከትለው የሚመጡ የጤና ሁከቶችን መከላከያ ቅድመ ጥንቃቄ – VOA Read more »

በዓለም በፍጥነት በማደግ ላይ ከነበሩ አስራ ሀገሮች ሰባቱ የአፍሪካ ሀገሮች ሲሆኑ፤ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ሆና ቆይታለች። የያዝንው የአውሮፓዊያን ዓመት ግን ይሄ ሁኔታ እንደሚቀየር ነው የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ (IMF)በየዓመቱ የሚያወጣው የዓለም ምጣኔ ሀብት ግምገማ ዘገባው አስታውቋል። ባለፈው ዓመት …

የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል የዓለም የገንዘብ ድርጅት IFM አስታወቀ – VOA Read more »

በነዳጅ የከበረችው የናይጄሪያ ናይጄር ዴልታ የቀድሞ አገረ ገዢ፣ የሌላዋ የነዳጅ ባለጸጋ ሃገር የኣንጎላ የነዳጅ ሚኒስትር፣ የሙዋቹ የጊኒ መሪ ላንሳና ኮንቴ ባለቤት እንዲሁም የቀድሞ የተ መድ ዋና ጸሓፊ ኮፊ አናን ልጅ ስምም በፓናማው ሰነድ በተጋለጡት የባንክ ሂሳቦች ስማቸው ተነስቱዋል።

ይህ የከተሞች አዋጅ በክልሉ ከተጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መነሻዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል። አንቀጾቹ የተሠረዙት ጉዳት ስላላቸው ሳይሆን በሕዝቡ ጥያቄ ስለተነሳባቸው መሆኑን የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ አብራርተዋል።

የተለያዩ የኤርትራውያን ተቃዋሚዎች ሬድዮዎችና ድረ-ገጾች ግን የሞቱት ወጣቶች ብዛት ከአራት እስከ 11 ነው ይላሉ።

የቢሾፍቱ መሰናዶ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች ትናንትና እና ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ ማድረጋቸውንና በፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎችና ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ በከተማይቱ የሚገኙ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች ሰሞኑን በየትምሕርት ቤታቸው ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር የተናገሩት የዐይን እማኞች ከ50 በላይ …

በቢሾፍቱ ወደ 50 የሚጠጉ ተማሪዎች ታሠሩ – VOA Read more »

የህገ-ወጥ አበራታች መድሀኒትን (performance-enhancing drugs) በመመርመር ረገድ አይኤኤኤፍ (IAAF) “ወሳኝ ደረጃ ላይ” ካስቀመጣቸው አምስት ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት ተብሏል። ሌሎቹ ኬንያ፣ ሞሮኮ፣ ዩክሬይንና ቤላሩስ ናቸው። ምርምራውን ካላካሄደች ያለው አማራጭ የአለም የህገ-ወጥ አበራታች መድሀኒት የሚቆጣጠረው ድርጅት (World Anti-Doping Agency)እርምጃ እንደሚገጥማት ምናልባትም ከአለም-አቀፍ …

ኢትዮጵያ 200 በሚሆኑ አትሌቶች ላይ ህገ-ወጥ አበራታች መድሀኒት ተጥቅመው እንደሆነ ምርመራ ትጀምራለች – VOA Read more »

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ ላይ ቃጠሎ ደርሷል። ቃጠሎው መድረሱን ያረጋገጡት የዩኒቨርሲቲው የፀጥታና ደኅንነት ኃላፊ በሕይወት ላይ ያጋጠመ ጉዳት አለመኖሩን ለቪኦኤ ገልፀዋል። ቃጠሎው ዳመራ በሚባለው የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ውስጥ በሚገኘው የተማሪዎች ማደሪያ ላይ የተነሣው ትናንት፤ ማክሰኞ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ እንደነበረ …

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቃጠሎ ደረሰ – VOA Read more »

በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል። በወታደራዊ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ያልፉ በነበረበት ወቅት አንዳንዶቹ ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ እንደከፈቱባቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጠቁመዋል። በተኩሱና ተያይዘው በደረሱ ጉዳቶች የሞቱና የቆሰሉ …

በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል – VOA Read more »

ባለፈዉ ክረምት በቂ ዝናብ ባለመጣሉ ግድቦች የሚጠበቀዉን ያህል ዉሃ እንዳልያዙና ያ ለእጥረቱ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ባለስልጣናት ገልጸዋል።