60ኛ ዓመቱን ያከበረዉ ብሔራዊ ቲያትር
በቅርቡ 60ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓልን ያከበረዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር፤ ከምሥረታዉ ጀምሮ የኅብረተሰቡን እሴትና ባህል መገንባቱን በቲያትር ቤቱ ያገለገሉና በማገልገል ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች ይናገራሉ። «ብሔራዊ ቲያትር ያደጉበት ቤቴ ነዉ» ያለችንን፤ የተውኔት ጸሐፊ፣ የቲያትር አዘጋጅ፣ ተዋናይና ገጣሚ ዓለም ፀሐይ ወዳጆ «ብሔራዊ ትያትር በእድሜ የበለፀገ፤ 60 ዓመት ማስቆጠሩ ብቻ ሳይሆን፤ ክላሲካል የሚባሉ ዛሬ በዓለም ላይ ድንቅ የሚባሉ ትያትሮች፤ እኔ አሁን ከአገር ወጥቄ ተሰድጄ ሳይና ሳወዳድር በዉጭ እንኳ ሊደፈሩ የማይችሉ፤ በዛ ደረጃ ይቀርባሉ ተብሎ የማይታመኑ፤ የነሼክፒርን ወይም ሌሎችን የዓለም ታላላቅ ደራስያን ሥራ ትርጉሞችን በትያትር መልክ ያቀረበ ቤት ነዉ፤ ብሔራዊ ትያትር። መድረኩ አመቺ ነዉ፤ አዳራሹ በዘመናዊ መልክ ተሰርቶ በጣም የተከበረና የተወደደ ቤት ነዉ። በዕለቱ ዝግጅታችን የዛሬ ስድሳ ዓመት ሕዳር 3, 1948 ዓ,ም በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተመርቆ ሥራዉን ስለጀመረዉ ስለቀድሞዉ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የአሁኑ ብሔራዊ ቲያትር የኪነ-ጥበባዊ ኤኮኖሚያዊ ብሎም ማኅበረሰባዊ ጉዞን እንቃኛለን። ያዳምጡ ↓