እንቅልፍ ከመተኛትዎ በፊት ማድረግ የሌለብዎን ያውቃሉ?  (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ✔ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የአካል ብቃት እቅስቃሴ ማድረግ ለጤናማ ሕይወት መሰረትና ለጥሩ እና ሰላማዊ እንቅልፍዎ ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡ ነገር ግን እንቅልፍ ከመተኛትዎ በፊት በ3 ሰዓታት ውስጥ የሚሰሩ ከሆነ የሰውነት ሙቀት …

እንቅልፍ ከመተኛትዎ በፊት ማድረግ የሌለብዎን ያውቃሉ? Read more »

ተስፋሁን አለምነህ – የምስራቅ አፍሪቃ መንግስታት ካላቸዉ አባገነንነት የተነሳ የጎንዮሽ ትብብራቸዉ ስልጣናቸዉን ማስቀጠል ላይ መሰረት ያደረገ ነዉ። የሃገር ሉአላዊነትን ባላስጠበቀ መልኩ መንቀሳቀስ ደግሞ ለወያኔ ልምዱ ነዉ። የኢትዮ-ሱዳን በአዲስ መልክ የድንበር ማካለል እንደ ሚደረግ የሱዳኑ ትሪቡን ጋዜጣ መዘገቡን ተከትሎ ግጭቱ አገርሽቶ …

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማካለል እንደሚደረግ መዘገቡን ተከትሎ ግጭቱ አገርሽቶ ወደ ለየለት የሞት ሽረት እያመራ ነዉ። Read more »

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

በፈረንጆች ባህል እውቀት ሥልጣን ነው፤ እንዲያውም እውቀት ኃይል ነው ይላሉ፡፡

በኢትዮጵያ ባህል እውቀት ሥልጣን የለውም፤ እንዲያውም ሥልጣን እውቀት ይመስለናል፡፡

በ1951 ዓ.ም. በትግራይ ችጋርን በዓይኔ አይቻለሁ፤ በጆሮዬ ሰምቻለሁ፤ በአካሌ ቀምሼዋለሁ፤ ጠኔ ይዞኝ ተደግፌ ወደቤቴ ገብቻለሁ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

በኦሮሚያ – ጊንጪ ከተማ ህዳር ዘጠኝ ቀን የጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም በምዕራብ ወለጋ ሁለት ከተሞች መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

በቆሎን የመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ✓ ለኪንታሮት ህመም እና ለፊንጢጣ ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል በቆሎ በፋየበር የበለፀገ ስለሆን እንደ ሆድ ድርቀት እና ተያይዞ የሚመጣውን የኪንታሮት ህመም ተጋላጭነት በእጅጉ ይቀንሳል። ✓ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ይዟል እንደ …

በቆሎ በፋየበር የበለፀገ ስለሆነ በቆሎን የመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

ኩባንያው ከስምንት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ እጅግ ሰፊ መሬት በርካሽ ሊዝ ዋጋ ሲወስድ «ይህ ክስተት በርካታ ገበሬዎችን ያፈናቅላል፣ ለተፈጥሮ ሐብት ውድመትም ያጋልጣል» በማለት ሲቃወሙ የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን «የጸረ ልማት ሃይሎች አጀንዳ ነው» በማለት መንግስት ሲያጣጥል መቆየቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ …

የህንዱ ካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ ኃ/ተ/የግ/ማ ጨረታ ወጣበት፡፡ Read more »

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News የህዳር 15 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (November 25, 2015 News) በድርቁ ምክንያት ከአሩሲ ተማሪዎች እየተሰደዱ መሆናቸው ታወቅ፤ በምስራቅና በምዕራብ ሀርርጌ በአንድ ወር ውስጥ የተረጅው ቁጥር በግማሽ ይጨምራል ተባለ የሳኡዲ ቱጃሮች ንብረታችን በወያኔ …

በድርቁ ምክንያት ከአሩሲ ተማሪዎች እየተሰደዱ መሆናቸው ታወቅ፤ በምስራቅና በምዕራብ ሀርርጌ በአንድ ወር ውስጥ የተረጅው ቁጥር በግማሽ ይጨምራል ተባለ Read more »

የዓዲ ግራት ወይም የዓጋመ ኣገር ሽማግሌዎች ቁጣ ህወሓትን ክፉኛ ኣስደንግጠዋል። Amdom Gebreslassie የኣገር ሽማግሌዎቹ ሰሞኑ የምስራቃዊ ዞን ኣስተዳዳሪ ወይዘሮ ያለም ፀጋይና ከክልል የመጡ ባለስልጣናት ያደረጉት ስብሰባ በዓጋመ ብሎም በትግራይ ኣጋጥሞ ያለው ምስቅልቅሉ የወጣው ዘርፈ ብዙ ችግር ለመፍታት ያለው ብቸኛ ኣመራጭ …

የዓዲ ግራት ኣገር ሽማግሌዎች ቁጣ ህወሓትን ክፉኛ ኣስደንግጠዋል። Read more »

ወያኔ ትግሬ ስጋ እንጂ ነብስ የለውም ( ኄኖክ የሺጥላ ) የፍገራ ፖለቲከኛ ፣ ወያኔና ትግሬ አንድ አይደሉም ይላል ። ይህ የሞግዚት ፖለቲካ ነው፣ ይህ ቀላዋጭነት ነው ፣ ይህ ስቃይን በአንቀልባ መሸከም ነው ፣ ይህ ራስን መካድ ነው ። እውነቱ ግን …

ወያኔ ትግሬ ስጋ እንጂ ነብስ የለውም ( ኄኖክ የሺጥላ ) Read more »

Minilik Salsawi – ከሃገር ውስጥ ነጋዴዎች ተገዝተው በተለያዩ ግለሰቦች አና የግል ተቋማት በኩል በድርቅ አና በረሃብ ለተጎዳው ሕዝብ በኣገዛዙ በኩል እንዲደርሱ የተለገሱ እህሎች በኣገዛዙ የደህንነት ሰዎች አና በስግብግብ ነጋዴዎች በተደረገ ስብጥር በተዘዋዋሪ አየተዘረፉ ለገበያ አንደሚቀርቡ ታውቋል። የእርዳታ አህሎቹ በድርቅ ለተጎዱ …

ክሃገር ውስጥ በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች ለእርዳታ ተለግሰዋል የተባሉ እህሎች በተዘዋዋሪ እየተዘረፉ ነው። Read more »

የስኳር በሽታን ተከትለው በዓይን ላይ የሚደርሱ ዋና ዋና የጉዳት ዓይነቶች ምን ይሆኑ? አስቀድሞ የሚታዩ ምልክቶችስ ይኖሩ ይሆን? ተከታታይ ቅንብራችን የሚመለከታቸው ጭብጦች ናቸው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ኒው ዮርክ ከተማ (የተራድኦ ድግስ ምሽት፥ ኅዳር ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ. ም. – November 14, 2015) [ ጌታቸው ኃይሌ ] ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንድታገለግሉ የተመረጣችሁ የተከበራችሁ ካህናትና ዲያቆኖት፥ የመድኃኔ ዓለም አባላት እንድትሆኑ የሐዋርያትን …

“በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የጽሑፍ ቅርስ ላይ ከአለኝ ትዝብት” (ዳንኤል ክብረት) Read more »

የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰሞኑን የኬንያን ድንበር ተሻግረው ሦስት የኬንያን ፖሊሶች በደፈጣ መግደል የሚናገሩ ዘገባዎች በኬንያ ጋዜጦች መውጣታቸው ይታወሣል፡፡ እኛም ጉዳዩን ለማጣራት እያደረግን ባለነው ጥረት ትናንት ያነጋገርናቸው የኬንያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ቻርልስ ኦዊኖ ደፈጣውን የፈፀሙትና የኬንያ ፖሊሶችን የገደሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮች ሳይሆኑ …

ኦነግ የመርሳቢቱን ጥቃት አልፈፀምኩም አለ – VOA Read more »

ኀዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አወዛጋቢው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም ከአመት በፊት አደባባይ የወጡ የኦሮምያ ክልል ወጣቶችና ተማሪዎች ህይወታቸው በመንግስት ታጣቂዎች ከተቀጠፈ በሁዋላ፣ ኢህአዴግ እቅዱን በድጋሜ ተግባራዊ ለማድረግ መንቀሳቀሱን ተከትሎ በአምቦ፣ በማንዲና በዙሪያ ከተሞችና ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። ለኢሳት ደረሱት መረጃዎች እንደማለከቱት አካባቢው ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሁሉ …

ኀዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፎገራ ወረዳ፣ ወረታ ከተማ በቁሃር ሚካኤል ቀበሌ ነዋሪ የሆነው መንግስቴ ቢምር የተባለ የአካባቢ ሹም የህብረተሰቡን መሳሪያ በማስፈታት ከኢህአዴግ ጋር ሲሰራ ነበር በሚል መገደሉን ተከትሎ፣ እስካሁን በቁጥጥር ስር ያልዋሉት ገዳዮች በተገኙበት እንዲገደሉ መወሰኑን ምንጮች ገልጸዋል። ከሹሙ ግድያ ጋር በተያያዘ እየተፈለጉ ያሉትና ባለቡት ይገደሉ የተባሉት አርሶ አደር መንጋው …

መቀመጫዉን ዬኤስ አሜሪካ ኒዮርክ ከተማ ላይ ያደረገዉ ለጋዜጠኞች የሚሟገተዉ ድርጅት «ሲፒጄ» የተባለ ተቋም ለዞን ዘጠኝ ጦማርያን የ 2015 ዓ,ምን ዓለማቀፍ የፕሪስ ነፃነት ሽልማት አበረከተ።

ፓፓያ በሆድ ውስጥ የሚገኙ ትላትሎችን ለማጥፋት እና የጨጓራን አሲድነት ይቀንሳል፡፡ የፓፓያ ጁስ መጠጣትን ልምድ ማድረግ በአንጀት ውስጥ የሚፈጠርን ኢንፌክሽን እና ጎጂ ፈሳሽ ጠርጎ ያወጣል፡፡ ፓፓያ ዝቅተኛ የካሎሪ እና ከፍተኛ የጠቃሚ ምግብ ይዘት ስላለው በውፍረት መቀነስ ሂደት ውስጥ ላሉ ሰዎች አስተዋጽዖው …

ፓፓያ እና የጤና ጥቅሞቹ Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

የፊታችን ማክሰኞ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በብራስልስ ቤልጄም በሚገኘው የኣውሮፓ ሕብረት ፓርላማ ላይ በረሃቡ አና ድርቁ ዙሪያ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፥ለትጥቅ ትግል ኣስመራ የገቡት ፕሮሬሰሩ በኣውሮፓ ፓርላማ አባል በሆኑት በወይዘሮ ኣና ጎሜዝ ጋባዥነት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በረሃቡ አና …

የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር በኣውሮፓ ሕብረት በረሃቡ አና ድርቁ ዙሪያ ንግግር አንዲያደርጉ በኣና ጎሜዝ ተጋበዙ። Read more »

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ከሲፒጂ የኣለም ኣቀፍ የፕሬስ ነጻነት የ2015 ሽልማት በክብር ተቀበሉ። Ethiopia’s Zone 9 bloggers were honored with the 2015 International Press Freedom Awards on Tuesday in New York City.  http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=107092

ጋዜጠኞች ከመንግስት አካላት መረጃ በማግኘት ረገድ ከፍተኛ ችግር እንዳለባቸዉ ተመለከተ። ይህ የተገለፀዉ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ዛሬ በሂልተን ሆቴል ባካሄደዉ የምክክር መድረክ ነዉ።

በኣምቦ አና ኣከባቢዋ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ከፍተኛ ተቃውሞ ሲሰማ ውሏል፥ይህም ተቃውሞ በጎረቤት ከተሞን የተዛመተ መሆኑ ታውቋል። Protest has erupted in Ambo and spreading to neighboring towns ~Protesters in Mandi have blocked the road that pass through the town

ረሃብ የወለደው መርዶ ************* ዛሬ እሮብ 15 / 03 / 2008 ዓ/ም ከቀኑ ኣምስት ሰዓት ኣከባቢ ከሑመራ ኣደባይ ቀበሌ የደረሰኝ የስልክ ጥሪ እጅግ የሚያሳዝን ረሃብ የፈጠረው መርዶ ነበር። ዛሬ ረፋድ የኣደባይ ከተማ ህዝብ ኣንዲት በረሃብ የሞቱት እናት ቀብር መዋሉን ከቦታው …

በረሃብ ጠኔ ኣደጋ የሟቾች ቁጥር አየጨመረ ነው፥ በሁመራ ሰዎች አየሞቱ ነው። Read more »

–    በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀ መተዳደርያ ደንብ ያለው የማኅበረ ቅዱሳን ፕሮግራም ይገኝበታል –    ጉዳዩ ለምእመናንና ለቤተ ክርስቲያኒቱ ግርታና ክፍተት እንዳይፈጥር ማኔጅመንቱ ጠይቋል   ሕጋዊነቱና ተቀማጭነቱ በአሜሪካ የኾነው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (ኢ.ቢ.ኤስ) ቴሌቪዥን ሜኔጅመንት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም መንፈሳዊ ዝግጅት …

ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን፤ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስም በሚተላለፉ ፕሮግራሞች ላይ ጊዜያዊ እገዳ አስተላለፈ Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ቁጭ ብሎ የማህበራዊ ድረ ገጽ ፉጨቶችን ልትሚያዎችን ጡዘቶችን እያዩ መታዘብ ደስ ይላል::የረሃቡን እና የድርቁን አጀንዳ ለመደበቅ ካርታውን ለመፐወዝ በወያኔ የተደረጉ ጥረቶች ከሞላ ጎደል ተሳክተዋል ቢባልም ወያኔ አስቻ ሰአት እየጠበቀ የሚጫወተው ሚና ስሜታውያን እና ያልበሰሉ ፖለቲካኛ …

ክሕወሓት ብኣዴን ተፋጩ እስከ ሰማያዊ ፓርቲ የስልጣን ማግለል አጀንዳ በማህበራዊ ድረ ገጽ ሲፈተል (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

መራዊ ላይ የታሰሩት ወጣቶች ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባቸው • ሁለቱ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ናቸው ህዳር 4/2008 ዓ.ም በምዕራብ ጎጃም ዞን መራዊ ከተማ የታሰሩት 8 ወጣቶች ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ ህዳር 4/2008 ዓ.ም በሌሊት ቤታቸውን ተበርብሮ ከታሰሩት መካከል በተለይም …

በምዕራብ ጎጃም ዞን መራዊ ላይ የታሰሩት ወጣቶች ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባቸው Read more »

ተለጣፊው የትእግስቱ ኣወሉ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ላለፉት ስድስት ወራት የተጠቀመበትን የቢሮ ኪራይ ባለመክፈሉ፣ የቤቱ አከራይ አቶ ዘካሪያስ ብርሃኑ ክስ መመሥረታቸውን ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡ ቀበና አካባቢ የሚገኘውን ይህ ቤት ፓርቲው ላለፉት አራት ዓመታት ያህል በዋና ጽሕፈት ቤትነት እየተገለገለበት የሚገኝ ሲሆን፣ …

ተለጣፊው የትእግስቱ ኣወሉ አንድነት ፓርቲ የቢሮ ኪራይ ባለመክፈሉ ክስ ተመሠረተበት Read more »

ከኤልኒኖ የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች የተከሰተው ድርቅ እያሳረፈ ያለው ተፅዕኖ እየሰፋ መምጣት የተረጂዎችን ቁጥር እንዲጨምር እያደረገ ነው፡፡ ሰሞኑን በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመቃኘት የተንቀሳቀሰው የጋዜጠኞች ቡድን ከተመለከታቸው አካባቢዎች መካከል፣ የምዕራብና የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ውስጥ ከወራት በፊት የነበሩት …

የምሥራቅና የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ተረጂዎች ቁጥር ከ50 በመቶ በላይ ጨምሯል Read more »

ማክሰኞ ኅዳር 14 ቀን 2008 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ በፌስቡክ ገጹ ከፓርቲው ጋር መለያየቱን፣ ከአሁን በኋላ የሚወክለው የፖለቲካ ድርጅት እንደሌለና የሚወክለው ራሱን ብቻ እንደሚሆን ገልጿል፡፡ ‹‹ከአሁን በኋላ ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ቡድን የማልወክል እንደሆነ አሳውቃለሁ፡፡ የእኔ ውክልና ለራሴ ብቻ ነው፤›› ይላል …

የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው ወጣቱ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ከፓርቲው ጋር መለያየቱን አስታወቀ፡፡ Read more »

ሁለት ወጣቶች በሚንያፖሊስ ከተማ፣ ሚነሶታ መኪና ውስጥ በተኩስ ተገድለው መገኘታቸውንና ሶስተኛው ወጣት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገለት መሆኑ ታውቋል። ባለፈው እሁድ እአአ ሕዳር 22 2015 ምሽት ላይ ሁለት ወጣቶች በሚንያፖሊስ ከተማ፣ ሚነሶታ መኪና ውስጥ በተኩስ ተገድለው መገኘታቸውንና ሶስተኛው ወጣት …

በሚነሶታ ሁለት ኢትዮጲያውያን ሞቱ ፣ አንዱ ደግሞ የከፋ ጉዳት ደርሶበታል – ህዳር 25, 2015 Read more »

የግዳጅ የቦንድ ግዥን ተግባራዊ ለማድረግ ወያኔ ለባንኮች ለኤንሹራንስ ኩባንያዎችና ለጡረታ ተቋሞች ተጨማሪ መመሪያ ሊያወጣ ነው፤ በወሰን አካባቢ በወያኔ ወታደሮችና በኬኒያ መካከል ውጥረቱ አለ ይባላል፤ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ጫና እያሳደረ ነው፤ በዚህ ሳምንት ካርቱም ውስጥ ሊደረግ ታቅዶ የነበረው የሶስትዮሽ ስብሰባ ላልተወሰነ …

የግዳጅ የቦንድ ግዥን ተግባራዊ ለማድረግ ወያኔ ለባንኮች ለኤንሹራንስ ኩባንያዎችና ለጡረታ ተቋሞች ተጨማሪ መመሪያ ሊያወጣ ነው፤ Read more »

በመሰራጨት ያለው ጥቂት የእርዳታ እህል ለመዳበርያ፣ ለደደቢት፣ ለማህበራት፣ ለወይን ጋዜጣ ፣ ለኣንቡላንስ ወዘተ እየተባለ እየተቆረጠ ነው። ቅምያው ህዝቡ ክፉኛ እየተቃወመው ይገኛል።ረሃቡ በሰውና በእንስሳ ሂወት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ የሚታወቅ ነው። የደጉዓ ተምቤን ወረዳ ሃላፊዎች በድርቅ የተጠቁ ቀበሌዎች ኣመራሮች ሰብስበው ” …

በመሰራጨት ያለው ጥቂት የእርዳታ እህል ለመዳበርያ፣ ለደደቢት፣ ለማህበራት፣ ለወይን ጋዜጣ ፣ ለኣንቡላንስ ወዘተ እየተባለ እየተቆረጠ ነው። Read more »

የጆሮ ኢንፌክሽን በባክቴሪያ ወይንም በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ችግር ሲሆን ከ3 ወር እስከ 3 ዓመት ባሉ ሕፃናት ላይም ጎልቶ ይታያል፡፡ ነገር ግን በሁሉም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች በህመሙ ሊጠቁ ይችላሉ፡፡ በአብዛኛው ከጉንፋን በኋላ የሚመጣ ችግር ሲሆን ምክንያቱም የመካከለኛው የጆሮ ክፍል ከኋለኛው …

የጆሮ ኢንፌክሽን (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

*ለካንሰር ህመም የክሮሽያ ተመራማሪዮች ጥቁር አዝሙድ በውስጡ የያዛቸው ንጥረ ነገሮች የካንሰር ሴሎችን የመቀነስ ሀይል እንዳለው ይናገራሉ። *ለጤናማ ጉበት ጥቁር እዝሙድ ለጉበት ጤና እጅግ ጠቃሚ ሲሆን መድሀኒት በብዛት በመውሰድ፣ በአልኮል መጠጥ ወይንም በሌሎች ህመሞች ምክንያት የተጎዳን ጉበት የመዳን ሂደትን ያፋጥናል። *ለቆዳ …

የጥቁር አዝሙድ የጤና ጥቅሞች (በዶር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

የጆሮ ሕመም በአብዛኛው በልጆች ላይ የሚከሰት ሲሆን በአዋቂዎች ላይም ይታያል፡፡ የሕመሙ ዓይነት አልፎ አልፎ የሚመጣ ወይንም ዘላቂ የሆነ ሊሆን የሚችል ሲሆን በአንደኛው ጆሮ ብቻ አልያም በሁለቱም ጆሮዎች ሊከሰት ይችላል፡፡ ✔ የጆሮ ሕመም መከሰት ምክንያቶች የጆሮ ሕመም በራሱ በጆሮ ላይ በሚደርስ …

የጆሮ ሕመም(Ear Pain) (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ በአዛዙ የአፈና መዋቅር የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነትና የእኩልነት ትግል አይቀለበስም! ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱና በሌሎች ራሱ ባወጣቸው ህጎች በርካታ መብቶችን ለይስሙላ ቢደነግግብ ቅሉ፤ በተግባር ግን እነዚህን መብቶች ሆነ ብሎ ባደራጀው የአፈና መዋቅሩ እየደፈቃቸው ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን አገዛዙ የመደራጀት …

በአገዛዙ የአፈና መዋቅር የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነትና የእኩልነት ትግል አይቀለበስም! – ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ Read more »

የማለዳ ወግ … የሳውዲው ባለሃብት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ቅሬታ ማሰማት ጀመሩ ! ========================================= * “በኢትዮጵያ በደልና ዘረፋ ተፈጸመብን !” ባለሃብቱ! * ” ቅሬታ ውንጀላው መሰረት ቢስ ነው ” የኢትዮጵያ ዲፕሎማት ዛሬ በወጣው ታዋቂው የሳውዲ ጋዜጣ አረብ ኒውስ የኢትዮጵያ መንግስት አንዳንድ …

የሳውዲው ባለሃብት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ቅሬታ ማሰማት ጀመሩ ! Read more »

የአንከር ወተት ማስታወቂያ ታገደ

ከኢትዮጵያ መድኃኒት፣ ምግብና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን ጥቅምት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ለብሮድካስት ባለሥልጣን በተጻፈ ደብዳቤ የአንከር ወተት የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ኅዳር 2 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዲታገድ

መደረጉን፣ የባለሥልጣኑ ሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ጣፋ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ሪፖርተር ከመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባሥልጣን ምንጮችና ከብሮድካስት ባለሥልጣን መረዳት እንደቻለው፣ ማስታወቂያው እንዲቋረጥ የተደረገው በሦስት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመርያው ወተቱ ከኒውዚላንድ መጣ የሚለው የማስታወቂያው ነጥብ እየተነገረ እንዳለው ሳይሆን፣ እዚህ አገር የሚቀነባበርና የሚታሸግ መሆኑ መገለጽ አለበት የሚል ነው፡፡ 

ሁለተኛው ደግሞ ምንም እንኳ የወተቱ ማሸጊያ ላይ የተቀመጠ ቢሆንም፣ በቴሌቪዥን በሚነገረው ማስታወቂያ ወተቱን ሊጠቀሙ የሚችሉ የዕድሜ ገደብ ሊገለጽ ይገባል የሚል ነው፡፡ የመጨረሻው ከሰላሳ በላይ ንጥረ ነገሮች ያሉት ተብሎ መነገሩ የሚያሳየው ይህ ነው የሚባል ግልጽ ቁጥር ባለመኖሩ፣ በትክክል በውስጡ የሚገኘው ንጥረ ነገር መጠን መቀመጥ ይኖርበታል የሚል ነው፡፡ 

የኒውዚላንድ ሚልክ ፕሮዳክትስ ኢትዮጵያ ሼር ካምፓኒ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘኮ ኢብሮ ማስታወቂያው ሲነገር መገለጽ ነበረባቸው የተባሉት መረጃዎች በወተቱ እሽግ ላይ መገለጻቸውን በመጠቆም፣ በማስታወቂያው ያልተነገሩት በሰላሳ ሰከንድ ውስጥ ዋና ዋና ነገሮችን ለመግለጽ ሲባል መሆኑን ይናገራሉ፡፡ 

የወተቱ ዱቄት በእርግጥም የኩባንያው እናት ኩባንያ ከሆነው የኒውዚላንዱ ፍሮንቴራ ኩባንያ እንደሚመጣ ገልጸዋል፡፡ ያላቸው የንግድ ፈቃድም እዚህ አገር ለማደባለቅና ለማሸግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

እሳቸው እንደገለጹት፣ የተጠቃሚዎች ዕድሜን ስለመግለጽና የወተቱን ‹ከኒውዚላንድ የመጣ› በሚል መተዋወቅን በሚመለከት፣ ከመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር ተነጋግረው መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ማስታወቂያውን ሲያሠራጭ ከነበረው ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ጋርም እንዲሁ ተነጋግረዋል፡፡ 

ወተቱ ምን ያህል ንጥረ ነገር አለው? (ትክክለኛ ቁጥር) የሚለውን ለማወቅ የላብራቶሪ ምርመራ እንዲደረግ ስምምነት ላይ ተደርሶ ናሙና ወደ ውጭ ተልኮ ውጤት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን አቶ ዘኮ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

ማስታወቂያው እንዲቋረጥ የተደረገው ትክክለኛውን ምግብና ምግብ ነክ ነገሮች የሚተዋወቁበትን አግባብ ተከትሎ እንዲተዋወቅ ለማድረግ ሲባል እንደሆነ፣ በሚመለከታቸው የቁጥጥር ተቋማት ተገልጿል፡፡ 

በፋፋ ፉድስ ኢትዮጵያና በኒውዚላንድ ወተት አምራች ድርጅት ፎንቴራ የአሥር ሚሊዮን ዶላር የጋራ ኢንቨስትመንት፣ አንከር ወተት በዚህ ዓመት መጀመርያ ላይ ለገበያ መተዋወቁ ይታወሳል፡፡ 

 

ፖሊስ የቤተሰብ አባላትን እየጠረነፈ ነው ፖሊስ ቤተሰብን በወረዳ፣ በብሎክ ብሎም በቤት ደረጃ በማደራጀት እየጠረነፈ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በየካ ከፍለ ከተማ በየግቢው የታደሉ ‹‹የቤተሰብ ተጠሪ ፎረም›› የሚሉ ቅፆችን በማስደገፍ መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን በሳሪስ በተመሳሳይ አደረጃጀት ቤተሰቦችን …

ፖሊስ ቤተሰብን በወረዳ፣ በብሎክ ብሎም በቤት ደረጃ በማደራጀት እየጠረነፈ ነው:: Read more »

በዛሬው አለት ሉሲ (ድንቅነሽ) በኣፋር ክልል በ፲፱፮፮ ኣመተምህረት የተገኘችበት ኣርባ ኣንደኛ ፵፩ ኣመቷ ነው። http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=107047  

News Ethiopia Wetatoch Dimts 99 23.11. 2015 መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም የስፖርት ዘገባዎች መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ [youtube http://www.youtube.com/watch?v=xYH0l834N44]  

በጦርነቱ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች መሞታቸውና ንብረት መውደሙ ተገልጿል

በደቡብ ክልል ሸካ ዞን ይዞታቸው ለኢንቨስተር በመሰጠቱ ምክንያት ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው ጥያቄ በማቅረባቸው ‹‹ለሕግ ተገዢ አይደሉም›› በማለትና በሽፍታነት በመፈረጅ፣ በሸኮዎች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ሸካዎችን በማስታጠቅና

የእርስ በርስ ጦርነት በማነሳሳት የተጠረጠሩ፣ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ 12 ተሿሚዎች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ 

የደቡብ ክልል መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተዘዋዋሪ አንደኛ ወንጀል ችሎት ኅዳር 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ያቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው፣ የሸኮ ብሔር ተወላጆችና የየኪ ወረዳ ፃኑ ቀበሌ ጉፍታ ንዑስ መንደር ነዋሪዎች ይዞታ ለኢንቨስተር ተሰጥቷል፡፡ ነዋሪዎቹ ለረዥም ዓመታት ምትክ ቦታና የንብረት ግምት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ጥያቄያቸውን በመቀበል ምላሽ መስጠት ያልፈለጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝመራ አንደሞና የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ‹‹ለሕግ ተገዢ አይደሉም›› በማለትና በወንጀለኛነትና በሽፍታነት በመወንጀል፣ በዞኑ ፖሊሶች ተይዘው እንዲታሰሩ ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡ 

ሕጋዊ መብታቸውን በመጠየቃቸው ወንጀለኞች የሚል ስያሜ በመስጠት ነዋሪዎቹን በመተባበር በማሰርና የእርስ በርስ ጦርነት እንዲነሳ ያደረጉት ተጠርጣሪዎች የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝመራ አንደሞ፣ በዞኑ የደኢሕዴን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ፣ የየኪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ሻረው፣ የየኪ ወረዳ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አምሳሉ ከሴቶ፣ የቴፒ ከተማ ከንቲባ አቶ ሻሎ አድሎና ሌሎችንም ተጠርጣሪዎች ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሯል፡፡ 

ተጠርጣሪዎቹ ከ30 በላይ የፖሊስ አባላትን መሣሪያ በማስታጠቅ፣ ሚያዝያ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ፃኑ ቀበሌ ጉፍታ ንዑስ መንደር በመሄድ የሸኮ ብሔር ተወላጆችን ከበው መያዛቸውን የሚገልጸው የዓቃቤ ሕግ ክስ፣ ያልተያዙት የአካባቢው ነዋሪዎች በሁኔታው በመደናገጥና በመረበሽ ንብረታቸውንና ቤታቸውን ጥለው አጎራባች ወደሆነው ጋምቤላ ክልል ዶንቻዬ ቀበሌ መሰደዳቸውንም ያስረዳል፡፡ 

የሸኮ ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ትተው ሲሰደዱ ተጠርጣሪዎቹ ‹‹አካባቢውን ተቆጣጥረነዋል›› በማለት አካባቢው ላይ ባንዲራ መትከላቸውንና ተመልሰው ሲመጡ ዕርምጃ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን ንዑስ የፖሊስ ጣቢያ መክፈታቸውም ተገልጿል፡፡ በአካባቢው ምሽጎችን ቆፍረው ለውጊያ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አካቷል፡፡ 

ድንገት በተፈጠረባቸው ወረራ ወደ አጎራባች ክልል የተሰደዱት ሸኮዎች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ ሕገወጥ ድብደባና እስር በተጠርጣሪዎቹ ሲፈጸምባቸው ቆይቶ፣ ድርጊቱ ወደ እርስ በርስ ግጭት ተቀይሮ በሸኮዎችና በሸካ ብሔረሰቦች መካከል ጦርነት እንዲፈጠር ማድረጋቸውንም የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ 

በሸኮዎችና በሸካ ተወላጆች መካከል በተደረገ የእርስ በርስ ጦርነት ስማቸው የታወቁ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ማረጋገጡን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡ በተጨማሪም ስማቸውን ማወቅና መለየት ያልተቻለ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን ባቀረበው ክስ ላይም ገልጿል፡፡ ከሰባት የሚበልጡ ነዋሪዎችም ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና የገቡበት እንዳልታወቀም አክሏል፡፡ ጦርነቱ ከእነሱ አልፎ ወደ አጎራባች ቀበሌዎች እንዲስፋፋና በዞኑ የፀጥታ ችግር እንዲሰፍን ምክንያት መሆናቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ አስረድቷል፡፡ 

ተከሳሾቹ ‹‹ወደዳችሁም ጠላችሁም የዞኑና የወረዳው ቁልፍ ያለው በእኛ እጅ ነው›› በማለት በሁለቱ ብሔረሰቦች መካከል የተነሳው ግጭት ወደ ቴፒ ከተማ አስፋፍተዋል፡፡ በግንቦት ወር 2007 ዓ.ም. የቴፒ ከተማ ፖሊስ አባላት የሆኑ አምስት ፖሊሶች ወደ ጫካ ገብተው በነበሩ የሸኮ ተወላጆች እንዲገደሉ ማድረጋቸውንና ግጭቱ እስካሁን እንዲቀጥል ማድረጋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ ተከሳሾቹ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቀዬአቸው እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸውን፣ በሕዝብ ደኅንነትና ኑሮ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ማስከተላቸውንና የእርስ በርስ ጦርነት የማነሳሳት ወንጀል መፈጸማቸውን ዓቃቤ ሕግ አብራርቷል፡፡ 

ተከሳሾቹ በተሰጣቸው ሥልጣንና ኃላፊነት ሕግና ሥርዓትን ተከትለው ኅብረተሰቡን ማገልገል ሲገባቸው፣ ሥልጣናቸውን ተገን በማድረግ ሆን ብለውና አስበው በሕገወጥ ተግባራት በመሰማራት በሕዝብና በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አብራርቶ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን ጉዳይ የሚያየው በተዘዋዋሪ ችሎት ቢሆንም፣ የሚቀጥለው ችሎት መቼ እንደሚሰየም አልታወቀም፡፡ 

 

ለሕመም ማስታገሻ የሚውለው ኮዴይን ጥቅም ላይ እንዳይውል ታገደ

የኢትዮጵያ የመድኃኒት፣ የምግብና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 1 ቀን 2015 ባሠራጨው ሰርኩላር፣ ኮዴይን የተባለው የሕመም ማስታገሻ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡ 

ባለሥልጣኑ ለክልሎችም ሆነ ለፌዴራል መንግሥት የጤና ቢሮዎች በላከው ደብዳቤ እንደገለጸው፣ ኮዴይን የተባለው መድኃኒት ለኢትዮጵያውያን የዘረ መል አወቃቀር (Genetic Makeup) የማይስማማ መሆኑንና ጥቅም ላይ ከዋለም እስከ ሞት ሊያደርስ እንደሚችል በጥናት መረጋገጡን አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣኑ ዕገዳውን ያደረገው የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር በኢትዮጵያና በሌሎች አገሮች ላይ አተኩሮ ባከናወነው ጥናት፣ ኮዴይን የተባለው የሕመም ማስታገሻ እስከ ሞት የሚያደርስ መሆኑን በማሳወቁ ነው፡፡ 

የተሠራው ጥናት እንዳመለከተው በዘረ መል አወቃቀር ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ኮዴይን ሲወስዱ ወደ ሞርፊን እንደሚቀየር፣ በዚህም ምክንያት በደም ውስጥ የሚገኘውን የሞርፊን መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር ለመተንፈስ ችግር ብሎም ለሞት እንደሚያደርስ ተገልጿል፡፡ 

በመሆኑም ማንኛውም የጤና ባለሙያና የጤና ተቋም ኮዴይን የተባለውን የሕመም ማስታገሻ በየትኛውም ዕድሜ ለሚገኙ ታካሚዎች በሕመም ማስታገሻነት ወይም ለብርድና ለሳል ሕመሞች እንዳያዙ ደብዳቤው የደረሳቸው የጤና ቢሮዎች፣ በሥራቸው ለሚተዳደሩ የጤና አገልግሎት ተቋማት እንዲያስተላልፉ አዟል፡፡ ዕገዳው የተደረገው ላልተወሰነ ጊዜ እንደሆነ ቢገልጽም፣ ላልተወሰነ የተባለበት ጊዜ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ደብዳቤው አይገልጸም፡፡ 

ጉዳዩን በተመለከተ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ በተደጋጋሚ ቢደወልም ጥሪውን አልመለሱም፡፡ የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ምርመራ ከተካሄደባቸው 122 ኢትዮጵያውያን መካከል 29 በመቶ የሚሆኑት ወይም 35 ኢትዮጵያውያን የዘረ መል አወቃቀር ኮዴይን በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ሞርፊን የሚቀይር ኢንዛይም አላቸው፡፡ 

ይህ የጥናት ውጤት ከተገለጸ ስድስት ወራት ቢሆነውም የኢትዮጵያ የመድኃኒት፣ የምግብና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ውሳኔ ሳይወስድ እስከተጠቀሰው ቀን ቆይቷል፡፡ በተመሳሳይ ጥናት የአዲስ አበባ የወተት አቅርቦት ለካንሰር የሚዳርግ አፍላቶክሲን የተባለ ውህድ እንዳለው ከተገለጸ ከስድስት ወራት በኋላ መረጃው በተለያዩ የማኅበራዊ ድረ ገጾች ሲለቀቅ፣ ባለሥልጣኑ የራሱን ተጨማሪ ጥናት እያከናወነ መሆኑን ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን መግለጹ አይዘነጋም፡፡ 

 

“የኢትዮጵያ ወታደሮች የኬንያን ድንበር ዘልቀው ሦስት የኬንያ ፖሊሶችን ገደሉ” ሲሉ የኬንያ ጋዜጦች ፅፈዋል፤ የሃገሪቱ ፖሊስ ግን ሰዎቹን የገደሉት የኢትዮጵያ ታጣቂ አማፂያን እንጂ የመንግሥቱ ወታደሮች አይደሉም ይላል፡፡

ኅዳር 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ ከጓንግዙ ቻይና ወደ አዲስ አበባ በመብረር ላይ የነበረ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 777 አውሮፕላን ውስጥ የተሳፈረ መንገደኛ፣ በስካር መንፈስ ሁከት በመፍጠሩ በመንገደኞች ርብርብ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡

የበረራ ቁጥር ኢቲ607 ከ300 በላይ መንገደኞች አሳፍሮ ከጓንግዙ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የተነሳው ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ነበር፡፡ አንድ ሰዓት ተኩል ከበረረ በኋላ በበረራ አስተናጋጆች አማካይነት ለመንገደኞች እራት ቀርቦ ካበቃ በኋላ፣ አብዛኛዎቹ መንገደኞች አሸልበው ነበር፡፡

በአውሮፕላኑ የተሳፈሩ መንገደኞች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ከእንቅልፋቸው የነቁት በሰሙት ጩኸት ምክንያት ነበር፡፡ በኢኮኖሚ ክፍል የነበሩ የበረራ አስተናጋጆች እየተጯጯሁ ወደ ቢዝነስ ክፍል ሲሮጡ መመልከታቸውን መንገደኞች ተናግረዋል፡፡ ከእንቅልፋቸው ተደናግጠው የተነሱ የተወሰኑ መንገደኞች የበረራ አስተናጋጆቹን ተከትለው ሮጠዋል፡፡

‹‹የበረራ አስተናጋጆቹ ሊገለን ነው›› እያሉ እየሮጡ ወደ ቢዝነስ ክፍል መምጣታቸውን የገለጹት ተሳፋሪዎች፣ ዕድሜው በ30ዎቹ መጨረሻ የሚገመት ናይጄሪያዊ መንገደኛ በስካር መንፈስ ተገፋፍቶ የበረራ አስተናጋጆችን ለመደብደብ ሲያባርር መመልከታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በዚህን ወቅት በቢዝነስ ክፍል ውስጥ የተሳፈሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት፣ በቢዝነስ ክፍል መግቢያ ላይ ጠብቀው ከሁከት ቀስቃሹ ናይጄሪያዊ ጋር ግብግብ ፈጥረዋል፡፡ ናይጄሪያዊው ግዙፍ ቢሆንም ኢትዮጵያዊው ባለሀብት እንደምንም ብለው መተናነቃቸውን ገልጸው፣ ሌሎች ናይጄሪያዊያን መንገደኞች ባደረጉላቸው እገዛ ግለሰቡን ከወለል ላይ ሊጥሉት ችለዋል፡፡ መንገደኞቹ ነውጠኛውን ተሳፋሪ በደረቱ በማስተኛት እጁን የኋሊት አስረውታል፡፡ ግለሰቡ መጠጥ መጠጥ ይሸት እንደነበር መንገደኞች ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሪፖርተር በላከው ማብራሪያ፣ ግለሰቡ በአውሮፕላኑ ውስጥ የአልኮል መጠጥ እንዳልቀረበለት ገልጿል፡፡ ለመንገደኛው የቀረበለት ለስላሳ መጠጥና ምግብ ብቻ እንደሆነ የጠቆመው አየር መንገዱ ግለሰቡ ግን ሰክሮ እንደነበር ይታመናል ብሏል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው መንገደኞች ግለሰቡ አውሮፕላኑን ከመሳፈሩ በፊት፣ የአልኮል መጠጥ በብዛት ሳይወስድ እንዳልቀረ ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡

የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ነውጠኛው ግለሰብ በሌሎች ተሳፋሪዎችና በአውሮፕላኑ ላይ ጉዳት ሳያደርስ፣ ከሌሎች ተሳፋሪዎች ጋር በመተባበር ሁኔታውን መቆጣጠራቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ አውሮፕላኑ ለሰባት ሰዓታት ያህል በመብረር ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በሰላም አርፏል፡፡ መንገደኞቹና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ግለሰቡን ለኤርፖርት ደኅንነት ሠራተኞች አስረክበዋል፡፡ ግለሰቡ ለፌደራል ፖሊስ ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ፣ ፖሊስ ምርመራ እያካሄደበት መሆኑ ታውቋል፡፡

ከግለሰቡ ጋር ግብግብ የፈጠሩት ተሳፋሪዎች ለወደፊቱ ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጠር በግለሰቡ ላይ ጠንከር ያለ ቅጣት ሊጣል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ‹‹የፖሊስን ሪፖርት ተመልክተን በቀጣይ መደረግ ስላለበት ጉዳይ እንመክራለን፤›› ያለው አየር መንገዱ፣ የፖሊስ ምርመራ ከተጠናቀቀ በኋላ በግለሰቡ ላይ የወንጀል ክስ ይመሠረታል የሚል እምነት እንዳለው አስታውቋል፡፡

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ኀዳር ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወሎ፣ቆቦና ዋግ ህምራ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች የዘንድሮው ድርቅ ከ1977ቱ ያልተለየ ነው በማለት ለኢሳት ተናገሩ፡፡ ተጎጂዎች በድርቁ በርካታ ሃብት ንብረታቸውን በመጨረሳቸው ባዶ እጃቸውን እንደቀሩ ይናገራሉ፡፡የገዢው መንግስት ሚዲያዎች በድርቁ የሞተ ሰው የለም በማለት ለማስተባበል ቢሞክሩም ተጎጅዎቹ ‹‹ ከሃብታችን ባሻገር ልጆቻችን እየተነጠቅን ነው፡፡ ›› በማለት በተጨባጭ ያለውን የወቅቱን …

ኀዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጊቱ የተፈጸመው ባለፈው መስከረም ወር ሲሆን የቀብሩ ስነስርዓት የተፈጸመው ግን ባሳለፍነው ሳንምት ነው። በመተከል ዞን በዳንጉር ወረዳ 12 የአማራ ተወላጆች ለቀን ስራ ተብለው ከተወሰዱ በሁዋላ በወረዳው አስተዳደሪ ትእዛዝ ኮከል ቀበሌ ላይ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተረሽነዋል።አስከሬናቸው ተቆራርጦ በጆንያ ተጠቅሎ መገኘቱንና የቀብር ስነስርዓታቸውም መፈጸሙን ምንጮች ገልጸዋል። የተገደሉት ነዋሪዎች …