ለሕጋዊው ሲኖዶስ የተጻፈ ግልጽ ደብዳቤ
ከፖርትላንድ ኦሬገን ቅድስት ማርያም ምዕመናን ከሁሉም በፊት የእግዚአብሔር ሠላምታችን እናስቀድማለን። ይህን ግልጽ ደብዳቤ እንድንጽፍ ያነሳሳን ወይም ያስገደደን በአጥቢያ ቤተክርስትያናችን ማለትም በፖርትላንድ ኦሬገን የደብረ-ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን አገልጋይ ካህን በሆኑት ቀሲስ ኤፍሬም የኋላሸት እና በምእመናን መካከል ያለው ሥር የሰደደ ችግር ነው። …