የአፍሪካ የጥሩ መሪነትን የብቃት ደረጃ ይፋ ሆነ: አቶ መለስ 39 ደረጃ ላይ ይገኛሉ

በታምሩ ገዳ
አቶ መለስ ዜናዊ በአፍሪካ ውስጥ ካሉ መሪዎች በአስተዳድራቸው ደካማ ነጥብ ከተሰጣቸው ከመጨረሻዎቹ እና ሰልጣንን ሙጥኝ ከአሉት በጣት ከሚቆጠሩት የአገር መሪዎች ተርታ ተካተቱ፡፡
የፈርንጆቹን አሮጌ አመት መገባደድን ተከትሎ በአህጉሪቱ ውስጥ የተደረጉ የተለያዩ አገራዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮችን በመዳስስ እና የሃምሳ ሁለት (52) የአፍሪካ አገሮች መሪዎችን የጥሩ መሪነትን የብቃት ደረጃን በተመልከተ ጥናት ያደርገው ዘ ኢስት አፍሪካን የተባለው መጽሔት ሰሞኑን ባወጣው የደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት አቶ መለስ በሰላሳ ዘጠነኛ (39) ደረጃ ላይ አስፍሯቸዋል፡
ይሔ የአፍሪካ የመሪዎችን የብቃት ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የፋ ያደርገው መጽሔት ለጥናቱ መነሻ ነጥቦች ያደርጋቸው ከ ሁለት አመታት በፊት ለአገራቸው ጥሩ ሰርተው ስልጣን የለቀቁ የአህጉሪቱን መሪዎችን የአምስት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ጉርሻ ለመሸለም እንቅስቃሴ ያደርጉት ሱዳናዊው ቱጃር ሞ ኢብራሄም(15%) ፣ሰለ አገሮች የሚገልጸው የዲሞክራሲ መለኪያ(15%) ፣የሐሳብን በነጻ የመግለጫ መለኪያ(15%) ፣የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሸናል ሙስና መለኪያ(15%)፣የአለማቀፉ የሰው ሃይል ልማት መለኪያ (5%)፣የኢስት አፍሪካ መጽሔት ጋዜጠኞች አመታዊ ዳሰሳ (35 %) ( ይሕ አሃዝ መሪዎች ለብሔራዊ ግንባታ ያላቸው ቁርጠኝነት ፣ግሎባላይዜሽንን ያካተተ ነው ወዘተ ያካተተ ፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት እጅግ በጣም ጎበዝ የተባሉ መሪዎች (A)፣ ጥሩ መሪዎች (B) ፣ ፈተናውን ያለፉ(C) ፣ ከደረጃ በታች ውጤት ያስመዘገቡ (D and F) ነጥብ ተሰጥቷቸዋል፡፡በአጠቃላይ አማካኝ ነጥብ 32.68 ያገኙት አቶ መለስ ዜናዊን በተመለከተ በቀረበው ትንታኔ ከደረጃ በታች ውጤት ካገኙት ተርታ ገብተዋል፡፡

አቶ መለስ በቅርቡ “ከግብጽ ጋር ጦርነት ውስጥ ልንገባ አንችላልን…ወዘተ” በማለት ለዜና ሰዎች የመናገራቸው ጉዳይ “ያልተጠበቀ እና ያልሰከነ” የአመቱ ክስተት ተብሏል ፡፡ዜናውን ተከትሎ የካይሮ ባለስልጣናት በወቅቱ ማሰተባበላቸው አይዘነጋም፡፡ በአጠቃላይ ይህ አባባላቸው የአመቱ ታላቅ የፖለቲካ ኪሳራ ተደርጎ ተዘግቧል ፡፡በመጽሔቱ ዘገባ መሰረት በ2010 እኤአ በወረሃ ግንቦት በኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ም\ቤት አባላት የምርጫ ውድድር ላይ ኢሕአዲግ ተቃዋሚዎችን በማዋከብ 96.6% መቀመጫን በማግኘት እስከ መጬው አምስት አመት በስልጣን ላይ የሚያቆየውን እድል እንዳገኘ መነገሩ እና የአገሪቱ ኢኮኖሚ በ2009 እኤአ በ10% አድጓል መባሉ ለገዤው ፓርቲ የጥሩ አመት መልክቶች ነበሩ ብሏል፡፡፡ምርጫውን ተከትሎ አለማቀፍ ደርጃውን ያለጠበቀ መሆኑን የሚገልጽ የወቀሳ ደብዳቤ ምርጫውን ከታዘቡ ጥቂት የውጪ ታዛቢዎች መካከል አንዱ ከሆነው የአውሮፓ ህብረት የቀረበባቸው አቶ መለስ ዜናዊ “የቀረበው የአቤቱታ ሰነድ ጥቅም አልባ በመሆኑ ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ሊወረወር ይገባል… “ወዘተ ማለታቸው በአመቱ ውስጥ ኢትዮጵያን በተመለከተ ጎላ ብለው ከታዮት ከንውኖች ውስጥ በዋንኛነት ሰፍሯል፡፡

መጽሔቱ በአፍሪካ ውስጥ ስልጣናቸውን በሰላማዊ መንገድ እና በነጻ በምርጫ ተወዳድረው ያሸነፉ የመኖራቸውን ያህል አንዳንዶቹ መሪዎች እስከ አርባ አመት ድረስ በመግዛት እና ስለጣንን የግል ሐብታቸው እስኪመስል ድረስ ሙጥኝ በማለት ሕዝባቸውን በመጨቆን፣የፖለቲካ ምሕዳሩን በማጥበብ በጨቋኝ አገዛዛቸው የሚገኙ ብሎ ከጥቀሳቸው መካከል የኡጋንዳው ሙሴቪኒ፣የግብጹ ሙባረክ ፣የኢትዮጵያው አቶ መለስ ፣የኤርትራው አቶ ኢሳያስ ፣ የሱዳኑ አልባሽር እና የአንጎላው ጆሻንቶስ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

(ሀ) ምርጥ መሪዎች :- የዲሞክራሲ ስርአት አክባሪዎች ፣ ነጻ ንግድን ያበረታታሉ፣ የጸረ ድህነት ታጋዮች ናቸው ፣ ብሩህ አይምሮ አላቸው::
(የጋና፣የላይቤሪያ፣የሴራሌዮን፣የሩዋንዳ፣የሞሪሸስ፣ የሲሸልስ፣የቦትስዋና እና የኬፕቭርድ መሪዎች ናቸው)
(ለ) የስልጣን ጥመኞች:-በእጆቻቸው የንጹሃን ደም ያፈሰሱ፣ የሕዝባቸውን መጻኤ እድል ያፈኑ፣በመፈንቅለ መንግስት \ሰው በመግደል ስልጣን የጨበጡ
(የሊቢያ፣የአንጎላ፣ የግብጽ፣ የኢትዮጵያ፣የኤርትራ እና የሱዳን መሪዎች)
(ሐ) የሙስና ቁንጮዎች

በተለያዩ አገሮች ውስጥ ገንዘብ ያሸሹ

የኮንጎ ሪፖብሊክ፣የካሜሮን ፣የኢኳቶሪያል ጊኒ እና የቀድሞ የጋቦን መሪ የገኙበታል፡፡
የአመቱ የአፍሪካ መሪዎች የብቃት ደርጃ እና ያገኙት ውጤት በ መቶኛ(100%) ስሌት እንደቅደም ተከተል ፡

*( 100-70 A ፣ 70-60 B፣ 60-50 C፣50-45D፣ 45-40 F፣40-30ICU ፣ 30-0 Morgue )

1. ሰር አኖር እድ ጁጋኑትህ -ሞሪሸስ – 83.54
2 . ፔድሮ ፒርስ – ኬፕቭርድ- 78.91
3. ኢያን ካማህ – ቦትስዋና- 78.7
4 . ጆን እታ ሚልስ -ጋና-72.56
5. ሄፊኬፑኔያ ሉካስ ፖማባ- ናሜቢያ- 71.07
6. ጃኮ ዙማ -ደ\እፍሪካ – 69.93
7. ጀምስ ማይክል -ሲሼልስ- 66.4
8. እማዱ ቱማኒ -ቱሬ- ማሊ- 64.4
9. ኤርነስት ባይ ኮሮማ -ሲራሌዮን -61.89
10. ጃካያ መሪሾ ኪዋቲ – ታንዛኒያ -60.39
11. ኤለን ጆንሰን – ሴራሌዮን-60.32
12. ፑፒሃ ባንዳ – ዛምቤያ- 59.59
13. ንጉስ መሃመድ – ሞሮኮ- 54.84
14. ቤቱል ፓካሊታ – ሌሱቶ- 54.5
15. ቶማስ ያዪ ቦኒ – ቤኒን- 53.91
16 . ሙዋዊ ኬባኪ – ኬኔያ- 53.43
17. ቢንጎ ዋ ሙታሪካ – ማላዊ 53.04
18. አብዱላዬ ዋዲ – ሴኒጋል-51.68
19. ፖል ካጋሜ – ሩዋንዳ-51.31
20. ዮዌሪ ሙሴቬኒ- ኡጋንዳ-49.91
21. አልሳኔ ኦታራ -ክቶትዴቯር (አይቮሪ ኮስት)-49.69
22. አርማንዶ ጉቡዛ -ሞዛምቤክ- 49.35
23. ዚን ኤ አቢዲን ቤን አሊ -ቱኔዚያ-49.01
24. ሳሉ ደጂቦ -ኒጀር- 48.55
25. ጉድላክ ጆናታን -ናይጄሪያ-46.06
26. ፒርር ኑኩሩንዚዛ -ብሩንዲ-45.2
27. ኡማር ጋዳፊ- ሊቢያ-44.64
28. አብዱል አዚዝ ቡተፈሌካ – አልጄሪያ- 43.42
29. አልፓሃ ኮንዴ -ጊኒ- 41.94
30. መሀመድ ሆሲኔ ሙባረክ -ግብጽ-40.24
31. ንጉስ መሰዋቲ-ስዋዚላንድ- 40.05
32. አህመድ አብዱላሄ ሳምቢ- ኮሞሮስ-36.97
33. መሀመድ አላድ አብዱልአዚዝ -ሞሪታኔያ- 36.29
34. ቢሌስ ኮምፓወሬ -ቡርኬና ፋሶ- 35.7
35. ኢሊቤን ቦንጎ ኦዲማባ -ጋቦን- 3428
36. ዲኒስሳሶ ኒጉሶ -ኮንጎ- 33.43
37. ፋወር ጋን ሰንግቤ – ቶጎ- 33.38
38. ማሊሞ ባሊያ ሳና -ጊኒ ቢሳው-
39. መለስ ዜናዊ አስረስ -ኢትዮጵያ-32.68
40. ያያ ጃሜ -ጋምቤያ-32.48
41. ኢስማኤል ኡመር ጉሌ -ጅቡቲ- 31.53
42. ጆሴፍ ካቤላ ካባንጅ -ዴሞክራቲክ- ኮንጎ 30.18
43. ጆሴ ኤድዋርዶ ሳንቶስ- አንጎላ- 30.17
44. ፖል ባያ -ካሜሮን- 29.52
45. አንዲ ራጆሊኔያ -ማዳጋስካር- 29.31
46. ፍራንሲስ ቦዚያዝ ያንጎንዳ -ማእከላዊ አፍሪካ- 28.22
47. ሮበርት ገብሬል ሙጋቤ- ዙምባብዊ- 22.62
48. ሼክ ሸሪፍ ሼክ አህመድ- ሱማሌያ -22.41
49. ኢድሪስ ዳቢይ ኢትዮ -ቻድ- 20.81
50. ቴድሮ ኦቢንግ ነጉማ -ኤካቶሪያል ጊኒ- 20.72
51. ኦማር አልባሽር -ሱዳን- 15.67
52. ኢሳያስ አፈወርቂ -ኤርትራ- 12.14