መደማመጥና መነጋገር ከቻልን የማንፈታቸው ልዩነቶች የሉም!!!
አገራችን እና ሕዝቧ በአንድ ጠባብ ዘረኛ ቡድን መዳፍ ውስጥ ናቸው። በአገራችን የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የግለሰብም ሆነ የቡድን መብቶቻቸው ተረግጠው በባርነት እየተገዙ፤ ጉልበታቸውና ሃብታቸው እየተመዘበረ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የምገኝ ዜጎችና ማኅበረሰቦች ሁሉ እጣ ፈንታችን ተሳስሯል። ሁላችንም ነፃ ካልወጣን በስተቀር ማናችንም በተናጠል የነፃነት አየር መተንፈስ አይቻለንም። ስለሆነም ለራሳችን የግልም የሆነ የቡድን ጥቅም ስንል እያንዳንዳችን ስለሁላችን ማሰብና መጨነቅ […]